cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Master Mind Group

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ። ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን። . የሰራ ፈጠራ ስልጠና . ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና . የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ . ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ። . አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ . በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Show more
Ethiopia3 224Amharic3 102The category is not specified
Advertising posts
2 615
Subscribers
No data24 hours
-137 days
-5830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from Ambassador
Photo unavailableShow in Telegram
ዲሲፕሊን! ዲሲፕን ማለት አንድን ነገር የማድረግ ፍላጎቱ ባይኖረንም እንኳ ጠቃሚ ስለሆነ ብቻ ራስን በማስገደድ በየእለቱ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዲሲፕሊን ማለት አንድን ነገር የማድረግ ፍላጎት እያለን ሳለ፣ ነገሩ ጥቅመ-ቢስና ጎጂ ስለሆነ ብቻ ራሳችንን በመግዛት ከማድረግ ራስን መከልከል ማለት ነው፡፡ በእነዚህ በሁለቱ የዲሲፕሊን ትርጉሞች መሰረት የማያቋርጥ ልምምድ ያለው ሰው 80 በመቶው የሕብረተሰቡ ክፍል ያልተለማመደው አስገራሚ ልምምድ ላይ ደርሷል፤ ለላቀ ስኬትም ራሱን እያዘጋጀ ነው፡፡ ይህ የዲሲፕሊን ልምምድ ወደ አንድ አስገራሚ ዓለም ያሻግረዋል፡፡ ይህ አስገራሚ ዓለም የልማድ ዓለም ነው፡፡ ልማድ ማለት አንድን ቀድሞ ማድረግ የማንችለውን ወይም የማንፈልገውን ነገር ራሳችንን በዲሲፕሊን በማስገደድ ከመደጋገማችን የተነሳ ላለማድረግ እስከማንችል ድረስ ስንለምደው ማለት ነው፡፡ በአንድ ነገር ዙሪያ ዲሲፕሊን እንደከምታዳብሩ ድረስ ከተለመደው አዙሪት አትወጡም፡፡ አንድን ዲሲፕሊን ደግሞ ልማድ እስከሚሆን ድረስ ካልደጋገማችሁት የጀመራችሁት ነገር ስለማይጸና ታቋርጡታላችሁ፡፡ ይህ ጀምሮ የማቋረጥ ሁኔታ ደግሞ የራስ-በራስ ምልከታችሁን፣ እንዲሁም ለራሳችሁ ያላችሁን አክብሮትና ግምት እጅጉን ያወርደዋል፡፡ በርቱና የዲሲፕሊንና የልማድ ሰው ለመሆን ስሩ!  መልካም ቀን!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በህብረት ስራ ማህበራት አማካይነት የሚመረቱ የግብርና ምርቶች በቀጥታ ለሸማቹ ማድረስ  እንዲችሉና አምራቹም ባመረተው ምርት ተጠቃሚ ሆኖ የተሻለ አምራች እንዲሆን በ ኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የኢትዮጲያ ህብረት ስራ ኮሚሽን የተለያዩ አማራጮችን አቅዶ እየሰራ ይገኛል። በዚህም መሰራት ከሳምንት በፊት ኮሚሽኑ በስካይላይት ሆቴል ባዘጋጀው የባለድርሻ አካላት ምክክር እና ትስስር ፕሮግራም ድርጅታችን እንዲገኝ በተጋበዘው መሰረት የድርጅታችን መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማቲዎስ መባ የተገኙ ሲሆን በምክክር መድረኩ ከተገኙ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች እና የህብረት ስራ መሀበራት አመራሮች ጋር በቀጣይ አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዬች ላይ ምክክር አድርገዋል። www.etcareproduct.com #etcare #icare #youcare #wecare @etcareofficial
Show all...
Repost from Dr. Eyob Mamo
Photo unavailableShow in Telegram
በቃ ልመዱት !!! • ሰዎች “አደርገዋለሁ” ብለው የገቡላችሁን ቃል ኪዳን ላይፈጽሙ ይችላሉ - ልመዱት! • ዛሬ የሚወዷችሁና የሚያከብሯችሁ ሰዎች ነገ ሊጠሏችሁና ሊንቋችሁ ይችላሉ - ልመዱት! • ዛሬ ምስኪን መስለው ለሕልውናቸው በእናንተ እርዳታ ላይ የተደገፉ ሰዎች ነገ ውለታ-ቢስ ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ - ልመዱት! • ሰዎች የሆናችሁትን ማንነት ሳይሆን ያላችሁን ቁሳቁስ አይተው እንደቀረቧችሁ ልትደርሱበት ትችላላችሀ - ልመዱት! • አንዳንድ ሰዎች በሰላሙ ጊዜ የሰሙትን ምስጢራችሁን ግንኙነታችሁ ሻከር ሲል ለወሬና እናንተንው ለማጥቃት ሊጠቀሙበት ይችላሉ - ልመዱት! እነዚህንና እነዚህን መሰል በማንኛውም ሕብረተሰብ መካከል የሚንጸባረቁ የሰዎች ባህሪያትን መልመድ ማለት፣ ሁል ጊዜ ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር እንደማናገኝ መገንዘብና ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ ከሰዎች የምንጠብቀውን መልካም ነገር ስናገኝ ደስ የመሰኘታችንንና ሰዎቹንም የማመስገናችን ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለማንኛውም አይነት ወጣ ያለ የሰዎች ሁኔታ ራስን ማዘጋጀትና ከሁኔታው ባሻገር አልፎ ለመሄድ የውስጥ ውሳኔን መወሰን እጅግ ጠቃሚ ልምምድ ነው፡፡ እንደሰው የመለዋወጥ ሁኔታ የሚለዋወጥ ሰባራ ማንነት እንደሌላችሁ ለራሳችሁ የምታስመሰክሩበት ቀን ይሁንላችሁ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አይቀርም
Show all...
Repost from Dr. Eyob Mamo
Photo unavailableShow in Telegram
ቀኑ የሰላም ቀን ነው! የዛሬዋ ቀን የሰላምና ደስ የምትል ቀን ናት! • ዛሬ ከምንም ነገር በፊት ሰላማችሁን አስቀድሙ! • ሰላማችሁን ከሚረብሽ ሰው ራቁ! • ሰላማችሁን ከሚነጥቅ ንግግር ተቆጠቡ! • ሰላማችሁን ከሚቀማችሁ ተግባር ራሳችሁን ጠብቁ! • ሰላማችሁን ከሚወስድ ማሕበራዊ ሚዲያ ተጠበቁ! ሁሉም ነገር የሚጥመው በቅድሚያ ሰላም ስንሆን ነው! የሰላም ቀን ይንላችሁ! ይህንን የሰላም መልእክት ቢያንስ ለሶስት ሰዎች በማጋራት የሰላም መሳሪያ ሁኑ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Repost from Elite Ambassadors
My REALIZATIONS about GETTING STARTED. 1) You only need ONE thing to get started. One smile can start a friendship. One hand can lift a soul. One candle can wipe out darkness. One word, one child, one teacher, one pen and one book can change the world. Be that ONE. 2) You don’t have to be smarter than the rest. You just need to be more disciplined than the rest and get started. 3) Conquer yourself. Your success or failure in life or at work isn’t about other people. It’s your procrastination and excuses. Success happens when you grow yourself, not outgrow others. Winners focus on winning. Losers focus on winners. 4) Nothing changes if nothing changes. When you change how you see things, both you and the things you see change. You see the world what you carry in your heart. 5) Every teacher once was a student. Every winner once was a loser. Every expert once was a beginner. Small steps taken every day leads you to your success. 6) Perseverance is the multiplier of Talent and Potential. Success is not about who has more talent, but who is hungrier. A river cuts through a rock not because of its power, but its persistence. You can do anything you set your mind to, but it takes action, persistence, and the courage to face your fears. 7) Stress comes from ignoring things that you should not be ignoring. Break down the task and start small. A journey of 1000 miles start with one step. Don't wait to be in the mood to do a certain task. Motivation follows action. Get started, and you'll find your motivation will follows. Don't worry about the darkness when you take that first step, for that is when the stars shine brightest. 8)You can become a person of value in a matter of months. Every mountain top is within your reach if you keep climbing. If you aren’t winning, you must be learning. 9) Once you start, no matter how long you have travelled in the wrong direction, you can always turn around. When you can’t change a situation, change yourself. Intelligence is the ability to adapt to change. 10) Risk is better than regret. Take that first step. The biggest risk is not getting started. If you want something you’ve never had, then you must do something you’ve never done. Don’t procrastinate. Take that first step. Written By Cedric Ng
Show all...
Repost from Elite Ambassadors
FOCUS! Imagine you're on a path to achieving your goals, but suddenly, the dogs start barking. Their noise is distracting, but remember, dogs bark. It's what they do. You can't control their barks, but you can control your response. Ignore them, focus on your journey, and keep moving forward. Life is too short to let the barking dogs of distraction steer you off course. Stay true to your purpose, keep your eye on the prize, and stay focused. Embrace the challenge, keep pushing, and one day you'll look back and realize that those barking dogs were just background noise on your path to greatness. Have beautiful dream! great time @ etcare torhayiloch!
Show all...
Repost from Dr. Eyob Mamo
ራእይ እያለ እንደሌለ! (“ራእይን ማወቅና መኖር” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) ከራእይ አውድ አንጻር፣ ይህንን ጽሑፍ የምናነብ ሰዎች በሶስት እንከፈላለን፡- 1. ምንም አይነት ራእይ የሌለን ወይም ራአያችንን የማናውቅ፡፡ 2. ራእይ እያለንና እያወቅነው በዚያ አቅጣጫ መሄድ ያልቻለን፡፡ 3. ራእያችንን በማወቅ በዚያ አቅጣጫ መንገድ የጀመርን፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ ምድር ላይ ካለምንም ራእይ (ካለምንም ዓላማ ማለት ነው) የሚወለድ ሰው አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ልዩነቱ ያለው ከተወለድን በኋላ የምልፍባቸው ሁኔታዎችና ያሳደጉን ሰዎችም ሆነ የአካባቢያችን ሕብረተሰብ የአኗኗር ዘይቤ ያመጣብን ጫና ራእይ እያለን ልክ እንደሌለን ኖረን እንድናልፍ ያደርገናል፡፡ ራእይ እያለን ልክ እንደሌለው ሰው ታስረን እንድንቀመጥ ከሚያደርጉን እንቅፋቶች መካከል የሚገኙትን ይገኙበታልና በጥንቃቄ መመልከቱና ከመንገዳችን ላይ ማስወገዱ አስፈላጊ ነው፡፡ 1. ባለፈው ታሪክ መኖር የራእይ ጉዳይ ከወደፊታችን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ የወደፊታችንን በሚቀርጽ ጉዳይ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ካላቸው ነገሮች አንዱ የኋላችን ላይ የማተኮር ሁኔታ ነው፡፡ ያለፈው ታሪካችንና ልምምዳችን በወደፊቱ ራእያችን ላይ መልካም መዋጮን የማድረጉን ያህል ወደ ኋላ ሊጎትተንም እንደሚችል በማሰብ ያለፉ ስህተቶችን በጥንቃቄ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ሕይወት እስከኖርን ድረስ የስህተትም ሆነ የስኬት ልምምዶች እንዳሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህን የተለያየ ገጽታ ያላቸውን ልምምዶች በተገቢው መንገድ መያዝ ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በሃሳባችን እየተመላለሰ ውስጣችንን የሚያደክመውን ያለፈ ስህተት ጉዳይ ማሸነፍ አስፈላጊ ነው፡፡ ልናተኩር የሚገባን በወደፊት ራእያችን ላይ ሊሆን ሲገባው ባለፈው ታሪክ መያዝና ወደኋላ መጎተት ከብዙ ስኬታማ ጉዞ የሚገታን ጉዳይ ነው፡፡ 2. የስኬት ማጣት ፍርሃት ፍርሃት ብዙ አይነት ገጽታ አለው፡፡ ይህ ስኬትን የማጣት የፍርሃት አይነት ማንኛውም አዲስ ነገርን ለመጀመር የሚፈልግ ሰው የሚጋፈጠው ፍርሃት ነው፡፡ በፊታችን ልንገባበት የምናስበውና ራእይ ብዙ ነገራችንን ዋጋ ሊያስከፍለን ስለሚችል ምናልባት ካልተሳካ ሊደርስብን ይችላል የምንለው ቀውስ ያስፈራናል፡፡ በተሳካ ሁኔታ ወደፊት ለመቀጠል ግን ይህንን እንቅፋት ማሸነፍ ግን የግድ ነው፡፡ የስኬት ማጣትን ፍርሃት ለማስወገድ ካስፈለገ የስኬትን ትርጉም በሚገባ መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ ስኬት ማለት አለመድከም፣ አለመወላወል፣ እንቅፋትን አለመጋፈጥ፣ አለመውደቅና … እንደሆነ ከማሰብ መጠበቅ አለብን፡፡ በዚያ ምትክ ስኬት ማለት የብዙ ውጣ ውረዶች ጎዳና መሆኑን በመገንዘብ ሁኔታዎች ለጊዜው ተሳኩም አልተሳኩም ከራእያችን አቅጣጫ አንጻር ወደፊት የመሄድን ልምምድ ማዳበር የግድ ነው፡፡ 3. ሰው-ተኮር መሆን በእያንዳንዱ በምናደርገው ነገር ላይ ሰዎች ያላቸው አመለካከት ምን እንደሆነ የመጨነቅ ዝንባሌ ካለን፣ ራእያችንን በጽንአትና በትኩረት ለመከተል ያስቸግረናል፡፡ ራእዩን ለይቶ ለማወቅ፣ ለመቅረጽና ለመከተል በተነሳ ሰው ላይ ሰዎች የተለያዩ ወደ ኋላ ሊጎትቱ የሚችሉ አመለካከቶችን ሊያንጸባርቁ ይችላሉ፡፡ ይህንን የተለመደ እውነታ ደግሞ ለማለፍ የቆረጠ ማንነት ያስፈልጋል፡፡ እኛ እውነት ሆኖና በሚገባ ገብቶን በምንከተለው ራእይና ዓላማ ላይ ሰዎች ምንም አይነት አመለካከት ለመያዝ መብት እዳላቸው መቀበል ልቦናን ያሳርፋር፡፡ ሰዎቹ የሚያስቡትና የሚናገሩት ላይ ከማተኮር ይልቅ ራእያችን ላይ ማተኮር ስኬታማ ያደርገናል፡፡ በተጨማሪም፣ የሚቃረን ሃሳብ ያላቸውን ሰዎች ከመስማት ይልቅ ሊያበረታን የሚችል ሃሳብ ያላቸው ሰዎች አካባቢ መሆን ይበጃል፡፡ 4. የክህሎት ችግር አንዳንድ ሰዎች ምንም እንኳን ራእያቸውን ወደማወቅ ቢመጡም ያንን በውስጣቸው የሚያውቁትን ራእይ በምን መልኩ መስመር እንደሚያስይዙት፣ እንደሚገልጹትና ተግባራዊ ወደመሆን እንደሚያመጡት መላውን አያውቁትም፡፡ ይህ ሁኔታ ከክህሎት ጋር የተገናኘ ሁኔታ ነው፡፡ አንድ ሰው ራእዩን ካወቀ በኋላ ወደ የት እንደሚወስደው ካላወቀ ያንን ክህሎት የማሳደግ ጉዞ ሊጀምር ይገባዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የክህሎቱ አቅም ሲያንሳቸውና ያንንም ማሳደግ ካልፈለጉ አንድ ሰው ሊኖረው የሚገባውን ራእይ-ተኮር ጉዞ ከብዙ ፍልስፍና ጋር በማነካካት የራእይ እውነታ የማጣጣል ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሰዎች፣ የምንኖረው አስቀድሞ የተወሰነልንን ነገር ስለሆነና እኛ በዚያ ነገር ላይ ምንም ቁጥጥር ስለሌለን የመጣውን ዝም ብለን መቀበል እንዳለብን ያስባሉ፡፡ ይህ የተዛባ ፍልስፍና ከራእይ ቀጠና ያወጣናል፡፡ (መጽሐፉን ለመግዛት፡- 0924126841) https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Repost from Dr. Eyob Mamo
Photo unavailableShow in Telegram
ራእይ እያለ እንደሌለ!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ዝግጁ ናችሁ? የኢቲኬር የ1 አመት ጉዞ የሚበሰርበት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የምርት አስተዋዋቂ የሚገኝበት የኢቲኬር 1ኛ አመት ክብረበዓል ቅዳሜ ግንቦት 19 2015 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል www.etcareproduct.com #icare #youcare #wecare #etcare @etcareofficial
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.