en
Feedback
Education News

Education News

Open in Telegram
880
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-2630 days
Posts Archive
2. VERB(ግስ) VERB: What is a Verb? (ግስ) The second more basic part of a sentence is a Verb. VERBS have special role in a sentence to understand what is taking place, what is happening, what is going on, what happens, what action happened or will  happen. A Sentence without a Verb is meaningless and CANNOT a give complete information about the action. If a Sentence is formed without a Verb, or if there is NO VERB in a Sentence, we cannot understand what an idea of the Sentence is. A VERB indicates whether the subject performs action, receives an action or is in a state of being. A verb may include helping words called auxiliaries. A VERB expresses what a person, animal, place, thing, or concept does. We can find a Verb in a Sentence by asking the question “What was the action or what happened?” (ሁለተኛው በጣም አሰፈላጊ እና ወሳኝ የሆነው የዐ.ነገር አካል(part) verb ነው። Verbs በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ እጅግ አስፈላጊ እና የተለየ ከፍተኛ ሚና አላቸው። በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ ምን ተደረገ? ምን ተፈፀመ? ምን እየተካሄደ ነው? ምን እየተከናወነ ነው? ምን ተባለ? ምን ሊደረግ ነው? ምን ሊሰራ ነው?፣ በአጠቃላይ "ምን" ለሚለው ጥያቄ ምላሽ እና ሀሳብ ማወቅ የምንችለው በዐ.ነገር አመሰራረት ውስጥ verb ሲኖር ብቻ ነው። አንድ ዐ.ነገር verb ከሌለው በምንም ዓይነት መንገድ ምን እንደተፈጸመ፣ ምን እንደተደረገ ሀሳብ ወይም መረጃ ማግኘት አንችልም። አንድ ዐ.ነገር ያለ verb ትርጉም ሊኖረው አይችልም፣ የሚፈለገውን ስለ ድርጊቱ መልዕክት ማስተላለፍ አይችልም፣ እናም ስለ ዐ.ነገሩ ትክክለኛውን መረጃ እና ሀሳብ ማግኘት አንችልም። ዐ.ነገሩም የተሟላ ዐ.ነገር ሊሆን አይችልም። ስለዚህ Verb በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ ሰብጀክቱ ምን አንዳደረገ፣ ምን አያደረገ እንደሆነ፣ ምን ሊያደርግ እንደሆነ፣ ምን እንዳለ፣ ምን እያለ እንደሆነ፣ ምን እንደ ፈፀመ እና ምን እያከናወነ እንሆነ እና ሌሎች የሰብጀክቱ ድርጊቶች ሁሉ ሙሉ ሀሳብ እና መልዕክት ያስተላልፋሉ። ስለዚህ ዐ.ነገሮች የተሟላ ዐ.ነገር ሆኖ የተሟላ መረጃና ሀሳብ መስጠት የሚችሉት በአመሰራረታቸው ውስጥ verb ሲኖር ብቻ ነው ማለት ነው። EXAMPLES: የሚከተሉት ዐ.ነገሮች ሁሉም verb ስላላቸው የተሟላ ዐ.ነገር(complete sentence) ናቸው። ቬርቦቹ የተሰመሩበት ሆኖ የተለያየ tense structures አላቸው፣ የተለያዩ የድርጊቶቹን ግዜም ይገልፃሉ። I like dog. (ውሻ እወዳለሁ።) I- subject, like- verb, dog- object  Don't smoke here. (እዚህ አታጭስ።) verb- smoke He reads many books. ([አሱ] ብዙ መፅሐፎች ያነባል።) He- subject, reads- verb, many books- object  The students are studying in the library. (ተማሪዎቹ ላይብረሪ ውስጥ እያጠኑ ነው።) Subject- The students, verb- are studying, object- library People use smart phones. (ሰዎች አዳዲስ ስልኮች ይጠቀማሉ።) use- verb Did she pass the test? (ፈተናውን አልፋለች?።) Subject- she, verb- did/pass, object- the test He played football. (ኳስ ተጫውቷል/ተጫውቶ ነበር።) Subject- He, verb- played, object- football  Does he speak English? (እንግሊዝኛ መናገር ትችላለች?) Subject- she, verb- Does/speak, object- English My parents will arrive tomorrow. (ወላጆቼ ነገ ይደርሳሉ።) Subject- My parents, verb- will arrive Many Ethiopians can't read and write English. Subject- Many Ethiopians, verb- read and write, object- English. (ብዙ ኢትዮጵያውያን ማንበብ እና መፃፍ አይችሉም። ይህ ዐ.ነገር 2 ዋና verb አለው፣እነሱም፣ ''read' እና 'write' ሲሆኑ 'compound verbs' ይባላሉ። ለምሳሌ፣ 'I play football and watch movies every weekend.' በዚህ ዐ.ነገር ውስጥ ሁለት ቬርቦች አሉ፣ 1. 'play' እና 2. 'watch' ሲሆኑ በአያያዥ ቃል በ'and' joined ተደርጓል። እንዲሁም በእንድ ዐ.ነገር ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ subject ያላቸው ዐ.ነገሮች ደግሞ 'compound subjects' ይባላሉ። ለምሳሌ፣ 'My sister and her husband works in a hospital.' ይህ ዐ.ነገር ሁለት subject አለው። አነሱ፣ 1. 'My sister' እና 2. 'her husband' ናቸው። ስለዚህ compound subjects ተብለው ይጠራሉ።) More examples about verbs Have you seen the car crash? (የመኪናውን ግጭት አይተሻል/አይተኸዋል?) Where do you wash your clothes? (ልብሶችህን የት ነው የምታጥባቸው?) My mother tells me stories every night. (እናቴ ማታ ማታ ተረት ትነግረኛለች።) Would you tell me the truth? (እውነቱን ልትነግረኝ ትችላለህ?) In the above examples, all the bolded and underlined words are verbs and they are used in the sentences in different tense forms. They tell us complete information about what each of the subject does, what is happening in the sentence. A VERB is a single word, or a group of words, that describe an action or state.VERBS are generally essential to the structure of a sentence, and they can be inflected to show features such as tense, number, and person: for example, the verb remember can be put in the past tense form remembered or the third person present singular form remembers. In English, verbs are either transitive(Verbs that take an Object) or intransitive(Verbs that do not take object or has no object).

ሙሉ ማስታወሻውን(ኖቱን) የምትፈልጉት በPDF ማግኘት ትችላላችሁ።

ከላይ ከተጠቀሱት ዐ.ነገሮች(ምሳሌዎች) sentence structures (እስትራክቸራቸውን) መይም ዐ.ገነሮቹን አወቃቀር በማየት ብዙ ሀሳቦችን ማንሳት እንችላለን። ለምሳሌ: The dog died. (ውሻው ሞተ።) 1. የዚህን ዐ.ነር structure ካየን፣ ሁለት የተለያየ የቃል ክፍል ያላቸውን ቃላት በማገናኘት እና ዐ.ነገር በማድረግ ሙሉ ሀሳብ መስጠት የሚችል ዐ.ነገር አደረግነው። እነሱም፣ 1. The dog የሚል እና 2. died. ናቸው። እነዚህ ዐ.ነገሮች የሚመደቡበት የራሳቸው የቃል ክፍል(Parts of Speech) አላቸው። እነሱም፣ 1. dog- noun 2. died- verb ናቸው። 'died' የ'die'  past form ሲሆን የድርጊቱን ግዜ ይነግረናል። በዚህ መሠረት፣ ከላይ እንደገለፅኩት አንድ ዐ.ነገር ዐ.ነገር ነው የሚያስብለው በትንሹ ሁለት ቃላት እና ከዚያ በላይ ትክክለኛው ቅደም ተከተላቸው (Sentence Order) ወይም አወቃቀራቸው ተጠብቆ፣ ትክክለኛውን Subject እና Verb በመጠቀም፣ እነዚህ ሁለቱ Subject እና Verb ደግሞ የሚስማሙ(የተጣጣሙ) ሆኖ ከተፃፉ ሙሉ ዐ.ነገር ወይም የተሟላ ዐ.ነገር(Complete Sentence) ይባላል፣ የተሟላ ዐ.ነገር እና ሙሉ መልዕክት(ሀሳብ/መረጃ/ ማስተላለፍ(መግለጽ) የሚችል(a Sentence with Complete thought) ተብሎ ይጠራል። በዚህ የዐ.ነገር አወቃቀር ውስጥ ዐ.ነገሮችን በፅሁፍ እና በንግግር ሂደት ውስጥ የምንጠቀመው ሀሳብን(Idea) ለማስተላለፍ ነው። ድርጊትን ለመግለጽ ነው። ሀሳብ እና ድርጊት ደግሞ ባለቤት አላቸው፣ ባለቤቱ(Subject) ደግሞ ምን አለ? ምን አደረገ? ለሚሉት እና ለሌሎች ሀሳቦች መልስ ማግኘት የምንችለው ደግሞ በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ Verb ሲኖር ብቻ ነው። በዚህ መሠረት፣ በዚህ የዐ.ነገር አፃፃፍ፣ አመሰራረት(አወቃቀር) ውስጥ፣ ማንኛውም ሙሉ የሆነ ዐ.ነገር 3 ክፍሎች አሉት። Any COMPLETE SENTENCE with COMPLETE IDEA has three parts: እነሱም፤ 1. SUBJECT 2. VERB 3. OBJECT ናቸው። 1. SUBJECT ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት፣ ዐ.ነገሮችን በፅሁፍ እና በንግግር ሂደት ውስጥ የምንጠቀመው ሀሳብና ድርጊትን ለመግለፅ ነው። ሀሳብ እና ድርጊት ደግሞ አድራጊ(ፈፃሚ) አላቸው፣ ማንኛውም ድርጊት፣ ድርጊቱን የፈፀመው(ያደረገው) አካል አላቸው። ስለዚህ አንድ ዐ.ነገር ሙሉ የሚሆነው፣ የተሟላ ሀሳብ ሊነግረን የሚችለው፣ በዐ.ነገሩ ውስጥ Subject ሲኖር ነው። Subject ማለት፣ - በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ ድርጊቱን የፈፀመው አካል፣ - የድርጊቱ ባለቤት፣ the doer of the action - የሀሳቡ ባለቤት፣ - አድራጊ፣ ድርጊቱን ማን መፈፀም? ማን አደረገ? በምን ተደረገ? በማን ተፈፀመ? ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ የምናገኝበት ነው። - አንድ ዐ.ነገር Subject ከሌለው ሙሉ ዐ.ነገር አይሆንም፣ የተሟላ ሀሳብም ማስተላለፍ አይችልም። - በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ Subject ከሌለ፣ ድርጊቱን ማን ፈፀመ? በማን ተፈፀመ? ማን አደረገ? ማን አለ? እና ለሌሎች ጥያቄዎች መልስ አናገኝም፣ ስለዚህ የተሟላ መረጃ ማግኘት አንችልም ማለት ነው። ምሳሌ እንይ፣ 1. Ate the banana. (Who?) 2. Bought me a book. (Who?) 3. Like watching movies. (Who) 4. Has been playing football. (Who?) 5. Killed the dog. (Who?) 6. Doing their assignments. (Who?) ከላይ የተጠቀሱት ዐ.ነገሮች ምን አስተዋላች? ዐ.ነገሮቹ(6ቱም) የተሟሉ ዐ.ነገሮች ናቸው? ሙሉ ሀሳብ ይነግሩናል? አንብበን ሙሉ መረጃ እናገኝባቸኋለን? ከላይ ያነሳኋቸውን ጥያቄዎች ከተሰጡት ከ 6ቱም ዐ.ነገሮች መልስ ማግኘት አንችልም፣ ምክንያቱም ሙሉ ዐ.ነገር ስላልሆኑ፣ Subject(የድርጊቱ ተፈፃሚ ማን እንደሆነ) ስላልተገለፀ ስለተፃፈው ነገር የተሟላ መረጃ/ሀሳብ/ ማግኘት አንችልም። እስኪ ለዐ.ነገሮቹ Subject ሰተን እንደገና እንያቸው፣ 1. We ate the banana. (Who? We) ሙዙን በላን። ማን? እኛ- Subject 2. My father bought me a book. (Who? My father) አባቴ መፅሐፍ ገዛልኝ። ማን? አባቴ- subject 3. I like watching movies. (Who?I) ፊልም ማየት እወዳለሁ። ማን? እኔ። 4. She has been playing football. (Who? She) ኳስ እየተጫወተች ነበር። ማን? እሷ። 5. The boys killed the dog. (Who? The boys) ልጆቹ ውሻውን ገደሉት። ማን? ልጆቹ- subject 6. The students are doing their assignments. (Who? The students ) ተማሪዎቹ አሳይመንታቸውን እየሰሩ ነበር። ማን? ተማሪዎቹ- subject አሁን ዐ.ነሮቹን እንዳነበባችሁ፣ እያንዳንዱ ዐ.ነገር ዶርጊቱ ማን ፈፀመ? ለሚለው ጥያቄ መልስ አላቸው፣ የድርጊት ፈፃሚ አካል ተገልጿል።  ስለዚህ ሙሉ ዐ.ነገር ናቸው፣ የተሟላ ሀሳብ ይሰጣሉ። እኛም አንበበን ሙሉ ሀሳብ እንድናገኝ በዐ.ነገሮቹ ውስጥ የተገለፁት subject ረድቶናል ማለት ነው። በአጠቃላይ፣ በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ የድርጊቱ ባለቤት፣ ድርጊቱን(Action) የፈፀመው አካል መኖር አለበት ማለት ነው። ምክንያቱም ሀሳቡን ማን አለ? ድርጊቱን ማን ፈፀመ? ማን አደረገ? ለሚሉት እና ለሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ የምናገኘው በዐ.ነገር ውስጥ Subject ሲኖር ብቻ ነው። ስለዚህ በዐ.ነገር አመሰራረት ውስጥ አንድን ዐ.ነገር ሙሉ ዐ.ነገር እዲሆን ከሚጠበቁት የዐ.ነገር አካል ውስጥ አንዱ SUBJECT ነው ማለት ነው። 2. VERB

Sentence ቃሉን ስናነበው ቀላል አና ተራ ቢመስልም አመሰራረቱ ግን በጣም ውስብስብ ነው። አንድን ዐ.ነገር ተፅፎ ስናነበው፣ ተፅፎ ማንበባችን ብቻ ሳይሆን በውስጡ አመሰራረቱ እና መዋቅሩ ከተራ ባለ 2 ቃላት ዐ.ነገር ጀምሮ እስከ በጣም ውስብስብ የሆነ ዐ.ነገር በጣም የሚከብድና የሚወሳሰብብን መዋቅሮች አሉት። የSentence(ዐ.ነገር) መነሻው ቃላት ናቸው። ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ በgrammar እና sentence structures ቅደም ተከተላቸውን ጠብቆ ከተፃፉ የተሟላ ዐ.ነገር (complete sentence) ይባላሉ፣ የተሟላ ሀሳብ(መልዕክት- complete idea or thought) ይሰጣሉ ማለት ነው። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቃላት joined ሆኖ ወይም ተገናኝቶ ዐ.ነገር(sentence) ይመሰርታሉ፣ የዐ.ነገር(sentence) ስብስብ ደግሞ paragraph(አንቀጽ) ይሆናሉ፣ የአንቀፆች ስብስብ ደግሞ passage(ምንባብ) ይባላሉ፣ እንዲህ እንዲህ እያለ ዐ.ነገር ከቀላል እና ከተራው ባለ ሁለት ቃላት ዐ.ነገር(Simple sentence) ተነስቶ እየተወሳሰበ እና እየከበደ(complex and complicated) እየሆነ እና እያለ ወደ ትልቅ ድርሰት እና መፅሐፍ ያድጋል። ለዚህም ነው ከላይ ዐ.ነገር ቀላል ሲመስለን፣ ግን grammatical እስትራክቸሩ ግን እጅግ ውስብስብ ነው ያልኩት። ለምሳሌ: የሚከተሉትን ዐ.ነገሮች እንይ፣ A. 1. The dog died. 2. The dog died on the road. 3. The dog died on the road and it was badly smelled. 4. Although the dog is died on the road, no body saw and picked it up from the rood, because it was badly smelled. B. 1. I like horror movies. 2. I like horror movies, but my sister doesn't watch it. 3. I like horror movie, because it makes me relax although my sister doesn't watch it. 4. Although horror movie makes me relax, I don't have enough time to watch it, because I must study for my exams; so I watch it on weekends. ........................ ከላይ ከዘረዘርኳቸው ዐ.ነገሮች የምንረዳሁ ነገር አለ። ብዙ ሀሳቦችን እናነሳለን፣ እነዚህን ምሳሌዎች መሰረት በማድረግ። .................. እመለስበታለሁ!

ተማሪዎች፣ የጀመርኩትን ስለ Sentence እቀጥላለሁ። ትምህርቱ እና ማስታወሻው እጅግ ጠቃሚ እና የሚጠቅማችሁ በመሆኑ አንብባችሁ መተው ሳይሆን የራሳችሁን ማስታወሻ እንድትወስዱ በትህትና እምክራችኋለ
ተማሪዎች፣ የጀመርኩትን ስለ Sentence እቀጥላለሁ። ትምህርቱ እና ማስታወሻው እጅግ ጠቃሚ እና የሚጠቅማችሁ በመሆኑ አንብባችሁ መተው ሳይሆን የራሳችሁን ማስታወሻ እንድትወስዱ በትህትና እምክራችኋለሁ። ወላጆችም ተማሪዎች ትምህርቱን እንዲያጠኑ፣ ማስታወሻውንም እንዲወስዱ ሁኔታዎችን በቻላችሁት አጋጣሚ እንድታመቻቹላችሁ በአክብሮት ለማሳሰብ አወዳለሁ። ሙሉ ኖቱን በ PDF format ስላዘጋጀሁት ገፁ በዛ ቢልም ፋይሉን download እና print በማድረግ እንዳመቻችሁ፣  ባመቻችሁ ሁኔታ እንድታጠኑ መልካም ነው። ...................... ሙሉ ኖቱን ከ ELIC channel ታገኙታላችሁ።

D. The sentence must be grammatically correct.(አንድ ዐ.ነገር ትክክለኛውን መልዕክት ማስተላለፍ የሚችለው ግራማትካሊ ትክክለኛ(ትክክለኛውን ግራመር) ተጠቅሞ ሳጻፍ ነው።) E. There must be a verb in a sentence.(አንድ ዐ.ነገር ውስጥ በትንሹ አንድ verb መኖር አለበት።) F. The sentence must begin with a capital letter and end with a period or any other terminal punctuation marks. A complete sentence is a group of words which expresses a complete thought and contains a a subject and a predicate (verb). It is an expression of thought or feeling by means of a word or words used in the  statement. A SENTENCE is a grammatical structured composed of one or more clauses and at least must have asubject and a verb, but may also contain object and other grammatically structured forms. The Verb form of a sentence must be matched with the Subject of a Sentence.(በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ ያለው subject እና verb አብሮ የሚሄዱ እና የተጣጣሙ መሆን አለባቸው።) A Complete sentence contains two parts: a Subject and a Predicate(a Verb). (ሙሉ የሆነ፣ የተሟላ ሀሳብ መስጠት የሚችል ዐ .ነገር ሁለት ክፍል አለው፤ subject እና verb). The Subject is what or whom the sentence is about, while the Predicate(Verb) tells something about the Subject. ........................... እንቀጥላለን .......................... ሰላም ያሳድረን!

ELIC - ኤሊክ: ለቅምሻ ........................ 1. SENTENCE (. ነገር) WHAT IS A SENTENCE? (ዐ.ነገር ምንድነው?) BRIEF DEFINITIONS OF A SENTENCE A SENTENCE is a group of words that contains a SUBJECT and a VERB. (Sentence(0. ነገር) የቃላት ስብስብ ነው። ሁለት እና ከዚያ በላይ ቃላቶችን በማገናኘት ቅደም ተከተላቸውን በትክክል ጠብቀን የሚፈለገውን ሀሳብ፣ መልዕክት ወይም መረጃን እንዲሰጡ አድርገን ስንጽፍ ወይም ስንናገር ዐ.ነገር ይባላል። በዚህ ሂደት ውስጥ አንድ ዐ.ነገር የሚፈለገውን ሙሉ ሀሳብ እና መልዕክት ማስተላለፍ የሚችለው subject እና verb ሲኖረው ብቻ ነው። በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ እነዚህ የተጠቀሱት ካሉ(subject እና verb) ማለት ነው፣ ያ 0.ነገር ሙሉ ይሆናል፣ በትክክለኛው መንገድ ትክክለኛውን መልዕክት ማስተላለፍም ይችላል ማለት ነው።) A SENTENCE is A sentence is a group of words that tells a complete thought. A sentence needs a noun or pronoun that names the person or thing the sentence is about. A sentence needs a verb to tell what  happens. (ከአንድ ዐ.ገነር የተፈፀመውን ድርጊት ወይም ሀሳብ ማወቅና መረዳት የምንችለው ዐ.ነገሩ ውስጥ verb ሲኖር ነው። ማን ምን አደረ?፣ ማን ምን ተናገረ? ማን ምን ፈፀመ? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት የምንችለው በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ verb ሲኖር ነው። The noun or pronoun functions as subject, in the active sentence, and the verb functions as predicate. All the words that tell whom and what a sentence is talking about are called the Subject.(አድራጊድርጊቱን ፈፃሚ፣ የዐ.ነገሩ ባለቤት) To find the subject, ask whom or what the sentence is talking about.(ያንድን ዐ.ነገር subject ለይተን ለማወቅ በቀላሉ "ማን?" ወይም "ምን?" ብለን በመጠየቅ ወይም በማሰብ የድርጊቱ ባለቤት(subject) ማወቅ እንችላለን) All the words that tell what the subject does are called the Predicate( Verb). To find the predicate, firstly find the subject then ask what the subject does.(በአንድ ዐ.ነገር ውስጥ ያለውን verb ለይተን ለማወቅ ደግሞ ሰብጀክቱ ምን አደረገ? ምን አለ?  ምን ፈፀመ? የሚሉትን ጥያቄዎች በማሰብ በቀላሉ ቬርቡን ለይተን ማወቅ እንችላለን ማለት ነው።) A sentence is a set of words that is complete in itself; (አንድን ዐ.ነገር ዐ.ነገር ሊባል የሚችለው በራሱ ራሱን ችሎ ሀሳብ መንገር ወይም ማስተላለፍ ሲችል ብቻ ነው።ያ ዐ.ነገር ደግሞ መደበኛውን ዐ.ነገር፣ ጥያቄትዕዛዝ ወይም የአድናቆት ሀሳብ ያለው ሊሆን ይችላል፣ እንደ ዐ.ነገሩ አላማ), means when a set of words introduce something (StatementQuestion, Command , Idea) clearly , it is called as a sentence. The basic part of any sentence is a Subject and a Predicate(verb). A Sentence enable us to communicate complete thoughts or ideas in both speaking and writing. (ዐ.ነገሮች በፅሁፍ እና በንግግር ሂደት ውስጥ ሀሳብንመልዕክትንጥያቄንትዕዛዝንማሳሰቢያንአድናቆትንስሜትን እና ሌሎች ሀሳቦችን በፅሁፍ ወይም በንግግር ለመግለፅ (ለማስተላለፍ) የምንጠቀምባቸው ናቸው።) A Sentence is: - an expression of thought or feeling by means of a word or words used in such forms and manner as to give the meaning in different forms and purposes.(ዐ.ነገሮች ሀሳብ፣ ስሜት እና ድርጊት መግለጫ ናቸው።) - is an oral or written communication made up of one or more units, each of which contains a complete  thought formed according to a definite pattern of the sentence. - is a communication in words conveying a sense of completeness containing at least one independent clause with its subject. - is a word or group of words standing between the initial Capital letter and a mark of end punctuation or between two marks of end punctuation. A SENTENCE is a group of words, usually containing a VERB that expresses a thought in the form of a STATEMENT (መደበኛ ዐ.ነገር), QUESTION (ጥያቄያዊ ዐ.ነገር), INSTRUCTION (ማሳሰቢያ), COMMAND(ትዕዛዛዊ) or EXCLAMATION(አድናቆት ወይም አግራሞት)and starts with a capital letter when written. In written English, sentences begin with a capital letter and end with a Full stop/period (.), a Question mark (?) or an Exclamation mark/exclamation point (!). A SENTENCE consists of a Noun (subject/ person/ place/ thing). It consists of a Verb (action/ state/ occurrence). A SENTENCE is used to express ideas in our mind. Sentences are needed to convey thought and feeling. A sentence has characteristics as follow: (ዐ.ነገሮች በአጭሩ የሚከተሉት ባህርያት አሏቸው) A. All the words of sentence must have meaning.(በእንድ ዐ.ነገር ውስጥ የተገናኙት ቃላቶች የዐ.ነገሩን የሚፈለገውን ትክክለኛ ሀሳብ በሚገባ ማስተላለፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው።) B. The words of the sentence must be arranged in the correct order for the sentence to have meaning. (የቃላቶቹ ስብስብ እንደ ዐ.ነገሩ ሀሳብ ትክክለኛውን ቅደም ተከተላቸው ተጠብቆ መፃፍ አለባቸው።) C. The sentence must be complete(with the S+V/S+V+O/ structure)

ሰላም ተማሪዎች፣ ስለ SENTENCE ጀምረን ነበር፣ ገና ብዙም አልሄድንበትም። ለእናንተ በሚመች መልኩ፣ እናንተ በቀላሉ መረዳት በምትችሉት መንገድ ማስታወሻ(note) እያዘጋጀሁላችሁ ስለ ሆነ፣ እሱን
+2
ሰላም ተማሪዎች፣ ስለ SENTENCE ጀምረን ነበር፣ ገና ብዙም አልሄድንበትም። ለእናንተ በሚመች መልኩ፣ እናንተ በቀላሉ መረዳት በምትችሉት መንገድ ማስታወሻ(note) እያዘጋጀሁላችሁ ስለ ሆነ፣ እሱን ጨርሼ ከላኩላችሁ በኋላ በሰፊው ስለ Sentence, Types of Sentences: Simple, Compound, Complex and Compound complex sentences, Subject, Verb and Object, Declarative, Interrogative, Imperative and Exclamatory Sentences, Dependent clause and Independent clause እና ሌሎች ሀሳቦችን እንወያይበታለን።

ሰላም እንዴት ሰነበታችሁ የጨፌ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች? የ2015ዓም ማጠቃለያ ሰርተፍኬት የሚሰጠው በ09/11/2015ዓም መሆኑን እያሳወቅን በዕለቱ ጠዋት በመገኘት ሰርተፍኬት መውሰድ ትችላላችሁ። ከዚህ በፊት ደግሞ ያላጠናቀቃችሁት ነገር ካለ ማጠናቀቅ ይጠበቅባችሗል። ማለትም የተዋሳችሁት መፅሀፍ ካልመለሳችሁ እና የልማት ክፍያ ካልከፈላችሁ እንድትከፍሉ እንላለን። ሰርተፍኬት የሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን አይመለከትም። እናንተ የሚኒስትሪ ፈተናን ትምህርት ቢሮው አጠናቆ ሲለቅ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ለተማሪዎች በሙሉ
ለተማሪዎች በሙሉ

Today, we will begin with 👉 SENTENCE. QUESTIONS referring SENTENCES DEFINING SENTENCE What is a SENTENCE? What are types of SENTENCE? And each type of SENTENCE definitions? ............................................ ዛሬ ከ SENTENCE(ዐረፍተ ነገር) እንጀምራለን። እስቲ 'SENTENCE' የሚለውን ቃል በራሳችሁ define አርጉት። ቃሉን ስትሰሙት፣ ስታነቡት ወይም ስትጠየቁ ወደ አእምሮአችሁ የሚመጣውን ሀሳብ በማስታወሻችሁ ፃፉ። ............................................. As far as a SENTENCE can be used in spoken and written for different purposes, it has different types. We will see their types in two categories next. ............................................... አንድን ዐ.ነገር ስንጽፍ፣ ስንናገር ወይም ስንሰማ ያ ዐ.ነገር ያገለገለው ወይም የሚጠቅመው ለአንድ አላማ(purpuse) ነው። ማንኛውም ዐ.ነገር(SENTENCE) የሚጻፍበት ወይም የሚነገርበት የራሱ አላማ አለው። በራሱ መንገድ(form) የራሱ የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው። 1. ለምሳሌ የሚከተሉትን ምሳሌዎች እንይ። 👉 ቡና በጣም እወዳለሁ።       I like coffee. 👉 ለምን ትምህርት ቤት ቀረሽ?       Why did you absent school? 👉 ምንም ነገር እንዳትናገር።       Never say a word. 👉 አቤት! እንዴት የሚያምር ልጅ ነው!       Wow, what a beautiful baby! ከላይ የጠቀስኳቸው ምሳሌዎች አራቱም ዐ.ነገር(SENTENCE) ናቸው፣ ነገር ግን የተለያ form እና የተለያየ መልዕክት በተለያየ መንገድ ያስተላልፋሉ። .............................................. 2. ሌላ SENTENCEን በተመለከተ የሚከተሉትን ምሳሌ እንይ። 👉 ሜሮን እንግሊዝኛ ታጠናለች።       Meron studies English. 👉 ሜሮን እና ህሊና እንግሊዝኛ በጣም ያጠናሉ።       Meron and Hillina study English very well. 👉 ሜሮን የእንግሊዝኛ ፈተናን አልተፈተነችም፣ ምክንያቱም አርፍዳ ስለመጣች።     Meron didn't take an English test, because she arrived late. 👉 ሜሮን ጎበዝ ተማሪ ናት፣ ጥሩ ውጤት አመጣች፣ ምክንያቱም በርትታ ስላጠናች።       Meron is a clever student; she scored a good mark, because she studied hard. ........................................... በተጨማሪ በተራ ጥቁር 2 ላይ የጠቀስኳቸው ሌላኛው የዐ.ነገር form ወይም ሌላው ዐ.ነገር(SENTENCE) የምንጠቀምበት መንገድ ነው። አራቱም SENTENCES(ዐ.ነገሮች) የራሳቸው form or structure እና type አላቸው። ስለዚህ ማንኛውም ዐ.ነገር(SENTENCE) በንግግርም በጽሑፍ ስንጠቀምባቸው የተለያየ form ያላቸውን SENTENCE(ዐ.ነገር) ለተለያየ አላማ ነው ያልኩት ከላይ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የጠቀስኳቸውን ምሳሌዎች ምክንያት በማድረግ ነው። .......................................... ስለዚህ፣ 👉 DEFINITION OF SENTENCE እና 👉 TYPES SENTENCE ማወቅ ግድ ይለና። እናንተ ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ እና ምሳሌዎችን እያነበባችሁ፣ እየቀየቃችሁ እና እያሰባችሁበት ቆዩ። እኔ በኋላ ከሙሉ ማብራሪያ እና ምሳሌዎች ጋር እመለሳለሁ። .......................................... መልካም ቆይታ።

ትምህርት ቤቶች ላይ ያለውን ችግር ለነገ ልንተወው የሚገባ ባለመሆኑ ፊት ለፊት ልንጋፈጠው ይገባል ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ይህ የትውልድና የሀገር ጥሪ መሆኑን አውቃችሁ ልትደግፉ ይገባል በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ኢትዮጵያውን ከተባበርን የማናስተካክለው ነገር የለም በዚህም በሚመጡት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያን ትምህርት ቤቶች ችግር ሙሉ በሙሉ እንፈታለንም ብለዋል፡፡ በትምህርት ቤቶቹ ከሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ችግሮች መካከልም የመማሪያ ክፍል ፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ አገልግሎት፣ የመጸዳጃ ቤት፣ ኤሌክትሪክ እንዲሁም የትምህርት ግብዓት እጥረት በዋናነት ይጠቀሳሉም ተብሏል፡፡ ይህ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ በቀጣይም በየደረጃው በሁሉም ክልሎች በተዋረድ እንደሚካሄድ በመደረኩ ተገልጿል፡፡ በመድረኩም የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ባለሀብቶች፣አጋር ድርጅቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ... TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- aacaebc@gmail.com Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/ flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/

ቀን 25/10/2015 ዓ.ም አሁን ያለውን የትምህርት ስርዓት መቀየር ካልቻልን በቀጣዩ አለም ተወዳዳሪ ሀገርና ትውልድ መፍጠር አንችልም¬- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህር
+4
ቀን 25/10/2015 ዓ.ም አሁን ያለውን የትምህርት ስርዓት መቀየር ካልቻልን በቀጣዩ አለም ተወዳዳሪ ሀገርና ትውልድ መፍጠር አንችልም¬- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ማሻሻል ላይ ያተኮር ህዝባዊ ንቅናቄ ለማካሄድ ያለመ የማስጀመሪያ ሀገር አቀፍ መድረክ ዛሬ አካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁሉም ዜጎችና ተቋማት ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻል“ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄን አስጀምረዋል፡፡ ዛሬ የተገናኘነው ትናንት ያሰተማረን ማህብረሰብ እዳ ስላለብን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በየትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ የተማራችሁ ሁሉ የተማራችሁባቸው ትምህርት ቤቶች ዛሬ የናንተን ድጋፍ ይሻሉ ብልዋል፡፡ 12ኛ ክፍል ሲደርሱ ተማሪዎችን ሰብስቦ መፈተን ብቻ ሳይሆን ከታች መሰረቱ ላይ መስራት ይጠበቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁን ያለውን የትምህርት ቤት ሁኔታ ለመቀየር በገንዘብ፣ በጉልበት እንዲሁም በዕውቀት ተባብረን የላቀች ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ ቀድመን የላቁ ትምህርት ቤቶችን አብረን እንገንባ!ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው በተለያየ ጊዜ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ የተሄደው ርቀት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ ነበረው ብለዋል፡፡ ለተማሪዎች ትምህርት መቀበል ዋናው ነገር የትምህርት መሰረተ ልማት ቢሆንም አሁን ካሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86 ከመቶ የሚሆኑት ከደረጃ በታች ናቸው ብለዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ትምህርት ቤቶች በመንግስት አቅም ብቻ መገንባት የማይቻል በመሆኑ ሁሉንም ገንዘቡ፣ እውቀቱ እና ጉልበቱ ያላቸውን ማሳተፍ በማስፈለጉ ይህ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡

ሰላም ተማሪዎች፣ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ግዜ መጠናቀቁን ተከትሎ እረፍት እንድታረጉ በማሰብ ትምህርቶችን ሳላካፍላችሁ ለተወሰነ ግዜ ቆይቻለሁ። ከዚህ በኋላ ግን ያላችሁን የእረፍት ግዜ ክረምቱን ሙሉ እናንተን የሚጠቅም፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታችሁን በተሻለ ለማዳበር የሚጠቅሟችሁን ትምህርቶች እንማማራለን። እንዲሁም በሚቀጥለው አመት 8ኛ ክፍል የምትማሯችሁን መፅሐፍቶችን(Subjects) እልክላችኋለሁ። ክረምቱን እያጠናችሁ ለሚቀጥለው ክፍል ቀድማችሁ ራሳችሁን  ዝግጁ እንድታረጉ እጅጉን ይጠቅማችኋልና። እኔም በተሻለ እና በልዩ ሁኔታ 8ኛ ክፍል ላይ የምትማሯቸው ትምህርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የተሻለ ትምህርት እና ዕውቀት እንድታገኙ የበኩሌን ጥረት አደርጋለሁ። በርግጥ የሚቀጥለው አመት 8ኛ ክፍል የምትማሩት የእንግሊዝኛ ትምህርት ከ7ኛ ክፍል በጣም የተለየ አይሆንም፣ ምክንያቱም ትምህርቶቹ ተያያዥነት ስላላቸው። ሌላው ጠቃሚ ነገር ከዚህ ቀደም አዘጋጅቼ የላኩላችሁን ወርክሺቶች በድጋሚ በማጥናት መስራት፣ ግልጽ ያልሆነላችሁን በመጠየቅ መስራት ትምህርቱን በተሻለ ለመረዳት በጣም ይረዳችኋል። ሌላው ማሳሰብ የምፈልገው ወርክቶቹን እና ኖቶቹን መጣል የለባችሁም፣ ምክንያቱም እንግሊዝኛ ቋንቋንም ሆነ ትምህርቶቹን በተሻለ ለመረዳት ሁሌም ይጠቅማቸኋልና። እናም የክረምት የእረፍት ግዜያችሁን በአግባቡ ለሚጠቅማችሁ ነገር ተጠቀሙ። እንግሊዝኛ ቋንቋ ለሌሎች ትምህርቶች ሁሉ መሰረት ነውና ለእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለየ ትኩረት ሰታችሁ ለመማር እና ለማጥናት ፍላጎት እና ተነሳሽነት እንድኖራችሁ ግድ ነው። ሁሌም እንደምላችሁ ቋንቋውን በደንብ ሳትረዱ፣ የተሻለ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዕውቀት እና ክህሎት ሳይኖራችሁ ሌሎች የምትማሯቸውን ትምህርቶች አንብባችሁ መረዳት እጅጉን ያስቸግራችኋል። ለዚህም ነው ሁሌም ለእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለየ ግዜና ትኩረት እንድሰጡ የምመክራችሁ። ስለዚህ ከላይ እንዳልኳችሁ ያላችሁን የክረምት የእረፍት ግዜ ለሚቀጥለው የትምህርት ክፍል ራሳችሁን ዝግጁ የምታረጉበትን የእንግሊዝኛ ትምህርቶች በተሻለ ሁኔታ ለእናንተ ለመስጠት ጥረት አደርጋለሁ። እናንተም መማር የምትፈልጉትን ማንኛውንም የእንግሊዝኛ ትምህርት በ ELIC DISCUSSION Group ጥቆማ ብትሰጡኝ በጣም ደስ ይለኛል። 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ELIC - ኤሊክ: Committed to teach you English in better ways. ELIC - እናንተን በተሻለ ሁኔታ እንግሊዝኛን ለማስተማር ጥረት ያደርጋል።       መልካም ግዜ።

photo content

SECOND SEMESTER GRADE 7 ENGLISH ANSWER KEYS: መልስ
SECOND SEMESTER GRADE 7 ENGLISH ANSWER KEYS: መልስ

SECOND SEMESTER GRADE 7 ENGLISH FINAL EXAM

የክፍል ድልድል በተመለከተ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች 7ኛ ክፍል ምትገቡ ይሆናል። ማለትም 6A ክፍል ተማሪዎች7A ክፍል; 6B ክፍል ተማሪዎች 7B ክፍል; 6C ክፍል ተማሪዎች7C ክፍል; 6D ክፍል ተማሪዎች 7D ክፍል; 6E ክፍል ተማሪዎች 7E ክፍል 6A/O ተማሪዎች 7A/O ክፍል እንድትገቡ እናሳውቃለን። ሌሎች ክፍሎች መፈተኛ ስለሆኑ። 8ኛ ክፍሎች ሁሉም በክፍላችሁ ነው?

በዚህ ፕሮግራም መሠረት ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ይሰጣል።
በዚህ ፕሮግራም መሠረት ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ይሰጣል።

ANSWER KEY FOR THE ENGLISH WORKSHEET ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ CHECK YOUR ANSWERS
ANSWER KEY FOR THE ENGLISH WORKSHEET ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ CHECK YOUR ANSWERS