cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . #ዝማሬ_ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Show more
Advertising posts
135 363Subscribers
+2624 hours
+2847 days
+71230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#እስመለአለም_ምህረቱ እስመለአለም ምህረቱ/4/ አያልቅም ብዙነው የአምላክ ቸርነቱ/2/ ከማርያም የነሳው ያቅዱስ ስጋው/2/ ቀራንዮ ሲውል የሚያሳዝን ነው/2/ በፈጠረው ፍጥረት እጅግ ተሰቃይቶ/2/ ነፍሳትን አወጣ ከሲኦል ጎትቶ/2/ የማይሞተው ሞቶ የተቀበረው/2/ ከገሀነም እሳት እኛን ሊያድን ነው/2/ አመስግኑት ጌታን ሁላችሁ በአንድነት/2/ መሀሪ ነውና ለሰው ልጆች ህይወት/2/ ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
53🕊 6
መች ይረሳል የበገና መዝሙር መች ይረሳል የዋለልን ውለታ ቸርነቱ እፁብ ፍቅር የጌታ የታተመው በልባችን ፅላት ሞትን ገድሎ የሠጠንን ህይወት በጥፋቱ ቢወጣ አዳም ከገነት ቃል ገባለት ዳግም ሊሰጠው ህይወት ህያው ጌታ አምላክ ፈጣሪ ሳለ ስለ ቃሉ በእፀ መስቀል ላይ ዋለ አዝ በአይሁድ እጅ በፅኑ ተንገላታ የፍቅር አባት ክርስቶስ የእኛ ጌታ ሥጋው ደክሞ ቅዱስ ደሙ ፈሰሰ እዳችንን በሞቱ ደመሠሠ አዝ ስንጠላው እርሱ አብዝቶ ወደደን ስለ ፍቅሩ ሞትን ገድሎ አዳነን ባርነትን ኃጢአትን ከኛ ጥሎ ነፃ አወጣን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ አዝ ሰላማችን የድንግል ማርያም ፍሬ ይገባዋል ምስጋና ዝማሬ ስለ ፍቅሩ ስላረገልን ሁሉ ተቀኙለት ፍጥረታት ዝም አትበሉ መምህር አቤል ተስፋዬ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
59🥰 6
በእጅ የያዙት ......... ። 👉 @ortodoxmezmur
Show all...
94😍 16
​​​​ኒቆዲሞስ 👉 የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት 🎤 በመምህር ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
56🕊 8
ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አዝ ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አዝ ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ ዲያቆን ዘማሪ ቀዳሚፀጋ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
81🥰 6😍 6🕊 3🔥 2
​​​​​​ኒቆዲሞስ - የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት። ''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። (ዮሐ 3:3-6) ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር። በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡ ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡ => ኒቆዲሞስ ማነው? ፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው 《ዮሐ 3-1》 ፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው《ዮሐ 3-1》 ፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው《ዮሐ 3-10》 ፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው 《ዮሐ 7-51》 => ኒቆዲሞስ ምን አደረገ? ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ 《ዮሐ 3:1-21) አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው 《ዮሐ 7-51》 ጌታን ለመገነዝ በቃ 《ዮሐ 19-38》 => ከኒቆዲሞስ ምን እንማር? አትኅቶ ርእስ ጎደሎን ማወቅ የእውነት ምስክር《ስምዐ ጽድቅ》መሆን ትግሃ ሌሊት እስከ መጨረሻ መጽናት በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡ የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡ የዕለቱ ምስባክ፦ "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ። አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕልየ። ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው"። መዝ17፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ3፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...

170🕊 9🔥 3😍 1
13/08/2016 ዓ.ምበዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ሮሜ. ፯፥፩ - ፲፪፤ ፩ ዮሐ. ፬፥፲፰ - ፍ፤ ግብ ሐዋ. ፭፥፴፬ - ፍ፤ የዕለቱ ምስባክመዝ ፲፮፥፫ ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፤ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው። ትርጉም፦ በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቤንም ፈተንኸው፤ ፈተንኸኝ ዓመፅ አልተገኘብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር። የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፫፥፩ - ፲፪ ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም 👉 @ortodoxmezmur
Show all...
63🕊 5🥰 2
🔰የዘማሪት የትምወርቅ ሙላት የበገና መዝሙሮች © ቤተ ዕንዚራ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
46🥰 8😍 5
በገና ክራር እና ከበሮ መማር የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን ምዝገባ ስለጀመርን። ሁላችሁም ደውላችሁ ትመዘገቡ እና በመንፈሳዊ ዝማሬ ልባችንን እናሳርፍ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ ለበለጠ መረጃ ☎️0912085085
Show all...
66🥰 17🔥 3