Automotive guidance
Open in Telegram
የተሽከርካሪ ሞያ ስልጠና የሀገራቀፍ ምዘና መረጃ ሞያዊ ድጋፍ፣ መፅሀፍት ሶፍትዌሮች ዜና የስራ ማስታወቂያ፣ የጨረታ ማስታወቂያዎች ሌሎችም ከተሽከርካሪ ጋር የተያያዙ መረጃዎች፤ ይቀላቀሉን ያተርፋሉ Trainings, COC Information, Professional Support, Books, Software, News, Job,Bid Announcement, Other Vehicle Related Information.
Show more333
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከመጪው ዓርብ ጀምሮ የአባልነት ምዝገባ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
በቤተ-መጻሕፍቱ አባል መሆን ልዩ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከነዚህም ውስጥ መጻሕፍት በነፃ መዋስ፣ ነፃ የውጭ የትምህርት ዕድል የማግኘት እንዲሁም ጆርናሎች እና የመመረቂያ ጽሑፎችን በኦንላይን እንዲያገኙም ይረዳል ብለዋል።
ለአባልነት ምዝገባውም የትምህርት ቤት እና ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ እንደሚያስፈልግ እና በኦንላይንም መስፈርቶችን በማሟላት አባል መሆን እንደሚቻል አመልክተዋል።
Repost from Tikvah-University
13 ድሮኖችን የሠራው የዩኒቨርሲቲ መምህር
ወጣት አማኑኤል ባልቻ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሜካኒካል ምህንድስና የተመረቀ ሲሆን አሁን ላይ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በመምህር እያገለገለ ነው።
በርካታ በአይነታቸው የሚለያዩ ድሮኖችን ሠርቶ የሙከራ በረራም አድርጓል።
የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ትምህርት ቤት በቅርቡ ሲመረቅ የሠራቸው ከ13 በላይ ድሮኖችን ለዕይታ አቅርቧል።
ወጣት አማኑኤል በመንግስታዊ እና የግል ተቋማት ድጋፍ ሁሉንም አይነት ድሮኖች የሚመረቱበት ትልቅ የድሮን ኩባንያ መክፈት እንደሚፈልግ ይናገራል።
ኩባንያው የድሮን ስልጠናዎችን የሚሰጥ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ስለ ድሮን የሚማሩበት ማዕከል እንደሚሆን ይገልጻል።
በተጨማሪም ማዕከሉ በትዕዛዝ ለተቋማት ድሮኖች የሚሠሩበት ይሆናል ብሏል።
ወደፊት እንዳደጉት አገራት እንደነቱርክ ግዙፍ ድሮኖች በኢትዮጵያ የመሥራት ተስፋ መሰነቁን ወጣት አማኑኤል ይናገራል።
@tikvahuniversity
ቀን፡ መስከረም 26/2015 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለን/ስ/ፖ/ቴ/ኮ የ2013 ዓ/ም እና የ2014ዓ/ም ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ
የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የስልጠና ዘርፎች ከደረጃ 2 – 4 በኮሌጁ በመደበኛ የስልጠና መርሀ ግብር ለተመረቁ ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ ውድድር አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ውድድር ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሰልጣኞች ለ10 ተከታታይ ቀናት የንግድ ስረ ፈጠራ ሥልጠና በመሰልጠን የንግድ ስራ እቅድ ውድድሩን ለሚያልፉ የስራ ቡድኖች የስራ ማስጀመሪያ ብር 150, 000 ኮሌጁ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀ በመሆኑ የዚህ እድል ተጠቃሚ እንድትሆኑ ኮሌጁ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
በውድድሩ የሚሳተፉ የስልጠና ዘርፎች
1. ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት
2. ሆቴልና ቱሪዝም
3. ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ
4. የልብስ ስፌትና የቆዳ ስራ
5. አውቶሞቲቭ
6. የብረታ ብረት ስራ
7. ቢዝነስ ማኔጅመንት
የምዝገባ ቀን፡- ከመስከረም 29 - ጥቅምት 01/2015 ዓ/ም ዘወትር በስራ ሰዓት
ስልጠናው የሚጀምርበት ቀን፡- ጥቅምት 02/2015 ዓ/ም
የምዝገባ ቦታ፡ በን/ስ/ፖ/ቴ/ኮ፣ የኢንተርፕሪየርሽፕ ስልጠና ማእከል አዳራሽ፣ 1ኛ ፎቅ
ማሳሰቢያ፡- በውድድሩ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆናችሁ የኮሌጁ ተመራቂዎች የት/ት ማስረጃችሁን ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ እና መታወቂያ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 0914537754 ይደውሉ
ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
አዲስ አበባ
Repost from "Melti" የመኪና ሽያጭ (Car Sell)
Melkamu Tigabu:
https://t.me/Melti
የመኪና መሸጫ ቻናላችን ይቀላቀሉ እናመሰግናለን ።
