cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

West Gojjam communicationS

West Gojjam Zon

Show more
Advertising posts
678
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
"ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ ገብተዋል፡፡" የቡሬ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በኢትዮጵያ ለሀገር እድገት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋል፡፡ ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አንደኛው ነው፡፡ ፓርኩ በሦስት ምዕራፎች ይገነባል፡፡ የፓርኩ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቅቆ ክፍት ከኾነ ቆይቷል፡፡ ባለሀብቶችም ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በመግባት እንዲያለሙ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ወደ ቡሬ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪያል ፓርክም በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት ያስመዘገቡ ባለሀብቶች እየገቡ ነው፡፡ የቡሬ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥራ አሥኪያጅ ዳኛቸው አስረስ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ያስመዘገቡ 37 ባለሀብቶች ወደ ፓርኩ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርኩ የገቡ ባለሀብቶች 102 ሄክታር የለማ መሬት መረከባቸውንም ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ይለማል ተብሎ ከታሰበው መሬት አብዛኛው ለባለሀብቶች መተላለፉንም ነው የገለጹት፡፡ የውጭ ሀገርና የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፕሮጄክት ቀርጸው እያስገቡ መኾናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ወደ ፓርኩ ለመግባት ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት በርካታ ከፍተኛ ሀብት ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ እንደሚገቡ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡ ክልሉ በአስቸጋሪ ሂደቶች ውስጥ እንዳለፈ ያነሱት ሥራ አሥኪያጁ ችግሮች ቢኖሩም የክልሉ መንግሥት ባለሀብቶች እንዲገቡ እያደረገው ያለው ጥረት እና የባለሀብቶችም ፍላጎት የሚበረታታ መኾኑን ነው የገለጹት፡፡ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መኾናቸውንም አንስተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ገብተው እንዲያለሙ የሚፈለጉት ባለሀብቶች ሙሉ ለሙሉ እንደሚገቡ ይጠበቅ እንደነበር ያነሱት ሥራ አሥኪያጁ የነበረው የጸጥታ ችግር በሚፈለገው ፍጥነት አለመሳካቱንም ነው የተናገሩት፡፡ አሁን ከገቡት ባለሀብቶች የበለጠ ባለሀብቶች ወደ ፓርኩ እንዲገቡ እንደሚጠበቅም አንስተዋል፡፡ አሁን ላይ የገቡት ባለሀብቶችም በቀላል የሚታዩ አለመኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ከገቡ ባለሀብቶች መካከል ወደ ምርት የገቡ መኖራቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ለሀገር የውጭ ምንዛሬ እያመጡ ያሉና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩ እንዳሉም አንስተዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት ፓርኩ የሚፈለገውን ዓላማ እንዲያሳካ በትኩረት እየሠራ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ ለዋናው ፓርክ መጋቢ የኾኑ ቅርንጫፎች ሥራቸው እየተጠናቀቁ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ወደ ፓርኩ ለመግባት ከፍተኛ ፍላጎት እያሳዩ መኾናቸውንም አስታውቀዋል፡፡ አሚኮ
Show all...
"የወረዳው ልማት ከሚጠበቀው በላይ እንዲፋጠን የአንበሳውን ድርሻ የተወጣው (AGP) የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ነው" አቶ ተስፋ ታደለ የጃቢጠህናን ወረዳ አስተዳዳሪ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም (AGP) ወይም FSRP የተባለው ድርጅት በምዕራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ መዋለ ንዋይ በመመደብ ከሚሰሩ ድርጅቶች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው። ይህንን አስመልክተው የጃቢጠህናን ወረዳ አስተዳዳሪ ፕሮግራሙ የወረዳውን ለሁለንተናዊ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ መሆኑን ገልፀው ፕሮግራሙ በግብርናው ዘርፍ ካበረከተው ባሻገር መንገዶችን እና ድልድዮችን በመገንባት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ብልጽግናችንን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። አስተዳዳሪው አያይዘው እንደገለፁት የጃቢጠህናን ወረዳ በየትኛውም ዘርፍ ለመሰማራት መልካዓምዱሩ የተመቸ ወረዳ ቢሆንም ካለው እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ አኳያ ሰፊ የመልማት ፍላጎቱ ያልተሟላለት ህዝብ የሚኖርበት ወረዳ መሆኑን አስረድተው ባለሃብቶችና ግብረሰናይ ድርጅቶች ወረዳው ላይ እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል። ጃቢ ጠህናን ኮሙኒኬሽን
Show all...
የመስኖ ካናል ፕሮጀክቱ መገንባቱ ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ በማምረት የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ እንደሚረዳቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን የጃቢጠህናን ወረዳ አርባይቱ እንስሳ ቀበሌ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡ በጃቢ ጠህናን ወረዳ አርባይቱ እንስሳ ቀበሌ የገራይ ቁጥር 3 የመስኖ ካናል ፕሮጀክት የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት ተመርቋል፡፡ አርሶ አደር ባድማ አድማሱና አርሶ አደር አለሙ ጫኔ እንዳሉት የበጋ መስኖ ካናሉ መገንባቱ ከዝናብ ጥገኝነት ተላቀው በአመት ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ በማምረት ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው ለገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግ እንደሚያግዛቸው ተናግረው የተሰራውን ካናል የመስኖ ማህበሩ በመንከባከብ ለትውልድ ተሸጋሪ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ በጃቢጠህናን ወረዳ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማረጉ ዝጋለ የገራይ ቁጥር ሶስት የመስኖ ፕሮጀክት ከግብርና እድገት ፕሮግራም በተገኘ 32 ሚሊዮን ብር 4.8 ኪሎ ሜትር ካናል የተገነባ ሲሆን 420 ሄክታር መሬት በማልማት 410 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የተገነባውን የመስኖ ፕሮጀክት አርሶ አደሮች በመስኖ ማህበራቸው ጉዳት እንዳይደርስበት እንዲከባከቡ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ የምዕራብ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጥላሁን አለምነህ የመስኖ ካናል ፕሮጀክቶች መገንባታቸው አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት ተላቆ በአመት ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ በማምረት ከራሱ ፍጆታ አልፎ ገበያውን ለማረጋጋትም ጉልህ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡ በቀጣይም በዘመናዊና በባህላዊ ዘዴ በተገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሽፈራው ክልሉ በመስኖ መልማት የሚችል ምቹ የመሬት አቀማመጥና የውሃ ሀብት ያለው በመሆኑ በመኸር ወቅት ከሚለማው በተጨማሪ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት አርሶ አደሩ በአመት ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ እንዲያመርት ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረለት ነው ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዳኝነት ፈንታ አማራ ክልል ከ2.2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ መልማት የሚችል ቢሆንም በስራ ላይ ያለው ዝቅተኛ በመሆኑ በሁሉም አካባቢዎች በመንግስት በጀት፣ የግብርና እድገት ፕሮግራም ድርጅትንና ሌሎች አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ዘመናዊ የመስኖ ካናሎችን በመገንባት አርሶ አደሩ በአመት ሁለት ጊዜና ሶስት ጊዜ እንዲያመርት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም በመንግስት ከሚገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ አርሶ አደሩ በራሱ አቅም ካናሎችን በመገንባትና በመንከባከብ መጠቀም እንዲችል የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡
Show all...
እንደ ሕዝብ ለመጽናት እንደሀገር ለመኖር የዉስጥ ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ መግባቢያችን ሊሆን ይገባል። ********* ሀገር ማለት የሰዉ ልጆች ማኅበራዊ ስሪት ነዉ። ይህ ማኅበራዊ መስተጋብር በዜጎች መካከል በሚፈጠር ተፈጥሯዊም ሆነ ሰዉ ሰራሽ ልዩነት ዉስጥ በሚፈጠር የተቃርኖ ስንጥቅ የሚሰፋዉ እና የሚደፈርሰዉ በሰላም እጦት ነዉ። ይህ ሁኔታ ሰላም የሰዉ ልጆች የእለት ከእለት ኑሮ ዉስጥ በአጽንዖት ከሚፈልጉት አንኳር ጉዳይ አንደኛዉና ብቸኛዉ መፍትሄ መሆኑን ያስረዳናል። በዘልማድ ሰላም ከዉስጥ የሚመነጭ መሆኑን ባለመረዳት አንዳንዶቻችን አንጋጠን ሰላምን ከኛ ዉጭ እንናፍቃለን። አለፍ ሲልም ሀሳብን ወደ ጠረጴዛ ከማምጣት ይልቅ ወደ አክሳሪ እና ከፋፋይ ግጭት እንወስደዋለን። ያኔ የሰላም አየር ከባለቤቱ ይርቃል፤ አብሮነት ይናጋል፤ አንድነት ይኮሰምናል። ሰላም በናፍቆት ወይም በመሻት አይመጣም ይልቅ ከራስ የሚጀምር አልፎም ለሌሎች የሚተርፍ ሰዋዊ እሳቤ ነዉ። በግርግር ወይም በብጥብጥ ዉስጥ ሰላምን መፈለግ ደመናን እነደመጨለፍ ይቆጠራል። በልዩነት እና በግጭት የሚገኝ ሰላም፣ የሚጸና አንድነት እና የሚቆም ሀገር የለም። የሚመለስ የክልሉ ህዝብ ፍላጎትና ጥያቄም አይኖርም። ፍላጎቶቻችንና ጥያቄዎቻችን ሁሉ የሚመለሱት በሰላማዊ ትግልና በሰላም ብቻ ነው። እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ የከረሩ ልዮነቾችን ምክንያት አድርጎ እየጎላ የመጣዉ መጠራጠር እና አለመተማመን ሰላምን የሩቅ አገር አድርጎብናል። የዚህ ፈተና እያደገ መምጣት ደግሞ ሰላምን ከራስ የሚመነጭ ሳይሆን ከሌሎች የሚቸረን አድርገን በማሰባችን ነዉ። እንደ ህዝብ አንድ ሆኖ ሰላም፣ ዲሞክራሲ እና ልማት ለማምጣት ከዉስጥ የጀመረ ሰላም ብቸኛዉ ጋሻ ነዉ። ሰላም ሲኖር አንድነት፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ እድገትና ልማት ተከታትለዉ ይመጣሉ። የተለያዬ አሰላለፍ ውስጥ የገባ ማህበረሰብ ወይም ህዝብ የተሰናኘ የህዝብ አቅም ኑሮት ችግሮችን በአሸናፊነት መሻገር እንደማይችል የምንረዳበት ጊዜዉ አሁን ነዉ። ስለሆነም እንደ ህዝብ ለመጽናት እንደሀገር ለመኖር ሰላም የወል ሀሳባችን እና የጋራ ቋንቋችን ሊሆን እንደሚገባ በመገንዘብ ለሰላም እና ለዉይይት በራችን ክፍት አድርገን ለጋራ ሰላማችን ዘብ በመሆን እንድ ሆነን በአንድ በመቆም በጋራ መስራት ለነገ የማይባል ተግባር መሆኑን ልንረዳ ይገባል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ አርባይቱ እንስሳ ቀበሌ ከ420 ሄክታር መሬት በላይ በበጋ በመሰኖ ማልማት የሚችል ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሁኗል። በመስኖ ፕሮጀክት ምረቃው የክልል፣የዞንና የወረዳ አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈዋል። የገራይ ቁጥር 3 የመስኖ ፕሮጀክት ከ32 ሚሊዮን በላይ በሆነ ወጭ 4.7 ኪሎ ሜትር የበጋ የመስኖ ካናል ግንባታ በክልሉ ግብርና ቢሮና በግብርና እድገት ፕሮጎራም በጀት ተገንብቶ ተጠናቆ በመመረቅ ላይ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ከ400 በላይ አርሶ አደሮችን የበጋ መስኖ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።👏👏👏 ተጨማሪ   መረጃወችን ለማግኘት ሊኮችን 👇👇👇 ይጎብኙ። በ Facebook 👉👉  https://www.facebook.com/westgojjamcommunicationofficecommunicationoffice በ Telegran👉👉👉👉 https://t.me/WestGojjamZon በ Twitter👉👉👉👉 https://twitter.com/WestGojjamcomm1
Show all...
በባለሀብቶችና በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒሰቴር ትብብር ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ተገንብተው የተጠናቀቁ ከ57 በላይ የሆኑ ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶች ለአቅመ ደካማ የከተማዋ ነዋሪዎች ርክክብ በመደረግ ላይ ናቸው።
Show all...
በፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር የተገነባው አዲሱ የላህ ወንዝ ድልድይ ከ19ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ። በከተማ አስተዳደሩ ከ21 በላይ ፕሮጀክቶች በመንግሥት እና በባለሀብቶች ትብብር ከ157 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት ግንባታቸው ተጠናቅቆ የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ተሾመን ጨምሮ የፌደራል ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ሀላፊ፣ የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ም/ቢሮ ኃላፊና በየደረጃው ያሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት በመሆን ላይ ናቸው።
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.