cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

EMAT GURAGE MEDIA እማት ጉራጌ ሚዲያ

እማት ጉራጌ ፕሮጀክት በተስፋ ነዳ ሀሣብ አመንጪነት የተጀመረ የጉራጌንባህል ፣ ሙዚቃ ፣ ከተሞች ና የተ ቱሪዝም ሀብቶች የማስተዋወቅ አላማ ያነገበ ፕሮጀክት ነው።

Show more
Advertising posts
4 518
Subscribers
+224 hours
-17 days
-2930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከ 3 ሚልየን ብር በላይ የወጣበት የጉራግኛ አልበም ለአድማጭ ሊደርስ ነው በሙዚቃዎቹ የጉራጌ እሴቶችን፣ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ሕይወትን በተባ ኪናዊ ለዛ በመሰነድ እና በማስተዋወቅ የራሱን አሻራ ያኖረው ድምጻዊ ደሳለኝ መርሻ "ኑድንያ" የተሰኘ አልበሙን ለአድማጭ ሊያደርስ ነው። ድምጻዊ ደሳለኝ ባለፉት 20 አመታትም ሙዚቃን ሕይወቱ በማድረግ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማዎችን ሰጥቷል። ከሌሎች አርቲስቶችም ጋር በጋራ አዚሟል፡፡ ከጣት ቁጥር በላይ ነጠላ ዜማዎችም ሰርቷል፡፡ በዘመናዊ ጉራግኛ ሙዚቃዎች ውስጥ ስሙ የሚጠቀሰው ደሳለኝ መርሻ "ኑድንያ" የተሰኘው አልበም 7ኛ ስራው ሲሆን ድምጻዊው ከሰራቸው የቀደሙት ስድስት ሆኑ ሌሎች አቻ ስራዎች በተለየ መልኩ አዳዲስ የሙዚቃ ቴክኒኮችና የጉራግኛ ሙዚቃ ጠቅላላ መልክ የሚቀይር ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በጉራግኛ "ኑድንያ" ማለት ጨዋ ሴት ማለት ሲሆን የአልበሙ መታሰቢያ ለኢትዩጵያ ሴቶች ነው ሲል ድምጻዊው አስረድቷል። አልበሙ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለማህበራዊ ህይወት የሚዳስስ ሁለገብ አልበም ነው፡፡ አልበሙ ላይ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በግጥም እና ዜማ እራሱ ደሳለኝ መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ ናቲ ኃይሌ፣ ዘነበ መርሃባ፣ ሀብታሙ አብርሃም፤ አለማየሁ ወልዴ ተሳትፈዋል። በቅርንብር አሌክስ ይለፍ፣ መህመድ ኑርሁሴን፣ ሰማገኘው ሳሙኤል፤ ፋኑ ጊዳቦ፤ ቢኒአነዴ ርሆቦት (ሮባ) የተሳተፉ ሲሆን በሚክሲንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም፣ ፍሬዘር ታዬ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ቢኒእንዴ የተሳተፉ ሲሆን በ ማስተሪንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም ተሳትፏል። አልበሙ ግንቦት 16 በ ደሳለኝ መርሻ ዩቲዩብ ቻናልና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያ ለአድማጭ ጆሮ ይደርሳል። Emat Gurage Media
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ ተፈፀሞበታል ተባለ፡፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ እንደተፈጸመበት ተነግሯል፡፡ በፖሊስ ጣቢያው ዝረፊያ የተፈፀመው ትናንት ሰኞ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 7፡40 ገደማ ነው ተብሏል፡፡ በዝርፊያው ለጊዜው ተለይተው ያልታወቁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ከፖሊስ ጣቢያው እንደተወሰዱ የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ትዕግስቱ ፉጅየ ነግረውናል፡፡ በተጨማሪም ከጣቢያው ተዘርፎ የነበረ ፓትሮል መኪና መንገድ ላይ ተገኝቷል ብለውናል፡፡ በአሁን ሰዓት ፖሊስ ጣቢያው ታሽጎ የማጣራት ሂደት እየተከናወነ እንደሆም ሰምተናል፡፡ ማንያዘዋል ጌታሁን መሰጃው የሸገር fm ነው
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የጉንችሬ ታዳጊዎች ከአመት በላይ ተበትኖ የቆየው ቡዳናቸውን አሰባስበው በወረዳ በዞን ውድድሮች ላይ የሚገርም ትግል አድርገው ለክልል የክለቦች ሻምፒዮን ደርሰዋል ። ሁለት ተጫዎቾችንም ክልሉን ወክለው በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲወዳደሩ አስመርጠዋል። አሁን የከተማው አስተዳደር በጀት ጨርሻለሁ ብሏል። እኛው ደግፈናቸው ሳምንት ለቀረው ውድድር ልናበቃቸው እየታገልን ነው። ከምር ስለ ጉንችሬ የምታስቡ በማስተባበርያ አካውንት ደግፏቸው። የማስተባበርያ አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000626756275 ሙሉጌታ ባደንጋ /ኸይሩ ተማም /ጣሰው ኮሬ የቴሌግራም ግሩፕ ተቀላቀሉ https://t.me/+3afchigloywyNjg8 .
Show all...
ታዳጊዋ አፋልጉን (HELP) ተፈላጊ ታዳጊ እሌኒ ጥበቡ ዛሬ ማለትም በቀን 29/2016 ዓ.ም ከምትማርበት መልከጻዲቅ ትምህርት ቤት እንደወጣች ወደ ቤት አልተመለሰችም። ታዳጊዋ ከምትማርበት ትምህርት ቤት ወደ ገዳም እሄዳለሁኝ በማለት የምትማርበት ደብተር ለጓደኞቿ ሰጥታ ለመሳፈር ወልቂጤ መናሀሪያ አካባቢ ገብታ እንደነበረም የአይን እማኞች ተናግረዋል። ታዳጊዋ በእለቱ የለበሰችዉ የመልከ ጻዲቅ ትምሀርት ቤት ዩኒፎርም ጉርድ በሸሚዝና ጭንቅላቷ ላይ ጥቁር ሻርፕ ጣል አርጋባታለች። ቤተሰብ ተጨንቋልና እችን ታዳጊ ያያችሁ ከስር በተቀመጡ ስልክ ቁጥሮች ይጠቁሙን። ስልክ ቁጥር 0913096992 ወይም 0983840200
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አቶ ታረቀኝ ደግፌ እና አቶ ሃይደር ሙራድ ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገባቸው። ሚያዝያ 14/2016 #ዘቢዳር_ቲዩብ በሃድያ ዞን ማረሚያ ለወራት በእስር የሚገኙት አቶ ታረቀኝ ደግፌ እና አቶ ሃይደር ሙራድ በተመሰረተባቸው ተደራቢ ክስ ሚያዝያ 07 ቀን ወልቂጤ ከተማ በዋለው የፌደራል ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ውጪ ሆነው እንዲከራከሩ ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወቃል። ፍርድ ቤቱም የቀረበውን የጽሑፍ መቃወሚያ መርምሮ አቃቤ ህግም መቃወሚያ ካለው አቅርቦ ብይን ለመስጠት ለዛሬ የፌደራል ተዘዋዋሪ ቡታጀራ ከተማ ምድብ ችሎት መቅጠሩ ይታወሳል። በዚሁ ቀጠሮ መሰረት ፍርድ ቤቱ የግራና ቀኝ ተከራካሪዎችን ክርክር አድምጧል። አቃቤ ህግ በመሰረተው ክስ በ2015 በወልቂጤ ከተማ "ውኃን ሰበብ አድርገው በጠሩትና ባስተባበሩት ተቃውሞ በጠፋው የሰው ሕይወት ፣ የአካል መጉደል እና ንብረት ውድመት ተጠያቂ ስለሆኑ ዋስትና እንዳይፈቀድላቸው" ሲል የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል። ተከሣሾች በበኩላቸው አሁን የተከሰስንበት ክስ ቀደም ሲል የይዘትም የጭብጥም ልዩነት ሳይኖረው ሌሎች ተከሰውበት በተመሳሳይ ፍርድ ቤት የዋስተና መብታቸው ስለተጠበቀላቸው የእኛም ዋስትና ሊከበር ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ የግራና ቀኝ ክርክሮችን ካደመጠ በኃላ በተከሳሾች በኩል የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ቆትየ (ኃብተ ማርያም) በኢትዮጵያ ወደር የሌለው የጀግና ሜዳይ ከተሸለሙት ሁለቱ ጄኔራሎች አንዱ ናቸው። የተወለዱት በቀድሞ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በጨቦና ጉራጌ አውራጃ ቸሃ ወረዳ ሲሰ መንደር ሲሆን የወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት በሀገረ አሜሪካ ጨምሮ በአለም ላይ ትልልቅ የጦር ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ማረግ አጠናቀዋል፡፡ ብዙዎች የሚያስታውሷቸው በዓለም ላይ ብዙም ተደርጎ የማይታወቀውና በጠላት ክልል ውስጥ በፓራሹት በመዝለል ለስድስት ወራት ተዋግተው በአስገራሚ ሆኔታ ምሽጉን ሰብረው መውጣታቸው ነው፡፡ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ በተለያዩ የጦር ግምባሮች ሲዋጉና ሲያዋጉ አንድም ቦታ የማፈግፈግም ሆነ የመሸነፍ ሁኔታ ያልገጠማቸው፤ በዚህም ጠላት ሳይቀር ተስፋዬ በር ብሎ በጀግንንነት የተዋጉበትን ቦታ የሰየመላቸው፣ ጡረታ ከወጡም በኃላ ሀገር በፈለገቻቸው ጊዜ ሁሉ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከፊት የሚሰለፉ፣ የዘመቻ ዕቅድና ፕላን ሊቅ፣ ምርጥ የጸጥታና ደህንነት መሪ የሆኑት ጂኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም “የጦር ሜዳ ውሎ” የተሰኘው መጻፋቸው የምርቃ እና   የውይይት መድረክ ላይ በክብር እንዲገኙ ከወዲሁ ተጋብዘዋል፡፡
Show all...
ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ በአለም አቀፍ የዶክተሮች ድርጅት ትብብር በ12 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የተሰራው የቆርቋት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየተመረቀ ይገኛል። ይህ ትምህርት ቤት በውስጡ የስብሰባ አዳራሾች የትምህርት ቁሳቁሶች፣የአስተዳደር ቢሮዎች፣የመማሪያ ክፍሎች እና ሌሎችም ይገኙበታል። የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማምጣት ተራዶ ደርጅቶች ፣ማህበራት፣ባለሀብቶች፣ የትምህርት ማህበረሰብ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል። በምርቃ ፕሮግራሙ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ክብሩ ፈቀደ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማረያም፣ የቸሀ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ሽምንሳ አቡነ ሙሴ ገ/ጊዮርጊስ የእምድብር ሀ/ስብከት ጳጳስ፣አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ የእምድብር ሀ/ስብከት ተተኪ ጳጳስ ሌሎች የመምሪያ እና የወረዳው የስራ ኃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ዝርዝሩ እናደርሶታለን።
Show all...
ይህ መልክት የሳሚ ጉራጌው ነው! ጉራግኛ ፊልም ሊሰራ ነው በዛሬው እለት ከአርቲስቶች እና ከሶሻል ሚዲያ ወጣቶች ጋር በመወያየት ተማሪ ቤት- ያርሺ የተሰኘው ጉራግኛ ፊልም እንዲሰራ ተወስኖአል ከዚ ቀደም በቲያትር የምናውቀው ሳሚ ጉራጌው ድርሰቱን ያዘጋጀው ሲሆን ዳይሬክቲኒጉ በትልቅ ዳይሬክተር እንደሚሰራ እና በሀገራችን ታዋቂ የሆኑ የጉራጌ ተወላጅ ተዋንያን እና ወጣት አክተሮች እንደሚሳተፉበት ተገልፆአል ባጣቃላይ 55 ተዋናይ ያሳትፋል የተባለው ይህ ፊልም 620000 ብር እንደሚፈጅ ታውቆአል ይህ ፊልም  በዋነኝነት ባህል ወግ ቅርስ አብሮነት ልማት ትምህርት የእርሻ ጥበብ የልጆች እና የልጃ ገረዶች ጨዋታ ውጆ ጕዝ የጉራጌ ባህላዊ ሸንጎ ያጋ ቃዋ ፍቅር ሰላም አብሮነት ጉርዳ በሰፊው ይዳስሳል ፊልሙ የህዝብ ፊልም እንዲሆን በጉራጌ ህዝብ ፕሮዲስ እንዲደረግ ተወስኖአል በ200 ብር ቻሌንጅ 3100 ሰው እንዲሳተፍ በኮሚቴዎች የተወሰነ ሲሆን የባንክ አካውንት በአርቲስት ደሳለኝ አሳምነው በሳሙኤል ከበደ እና በሶሊያና አስፋው ስም ተከፍቶአል በዚ ታሪካዊ ስራ ሁሉም የጉራጌ ተወላጅ እንዲሳተፍ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ለበለጠ መረጃ:-0948209039 ይደውሉ 1000621948591 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደረሰኝ 0948209039/0915832644         በዚ ስልክ ቁጥር ቴሌግራም ላይ ይላኩልን በይፋ የተገኘውን ገንዘብ የምናሳውቅ ይሆናል ደረሰኙ ስለምያስፈልገን እርሶም በቴሌግራም ይላኩልን እናመሰግናለን በመደገፍ እና ሼር በማድረግ እርሶም የታሪኩ ባለቤት ይሁኑ                       ጉራጌ ኧዞኒ
Show all...