EECSF
Open in Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
Show more508
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
508
1bread of life
2the gate
3the truth, way and life
4the ressurection and life
5true vine
6the good shepard
7light of the world
These are the answers😊
508
ስለ ቃሉ ጌታ የተባረከ ይሁን!!
እንግዲህ በተማርንበት መሰረት እንድንኖር እንድናስተውልም ጌታ ይርዳን።
ቃሉን ያካፈለችንን እህት ህልዳና እግዚአብሔር ይባርክልን፣ያሳድግልን!!
508
▫️ባልጠበቅነው ሁኔታ ከብዙ ነገሮቻችን ተቆጥበን ፣ የሚበዛውን ጊዜ ከራሳችን ጋር ለማሳለፍ ተገደናል ፤ ቃሉ እንዲህ ይለናል ፦
1⃣ ❝ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።❞
—ኤርምያስ 29: 11
▶️ በባቢሎን ለተማረከው የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ያልጠበቁትን መልዕክት ተናገራቸው - በምርኮ ሀገር ተደላድለው እንዲኖሩ። ከእነርሱ ፈጥኖ ነፃ የመውጣት ሀሳብ ይልቅ በመዘግየቱ ያለውን የጌታን ሀሳብ አስታወቃቸው።
🔴 የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ እንጣል! 1 ጴጥ 5፥7
2⃣ ❝እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።❞
—2ኛ ጢሞቴዎስ 1: 7
▶️ ጌታ ኢየሱስ አብሮአቸው እያለ ደቀመዛሙርቱ በብዙ ሀሳብ ፣ ፍርሀትና ጭንቀት ነበሩ - በባህር መናወጥ ፣ ለሕዝቡ በቂ ምግብ ስላለመያዝ ፣ ስለዓልአዛር ሞት ፣ ስለጌታ ከእነርሱ መለየት ወዘተ. የሐዋ. ስራ ምዕራፍ 2 ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ሆነላቸው!
◽️ሰው በስጋው ውስን ስለሆነ ዘላለማዊውን ሳይሆን የጊዜውን ብቻ ያስባል
🔴የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያስፈልገናል!
3⃣ ❝በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥
ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥
ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥
ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥
ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥
መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥
በጎነት ቢሆን
ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤❞
—ፊልጵስዩስ 4: 8
🔴ሰው በልቡ እንዳሰበው እንዲሁ ስለሆነ የምናስበውን እንምረጥ!
🗣❝ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።❞
—ሮሜ 8: 6
🖐ተባረኩ!
508
👋እንዴት ናችሁ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ?👋 የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ!
🙏 በልቤ ያለውን ጥቂት ሀሳብ አካፍላችኋለሁ ፤ጌታ ቃሉን ይባርክልን!
🗯የሰው ልጅ ከሀሳብ አለፍ ሲልም ከጭንቀት ነፃ አይሆንም። እንደሌሎች ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት የጤንነት መለኪያዎች ቢኖሩትም የሚለየው የጤንነት መስፈርት ማሰብ መቻሉ ይመስለኛል።
💭ሰው የሚፈልገውን ስለማግኘት ያስባል ፣ ካገኘ በኋላ እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያስባል፣ ጤነኛ ስለመሆን ጤነኛ ሲሆንም ማድረግ ስለሚገባው ነገር ያስባል ወዘተ. በየደረስንበት ደረጃ በሀሳብ መዋጣችን አይቀሬ ነው ።
♦️የዚህ መነሻ በዘፍ 1፥26 "ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር" እግዚአብሔር እንዳለ ፣ የመግዛትና የሀላፊነት ባህርይ ከእርሱ መካፈላችን እንደሆነ አስባለሁ ፤ ስለሆነም ተገቢና ተፈጥሮአዊ ነው።
♦️ልዩነቱም እኛ ሰዎች ማድረግ የምንችለውንም የማንችለውንም ማሰባችን ነው ፤ እግዜአብሄር ግን በቃሉ ተደጋግሞ እንደተፃፈ "አሰበ" ሲል ሊያደርግ መነሳቱን የምናይበት ነው -እርሱ ሁሉን ቻይና የጊዜ ባለቤት ስለሆነ።
▫️የተሰጠንን ከማሰብ የማያርፍ አእምሮ እንዴት እንጠቀመው ፤ የሰጠን እግዚአብሔር ምን ይላል?
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
508
አሁን የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት ጊዜ ይሆናል ዛሬ ከወትሮው በተለየ መልኩ በፅሁፍ(text) ነው የምንካፈለው የጌታን ቃል የምታካፍለን እህት ህልዳና ነች ቃሉን አብረን እንካፈል!!
508
ማስታወቅያ
* ፀሎት እንዴት ነው? ቃልስ? እየተጋችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን😊።
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የሆናችሁ
ቅዱሳን ሆይ በፀሎትና በቃሉ በተሰጣችሁ ጊዜ ሁሉ ትተጉ ዘንድ እኛ የሕብረቱ መሪዎች እንለምናችኃለን። አያይዛቹም ስለ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ አንዳቹ ስለ አንዳቹ በብርቱ ፀልዩ።
* ሌላው ደግሞ እንዲህ ቢሆን መልካም ነው፣ እንዲህ ማድረግ ወይም ማዘጋጀት እፈልጋለሁ የምትሉ ካላችሁ እባካችሁ እንድታሳውቁን እንፈልጋለንና please አሳውቁን!!
የጌታ ፀጋ ከእናንተ ጋር ይሁን!!!
508
አሜን!!
ስለነበረን የፀሎት ጊዜ ጌታ ይመስገን፡፡
አሁን አምላካችንን በዝማሬ የምናመልክበት ጊዜ ይሆናል በዝማሬ የሚያገለግለን ወንድማችን አማኑኤል ነው፤ ተባረኩበት፡፡
508
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡ እስከ ፕሮግራማችን ፍፃሜ ድረስ አብራችሁን ቆዩ፣ ተባረኩ፡፡
