ch
Feedback
EECSF

EECSF

前往频道在 Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

显示更多
508
订阅者
无数据24 小时
无数据7 天
无数据30 天
帖子存档
1bread of life 2the gate 3the truth, way and life 4the ressurection and life 5true vine 6the good shepard 7light of the world These are the answers😊

😱😱😱...ጌዲ 1st year ጥያቄውን በትክክል መልሶታል 12:52 ላይ

# 1. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ራሱን "እኔ ነኝ" ብሎ የገለፀባቸውን 7 ስሞች ጥቀሱ፡፡ 100 MB ቀድሞ ለመለሰ ብቻ!!! መልሳችሁን👉 @DETAE1

እህም እህም😊😂 ዝግጁ?

ጥያቄ ቁጥር 1 ዝግጁ?

አሁን ሽልማት ወደሚያስገኙ ጨዋታዎች እናልፋለን አብራችሁን ቆዩ፡፡

ስለ ቃሉ ጌታ የተባረከ ይሁን!! እንግዲህ በተማርንበት መሰረት እንድንኖር እንድናስተውልም ጌታ ይርዳን። ቃሉን ያካፈለችንን እህት ህልዳና እግዚአብሔር ይባርክልን፣ያሳድግልን!!

▫️ባልጠበቅነው ሁኔታ ከብዙ ነገሮቻችን ተቆጥበን ፣ የሚበዛውን ጊዜ ከራሳችን ጋር ለማሳለፍ ተገደናል ፤ ቃሉ እንዲህ ይለናል ፦ 1⃣ ❝ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።❞ —ኤርምያስ 29: 11 ▶️ በባቢሎን ለተማረከው የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ያልጠበቁትን መልዕክት ተናገራቸው - በምርኮ ሀገር ተደላድለው እንዲኖሩ። ከእነርሱ ፈጥኖ ነፃ የመውጣት ሀሳብ ይልቅ በመዘግየቱ ያለውን የጌታን ሀሳብ አስታወቃቸው። 🔴 የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ እንጣል! 1 ጴጥ 5፥7 2⃣ ❝እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።❞ —2ኛ ጢሞቴዎስ 1: 7 ▶️ ጌታ ኢየሱስ አብሮአቸው እያለ ደቀመዛሙርቱ በብዙ ሀሳብ ፣ ፍርሀትና ጭንቀት ነበሩ - በባህር መናወጥ ፣ ለሕዝቡ በቂ ምግብ ስላለመያዝ ፣ ስለዓልአዛር ሞት ፣ ስለጌታ ከእነርሱ መለየት ወዘተ. የሐዋ. ስራ ምዕራፍ 2 ሌላ የሕይወት ምዕራፍ ሆነላቸው! ◽️ሰው በስጋው ውስን ስለሆነ ዘላለማዊውን ሳይሆን የጊዜውን ብቻ ያስባል 🔴የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያስፈልገናል! 3⃣ ❝በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤❞ —ፊልጵስዩስ 4: 8 🔴ሰው በልቡ እንዳሰበው እንዲሁ ስለሆነ የምናስበውን እንምረጥ! 🗣❝ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።❞ —ሮሜ 8: 6 🖐ተባረኩ!

👋እንዴት ናችሁ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ?👋 የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ! 🙏 በልቤ ያለውን ጥቂት ሀሳብ አካፍላችኋለሁ ፤ጌታ ቃሉን ይባርክልን! 🗯የሰው ልጅ ከሀሳብ አለፍ ሲልም ከጭንቀት ነፃ አይሆንም። እንደሌሎች ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት የጤንነት መለኪያዎች ቢኖሩትም የሚለየው የጤንነት መስፈርት ማሰብ መቻሉ ይመስለኛል። 💭ሰው የሚፈልገውን ስለማግኘት ያስባል ፣ ካገኘ በኋላ እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያስባል፣ ጤነኛ ስለመሆን ጤነኛ ሲሆንም ማድረግ ስለሚገባው ነገር ያስባል ወዘተ. በየደረስንበት ደረጃ በሀሳብ መዋጣችን አይቀሬ ነው ። ♦️የዚህ መነሻ በዘፍ 1፥26 "ሰውን በመልካችን እንደምሳሌአችን እንፍጠር" እግዚአብሔር እንዳለ ፣ የመግዛትና የሀላፊነት ባህርይ ከእርሱ መካፈላችን እንደሆነ አስባለሁ ፤ ስለሆነም ተገቢና ተፈጥሮአዊ ነው። ♦️ልዩነቱም እኛ ሰዎች ማድረግ የምንችለውንም የማንችለውንም ማሰባችን ነው ፤ እግዜአብሄር ግን በቃሉ ተደጋግሞ እንደተፃፈ "አሰበ" ሲል ሊያደርግ መነሳቱን የምናይበት ነው -እርሱ ሁሉን ቻይና የጊዜ ባለቤት ስለሆነ። ▫️የተሰጠንን ከማሰብ የማያርፍ አእምሮ እንዴት እንጠቀመው ፤ የሰጠን እግዚአብሔር ምን ይላል? 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

አሁን የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት ጊዜ ይሆናል ዛሬ ከወትሮው በተለየ መልኩ በፅሁፍ(text) ነው የምንካፈለው የጌታን ቃል የምታካፍለን እህት ህልዳና ነች ቃሉን አብረን እንካፈል!!

ማስታወቅያ * ፀሎት እንዴት ነው? ቃልስ? እየተጋችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን😊። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የሆናችሁ ቅዱሳን ሆይ በፀሎትና በቃሉ በተሰጣችሁ ጊዜ ሁሉ ትተጉ ዘንድ እኛ የሕብረቱ መሪዎች እንለምናችኃለን። አያይዛቹም ስለ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ አንዳቹ ስለ አንዳቹ በብርቱ ፀልዩ። * ሌላው ደግሞ እንዲህ ቢሆን መልካም ነው፣ እንዲህ ማድረግ ወይም ማዘጋጀት እፈልጋለሁ የምትሉ ካላችሁ እባካችሁ እንድታሳውቁን እንፈልጋለንና please አሳውቁን!! የጌታ ፀጋ ከእናንተ ጋር ይሁን!!!

ስለ ዝማሬው ጊዜ እግዚአብሔር ይመስገን በዝማሬ ያገለገለን ወንድም አማኑኤል ጌታ ይባርክህ፣ያሳድግህ፡፡

* ዝማሬ አማኑኤል አበራ #EECSF_Tune Join and share EECSF Channel: @EECSF

አሜን!! ስለነበረን የፀሎት ጊዜ ጌታ ይመስገን፡፡ አሁን አምላካችንን በዝማሬ የምናመልክበት ጊዜ ይሆናል በዝማሬ የሚያገለግለን ወንድማችን አማኑኤል ነው፤ ተባረኩበት፡፡

* ፀሎት ሱራፌል ፈቀደ የማክሰኞ ሕብረት

መግቢያ.m4a7.16 KB

እስኪ ጥቂት ደቂቃ ከሱራፌል ጋር አብረን እንፀልይና ዛሬ ወዳዘጋጀናቸው የምንተናነፅባቸውን ፍሬ ነገሮች አብረን እንካፈላለን

ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለእርሱ
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡ እስከ ፕሮግራማችን ፍፃሜ ድረስ አብራችሁን ቆዩ፣ ተባረኩ፡፡

Be On---
Be On---

#EECSF_Graphics Join and share EECSF Channel: @EECSF
#EECSF_Graphics Join and share EECSF Channel: @EECSF