cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Womberma communications

Public channel

Show more
Advertising posts
274
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

23:00
Video unavailableShow in Telegram
ምሽት_12_00_ዜና_ሙዳይ_ባሕር_ዳር_ሐምሌ_19_2015_ዓ_ም_አሚኮ.mp4303.66 MB
የምዕ/ጎጃም ዞን የ2015 ዓ.ም. የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በአንድ ጀምበር ተከላ 29.91ሚሊየንችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ነበር። በተካሄደው የተከላ ዘመቻም 32.2ሚ በላይ መትከል ተችሏል። ሁሉም የዞናችን ወረዳዎችና 395 ቀበሌዎች በተሳተፉበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር 3300 ሄ/ር መሬት ተሸፍኗል። በዞናችን በ2014 ዓ.ም. በነበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር የተተከሉ ችግኞች 84% የፅድቀት ምጣኔ አላቸው።
Show all...
n
Show all...
null
Show all...
ቀን 20/10/2015 ዓ.ም በምቹ መማሪያ ክፍል በፈጠራ የታገዘና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት ጥረት መደረጉ ተገለፀ በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ በምቹ መማሪያ ክፍል በፈጠራ የታገዘና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት ጥረት መደረጉን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አዳሙ አድማሱ እንደገለፁት በ2015 የትምህርት ዘመን 21ሽህ 452 የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎችን እና 5ሽህ 534 የሑለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በአጠቃላይ 27ሽህ 395 ተማሪዎችን በማስመዝገብ ማስተማር ተችሏል፡፡ከዚህም ውስጥ 2ሽህ483 የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎችን እና 928 የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎችን ክልል አቀፍና ሃገር አቀፍ ፈተና ለማስፈተን ጥረት እየተደረገ ሲሆን ተማሪዎችን ለፈተና ብቁ ለማድረግም በተቃራኒ ፈረቃ የማጠናከሪያ ትምህርት ፣ቤተ መፅሃፍትን ዘወትር ክፍት ከማድረግ በተጨማሪም ጥያቄዎችን በማዘጋጀት የመስጠትና የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የመማሪያ መፅሃፍት እጥረት ቢኖርም በተቻለ መጠን ለማሟላት ጥረት የተደረገ ሲሆን የተለያዩ አጋዥ መፅሃፍትን ግዥ በመፈፀም ለተማሪዎች ማቅረብ መቻሉን ጠቁመው የተለያዩ ግንዛቤ ያላቸውን ተማሪዎች በመምረጥና በቤተ ሙከራ እየታገዙ ፈጠራን ማዳበር እንዲችሉ በመደረጉ በፈጠራ ስራ ከዞንና ከክልል ደረጃ መያዝ ችለናል ሲሉ አቶ አዳሙ አብራርተዋል፡፡ ተማሪዎች ትምህርት ቤቱን ወደውት እንዲማሩ ለማድረግም ከጭቃ ወደ ብሎኬት ገፅታን የመቀየር ስራ በሰፊው ተሰርቷል፡፡በዚህም ከ3 ዓመት ወዲህ 20 ብሎክ የመማሪያ ክፍሎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በ2014 በጀት ዓመትም 14 ብሎኮች እና 1 የትምህርት ቤት የአስተዳድር ህንፃ በመገንባት ላይ እንደሚገኙና 8 ብሎኮች በመጠናቀቅ ላይ እንዲሚገኙ አቶ አዳሙ ገልጸዋል፡፡ በ2016 በጀት አመትም በወረዳው 5 ብሎክ የመማሪያ ክፍልና 2 በሽንዲ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ለመገንባት ጥረት እያደረጉ ሲሆን በቀጣይ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባት ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከተቋማት ፣ከመንግስት ሰራተኞች ፣ከማህበረሰቡና ከተማሪዎች 15 ሚሊዮን 278ሽህ ብር በአልማ ድጋፍ በመሰብሰብ ወደ ግንባታ ሂደት ማዞር መቻሉንም አቶ አዳሙ ገልፀዋል፡፡ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማምጣት የሑሉንም ማህበረሰብ ክፍል ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን በማገዝና በመደገፍ ፣ምሁራን ችግር ፈቺ በሆኑ ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም ተግባር ተኮር ስራዎች ላይ ተማሪዎች ተመርኩዘው ውጤታማ ሆነው ለሃገርና ለትውልድ የሚጠቅም ዜጋ ለማፍራት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡ ውድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ተከታታዮች በያላችሁበት ሰላም ለእናንተ ይሁን እያልን ወቅታዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ እና አካባቢያዊ መረጃዎችን ለማግኘት ሁሌም ከዚህ በታች የተገለፁ ገፆቻችንን ይጎብኙ ! ✍️ በቲዊተር = https://twitter.com/yemirtmama ✍️ በፌስቡክ = https://www.facebook.com/womcommu ✍️ በዩቲዩብ = https://www.youtube.com/@WomCom ✍️ በቴሌግራም = https://t.me/wombermacommunications ✍️ በቲክቶክ = https://vm.tiktok.com/ZMFUk5Rg
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Photo unavailableShow in Telegram
ቀን 19/10/2015 ገቢን በመሰብሰብ የወረዳውን ልማት ለማፋጠን መሰራቱ ተገለፀ በምዕራብ ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ ገቢን በመሰብሰብ የወረዳውን ልማት ለማፋጠን እየሰራ መሆኑን የወረዳው ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለጸ ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አዝመራው በላይ እንደገለፁት በ2014/15 በጀት ዓመት 76 ሚሊዮን 853 ሽህ ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከእርሻ፣ ልዩልዩ ፣ከንግድ እና ሌሎች ዘርፎች ዘገባው እስከተጠናከረበት ድረስ 68 ሚሊዮን 610 ሽህ 714 ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከተሰበሰበው 52 ሚሊዮን 707ሽህ 604 ብር 22 ሚሊዮን 378 ብር ብልጫ ሲኖረው የዘንድሮው ገቢ አሰባሰቡም ከታቀደው 90 ነጥብ 25 ከመቶ መፈፀም ተችሏል፡፡ ገቢው በወቅቱና በአግባቡ እንዲሰበሰብ ለማስቻልም ለባለሙያዎች ፣ለባለድርሻ አካላትና ለሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ለመሰብሰብ የታቀደውን ለመሰብሰብም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው የንግዱ ማህበረሰብ ድርጅቱን ዘግቶ የመጥፋትና የመሰወር ፣የበጀትና የተሸከርካሪ እጥረት የገጠማቸው ቢሆንም ችግሩን ለመፍታት ጥረት መደረጉን አቶ አዝመራው አብራርተዋል፡፡ የገቢ ግብርን ቀጣይነትና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማስከፈልም ኮሚቴ በማዋቀር ከግንቦት 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን 1ሽህ 14 ደረጃ ሐ፣77 ደረጃ ለ ፣25 ደረጃ ሀ እና 305 አከራይ ተከራይ ለማጥናት ታቅዶ 282 አከራይ ተከራይ፣ 694 ደረጃ ሐ በአጠቃላይ 73 ከመቶ በማጥናት የግብር ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን አቶ አዝመራው ገልፀዋል፡፡ ግብር የዜግነት ግዴታ በመሆኑ ሁሉም ለተገለገለበት በወቅቱ የመክፈል ፣ቁርጥ ግብርን በድርጅት ወይም በንግድ ቦታ በመገኘት የማሥጠናት ስራ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመው ባለድርሻ አካላትም ለግብር ጥናት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሃላፊው አስገንዝበዋል፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰኔ 16/2015 ዓ.ም "የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ የማህበረሰቡን  የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እየተሰራ ነው" ::  አቶ ባይነሳኝ ቢተው የሽንዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ~~~~ የከተማ አስተዳደራችን በ2015 ዓ/ም እንዲሰበስብ የተፈቀደለትን ገቢ ከእቅድ በላይ በመሰብሰብ ውጤታማ አመርቂ ስራ መስራት ችለናል።ለዚህ ስራ መሳካት ደግሞ ልማት ወዳዱ የከተማችን  ማህበረሰብ እና መላ አመራሩ ሊመሰገን ይገባል። በበጀት አመቱ 35,802,868 ብር ሊሰበሰብ ታቅዶ 36,532,286.44 ብር በመሰብሰብ የእቅዳችንን 102.3% በማሳካት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መስራት ችለናል። በበጀት አመቱ ከተሰበሰበው ገቢ  11,860,538 ብር ለካፒታል ፕሮጀክት የተመደበ ሲሆን በዚህም የጠጠር መንገድ ጥገና 4 ኪ.ሜ ፣  የኮብል ስቶን ስራ 0.18 ኪ.ሜ  እንዲሁም የቢሮ ግንባታ ስራ  እና የሸድ ግንባታ ስራዎች በ 6,301,190.44 ብር ወጪ ልማቶች ተሰርተዋል ብለዋል::።በተጨማሪም ለመልሶ ልማት ተነሽዎች 1.6 ሚሊየን ብር የመብራት ዝርጋታና የትራንስፎርመር ክፍያ ተከፍሎ ስራው በመከናወን  ላይ ያለ መሆኑንም አስገንዝበዋል ። በማህበራዊ ልማት ዘርፉም ሁለቱንም የከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች በህንፃ ለመስራት የመሰረት ቁፋሮ እና የብረት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ  ግዥ ተፈፅሞ ወደ ግንባታ ለመግባት የሙያ ጫራታ ላይ ይገኛል።ሶስተኛው የለገሰማ ንዑስ ቀበሌ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በህንፃ እየተገነባ አጠቃላይ ግንባታው 80% ላይ ይገኛል። በሰላምና ደህንነት ዙሪያ የከተማ አስተዳደራችን በበጀት አመቱ ምንም አይነት ከፍተኛ ወንጀል ያልተፈፀመ ሲሆን ይህን የተገኘ አንፃራዊ ሰላም የበለጠ ዘላቂ ለማድረግ 24 መደበኛ ፖሊስና  21 ከልዩ ሃይል ወደ መደበኛ ፖሊስ የተቀላቀሉ ሲሆን 179 ሚሊሻና ሰላም አስከባሪ ሀይል ተሰማርቶ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን ማለትም ማጭበርበር የስርቆት ወንጀልና ኮንትሮባንድ ንግድን በመከታተል በርካታ ስራዎች እየተሰሩሲሆን በከተማችን ህገ-ወጥ ተኩስን ለማስቆም ሰፊ ስራ በመሰራቱ ችግሩን መሻገር ተችሏል።አሁን ያለውን ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታም ከግምት ውስጥ በማስገባት ከወምበርማ ወረዳ የፀጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት እስከ ሰኔ 20/2015 የሽንዲ ከተማ አስተዳደርን እና የወምበርማ ወረዳን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ልዩ ልዩ የተቀናጀ የፀጥታ አደረጃጅቶች ተዋቅረው ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን ባሳለፍናቸው ሁለት ቀናትም በርካታ ወንጀለኛ እና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ይህን መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጎን በመቆም መረጃ በመስጠትና ህገ-ወጦችን በማጋለጥ ሰላሙን የበለጠ አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ  ጥሪያቸውን አሰተላልፈዋል ። የሽንዲ ከተማ አስተዳደር  ኮምኒኬሽን ሰኔ 17/2015 ዓ/ም
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.