1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ስለ እንጦጦ - አራት ኪሎ ኮሪደር፦
ከእንጦጦ -አራት ኪሎ የተገነባው የኮሪደር ልማት የአካባቢውን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር ፍትሃዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን በተግባር ያረጋገጠ ነው።…
See more
ሌላ ስኬት !
ከ1521 በላይ ሱቆችን የያዘ ፣ በርካታ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ያገኙበት የሰዉ ሀብት ልማት፣ኮሪደር ልማት ፤ የዛሬው ስኬት ፣ ነገም ይቀጥላል‼️
የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ዛሬ የተመረቀዉ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ምን አካቶ ይሆን?… See more
የሁለተኛው ዙር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውና ዛሬ የተመረቀዉ ከ4 ኪሎ እስከ እንጦጦ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ምን አካቶ ይሆን?… See more
ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ባለፈ በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል ከመቼውም ጊዜ በላይ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ዛሬ የምናስመርቃቸው 4 ኪሎ እስክ እንጦጦ ኮሪደር እውነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ጋር በመሆን አዲሱን እና ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ ተሠርቶ የተጠናቀቀውን ኮሪደር ዛሬ ጠዋት ተመልክተናል። ይኽ አስደናቂ ለውጥ ከተካሄደባቸው የከተማችን ክፍሎች አንዱ ነው።
Together with Prosperity Party Central Council members, we have reviewed the entire pathway of the Entoto to Arat Kilo Plaza corridor development that has been completed unveiling anothe section of our city rang has undergone a great transformation.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ
ለረዥም ጊዜ የህብረተሰቡ የቅሬታ ምንጭ የነበሩ የመንገድ ላይ መብራት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ መደረጉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ፡፡ ለዝርዝር ዘገባው በቀጣዪ ቪዲዮ ይመልከቱ 👉👉
የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ የመንገድ መብራት ጥያቄ መፍታት የቻለ ተቋም መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።
ለረጅም ጊዜ የህብረተሰቡ የቅሬታ መንስኤ የነበሩ በርካታ የመንገድ መብራት ጥያቄዎችን በመፍታት ረገድ የከተማችን የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን እያከናወናቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎች ከተማ አስተዳደሩ በመንገድ ዳር መብራት ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት የተከተለውን ስትራቴጂካዊ ውሳኔ ትክክለኛነት ማሳያ እንደሆነ በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስገነዘቡ።
ለረጅም ጊዜ የህብረተሰቡ ቅሬታ ሆኖ የቆየውን የአራራት- ኮተቤ - ካራን የመንገድ መብራት ሙሉ በሙሉ በማብራት አገልግሎት መስጠት እንደተቻለ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ አና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የመንገድ መብራት ስራውን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት አረጋግጠዋል፡፡
ለዚህም የአራራት ኮተቤ -ካራ መንገድ ላይ የተከናወነው የመብራት መሰረተ-ልማት ዝርጋታና ጥገና ስራ አንዱ መሆኑን አንስተው፤ የታየው ለውጥ ከተማችን የቀን ብቻ ሳትሆን ምሽትም ጭምር የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ በማቀላጠፍና አካባቢውን ብርሀን በማድረግ ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ አፅንኦት የሰጡት ጉዳይ በከፍተኛ የህዝብ ሀብት የለሙ መሰረተ-ልማቶች አገልግሎት የሚሰጡት ለራሳችን በመሆኑ ከሚፈፀም ማንኛውም ስርቆት፣ ብልሽትና የተሽከርካሪ ግጭት ግንባር ቀደም ሆነን መጠበቅ ይገባናል ብለዋል፡፡
የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ያስጎበኙት የከተማው የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፤ ይህን አካባቢ ጨምሮ በከተማዋ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ዋና መንገዶች፣ የጋራ መኖሪያ አካባቢዎች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ አስፈላጊውን የመስመር ዝርጋታ፣ ተከላና ጥገና ስራዎችን በማከናወን ለህብረተሰቡ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የምሽት እንቅስቃሴ በቂ ብርሀን እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
በተለይም ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የተጎበኘው ይህ መንገድ፤ ህብረተሰቡ ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ሲያቀርብበት የነበሩ መሆኑን አስታውሰው፤ ባለስልጣን መ/ቤቱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማከናወን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ባደረገው የጥገና ስራ በሁለቱም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሬ አሁንም ያልተሸገርነው ዋነኛ ችግር ብለው ያነሱት መሰረተ-ልማቱን በመጠበቅና በመንከባከብ ረገድ ሲሆን ለዚህም በተሰራ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዚሁ መንገድ ላይ ከትራንስፎርመር ወደ ፖሎች የሚሄደውን የኬብል መስመር መንገዱን ቆፍረውና ኬብሉ ተቆርጦ መሰረቁ አንዱ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ከዚሁ አያዘው በለማው መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆት መልሶ ህብረተሰቡን ለዘርፈ ብዙ ችግር የሚዳርግ ከመሆኑ ባለፈ ከፍተኛ የህዝብ ሀብት እንዲባክን የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ከምንም በላይ ህብረተሰቡ የመሰረተ-ልማቱ ባለቤት መሆኑና በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ ተሳታፊ በመሆን ከባለስልጣኑ ጎን እንዲቆሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የእኛ ፖለቲካ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በዉጤት የታጀበ ስራ ነው ።
Siyaasni keenya fayyadamummaa uummataa kan mirkaneessu hojii milkaa'inaan dabaalameedha.
