cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሐቴርሳታ/Hatersata ✞

raise a generation that is suitable to God and his timely agenda.🙏👉የእግዚአብሔርን ቃልና ከቃሉ ጋር ሀሳባቸው የሚዛመድ መዝሙሮች : የድሮና የአሁን ጊዜ ዝማሬዎችን በዚው ቻናል የሚያገኙ ይሆናል። ሌላው ደግሞ የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ፅሁፎች ፤ ግጥሞች እና ሌሎችም የሚለቀቁ ይሆናል።

Show more
Advertising posts
399
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from #KALTUBE
#ተለቀቀ ቃልኛ መንፈሳዊ መፅሔት     💐ዘጠነኛ እትም    በቃልቲዩብ የተዘጋጀ 👆7ሜ.ባ PDF ያውርዱት ●18 ጥያቄዎች ለተወዳጇ ዘማሪት አይዳ አብርሀም 💐 የስራ ባህልና ክርስትና (በነቢይ መሳይ አለማየሁ) 💐ክርስትናችሁን ከወረት ጠብቁ (በፓስተር ስንታየሁ በቀለ) 💐ትናንቱን የረሳ ትውልድ ፤ የባህልና ትውፊት ክስረት (በቢንያም አዲሱ) 💐ጥሩ አድማጭ መሆን! (በአቤኔዘር አለማየሁ) እና ሌሎች . . . ... ለወዳጆቻችሁ ለአማኞች ፣ ለማያምኑ ሼር❤️   ለበፊት እትሞችን | ይሄን ይጫኑ | 💐💐💐💐💐💐💐💐💐          @KALTUBE          @KALTUBE          @KALTUBE
Show all...
➘ ➘ ➘ SHARE ➘ ➘ ➘
Repost from #KALTUBE
Photo unavailableShow in Telegram
💛ቃልኛ መፅሔት ዛሬ ምሽት 3:00 ይለቀቃል 💐ለወዳጆቻችሁ ሼር 👇👇👇👇 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Show all...
Repost from #KALTUBE
Photo unavailableShow in Telegram
💐ቃልኛ መንፈሳዊ መፅሔታችን 9ተኛ እትም በዚህ ሳምንት በነፃ ወደናንተ ይደርሳል። በዚህ እትም ●18 ጥያቄዎች ለተወዳጇ ዘማሪት አይዳ አብርሀም 💐 የስራ ባህልና ክርስትና (በነቢይ መሳይ አለማየሁ) 💐ክርስትናችሁን ከወረት ጠብቁ (በፓስተር ስንታየሁ በቀለ) 💐ትናንቱን የረሳ ትውልድ ፤ የባህልና ትውፊት ክስረት (በቢንያም አዲሱ) 💐ጥሩ አድማጭ መሆን! (በአቤኔዘር አለማየሁ) እና ሌሎች መንፈሳዊ ፁህፎች ፤ ወጎች ፤ የተለያዩ ነገሮች ይኖራሉ።        በዚህ ሳምንት ይጠብቁን በቃልቲዩብ ቴሌግራም በነፃ ይለቀቃል 💐💐💐💐💐💐💐💐💐          @KALTUBE          @KALTUBE          @KALTUBE     | የበፊት እትሞችን ለማግኘት👉 ይሄን ይጫኑ |
Show all...
Watch "Daniel Amidemichael @Live Worship 2022- ካረካህ - Karekah" on YouTube https://youtu.be/FL2YeqlQGoU
Show all...
Daniel Amidemichael @Live Worship 2022- ካረካህ - Karekah

በዚህ ዝማሬ እንደምትባረኩ እና ከፍ እንደምትሉ እናምናለን !Subscriber And Share The Channel Link

https://youtube.com/channel/UCJL3_lxwufvpr1oLz2EBL9g

Repost from #KALTUBE
Watch "Season 1 Episode -2 ባካኝ ነፍስ Koinonia -2022 By Mercy" on YouTube https://youtu.be/02xzLhHvJIQ
Show all...
Season 1 Episode -2 ባካኝ ነፍስ Koinonia -2022 By Mercy

በዚህ ቪዲዮ እንደምትባረኩ እና ከፍ እንደምትሉ እናምናለን !Subscriber And Share The Channel Link

https://youtube.com/channel/UCJL3_lxwufvpr1oLz2EBL9g

Watch "Christian TikTok MUST WATCH|የሳምንቱ እጅግ አዝናኝ እና አስቂኝ ቲክቶክ ቪዲዮች ስብስብ" on YouTube https://youtu.be/1g078GPOYFA
Show all...
Christian TikTok MUST WATCH|የሳምንቱ እጅግ አዝናኝ እና አስቂኝ ቲክቶክ ቪዲዮች ስብስብ

#christiantiktok #protestant #videos #mustwatch

Watch "Hanna Tekle እንደ ሰው Endesew lyrics ሀና ተክሌ 2022" on YouTube ይራራልናል ያስብልናል በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል ይመጣል ነገ ዛሬም ያልቅና ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናትና ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና በኢዲስ ዝማሬ በአዲሱ ዜማ https://youtu.be/jN_4B3OEE40 https://youtu.be/jN_4B3OEE40
Show all...
Hanna Tekle እንደ ሰው Endesew lyrics ሀና ተክሌ 2022

Hanna Tekle እንደ ሰው Endesew lyrics ሀና ተክሌ 2022 “ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።” — ዕብራውያን 4፥15 “For we do not have a High Priest Who is unable to understand and sympathize and have a shared feeling with our weaknesses and infirmities and liability to the assaults of temptation, but One Who has been tempted in every respect as we are, yet without sinning.” — Heb 4:15 (AMP)

Watch "Season 1 Episode -1 የጓደኝነት ምርጫ በሜርሲ Koinonia -Podcast 2022 By Mercy" on YouTube https://youtu.be/tt2j2zJFiec
Show all...
Season 1 Episode -1 የጓደኝነት ምርጫ Koinonia -Podcast 2022 By Mercy

በዚህ ቪዲዮ እንደምትባረኩ እና ከፍ እንደምትሉ እናምናለን ! Subscriber And Share The Channel Link

https://youtube.com/channel/UCJL3_lxwufvpr1oLz2EBL9g

Watch አይዳ አብረሀም 👇🏽 https://youtu.be/Wvjqbp02Ues https://youtu.be/Wvjqbp02Ues
Show all...
በሁሉ ላይ -አይዳ አብርሀም 2022 Live Worship Ayda Abraham -ID

#liveworship #Protestant በዚህ ዝማሬ እንደምትባረኩ እና ከፍ እንደምትሉ እናምናለን ! Taken From AYS Pre Event -House Worship

💐 ራስን መተዋወቅ የምሳ ሰዓት መልዕክት | በዮሐ 1፥ 41-43 ላይ የተመሠረተ የጸሀፊው ምናባዊ ዕይታ ነው። © እፎይ-ታ - KALTUBE ዮሐንስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴¹ ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ። ⁴² እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው። ⁴³ ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ፦ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው። 💐ዕድገቱና ኑሮው በገሊላ ባሕር ላይ የተመሠረተው ስምዖን ወንድሙን እንድሪያስን ቀኑን ሙሉ አላየውም። የዓሣ ማጥመዱን ሥራ ጥሎ የተሰወረበትን ምክንያት ለማወቅ አልቻለም። ማለዳ ከጓደኞቹ ጋር ዮሐንስ ወደ ሚያሰተምርበትና ወደ ሚያጠምቅበት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንደሄደ ቢያውቅም እንዲህ የሚያሰመሸው ጉዳይ ይኖራል ብሎ አልገመተም። ይህን ሀሳብ እያወጣና እያወረደ ሳለ ድንገት አንድ ሰው ወደ እርሱ እየተንደረደረ ሲመጣ ከሩቅ ተመለከተ። ወንድሙ እንድርያስ ነበር። ከወትሮው ለየት ባለ የጋለ ሰላምታ ያጣድፈው ጀመር። ስምዖን በወንድሙ ሁኔታ በመገረም “ምን ቢያገኝ ነው እንዲ የሚፈነጥዘው?” በሚል የፍንደቃውን ምሥጢር ለማወቅ ቸኩሏል። ደስታና መገረም ተቀላቅለው እንድሪያስ ፊት ላይ ይነበባሉ። 💐እንድርያስ ሕይወቱን ቀኝ ኋላ ያዞረውን ክስተት ሊሸሽገው አልቻለም፤ ትንፋሹ ቁርጥ፣ ቁርጥ እያለ “መሢሕን አገኘነው፣ አሥር ሰዐት ያህል አብረነው አሳለፍን፣ በእርግጥ እሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው።” አለው። "መሢሕ ?” ለስሞዖን ጆሮውን ማመን አልቻለም። ነቢያት የተናገሩለትን፣ ቅዱሳት መጽሐፍት የመሠከሩለትን፣ አስራ ሁለቱ ነገዶች በናፍቆት ጠብቀው ያላዩትን፣ የእስራኤልን ተስፋ፣ የዓለምን ንጉሥ አገኘሁት ነው የምትለኝ?" የማይመሥል ነገር ሆነበት። ሆኖም ወንድሙን ሊጠራጠር አልቻለም። አንድን ነገር በሚገባ ካላጣራ በስተቀር በቀላሉ የማይቀበል፣ የሰከነ ስሜት ያለው መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል። ስምዖን ጊዜ አልወሰደም "እና... እኔንም ልታስተዋውቀኝ ትችላለህ?” አለው የሰማውን ለማየት በተጣደፈ ድምጽ። “አዎን ማንም ሊቀርበው የሚችል፣ ከውጪ ስታየው ፈጽሞ የማይመስል፣ ስትቀርበው ግን ከውስጡ የሚወጣው ቃል ሕይወትህን የሚለውጥ አስገራሚ ሰው ነው።" አለው ትኩስ ትዝታውን እንደ ገና በሕሊናው እየሳለ። ስምዖን ከተቀመጠበት ተነሳ፤ ሥራ ላይ የዋለበትን ልብሱን አራግፎ፣ መጎናጸፊያውን ደርቦ እንድርያስ በመጣበት እቅጣጫ አብረው ነጎዱ። 💐ስምዖን ነገሩ ሕልም ይሁን እውን መለየት ተስኖታል። እግሮቹ በደመነፍስ ይራመዱ እንጂ ልቡ ቀድሞ ሄዷል። ድንገት ከሰመጠበት የሃሳብ ሰመመን ባነነና “አሁን በእግዚእብሔር የተቀባውን ፊት ለፊት ላየው ነው? ላነጋግረው ነው?” በማለት ራሱን ጠየቀ። አጠገቡ ሲደርስ እንዴት ራሱን ለመሢሑ እንደሚያስተዋውቅ ያወጣና ያወርዳል። ሳይታወቃቸው በፍጥነት ይራመዱ ነበርና ቀን እንድርያስና ጓደኛው ኢየሱስን ተክትለው ወደ ሄዱበት ቦታ ደረሱ። 💐ኢየሱስ በአንድ የበለስ ዛፍ ሥር ድንጋይ ላይ ተቀምጧል። እንድርያስ ጠጋ ብሎ ስላምታ ሰጠውና ወደ ጎን ፈቀቅ ብሎ ቆመ። ስምዖንም እንዴት ራሱን እንደሚያስተዋውቅ እያስበ “ስ-ም-ኦ-ን እባላለሁ፤ የዮና ልጅ ነኝ ..." ለማለት ሲዳዳው ኢየሱስ ቀደም ብሎ በተረጋጋ ድምጽ አንተ ስምዖን ነህ...” አለው። ስምዖን ራሱን ሳያስተዋውቅ ስም በመጠራቱ ተገርሞ "ይሄ እንድርያስ የቤታችን ሚስጥር አንድም እልቀረውም፤ ሁሉን ነግሮታል” በማለት አሰበ። “ስምዖን መሆንህን በማወቁ ምን ይገርምሃል! ይህንንማ አንተን የሚያውቁ ሰዎች ሁሉ ያውቁታል፤ ይልቅ ልንገርህ አንተ ኬፋ ነህ! ጴጥሮስ! ዓለት ነህ! ለመቅደስ መሠረት የሚሆን ጽኑ ዓለት። 💐ስምዖንና እንድርያስ ጊዜው ስለ መሸ ቆይታቸውን ፈጽመው ወደ ቤታቸው ለመመለስ መንገድ ጀምረዋል። ስምዖን ግን በተለየ ስሜት ውስጥ ሰምጧል “እኔ ጴጥሮስ ነኝ? ጽኑ ዐለት? የመሠረት ድንጋይ?” በማለት ራሱን ይጠይቃል። ራሱን ሊያስተዋውቅ ሄዶ፣ ራሱን ተዋውቆ መመስሱ አስገርሞታል። በእርግጥ ስምዖንን በዐለትነት ማንም አያውቀውም፤ ወላጆቹም እንዲህ አያውቁትም፤ ሌላው ቀርቶ እርሱ ራሱ እንኳ ራሱን እንዲህ እያውቀውም። ዛሬ ግን ገና በሆድ ሳይሠራ ከሚያውቀው ጋር ተገናኘና ራሱን ተዋወቀ። 💐ዛሬ ስንቶቻችን ነን ራሳችንን ወላጆቻችን፣ ጓደኞቻችን፣ ዘመዶቻችን፣ መምህራኖቻችን... ወዘተ እንዲህ ነህ! እንዲህ ነሽ ባሉን ተስማምተን “እኔ እኮ እንዲህ ነኝ” እያልን ያልሆነውን እየዘመርን የምንኖር? ኢየሱስ ክርስቶስን ስናገኝ ግን ዓለም ሳይፈጠር በሚያውቀን፣ በእናታችን ሆድ ሳንሠራ በመረጠን፣ እውነተኛ ማንነታችንን ሊነግረን በሚችል ጌታ ፊት እንቆማለንና ያኔ ክእውነተኛ ማንነታችን ጋር እንተዋወቃለን። እሱን ማውቅ ራስን መተዋውቅ ነው ........ 👉 ሙሉውን ለማንበብ ይሄን ሰማያዊ ጽሁፍ ይጫኑ 👈 አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ 😊 💐💐💐💐 @KALTUBE @KALTUBE @KALTUBE
Show all...
"ራስን መተዋወቅ"

በዮሐ 1፥ 41-43 ላይ የተመሠረተ የጸሀፊው ምናባዊ ዕይታ ነው።  © እፎይ-ታ ዮሐንስ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴¹ ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ። ⁴² እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው። ⁴³ ወደ ኢየሱስም አመጣው። ኢየሱስም ተመልክቶ፦ አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ አንተ ኬፋ ትባላለህ አለው፤ ትርጓሜው ጴጥሮስ ማለት ነው። ዕድገቱና ኑሮው በገሊላ ባሕር ላይ የተመሠረተው ስምዖን ወንድሙን እንድሪያስን ቀኑን ሙሉ አላየውም። የዓሣ ማጥመዱን ሥራ ጥሎ የተሰወረበትን ምክንያት ለማወቅ አልቻለም። ማለዳ ከጓደኞቹ ጋር ዮሐንስ ወደ ሚያሰተምርበትና ወደ ሚያጠምቅበት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንደሄደ ቢያውቅም እንዲህ የሚያሰመሸው ጉዳይ ይኖራል ብሎ አልገመተም። ይህን ሀሳብ እያወጣና…