en
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

Open in Telegram
1 474
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days
Posts Archive
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ

ይህ ዓመት የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዓመት ነው ባልነው መሰረት እየመጣ ያለው ለውጥ ይበል የሚያስብል ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ያካሄዳል የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ያካሂዳል። ምክር ቤቱ በዓድዋ መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው በዚህ ጉባኤው በከተማ አስተዳደሩ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ሪፖርት እና በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ይጠበቃል። AMN-Addis Media Network ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራን ጎበኙ ! የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀማቸውን ለሁለት ቀናት ሲገመግሙ የቆዩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በቅርቡ ለምርቃት የበቃውን የካዛንቺስ የኮሪደር ልማትን ጎብኝተዋል። በከንቲባ አዳነች አቤቤ የቅርብ ክትትል በጥራትና በፍጥነት ተጠናቅቆ በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተመረቀው የካዛንቺስ ኮሪደር ልማት አካባቢውን አዲስ ገፅታ አጎናፅፎታል ብለዋል ጎብኚዎቹ። አመራሮቹ 40 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የተሽከርካሪ ፣ የእግረኛ ፣ እና የብስክሌት መንገድ የተገነባለት የካዛንችስ ኮሪደር ልማት የህዝባችንን ውስብስብ ችግሮች የሚያቃልሉ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ማሳያ መሆኑንም ገልፀዋል። የከተማ አስተዳደሩ ለሁለት ቀናት ሲያከናውነው የቆየው የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀሙን ዛሬ ማምሻውን ማጠናቀቁ ይታወሳል:: ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ኤጀንሲው በነገው እለት ሐሙስ ሚያዚያ 23 ቀን ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን አስታወቀ። ለአዲስ አበባ ከተማ ወላጆች :- በነገው እለት ሐሙስ ሚያዚያ 23/2017ዓ.ም የተማሪዎች የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ አገልግሎት በሁሉም የወረዳ ጽ/ቤቶች የሚሰጥ መሆኑን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እየገለፀ በዕለቱ ምዝገባውን ያላደረጉ የከተማችን የግል እና የመንግስት ተማሪዎች ወደ ኤጀንሲው በመቅረብ እንዲመዘገቡ ወላጆች ሚናችሁን እንድትወጡ ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ኤጀንሲው አክሎም ከወረዳ ጽ/ ቤቶች በተጨማሪም በዋና መስሪያ ቤቱ እና ቅርንጫፎችም የማስረጃ ማረጋገጥ አገልግሎት በነገው እለት ክፍት ሆነው አገልግሎት እንደሚሰጡም አስታውቋል። ለበለጠ መረጃ ወይም ማብራሪያ በነፃ መስመር 7533 ይደውሉ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ቦሌ-ቡልቡላ ፤ እንኳን ደስአላችሁ !! "Boolee Bulbulaa , Baga gammaddan" Congratulations to Bole Bulbula.

ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት በ 21 ሄክታር ላይ የተገነባውን የቡልቡላ ፓርክ እና ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ ድረስ 14 ኪ/ሜ ላይ ያለው የአረንጏዴ ልማት ስራም ጎብኝተን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል:: ይህ ስፍራ ከዚህ ቀደም ለእይታ የማይመች፣ እጅግ ቆሽሾ የነበረ እና ማንም መለስ ብሎ አይቶት የማያውቀውን አካባቢ ወደ ሃብትነት ፣ ትልቅ መዝናኛ እና የህዝብ መዋያና መናፈሻ መቀየሩ መቻሉ በጣሙን ደስ ያሰኛል ።የአካባቢው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ:: ህዝብን በማስተባበር የተሰራው የቡልቡላ ፓርክ በርካታ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት የመዝናኛ ስፍራ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ እና ባለሃብቶች ፓርኩን ለማስዋብ ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ ታላቅ ምስጋና ይገባችኋል። የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮች ወደ ህዝብ ቀርባችሁ እና አስተባብራችሁ ይህንን ድንቅ ስራ በመስራታችሁ በራሴ እና በነዋሪዎች ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: ሌሎችም ክፍለከተሞች ከዚህ ተሞክሮ በመውሰድ ህዝቡን በማስተባበር አካባቢያችሁ ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ሰዉ ተኮር የልማት ስራ መስራት የሚቻል መሆኑን ከቡልቡላ ፓርክ ልምድ እንድትወስዱ እያልኩ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ይህ ፓርክ የእናንተ በመሆኑ በአግባቡ እንድትገለገሉበት፣ እንድትጠብቁት እና እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ:: በፎቶግራፎ እዚህ ላይ ከምትመለከቱት በአካል የበለጠ ዉብ በመሆኑ እንድት ጐበኙት እጋብዛችኋለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እኔ በህይወት ቆሜ አዲስ አበባ እንዲህ ሆና በማየቴ ደስ ብሎኛል" "ፅዱና ዘመናዊ አዲስ አበባ እውን እየሆነች ነው።" አርቲስት ፈለቀ ካሳ የፅዳት አምባሳደር

በተለያዩ መስኮች እያከናወንን ያለነው የተቋም ግንባታ እና ልማት ጥረታችን የሀገራችን ማንሰራራት ግልፅ ምልክት ነው። ይኽ ስኬት በሁሉም መስኮች እየታየ ነው። የዚህ ስኬት አስገራሚ ምልክት የቡልቡላ ፓርክ ነው። በአንድ ወቅት የቆሻሻ መጣያ የነበረ ስፍራ በጥቂት ወራት ውስጥ ዋጋው ከፍ ወዳለ የሕዝብ መጠቀሚያ ተቀይሯል። የቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች በራሳቸው ተነሳሽነት ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ብሎም ማኅበረሰቡን በማስተባበር አስደናቂ ስራ ሰርተዋል። የባለቤትነት መንፈሱ እና ቀድመው አስበው የመስራት ተነሳሽነታቸው በሁሉም ዘርፍ መቀዳት አለበት። እዚህ ስፍራ የፈሰሰው ሀብት የዛሬውንም የነገውንም ትውልድ ያገለግላልና የአካባቢው ነዋሪ እንዲንከባከበው ጥሪ አቀርባለሁ። ባለድርሻ አካላት ሁሉ ደግሞ ይኽን ጥረት በተቀሩት የከተማችን እና የሀገራችን ክፍሎች አሳድገው እንዲተገብሩ አደራ እላለሁ። Ijaarsi dhaabbileefi tattaaffiin misoomaa dameewwan garaagaraatiin taasisaa jirru mallattoowwan ifa biyyii keenya bayyanachaa akka jirru agarsiisanidha. Milkaa'inni kun dameewwan hundatti mul'ataa jira. Mallattoon ajaa'ibsiisaa milkaa'ina kanaa Paarkii Bulbulaati. Bakki kanaan dura balfi itti gatamaa ture jijjiiramee ji'oota keessaatti iddoo gatii olaanaa qabu kan uummanni itti fayyadamu ta'eera. Hooggantoonni Kutaa Magaalaa Boolee kaka'umsa mataasaaniitiin damee dhuunfaa waliin walta'uudhaan akkasumas hawaasa qindeessanii hojii dinqisiisaa hojjetaniiru. Miira abbummaafi kaka'umsisaanii dursanii yaadanii hojjechuuf qaban damee hundaan waraabamuu qaba. Qabeenyi bakka kanatti dhangala' dhaloota har'aas kan boriis ni tajaajila waan ta'eef jiraattonni naannichaa akka kunuunsanin dhaama. Qaamoleen isaan ilaallatu hundinuu tattaaffìi kana kutaalee magaalaafi biyya keenyaa hafanitti bal'isanii akka hojiirra oolchanin dhaamuu barbaada. The institution-building and development efforts we are undertaking across various areas are clear signs of our nation’s rise, and these achievements are being demonstrated at multiple levels. One striking example is Bulbula Park, which was once a dumping ground but has now been transformed into a valuable public utility space in just a few months. The leadership of Bole Sub-City, in collaboration with private entities in the area, has done a remarkable job by mobilizing the public and completing this transformation through its own initiative. This sense of ownership and proactive spirit must be replicated elsewhere. The investment made here serves both present and future generations, and I call upon residents to help maintain it, while urging all stakeholders to scale up such efforts in other parts our capital and country.

የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል:: ባለፉት ዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀማችን አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ፣ ጽዱ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የቱሪስት መተላለፊያ ብቻ ሳትሆን መዳረሻ የሆነች ከተማ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር እንዲሁም የአመራር ቁርጠኝነትንና ቅንጅትን በማጠናከር የጀመርናቸው ሁሉን አቀፍ ስራዎችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለዘጠኝ ወራት ያቀድናቸዉን ስራዎች በአማካይ 93% አሳክተናል። የነዋሪውን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ሌሎች ሰው ተኮር ስራዎቻችን የበርካቶችን ሸክም ያቃለሉ፣ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ ያበሱ እንዲሁም ማህበራዊ ፍታትህን ያረጋገጡ ሲሆኑ የፕሮጀክት አፈፃፀም፣ የገቢ አሰባሰብ፣የኑሮ ዉድነትን እና ገበያን የማረጋጋታ ስራ ፣የሰላምና ጸጥታ፣ የትራንፓርት መሰረተ ልማት ማስፋፋት፣ የከተማ ፅዳት ፣ የአረጓዴ ልማት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የበጀታችንን 71 % ለዘላቂ ልማት እና ደህነት ቅነሳ ማዋላችን፣ የስራ ባህል እየተሻሻለ መምጣቱ ዋና ዋና ውጤት ካገኘንባቸው ተግባራት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው:: ፈተናዎችን እየተሻገርን ባሳካናቸው ስኬቶች ሳንረካ ጥንካሬዎቻችንን በማጽናት በግምገማችን የለየናቸውን ድክመቶች ከነመንስዔዎቻቸው ነቅሰን በማውጣት እና ለላቀ ውጤታማ ስራ በመዘጋጀት በአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል፣ ኑሮ ውድነትን በመቀነስ፣ ቀሪ ኮሪደሮችን፣ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ እንዲሁም ሌብነትና ብልሹ አሰራር በማስቀረት ለነዋሪዎቻችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን ቀጥለናል:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ለዘመናዊነት" ከተፅእኖ ፈጣሪዎች፣ ከኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከእምነት አባቶችና የሲቪክ ተቋማት ተወካዮች ጋር የተካሄደውን ውይይት በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጀምሯል። በግምገማ መድረካችን ያለፉት ዘጠኝ ወራት ስኬታማ ስራዎችን በመፈተሽ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ዝርዝር ግምገማ የምናደርግ ሲሆን፣ ታቅደዉ ያልተፈፀሙ እና በስድስት ወራት የስራ ግምገማችን ወቅት በዝርዝር ለይተን በሰጠነው ግብረመልስ እና አቅጣጫ መሰረት የህዝብ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ ክፍተቶች አፈታትን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል። በተጨማሪ በመድረኩ የአመራራችንን ችግር የመፍታት አቅም፣ የሚመራውን ተቋም ክፍተት በመለየት ምን ያህል ማሻሻል እንደቻለ እና ክፍተቶችን አስቀድሞ ለይቶ በፍጥነት መፍታት ላይ የመጡ ለውጦች ይገመገማሉ። የግምገማ መድረኩ በቀሪ ሶስት ወራት እቅዶቻችንን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ መግባባቶች ላይ የምንደርስበት ሲሆን፣ የለየናቸዉን ክፍተቶችን በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለማገልገል ራሳችንን ይበልጥ የምናዘጋጅበትም ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager