cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Prince Faysul

:¨·.·¨: ❀  `·. @Princ_Faysul

Show more
Advertising posts
6 940Subscribers
+224 hours
-177 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በጀናዛ በማጠብ ላይ የተሰማራ አንድ ወንድም የሆነን አጋጣሚ እንዲህ ይተርክልናል.. ከእለታት አንድ ቀን አርባወቹ ያልደረሰ ወጣት ሙቶ ከጓደኞቹና ከቤተሰብ ጋር ታጥቦ እንዲሰገድበት ወደ መስጅድ መጣ.. ከመጡት ሰወቹ መሀል አንድ ወጣት በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሳበኝ ወጣቱ የሞቹ አይነት እድሜ ውስጥ ያለ ወጣት ነው  ። በጣም ያለቅሳል በየመሀሉ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ቃልን ይደጋግማል ራሱን ለመቆጣጠር ድምፁን ዝቅ ለማድረግ ቢሞክረም አልቻለም በጣም እያለቀሰ ነበር።   ከኔ ጋር ወደ ማጠቢያ ክፍል ገባ ወጣቱ በየመሀሉ  በጣም ሲያለቅስ አብሽር ታገስ ትግስት ማድረግ እንዳለበት እነግረዋለሁ ።    ምላሱ ይህን ቃል ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ደጋግሞ ይል ነበር ። ይህንን ቃል ስሰማ እኔ እርጋታ ይሰማኛል ለቅሶው በጣም ስራውን እንዳልሰራ እያደረገኝ ስለነበር ።      ለወጣቱም ወንድምህን አላህ ይማረው ካንተ በላይ አላህ ለሱ አዛኝ ነው ። ትግስት ማድረግ አለብህ አልኩት.... ወጣቱም ወደኔ እየተመለከተ ወንድሜ አይደለም አለኝ ! በጣም ተገረምኩ ይህ ሁሉ ለቅሶ ይህ ሁሉ እዝነት እንዴት አልኩ በውስጤ ...   ወጣቱም ከወንድሜ በላይ የሆነ ውድ የሆነ ጓደኛየ ነው ።  የልጅነት ጓደኛየ..የትምህርት ቤት ጓደኛየ ክፍል ውስጥ አብረን ተቀምጠን በረፍት ሰዓትም አብረን አሳልፈን ...በሰፈር ውስጥ አብረን ተጫውተን...አብረን አድገን ግንኙነታችንም አብሮ አድጎ አብረን ዩኒቨርስቲ ገብተን አብረን ተመርቀን አንድ አይነት ስራ ይዘን እህትማማቾች አግብተን ወንድና ሴት ወልጄ እሱም በተመሳሳይ ወንድና ሴት ወልዶ በአንድ አከባቢ ቤት ተከራይተን እየኖርን ደስታችንንም ሀዘናችንንም አብረን እያሳለፍን አብረን ደስታ ሲኖር ደስታው እየጨመረ ስንገናኝ ሀዘኑ እየቀነሰ  በሁሉም ነገር አብረን ነበር የምንኖረው ... ታሪካቸውን ሲነግረኝ አልቻልኩም በጣም አለቀስኩ... ያሸይኽ ምድር ላይ እንደኛ አይነት ግን አለ...⁉ ይች ንግግር ልቤን ነካው.. ሩቅ ያለውን ወንድሜን አስታወስኩና የለም አልኩት.... ሱብሐነላህ የሚለውን ቃል እየደጋገምኩ አጥቤው ጨረስኩ ወጣቱም የጓደኛውን ግንባር ሳመና በጣም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ..   ሰወች ይዘውት ወጡ ሶላቱል ጀናዛ እንድንሰግድበት .... ሰግደን እንደ ጨረስን ጀናዛውን ተሸክመን ወደ ቀብር ቦታ ሄድን ... ጥግ ላይ ቁሞ ወዳጅ ዘመድ እያፅናናው ቀብረን ጨረስን ሰወች ሲሄዱ ለጓደኛው ዱዓ አርጎ ተመለስን ....      በሚቀጥለው ቀን አሱር አከባቢ መስጂድ ትናንት የተመለከትኮቸው ሰወች አንድ ጀናዛ ይዘው መጡ.... ትናንት የተመለከትኩትን ወጣት መልክ ያለው አንድ አባት እያለቀሱ ተመለከትኩ ያ ሸይኽ ትናንት እኮ ጓደኛው ጋር ነበር ጓደኛውን ሸኝቶ ዛሬ ተከትሎ ሄደ ትናንት ለጓደኛው ከፈንና መቀስ ሲያቃብል ጓደኛውን እየገለባበጠ ሲነካ ነበር ትናንት በጓደኛው ሞት ልብ ተነክቶ ሲያለቅስ ነበር እያለ አባቱ ስቅስቅ ብሎ አለቀ..    የተሸፈነበትን ስገልጠው ትናንት በጓደኛው ሞት እያለቀሰ የነበረው ወጣት እንደሆነ አወኩ   በጣም ደንግጫ እንዴት ሞተ አልኮቸው ሚስቱ የሚበላ ብታቀርብለት አልበላ አለው  መተኛት ፈልጎ ተኛ አሱር ላይ ሚስቱ ስቀሰቅሰው ሙቶ ተገኘ ...    በጓደኛው ሞት ድንጋጤ አልቻለም ነበር ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን የሚለውን ደጋግሞ ይል ነበር....     ጀናዛውን አጥበን ሰግደንበት ወደ ቀብር ቦታ ስንሄድ ሌላ አስገራሚ ነገር አገኘን ከትናንት ሞች ብኋላ ሌላ የሞተ ሰው አልነበረም ይህ ብዙ ጊዜ አያጋጥምም ነበር ከጓደኛው ቀብር ጎን ቀብረነው ተመለስን
Show all...
👍 25😢 9 1
አዝና ተመለከታትና ምን ሁነሽ ነው ሲል ጠየቃት...? እቀፈኝና እነግረሀለሁ አለቺው...🥺 ሲያቅፍት ሀዘኖን ረሳች..😊 እሱም መጠየቁን ረሳ...😇 እኔም አፌን መክፈቴን ረሳሁ....😄 ምን እንደምላቹህ ረሳሁ......😎
Show all...
አንድ ወንድም አጋጣሚውን እንዲህ ይተርክልናል ።   የሆነ ጊዜ ወንድሜ አዲስ ቤት ሰራና ለመዘየር ሄኩኝ በአዲሱ ቤቱ ወንድሜም በጥሩ መስተንግዶ ተቀበለኝና ጥሩ ጊዜ አሳለፍኩ ወደ ሰዓቱ ስመለከት ለኢሻ ሶላት ግማሽ ሰዓት ይቀር ነበር ...! ለወንድሜ ወደ መስጂድ መሄድ እንደምፈልግ ስነግረው ገና ነው አዛን አልተባለም አለ...? ሶላት እስኪደርስ ድረስ ቁርዓን እየቀራሁ እጠብቃለሁ ልሂድ ብየ ሄኩኝ ... ወደ መስጂድ ስደርስ  መስጂዱ ባዶ ሁኖ አገኘሁት ቁርዓን አንስቼ መቅራት ጀመርኩ..! ከትንሽ ደቂቃ ብኋላ አንድ ልጅ ወደ መስጅድ በመግባት ሰላምታ አቀረበልኝና ሶላት ቆመ ሁለት ረከዓ ሰገደ አሰላመተ በድጋሜ ሶላት ቆመ ሱጁድ ላይ በጣም ይቆይ ነበር .... በሶላቱ በጣም ተገረምኩ በዚህ እድሜው በዚህ ልክ ኹሹእ ሲያደርግ አላህ ጋር ያለው ግንኙነት አስቀናኝ ። ሱጅድ ላይ ሲቆይ ምን እያለ ነው ብየ ጠጋ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ... ወደ ልጁ ተጠግቼ ሳዳምጠው ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ ማልቀስ ጀመርኩ ጌታውን እንዲህ እያለ ሲጣራ ነበር... ያረቢ አባቴ የሆነ ነገር ሲቸግረን ወደዚህ እንድመጣ አደራ ብሎኛል.. እኔም ኢሄው እጅህ ላይ የተናነሰ ደካማ ራሀብተኛ  የተቸገረ ሁኜ ቀርቤለሁ.... ያረቢ ትናንት ጀምሮ ምንም እንዳልበላን አንተም ታቃለህ .. ያረቢ ትናንሽ ወንድሞቼና እህቶቼ ረሀብን መቋቋም አይችሉም .. እኔና እናቴ ግን መቋቋም እንችላለን ... ነገር ግን ታናናሾቼ በረሀብ ምክንያት ሲያለቅሱ ሳይ ወደ አላህ ሂጄ  የሚበላ እንዲሰጠን እጠይቀዋለሁ አልኮቸው! አባቴ እንዳስተማረኝ  ያረቢ እባክህን እናቴና ታናናሾቼ ዘንድ አታሳዝነኝ እባክህን አንተ እኮ አሸናፊ ሀብታም አዛኝ በጣም ሩህሩህ መልካም ነገሮች በሙሉ በእጅህ ነው አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ ያረቢ የዱዓ አደራረጉ በጅጉ ልብ ይነካል እድሜው ገና አስር ቤት  ቢሆንም ሁኔታው ልብ ይነካል አላህን ደጋግሞ ይለምናል ሱጁድ ላይ እያለ  ታናናሾቹን አላህ ምግብ እንዲሰጣቸው እያለቀሰ ይማፀናል ። ሰወች መተው ኢሻን እስክንሰግድ ድረስ ተከታተልኩት ።  ኢሻን ሰግደን ስንጨርስ ወንድሜን አገኘሁትና  ይህ ልጅ ማነው ታቀዋለህ ወይ ስል ጠየኩት...? ወንድሜም አዎ አቀዋለሁ የመስጅዳችን ኢማም ልጅ ነው አባቱ ሙቷል አላህ ይዘንለት አለኝ ። የት እንደሚኖር ልጠቁመኝ ትችላለህ አልኩት ወንድሜም ታሪኩ ምንድን ነው አለኝ..? ምንም የለም ዝም ብለህ ቤቱን  አሳየኝ  ....! ከመስጅድ ወተን የልጁን ቤት አሳየኝ ወደ ሱቅ ሂጄ በርካታ የሚበላ ምግብና በርከት ያለ ገንዘብ በውስጡ አስቀምጫ ቤታቸው ደጃፍ ላይ ቆሮቁሬ ቶሎ ተደበኩኝ! ልጁም ወደ ውጭ ወጣና ቀይና ግራውን ሲመለከት ማንም የለም ወደ ታች ሲመለከት ምግቡን አየው የተቆጠሩትን ምግቦች እየነካካ እንዲህ ሲል ጮሀ እናቴ ሆይ በርካታ ምግብ አገኘሁ አላህ አመጣልን .... በጣም ደስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለአላህ ሱጁድ አደረገ .....
Show all...
40😢 14👍 8🔥 3
አንዲት ሴት ባሏ ይሞትባትና ሰደቃ መስጠት ትፈልጋለች... ጁመዓ ማታ ምግብ ሰርታ በሰፈራቸው ላሉ የአንድ ሚስኪን ቤት እንዲያደርስ የቲሙ ልጇን ላከቺው። ልጇም እናቱ የሰራቺውን ይዞ ሄደ መንገድ ላይ ግን በጣም ራበው ራሀቡን ተቋቁሞ አድርሶ ተመልሶ ቤት ገብቶ ተኛ እየራበው ። በሁለተኛው ሳምንት ጁመዓ ማታ እናቱ ለባሏ ሰደቃ መሰደቅ ፈልጋ ምግብ ሰርታ ለልጇ ላከች አሁንም በተመሳሳይ እየራበው ልጇ አድርሶ ተመልሶ ራቱን ሳይበላ ተኛ በሶስተኛው ጁመዓ በተመሳሳይ እናቱ ሰደቃ መስጠት ፈልጋ ለልጇ ምግብ ሰርታ ለሚስኪኖች ላከች ልጇም ምግብን ይዞ ሲሄድ ረሀቡን አልቻለም ነበርና ለሚስኪኖቹ የተዘጋጀውን ምግብ በልቶ ወደ ቤት ተመልሶ ገባና ተኛ ። የዛች ምሽት ለሊት እናቱ በህልሞ ባሏ ይመጣና የምሰጪው ሰደቃ ዛሬ ገና ደረሰኝ አላት ። እናቱ ስትነቃ ልጆን ጠየቀቺው የማታውን ሰደቃ የት ነው ያደረስከው ..? ልጁም ሁለቱ ሳምንታትን ራሀብን ተቆቁሜ ሰደቃውን ላልሺኝ ሚስኪን አደረስኩ የማታው ግን ከአቅሜ በላይ ነበርና ሚስኪኑ ቤት ስደርስ በጣም ራበኝ መቋቋም አቃተኝና በላሁትና ወደ ቤት ተመልሼ ጠግቤ አደርኩ አላት... እናትም የአባቱ ሰደቃ በቅድሚያ ለየቲሙ ልጁ እንደሚገባ አወቀች አህባቢ ቤት የተራበ ሰው እያለ ውጭ ሂደን አንሰድቅ ሰደቃ የሚጀምረው ከቤት ነው..
Show all...
👍 28 20
አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ሌሎች ስህተት እንደሠሩ እንዲያውቁ ለማድረግ ምርጡ መንገድ ነው። !
Show all...
16👍 1
የወደፊቱን ህይወት ለማሻሻል የሚሞክርን ሰው ያለፈውን ነገር አታንሳበት."
Show all...
👍 13🔥 3
ሁሉም ነገር ጊዜያዊ ነው" ችግሮቻችንም ጭምር። = #የማለዳ_መልዕክቶች
Show all...
👍 16
ይህንን ሰፊ አለም ተመለከታችሁት በውጭ ባለው ነገር በውስጥ ባለው ነገር ሁሉንም የያዘውን ነገር  አንዲትም ጉንዳን አታገኙም አላህ የሷን ሲሳይ የሰጣት ቢሆን እንጂ ..... አትፍራ  አላህ እኮ አንተንም ጠባቂ ነው
Show all...
16👍 7