en
Feedback
EECSF

EECSF

Open in Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

Show more
508
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ከህይወት የላቀ የ ምህረት ሁሉ ምንጭ,

የመጫወቻ ርዕስ(ቃል)👇👇👇 👉ምህረት👈 ጨዋታው ተጀምሯል

👍

የጨዋታው አሸናፊ 30 ደቂቃ voice package የ250 mb internet package የ20 sms package አሸናፊ ይሆናል።

የመጀመሪያውን ስንኝ ጀማሪ senior batch ሰለሆነ ዞላ ይጀምራል። ተጫዋቾች ዝግጁ ናችሁ🤔 ዝግጁነታችሁን ቢዚህ👍 emoji አሳዩኝ

የቃላት ጨዋታ ህግጋት 👉 ሁለት እንግዶች ይጫወታሉ። 👉 ከአጫዋች ቃላት ሊያስወረውር የሚችል ቃል ይሰጣል። 👉 በተሰጠው ቃል ላይ ተጫዋቾቹ ትርጉም ያለውና ቤት የሚመታ ስንኝ ከተቃራኒ ተጫዋች ስንኝ በመቀጠል ይፅፋሉ። 👉 አንድ ስንኝ ለመፃፍ አምስት ደቂቃ ይሰጣል። 👉 ከተሰጠው ደቂቃ ቀድሞ መፃፍ ይመረጣል አንድ ደቂቃ በቀደመው ልክ አንድ ተጨማሪ ነጥብ ያገኛል። 👉 ዘግይቶ የፃፈ ነጥብ ያጣል ግን ጨዋታውን ይቀጥላል። 👉 አስር ደቂቃ እና ከዚያ በላይ የቆየ ተሸናፊ ይሆናል። 👉 አሸናፊ በየሳምንቱ እርሱን የሚረታ ተጫዋች እንግዳ እስኪመጣ ድረስ ጨዋታውን ይቀጥላል። 👉 እንዲሁም አሸናፊው ከእርሱ ጋር ቀጣይ ሊጫወት የሚፈልገውን ሰው የመምረጥ እድሉ ይሰጠዋል። 👉 በየሳምንቱ ለአሸናፊ ሽልማት ይኖረናል። እዲሁም በተከታታይ ለሶስት ሳምንት ላሸነፈ ልዩ ሽልማት ይኖረናል።

ከዚ በመቀጠል የቃላት ጨዋታ የተሰኘው የእንግዶች ጨዋታ ይቀጥላል። ጨዋታውን የሚጫወቱት ተጫዋቾች ዞላ እና ካሌብ(ችዋ) ይሆናሉ።

📦 የዛሬው የሽልማት ስፖንሰራችን 📦 👉 @Bernoscrafts እናመሰግናለን 😷 Bernos Facemask 😷 0996737393 @Samuuel @Bernoscrafts
📦 የዛሬው የሽልማት ስፖንሰራችን 📦 👉 @Bernoscrafts እናመሰግናለን 😷 Bernos Facemask 😷 0996737393 @Samuuel @Bernoscrafts

የጥያቄው መላሽ ዞላ ነው። መልስ: የመንግስቱን እሴቶች መኖር! Living the kingdom values!

ጥያቄ ቁጥር አንድ: የEiABC fellowship የ2012 ዓ.ም መሪ ጥቅስ ምን የሚል ነበረ። መልሳችሁን በ @AbexAB አድርሱን። የጥያቄው መላሽ የ100 mb internet package የ20 sms package አሸናፊ ይሆናል።

በትረካው እንደተባረካችሁበት ተስፋ አለኝ። ከዚህ በመቀጠል ሽልማት ወደሚያስገኘው ጥያቄ እንሄዳለን።

AB_Audio_Art ____ጊዜ__ ፀሐፊና አንባቢ፡- ህይወት ያላዩ ሙዚቃ:- በለጠ ኤርሚያስ @AB_Audio_Art @AB_Audio_Art @AB_Audio_Art

እሺ አሁን በመቀጠል አንዲት ጥኡም የሆነች ትረካ አድምጠን እንመለሳለን። አሁንም እስከመጨረሻው አብራችሁን ቆዩ። ትረካው ከ @AB_Audio_Art ጋር በመተባበር ወደእናንተ ይቀርባል።

✨በጉን የለበስኩ ለት✨ ታናሽ ነኝ፡፡ ብኩርና ፈፅሞ የማይገባኝ ከታላቅነት ለሚገኝም በረከት ያልታደልኩ ነበርኩ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በኤሳው ቀንቼ አውቃለሁ፡፡ በታናሽነቴ የተበሳጨኹባቸው ቀናትም ብዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ታናሽ ነኝ፡፡ በኩርነት የማይገባኝ ከታላቅነት ሚገኝ ክብርና በረከት ማይመጥነኝ ታናሽ!! ከእለታት በአንዱ ግን በኩር ሆንኩ፡፡ ታናሽ ብሆንም ከታላቅነት ሚገኘውን ክብርና በረከት ተቀበልኩ፡፡ ማይገባኝን እንደሚገባኝ ያደረገው ታናሽነቴን በታላቅነት የለወጠው ማይመጥነኝን በረከትና ክብርን የሰጠኝ የለበስኩት የበግ ልብስ ነበር፡፡ አባታችን ይስሃቅ ሰውነቴን ሲዳስስ የነካው የበጉን ሰውነት ነበር፡፡ የሸፈነኝ በግ ታላቅ አደረገኝ፡፡ የታረደውን በግ የለበስኩ ለት ከታናሽነት ወደታላቅነት ተሸጋገርኩ፡፡ አባቴ ሰውነቴን ቢዳስስ ኖሮ አጉል እሁን ነበር፡፡ ዳሩ በጉ ሰውነቴን ሸፍኖት ነበርና ታሪኬ ተለወጠ፡፡ ያን ለት ከያእቆብነት ወደ እስራኤልን የመለወጥን ጉዞ ጀመርኩ፡፡ የታረደውን በግ ለብሼ ከአባቴ በረከትን ተቀበልኩ (ተስፋአብ ተሾመ) Christian Literature

እንደመግቢያ ከታደኑ ፅሁፎቻችን አንዱን ተከታትለን እንመለስስ።

ይህ የጥበብ ምሽት ወደእናንተ የሚቀርብላችሁ @AB_Audio_Art ከ @EECSF ጋር በመተባበር ነው። ✨እስከመጨረሻው አብሮን የሚቆይ ብዙ ያተርፋል።✨

✨ወድ የጥበብ ልጆች እነሆ የዛሬው ኘሮግራማችን አሁን ተጀመረ።✨ ✨የዛሬው ምሽት የጥበባችን ስንቆች✨ 👉ትረካ (ዘመን) 👉ምርጥ የታደኑ አጫጭር ፅሁፎች 👉የቃላት ጨዋታ ከእግዶች ጋር 👉ግጥም (ቀይ ናት) 👉የሚያሸልሙ ጥያቄዎች

https://youtu.be/ObWa9u3pmKk መጋቢ ዮናታን ተኬ ተልዕኮ መር ሕይወት ክፍል 2 ደቀመዝሙርነት እራሳችንን የምናስለምድበት ሂደት እንደሆነ፤ እግዚያብሔር እኛን የሚሰራበት እንደሆነ፤ ክርስቶስን ወደመምሰል የምናድግበትን እደሆነና፤ በእኛ አማካኝነት ለሌሎች የእግዚያብሔርን ክብር መግለጥ እንደሆነ ይስረዳል:: ቪዲዮውን ተመልከቱት ለሌሎችም ያጋሩት!

✨ዛሬ ማታ 2:30 ላይ ይጠብቁን✨ የጥበብን ጌታ በጥበብ የምናወድስበት ምሽት ይሆናል! ✨የዛሬው ምሽት የጥበባችን ስንቆች✨ 👉ትረካ 👉ምርጥ የታደኑ አጫጭር ፅሁፎች 👉የቃላት ጨዋታ ከእግዶች ጋር
✨ዛሬ ማታ 2:30 ላይ ይጠብቁን✨ የጥበብን ጌታ በጥበብ የምናወድስበት ምሽት ይሆናል! ✨የዛሬው ምሽት የጥበባችን ስንቆች✨ 👉ትረካ 👉ምርጥ የታደኑ አጫጭር ፅሁፎች 👉የቃላት ጨዋታ ከእግዶች ጋር 👉ግጥም 👉የሚያሸልሙ ጥያቄዎች