en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የእኛ ፖለቲካ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በዉጤት የታጀበ ስራ ነው ። Siyaasni keenya fayyadamummaa uummataa kan mirkaneessu hojii milkaa'inaan dabaalameedha.

4 ኪሎ ፕላዛ፣ 4 ኪሎ የገበያ ማዕከል እና መኪና ማቆሚያ የድል ሃውልታችንን ከበው ትላንታችንን ከዛሬ እና ከነገአችን ጋር አገናኝተው ደምቀው አድምቀውናል Pilaazzaa 4 kiiloo,Giddu gala gabaa 4 kiiloo fi bakka dhaabbii konkolaataa siidaa injifannoo keenya marsanii kaleessa keenya haraa fi boruu keenya waliin wal qunnamsiisanii miidhaganii nu miidhagsaniiru

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት አቶ አዲሱ አረጋን የግብርና ሚንስቴር ሚንስትር አድርገው ሾመዋል።

የአዲስ አበባ የዉንዝ ዳርቻ ልማት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንደበት ፦ Misooma qarqara laga Finfinnee afaan kabajamoo muummicha ministeeraa keenyaatiin! See less

ከሁሉም በላይ የልባችንን ቀና መሻት ተመልክቶ በነገሮች ሁሉ መሳካትን ለሰጠን ፈጣሪ ምስጋና ይሁን!! ራዕያችንን ተጋርታችሁ ደማቅ ታሪክ ለፃፋችሁ የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ! ዛሬ ማምሻዉን የፒያሳን መልሶ ማልማት፣ በ 4 ኪሎ እንጦጦ ፣ጉለሌ የእፅዋት ማዕከል የኮሪደር ልማትና የእንጦጦ ወዳጅነት አደባባይ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ስራ ላይ የላቀ አስተዋፆ ላበረከቱ አካላት የእዉቅናና የምስጋና ማበረታቻ አካሂደናል ። በሽታ አምጪ የነበረዉን የወንዞቻችንን ጠረን ተቋቁማችሁ ፣ ለክረምቱ ዝናብ እና ቁር ሳትበገሩ ፣ የጤና ሁኔታችሁን አደጋ ላይ ጥላችሁ ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ራዕያችንን ተጋርታችሁ ይህንን የመሰለ መጪዉ ትዉልድና መላዉ አገር ወዳድ ኢትዮዽያዊ የሚኮራበትን አስደናቂ ስራ በመስራታችሁ ወደፊትም ታሪክ ሲዘክራችሁ ይኖራል ። በተለይም የወንዝ ዳርቻ ልማት ከ2012 ዓ.ም አንስቶ የዉጭ መንግስታትን ፣ ደጋፊ አካላትን እገዛ ጠይቀን በርካታ ጥረት ብናደረግም በ5 አመት ከ 2 ኪ.ሜ በላይ ሊሰራ አልተቻለም ነገር ግን እራሳችን ቆርጠን ስንገባባት 45 ኪ.ሜን የወንዝ ዳርቻዎች እና 1000 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ልማት በኢትዮዽያ ልጆች ዲዛይነርነት፣ አርክቴክትነት፣መሪነትና አስተባባሪነት ባሰብነዉና ባለምነዉ ልክ በ5 አመት ረጅም ጊዜ ዉስጥ ያልተቻለን በ7 ወራት ጊዜ ዉስጥ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ አሳክተናል ። ኢትዮዽያን በሁለንተናዊ መልኩ ለማበልፀግ ባላቸዉ ራዕይ የሃሳቡ አመንጪና ከጐናችን ያልተለዩትን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ፣የልማታችን ዋነኛ አጋሮች ሆናችሁ አብራችሁን የሰራሁ ባለሀብቶች ፣ አመራሮች ፣ ሰራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ ማህበራት እንዲሁም የልማታችን ደጀን የሆናችሁ የከተማችንን ነዋሪ የላቀ ምስጋና ይሁን እላለዉ ። ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ! ከንቲባ አዴነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ወንዞች ትንሣኤ ፤ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያዎች!!… See more

ይህቺ የእኛዋ አራዳ - ፒያሳ ናት

ዛሬ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብልፅግና ምክርቤት አባላት የተጎበኘ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የፒያሳ መልሶ መልማት ፕሮጀክቶች በምስል “ እኛ የምንወደዉ ሀገር ፣ የምንቆምለት ሀገራዊ ዓላማ እና ሕልም አለን !” የምንገነባዉ ሀገር፣ የምንገነባዉ ከተማ አለን ፣ ባለፉት የለዉጥ አመታትም ይህንኑ በተግባር አረጋግጠናል ። ማምሻዉን ለብልፅግና ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ካስጎበኘናቸዉ የልማት ስራዎች መካከል ። #Ethiopia # AddisAbaba #prosperity ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጤናማ፣ በሚገባ የተጠበቁ የወንዝ ዳርቻዎች የከባቢ ሥርዓትን እና የውሃ ጥራትን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰብን የኑሮ ደህንነት የሚያሻሽሉ እና የከተሞችን ለፈተና አለመበገር የሚያጠናክሩ ደማቅ ሕዝባዊ ሥፍራዎችን ይፈጥራሉ። ዛሬ ከሰዓት ከብልጽግና ምክር ቤት ስብሰባ በኋላ የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሥራ ሂደትን በጋራ ተመልክተናል። ይኽ ሥራ አሁን በተያዘው ምዕራፍ በአምስት ክፍለ ከተሞች የሚዘልቅና 21.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው። ፕሮጀክቱ በጥቂቱ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገፍ፣ ሕዝባዊ ፕላዛዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፣ ሱቆች እና አምፊቴአትሮች የተካተቱበትም ነው። ከዚህ ግዙፍ ሥራ አላማዎች መካከልም የወንዞች ብክለትን ማስወገድ፣ የከተማዋን የጎርፍ ተጋላጭነት መቀነስ፣ ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን ቁጥር መጨመር እና የሥራ እድል መፍጠር ይገኙበታል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አካባቢያችንን ከመጠበቅ ባሻገር ለአዲስ አበባ ደማቅ እና ዘላቂ የወንዝ ዳርቻዎችን በማስገኘት የከተማዋን ኢኮኖሚ እና የኑሮ ደረጃ ከፍ ያደርጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ Healthy, well-maintained riversides in cities not only protect ecosystems and water quality but also create vibrant public spaces that enhance community well-being and strengthen urban resilience. This afternoon, following the Prosperity Party’s Central Council meetings, we collectively reviewed the progress of the Addis Ababa Riverside Project. The initiative in its current phase spans 21.5 km in length running across five sub-cities. It features walkways, bike lanes, public plazas, parking areas, children’s playgrounds, shops, and amphitheaters. The objective of this grand undertaking by the city includes stopping river pollution, reducing the city’s vulnerability to flooding, expanding public infrastructure, increasing green spaces, and creating jobs. Once complete, it will not only protect our environment but also give

ዛሬ የብልጽግና ምክርቤት አባላትን ያስጎበኘናቸዉ የፒያሳ መልሶ ማልማት ገፅታ በከፊል። ተመስገን እንጂ ሌላ ምን ይባላል!! Har'a miseensota mana maree Badhaadhinaaf kan daaw'achiisne fuula deebisanii misoomsuu Piyaassaa hamma tokko. Galatasaa malee kan biraa maal jedhama.

የብልፅግና ፓርቲ ም/ቤት የታሪካዊ ጠላቶችን የመጨረሻ ሙከራ ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን በቁርጠኝነት ለማከናወን ያስቀመጣቸው ሰባት ጉዳዮች፡- 👉ግጭትን ሊያስቀሩ የሚችሉ ሰላማዊ አማራጮችን በሁሉም አቅጣጫ ለመሞከርና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለሚወስኑ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ፤ 👉የሰላምን አማራጭ ባለመቀበል በሕዝብና በሀገር ንብረት ላይ ችግር ለመፍጠር በሚነሡ ኃይሎች ላይ በተጠናከረ መንገድ ሕግ ለማስከበር፤ 👉በየደረጃው የሚነሡ የሕዝብ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን በኢትዮጵያ ዐቅም ልክ በየደረጃው ለመመለስ፤ 👉ተገቢውንና እውነተኛውን መረጃ ለሕዝብ በየጊዜው ለመስጠትና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለማጋለጥ፤ 👉በየተቋማቱ ተመድበው የዲሲፕሊን ጉድለት፣ሙስናና የአስተዳደር በደል የሚያደርሱ የሥራ መሪዎችንና አገልጋዮችን ለመታገል፤ 👉በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ እንደዚሁም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመርናቸውን የልማት ሥራዎች የበለጠ ስኬታማ በማድረግ፤ የተጀመሩ ኢኒሼቲቮችን ለውጤት በማብቃት፤ የሕዝብን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ የከተማና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ፤ 👉በዲፕሎማሲው መስክ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሁሉም መንገድ ለማስከበር፤