en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው ለ2017 ዓ.ም ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እና ልዩ ልዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቅቋል:: በዚህም መሰረት:- 1. ወ/ሮ ቆንጆት ደበላ - የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ(በሽግሽግ) 2. አቶ አወሌ መሐመድ ኦመር - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ 3. ወ/ሮ አይሻ መሐመድ አደን - የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር 4. ኢ/ር ሕይወት ሣሙኤል ጸጋዬ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር 5. ሲ/ር ሶፊያ አለሙ - የሴቶች፣ የወጣቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ ሆነው ተሹመዋል:: በሌላ በኩል ተጨማሪ በጀቱ በከተማዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ .አገልግሎትን ከማዘመን አንፃር ኮሪደር ልማቱ የፈጠረልንን ቴክኖሎጂ የማዘመን እድል በአግባቡ በመጠቀም 347 በቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን ማዘመን ችለናል። • የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማዘመን በትኩረት መስራት ይኖርብናል። • የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ በመንግሥት ተቋማት ካደረግነው ውጤታማ ሪፎርም ጎን ለጎን በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ 1726 ሠራተኞችና ከ90 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል በልዩ ትኩረት እየሰራን ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጨማሪ በጀት አፀደቀ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለ2017 ዓ.ም የሚውል ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አፅድቋል፡፡ ተጨማሪ በጀቱ በከተማዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑ በምክር ቤቱ ተገልጿል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የኮሪደር ልማትን በተመለከተ 👉በኮሪደር ልማት የመጣው ለውጥ "አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን" ብለን ለህዝባችን ከገባነው ቃል የመነጨ ነው። ለአብነት የኮሪደር ስራችን ከመጀመራችን በፊት ባደረግነው ጥናት የአዲስ አበባ የመንገድ መሰረተ ልማት እና የአረንጓዴ ሽፋን እጅግ ከፍ እንዲል ያስቻለን ሲሆን ይህም ለከተማችን ነዋሪዎች አጠቃላይ ጤና ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው። 👉በኮሪደር ልማት መኪና መንገድ ብቻ ሳይሆን 80% በላይ ተሽከርካሪ የሌለውን የከተማችን ነዋሪዎች በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን የእግረኛ መንገዶችን አስፋፍተናል የሳይክል መንገዶችንም ማስፋፋት በመጀመራችን ህዝቡ ተጠቃሚ ሆኗል። 👉 በኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራ የታየው ወሳኝ ጉዳይ የህዝባችን ያላሰለሰ ድጋፍና ትብብር የተረጋገጠበት መሆኑ ነው። በዚህ ስራ ውስጥ ወጣቶች እና ሴቶች በጉልበታቸው አግዘዋል፤ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን አፍስሰዋል፤ የልማት ተነሺዎች አስደናቂ ትብብር አድርገዋል። 👉ኮሪደር ልማቱ የከተማችንን ገፅታ መቀየሩ እና ለህዝባችን ምቹ መኖሪያ እንድትሆን ከማድረጉ ጎንለጎን ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል። 👉 የከተማችን ነዋሪዎች ልማቱ ወደ ሁሉም የከተማችን አካባቢዎች እንዲመጣ መጠየቃቸው አግባብነት ያለው ጥያቄ ቢሆንም ስራው ሰፊ ሀብት እና ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በጥናት እና በቅደም ተከተል ወደ ሁሉም የከተማችን ክፍሎች በመምጣት የምናለማ ይሆናል:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ማህበራዊ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ባለፈ በቂ ስልጠና በመስጠት መስራት የሚችሉትን የማሸጋገር ስራ ሰርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኑሮ ውድነትና ጫናን ለማቃለል አለም አቀፋዊ ሁኔታን አገናዝበን ምላሽ ለመስጠት ሞክረናል። * ኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት በአምስቱም የከተማችን መግቢያ በሮች የግብርና ምርቶችን አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግና የደላሎችን ሰንሰለት መበጣጠስ ችለናል። * የኑሮ ውድነት ችግርን ማቃለል የምንችልበት መንገድ አምራችነትን በማሳደግ እንደመሆኑ መጠን የከተማችን ነዋሪ በተለያዩ አግባባች አምራችነቱ እንዲያድግ ስልጠና የመስጠትና የግብአት አቅርቦት እገዛ እያደረግን ነው። * የገበያ ማረጋጋት ስራን በተመለከተ በቁጥጥር፣ በክትትልና፣ በድጎማ ህቦረተሰባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው።ውጤትም አግኝተንበታል። * ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና የእናቶችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሰራነው ስራ ሁሌም የምንኮራበት ነው። * 26 የምገባ ማዕከላን በመክፈት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመመገብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸዉን ከማረጋገጥ ባሻገር ዜጎች አብሮ የማደግ ባህል እንዲጎለብት አድርገናል። * 2የገበያ ማዕከላት ተጨማሪ በመገንባት የምርት አቅርቦት እንዲጨምርና የግብይት ስርዓቱ እንዲዘምን በትኩረት እየተሠራ ነዉ:: ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ሃሳቦች:- - ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን እውን ለማድረግ በታቀደው መሰረት ለወጣቶች እና ለሴቶች ሰፋፊ የሆኑ የስራ ዕድሎች መፈጠራቸውን አንስተዋል። - በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድም ተስፋ ሰጪ የሆኑ ስራዎች መሰራታቸውን ነገር ግን ልክ በኮሪደር ልማት፣ መልሶ ማልማት እና በወንዞች ዳርቻዎች ልማት አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡ ሁሉ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይም መሰረታዊ ለውጦችን ለማምጣት የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት መስራት እንደሚገባው በአስተያየት እና ጥያቄ መልክም ተነስቷል። - የሰው ተኮር ስራዎች በተለይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ያሉ ዜጎች ከተማ አስተዳደሩ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ህዝቡም ተገቢውን እውቅና እየሰጠ ይገኛል። - የውሀ ስርጭት በስታንዳርድ እንዲሆን እየተሰራ ቢሆንም ፍትሀዊ ስርጭት እንዲኖር አሁንም ትኩረት እንዲሰጠው የህዝቡ ጥያቄ መሆኑን አንስተዋል። - ከመብራት ጋር ተያይዞ በተለይም መኃል ከተማ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች ያረጁ እና ሊወድቁ የደረሱ ፖሎች በነዋሪዎች ዘንድ ስጋት የደቀኑ በመሆናቸው አስቸኳይ እልባት ያስፈልጋል። - ከኑሮ ውድነት አንፃር የሰብል ምርቶች የዋጋ መረጋጋት ያሳየ መሆኑን ሆኖም የዘይት ዋጋን ጨምሮ በሌሎች ምርቶች ዙሪያ ዘላቂ እልባት እንዲሰጥ:: - የእሁድ ገበያዎች፣ የተማሪዎች ምገባ ፣ የትራንስፖርት አቅርቦት፣ በጤና መድህን እንዲሁም ዓለም አቀፍ አንድምታ ያለው የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የሚከናወኑ ሰው ተኮር ተግባራት አበረታች ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ኢ/ር ወንድሙ ሲታ በም/ከንቲባ ማአረግ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ 👉የከተማዋን የፍሳሽ ማስጋጃ ስርዓት የማዘመንና በአዲስ መልከ የመገንባት ስራ በስፋት እየተከነወነ ይገኛል፡፡ 👉የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን ለመቀነስ በልዩ በትኩረት አካባቢዎችን በመለየት እየሰራ ነው፡፡ 👉የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ላይ ያመጣነው ለውጥና ያስገኘነው ውጤት በከተማችን ገፅታ ላይ ግልፅ ለውጥ እያመጣ ነው:: 👉ቆሻሻን ወደ ኢነርጂ ከመቀየር አንፃር አሁንም የሚቀሩን ስራዎች አሉ፤ የከተማዋን ፅዳት አረጋግጠን ቆሻሻን ወደ ኢነርጂ መቀየር ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል። 👉ከውሃ ፍትሃዊ ስርጭት አንፃር 377,000 ሜ.ኪዩብ ውሃ የማምረት አቅም በማጎልበት ተደራሽነታችንን ለማሰደግ የተሰራ ሲሆን በቀጣይ 100,000 ሜ.ኪዩብ ተጨማሪ የውሃ አቅርቦት አቅም ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው:: 👉የመብራት መቆራረጥ ችግር መንስኤዎች በነባር መንደሮች ያለውን አሮጌ መሰረተ ልማት ጋር የተገናኘ በመሆኑ በቀጣይ የመብራት ሃይል አቅርቦት መሰረተ ልማትን በአዲስ መልክ ለመገንባት በማስተርፕላኑ ውስጥ ማስገባት በዘላቂነት ለመፍታት ያግዘናል ፡፡ 👉የኮሪደር ልማት ሰራችን ይህንን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager