❤የፍቅር ግጥም❤
Open in Telegram
✍የስነፅሁፍ ተሰጥኦዎች 📜ግጥም❤ 💆የጭንቅላት ጨዋታዎች 💭አባባሎዎች፣ 👽Psychology Facts🌷 ❤️ልብ_ወለድ እና ጠቃሚ ምክሮች ያለገደብ #ከልብ_ዲያሪ ወደናንተ ይደርሳሉ በተጨማሪም💎 ✍ግጥም 💖የፍቅር❤️ የይቅርታ🙏 የመልካም ምኞት መግለጫ
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 848
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
4 848
ሀረግ ዋርካ መስሎት አንገቷን አነቀው
አይኗን እየዞረ የእሳት ራት ሞቀው
አፏን ንብ ቀሰመው ጥርሷን ጠባው ጥጃ
በሷ የማይሳሳት መኖሩንም እንጃ
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
4 848
ቢቀናኝ እሰየው ባይቀናኝ ምን ገዴ
አንቺን ይዞ መኖር አይታክተው ሆዴ
.
.
የአለምን ጎዳና ብወጣ ብወርደው
አንቺን አይቼ እንጂ ብቻውን አሎደው
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
4 848
ውዴ
መልክሽ ይገርጣልሽ ውበትሽ ይጠንዛ
አንቺነትሽ ይርገፍ ብጉር ፊትሽ ይብዛ
ጥፍርሽ ዱምድም ይሆን ፀጉርሽም ይጠር
ሰላም ሚልሽ አይቶ ደንግጦ ይሰበር
አይንሽ ፈጦ ይውጣ አፍንጫሽም ይርዘም
መልከ ጥፉ ሁኚ የሚያይሽ ዬለም
ከዛ
አንቺን መሳይ ፋንጋ ሁሉም ስለሚሸሽ
እንዲ ያርግሽና ብቻዬን ላፍቅርሽ
4 848
#ቲቸር፦ አፍ ለምን ይጠቅማል
#ተማሪ፦ ለመሰዳብ!
#ቲቸር፦ሂድ!.....ዱርዬክፍት አፍ!
#ተማሪ፦ ይኸው አላልኮትም 😛 😃
ከታች ምርጫቹን መርጣችሁ ጥርሳችሁ እስክሰበር ሳቁልኝ
4 848
ቅርብ ጊዜ በተደረገው ትምርታዊ ቻናል ዉድድር ላይ በመቅረብ ለመሰናዶ ኦና ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች👉 PDFs
👉 Guide books
👉 Short notes
👉 worksheets
👉Mid exams
👉Final exams
👉Assignments
👉Lecturer's power points in .pptx format
እና ሌሎች መረጃዎች በማቅረብ ተመራጭ እና የዓመቱ ምርጥ ቻናል ተብሎ የተመሰከረለት ቻናል ነዉ።
ተማሪዎች ብቻ ይፈልጋል ተቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
4 848
ይሄ ንፁህ ሳቅሽ ጥርሴን አስገለጠኝ
እሄ ተአምር ቃልሽ እምባዬን አስዋጠኝ
ሳይዉል ሳያድር ጨነቀኝ በሀሳብ ገምቦ ተገፋው
ግዜያዊ ሳቅሽን ሳስብ ከመሞት በላይ ተከፋው
join @yefkr_gtm
4 848
[..ልክፍት..]
. .
አዉቃለሁ ጠልተሽኛል፣
አትወጅኝም ይገባኛል..፣
መቼስ አንዴ ለክፈሽኛል፣..
(መቼስ አንዴ..
ታምሜያለሁ፣)
ዛሬም አንቺን አስባለሁ።
.
(አዎ..!)
ከሄድሽ በሁዋላ...
'ምወዳቸዉ ሴቶች..
'ማደንቃቸዉ ሴቶች..
ከ'ኔ ጋር ያደሩ..
ከ'ኔ ጋር የዋሉ፣
(በጥቂቱም ቢሆን)
አንቺን ይመስላሉ።
.
ተመልከቻት እሷን፣
ዉብ አረማመዷን...
እግር አነሳሷን፣
'ያነጋገር ስልቷን
ደግሞ አለባበሷን፣
"ቁርጥ እራስሽን!"
(ማለት ቢያስቸግርም፣)
የሆነ ነገሯ..
እንዳ'ንቺ እንደሆነ
አያጠራጥርም!!
.
(እያት ደግሞ ያቺን...)
'ካፍንጫዋ በታች
ያለዉ ከፊል ገጿ፣
ከንፈርና ጥርሷ..
የንግግር ድምጿ፣
ደግሞ ሳቅ ስትል..
የጉንጯ ስርጉዳት፣
ያንችን በመምሰሉ
ነፍሴን ሲያሻፍዳት፣
ልቤን ሲያሟሽሻት፣
(አየሽኝ?)
አየሻት?
።
እናልሽ..
ከብዙ ሴቶች ላይ
ጥቂት አንችነትን እያነፈነፍኩኝ፣
ያቺንም
ያቺንም
"ወደድኩዋት" ስላልኩኝ፣
'ባገር በመንደሩ "ሴሰኛ" ተባልኩኝ።
.
ሰማሽልኝ ስሜን?!
ልክፍቴን ህመሜን?
ስራብሽ
ስጠማሽ
በሰዉ አፍ መክረሜን?!
.
አየሽልኝ ህልሜን?!
አንችን ባላገኝሽ...
'ካምሳያሽ ጋራ ነኝ
እድሜ ዘላለሜን!!
........
{}
/በቃሉ ሹምዬ/
Join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
@yefkr_gtm
4 848
ዘመንም ልክ እንደፊደል
እገልጥሽ ብሎ ቢታትር
በንቀት አይን አየሽው
ከፈልሽው በሳቅሽ በትር
በቁጥር ችሎ ላይዘልቀው
ላይረጋ ከነብስሽ እኩል
ፊትሽን ቋጥሮ ሊፈታው
መጣብሽ በእድሜ በኩል
ጠይም ነሽ ቡናማ መሳይ
አይደንቅሽ የከውኑ ግዳይ
ወተሻል ከሰውልጅ መደብ
ቀድመሻል ከግዜ አረንቋ
አታውቂም በቁስ መለካት
አይደለሽ ጌጣጌጥ ብርቋ
እኔ እንኳ
ሳቅሽን ተቋደስኩ እንጂ
ማን ችሎ ከዚ አተረፈኝ
ጥላዬን ይዤ ብማትር
ናፍቆትሽ ብቻ ገረፈኝ
ይበለኝ ይግረፈኝ በጣም
ያንድደኝ ለኩሶ በሳት
ድካሙስ የወጉ ነበር
መንገድ ነው የእግሬ ትኩሳት
መንገድሽ ተሰውሮኛል
ባልመጣም ስቀሽ ጠብቂኝ
ከዘመን አንሼ እንዳልቀር
ከራሴም እንዳታርቂኝ
✍ አዲብ
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
4 848
💔የማያሽር...ጠባሳ💔
፨።።።💘💘💘።።።፨
ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።
✨Join & Share✨
❣❣ @yefkr_gtm ❣❣
❣❣ @yefkr_gtm ❣❣
4 848
◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━ ◈
ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ወንድሜ ብለሽ ቀርበሽኝ
ቀልደሽ ተጫውተሽ ስቀሽ እያሳቅሽኝ
ሳታውቂው ሄደሻል ፍቅር አሲዘሽኝ
ለካ አንቺ ልብሽን አሳምነሽዋል
ንፁህ ወንድሜ ነው ብለሽ ነግረሽዋል
አልሰማ አለኝሳ የኔን ልብ ብነግረው
አንቺን እንደ እህትህ ውደድልኝ ብለው
ልቤን ብጠይቀው አጫወተኝ ብዙ
በመውደድ መስከሩን በፍቅርሽ መያዙ
ከዚያን ቀን ጀምሮ
ውስጤ ይፈራ ጀመር አንቺን ሲያይ አይኔ
ልቤ ሲሄድ ታየኝ ተለይቶኝ ከኔ
ጠየቁኝ ጓዶቼ
የኔ እንደዚ መሆን ግራ ቢገባቸው
የት እንሂድ ሲሉ አንቺ ጋር ስላቸው
ስለወደድኳት ነው ብዬ ነገርኳቸው
ስቀውብኝ ነበር ምቀልድ መስሏቸው
ጨዋታዬ ጠፍቶ በዝቶ መጨነቄ
ሲገባቸው ዛሬ በፍቅርሽ መውደቄ
ንገራት እያሉኝ እያለፍኩኝ ስቄ
ዘገየሁ
መሄጃሽ ደረሰ ካይኖቼ ልትርቂ
ስታወሪ ላልሰማ ላላይሽ ስትስቂ
ሳልነግርሽ ማፍቀሬን ዛሬ ነገ እያልኩኝ
ሄደሽብኝ አዘንኩ በሀሳብ ባከንኩኝ
ጨዋታሽ ሳይበቃኝ ሳልጠግብሽ አይቼ
ማፍቀሬ ሳይገባሽ ሳልነግርሽ ፈርቼ
መውደዴን ማስረጃ አንደበት አጥቼ
አዘንኩኝ በራሴ ሄደች ያሉኝ ለታ
ጨለመብኝ በቃ ቀኑም እንደማታ
አስጠላኝ ሰፈሩ አንቺ የሌለሽበት
ልቤ ሀዘን ገባው ሄደሽ ቀርተሽበት
ልነግርሽ ወስኜ
ጠይቄ ጓዶቼን ምን ልበላት ብዬ
ብነግርሽ ደፍሬ ፍራቻን ገድዬ
መውደዴን ጠላሽው ማፍቀሬን ገፋሽው
ለስንት የታሰበው በአጭር ቋጨሽው
እኔኮ ሆዴ
አልጠላም ነበረ ባይሽ እንደ እህቴ
ሳላስበው ገብተሽ ባትበይው አንጀቴ
አንቺን መርሳት አልቻልኩ አቃተኝ ሞክሬ
ከሀሳቤ አትጠፊም ትላንት ሲያልፍ ዛሬ
በሀሳብ አይሻለሁ ላይኔ ስትርቂብኝ
ትዝታሽን ብቻ ጥለሽ ሄደሽብኝ
ተጎዳሁኝ ውዴ አንቺን ስል ቀን ማታ
በአካል ነይልኝ በትዝታሽ ፈንታ፨
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
4 848
◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━ ◈
ማፍቀር መረገም ነው
ድሮ ልጅ እያለን ገና ጨቅላ ሆነን
ለእቃቃ ጨዋታ ባልና ሚስት ልኖን
አብረን ተሰብስበን ፊልም ላይ እንዳየነው
አንደኛው ሲፈቀር አንዱ ነው ሚያፍቅረው
እኛም ይሄን አይተን እኔ ነኝ ማፈቅረው እየተባባልን
ሁለት አፍቃሪ ሆንን ጠልተን መፈቀርን
በማፍቀር መጣላት አብዝተው ተገርመው
አንድ አባት እያዩን ሳቁ ጮክ ብለው
አባ እርሶ ይፍረዱን ማነው የሚያፈቅረው
እኔ ወይስ እሷ ብለን ጠየቅናቸው
እሳቸው በመልሱ እንባ ተናንቋቸው
መፈቀርን ፀጋ ማፍቀር መታደል ነው
ሄዋኗ ትፈቀር አፍቅር ደሞ አዳም
ብለው አስተማሩን ፍቅር አያጣላም
ታድያ እነዛ አባት እንዲህ ብለው መክረው
በልጅነት እድሜ ማፍቀርን ተርጉመው
ዛሬ ትልቅ ስሆን የእውነት አፍቅሬ
ማፍቀር መታደል ነው እያልኩኝ ተምሬ
ዛሬ ላይ ሄዋኔን አፈቀርኩሽ ብላት
ሴጣን እንደያዘው እንደ እብድ አረጋት
መፈቀር ፀጋ ነው ነበር የተባልኩት
ማፍቀር መታደል ነው ብዬም ነው ያደግኩት
#ታ
#ድ
#ያ
አፈቀርኩሽ ስላልኩ ልቤን ካደማችው?
ያፈቀራት ልቤን ካቆሳሰለችው?
አባ ተሳስተዋል ያስተምሩ ደግመው
ማፍቀርን ሀጥያት መረገም ነው ብለው
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██
join @yefkr_gtm
@yefkr_gtm
4 848
▓▓▓▓▓▓ ግጥም ▓▓▓▓▓▓
ቃላቶች ያንሱኛል ምን እደምልሽ
የኔ ፍቅር ብዬ በቃል አላሞግስሽ
ፍቅር የሚለዉ ቃል ዉዴ ያስብኛል
ቅድስቴ ማን እደምልሽ ግራ ይገባኛል
ፎርሙላ የለኝም የዉለታሽ የሚሰራ
እደዉ በፊዚክስ ወይም በማትስ ብሰራ
ዉዴ በየትኛዉ ቁጥር በምን ይጠራ
ያኔ የድሮዉ ኧረ እደዉ ይቅር ሳላስበዉ
ለምን እዳትይኝ ዝምብዬ አመሰግናለዉ
ዉድዋ እህቴ የልብ የዉስጤ አማካሪ ብርታቴ
ዉድ ወንድሜ አጋዥ ሙግቴ
ኧረ ልበልሽ የደስታዬ ምንጭ ፍቅረኛዬ
ሳዝንምታዝን ሊከፋኝ ማትፈልግ ነች እማዬ
እናቴ ሳትኖር ሆናለች ዉብዋ እማዬ
እደዉ ልበላት ምርጥ ወዳጅ ጓደኛዬ
ማን ልበልሽ ንገርኝ በየቱ ልሰይምሽ
በፍቅር አለም ማልሰለችሽ እህቴ
አብሬሽ ምትናፍቂኝ በሞቴ
ደግሞ በሂወት ብቸኛ የእቅልፌ ዳኛ
ድምፅሽ ካልሰማሁ ያመኛል
አይንሽ ካላየሁ ከልጅነቴ ጀምሮ ይከፋኛል
ልቤ በምድር ላይ እደ እሱዋ ሰዉ የለም ይለኛል
እስኪፍረጅኝ አንዱ ንገሪኝ
ይኸዉ ነዉ ልቤ ዛሬ እወቂኝ
ማነህ እዳትይ ማንነቴ አላዉቅም
ወንድምሽ አልልም አቅሙ የለኝም
እህትሽ አልልም አቅሙ የለኝም
እናትሽ አልልም አቅምሙ የለኝም
ፍቅረኛሽ አልልም አቅሙ የለኝም
ጓደኛሽ አልልም አቅሙ የለኝም
አባትሽ አልልም አቅሙ የለኝም
ግን ዉዴ ከሁሉ በላይ ብሆንሽ
ለሁሉም ቦታ ብሸፍ እደ ከፍ ባረግሽ
አሳዝናለሁ ግን መች ተሳካልኝ!!!!
ለዚ ነው አቅሙ የለኝም በቃኝ
ፈጣሪ አላደለኝ ልቤም አልሞላልኝ
አንድቀን እደምሆንሽ ሁሌም እተጋለሁኝ
እርስ የለዉም ግጥሜ እርስ ስጩ አለሜ
በገሀዱ አለም ያለሽ ብቸኛዋ ህልሜ
✍Barmura
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
4 848
▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓
ሶስተኛው አለሜ 🌍👼💘
🌍
በፊተኛው አለም በአካል ማንነት
ችግር ከሞላበት
ተድላውም ካለበት
አንዴ ጣፋጭ እለት
ቀጥሎም ውጥንቅጥ
መላ ቂጡን ያጣ ሁሉ ሚታይበት።
👼
ሁለተኛው ደግሞ መንፈሳዊው አለም
የሚታይ አይደለም
ሚዳሰስ አይደለም
ትልም ነው ሚተለም
በምናብ ሚታለም።
🌍👼
ስጋና መንፈሴ በጎራ ሲፋጅ
አንዱም ሳያሸንፍ ህይወቴን ሲፈጅ
ነፍሴም ከጭንቀት ለመውጣት ስትዳክር
ስትደርስ ከደጅ
💘💘💘
መጣሽና አንቺ
ፈጥረሽ ሌላ አለም ልቤ ምታርፍበት
ፍቅርና መውደድ ደስታ የሞላበት
ነፍሴ ሳትወጣ ከስጋዬ ላይ
ሌላኛውን አለም ገብቼ ሳላይ
በአካል እንዳለው እኔ በዚች አለም
ከልቤ ጥላቻ ክፋት ሲጠራቀም
ከዛ ወጣሁና
❤❤❤
የፍቅርሽን አለም ሳየው አስቀድሜ
መንፈሴ ሲነግረኝ እንዳለ ሰላሜ
ላልወጣ ወሰንኩኝ ዘጋሁት ጠርቅሜ
ፍቅርሽ
ፍቅርሽ ነው ሶስተኛው አለሜ
✍ተፃፈ;-በበሱ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
4 848
▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓
Block......un block
ቀን አትናፍቀኝም
ጭራሽ ትዝ አትለኝ
ስምህም ሲጠራ ድንቄም አልደነግጥ
ፎቶህንም ሳየዉ ልቤ አትልም ድልቅ።
ድንገት ትዝ ካልከኝ
ራሴን 'ረግማለሁ
ምን አጃጅሎኝ ነዉ ብዬ እገረማለሁ።
ያንተ ስም ሲጠራ
ብዙ መሠል ስሞች ይመጣል ከኔ ጋር
ሌላም አስባለሁ ከትዝታ ጋራ
የአፍቃሪዬን ብዛት..............
በቃ ረስቻለሁ ብዬ ስደሳሰት
Block🤜
ልክ ሲመሻሽ ደርሶ
ስምህ ይጨንቀኛል
ሳቅህ ይሰማኛል
እንደ ቀኑ አይደለ ፎቶህ ግርማ አለዉ
መፀፀት አይደለ ልቤ አምጪዉ ነዉ ሚለዉ
ምን አተሽ ነዉ ከሱ
እድል ነበር እሱ
እያለኝ እንደቀልድ
ቀን ያመንኩት ልቤ ካንተ ጋራ ሲነጉድ
እንዲሁ አነጋለሁ
ስላንተ አነባለሁ።
ከዛ..............
un block ሳደርግህ ራሴን አገኛለሁ።
ድሮስ ከጨለማ ምን ነበር ጉዳዬ
አንተ መቼም አታዉቅ ሆነ እድል ፈንታዬ
አንተና ጨለማዉ ግብራችሁ አንድ ነዉ
ብቸኝነት ፍርሀት መልሳችሁ ዝም ነዉ።
ደሞ ዛሬም ነጋ.................
ተፃፈ በትዝታ ወልዴ✍
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
4 848
▓▓▓▓▓▓▓ ግጥም ▓▓▓▓▓▓▓
ቃል ብዬ ጠራሁሽ
ስላንች ለመፃፍ ብእር እቀርፅና
ቀለሙን አቅልሜ ፈቅፍቄ ብራና
ፊደልና ቃላት እንደልጅ እያማጥኩ
ሀረግ እየመዘዝኩ ምሳሌ እየጠቀስኩ
ቃል ባጣው ልሳኔ ስፅፍ ውዬ አድሬ
ገልጨሽ ሳይበቃኝ ትደርቃለች ብእሬ
ደግሞ ተመልሼ................
ደሜን አንጠፍጥፌ ቀለሙን አቀለምኩ
አጥንቴን ፈቅፍቄ ላንች ብእር ቀረፅኩ
ብእሬን በደሜ ነክሬ ሳወጣው
አንችን እገልፅበት ቅንጣት ቃላት አጣው
ለካንስ ቃልዬ!!!
በፍቅር ነሁልሎ መንፈስ ከደከመ
ናፍቆት አገርጥቶት ልብ ከታመመ
እንኳን ቃል ተዋቅሮ ቅኔ ሊመሰጠር
ደግሞ ስንኝ ሁኖ ግጥም ሊደረደር
ደህና አደርክ ሲባል ለእግዚአብሄር ይመስገን
አንደበት ቃል ያጣል ሲመርቁት ለአሜን
ለዛ ነው ቃልዬ!!!
መግለጫ ቃል ባጣ እልፍ ዘመን ሙሉ
የብራናዬ ገፅ ግራ ገብቶት ውሉ
እየደጋገምኩኝ የፃፍኩት አንድ ቃል
እ
ን
ዲ
ህ
ብቻ ይላል
ሌላ ቃል ተገኝቶ
ወይ ልሳንህ ፈቶ
ህቡእ በሆነ ቃል እስከምትገልፃት
ቃልህ እሷ ነችና ቃሌ ብለህ ጥራት
እናም አንች ቃሌ ነሽ ሀረግና ስንኝ
ካጠገቤ ሁነሽ ሰርክ የምትርቢኝ
እናም የኔ ንግስት
ገፅሽን አድምቄ በልቤ መዝገብ ላይ
ቃሌ ብዬ ፃፍኩሽ ቃል አጣው ቃሌ ላይ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
🇪🇹 ሠላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹
4 848
▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM ▓▓▓▓▓▓▓
የፍቅር ፀብ
( በላይ በቀለ ወያ )
ባብሮነታችን ውስጥ
ጥላቻ ባይኖርም - በመናናቃችን
በመናናቃችን
መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ
አብሮ መብላት ቀረ
አብሮ መዋል ቀረ
አብሮ ማደር ቀረ
ቀረ
ቀረ
ቀረ
ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ
በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ
እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን
እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡
ባብሮነታችን ልክ
መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ
አሁን የሚታየኝ
ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡
እንኳን ተለያየን!
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
4 848
▓▓▓▓▓▓▓ ግጥም ▓▓▓▓▓▓▓
ሰባኪ ነው መሪ
መግደል መሸነፍ ነው ቢል ንጉስ ተብየው
እና ለማሸነፍ ሞትኩ ብየ ተኛሁ
ከእንቅልፍ ስነቃ ግን
የንጉሱ ስብከት ቃሉ ተገልብጦ
ሲያሸንፍ አየሁት ገዳይ ጦር ጨብጦ
ከዘመናት በፊት ሞቶ ያሸነፈ
ቆሽሸሀል ብሎ ሰው ያልተፀየፈ
በጅራፍ ሲነቅሱት ጀርባው ሲቆሳስል
መስቀል ላይ የወጣ ስለሀጥያን በደል
የመውደዱ ልኬት የማይመረመር
እንደተቀበረ ከመሬት የማይቀር
ሁሉን አሸናፊ በሞቱ ያዳነን
ሀሞት ተጎንጭቶ ወይን ጠጅ ያጠጣን
አንድ እሱ ብቻ ነው ስሙኝ ሰባኪያችን
እኛ አናሸንፍም ሞትን በሞታችን
ግን ደግሞ
አንድ ንጉስ አለ ሞቶ ድል ያመጣ
ውሀ እየተጠማ
ለናት ክብር ብሎ ባሩዱን የጠጣ
ከዚያ በኋላ ግን
ሞቶ ያሸነፈ ፈሪ ነው ልንገርህ
ገድለው ሲጨርሱህ አትመን ዝም ብለህ
ይልቅ አንተም ታገል ድል አምጣ ሰው ገለህ
መግደል ስታስብ ግን
መጀመሪያ ግደል እረኛውን ፈጥነህ
እሱኮ ነው አንተን
ለቀበሮ ሰጥቶህ በቀበሮ መሪ የተሸለመልህ
እሱ እኮ ነው ጠላት
ምርኩዝ ነህ እያልከው ገፍትሮ የጣለህ
እሱኮ ነው ገዳይ
ከእባብ ተፈልፍሎ እርግብ የሚመስልህ
እሱኮ ነው ዋሾ
መብራት ባጣች ሀገር አምፖል የሚያድልህ
እሱኮ ነው እባብ
በለስላሳ ምላስ መርዝ የሚረጭብህ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘
አዘጋጅ፦ @yefkr_gtm
➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
🇪🇹 ሠላም ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹
4 848
⊶⊷⊶⊷❍ የእብደት ሚስጥሬ ❍⊶⊷⊶⊷
ፍቅሬን በቃላቶች ~ ደርድሬ ባልገልፀው
የኔ ነሽ የምልሽ ~ ያንቺ ነኝ የምለው
ድምፅሽ መዳኒቴ ~ የህይወት እጣዬ
አካልሽ ጉልበቴ ~ የስኬት ማማዬ
ሌላ ማንም የለም ~ ባንቺ ነው ማማሬ
እውነት እልሻለሁ ~ የእብደት ሚስጥሬ
↪️➖ @yefkr_gtm
━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━
4 848
✳️ ሐበሻን Tech በሀገራችን ትልቁ የቴክኖሎጂ ቻናል ሲሆን አባል በመሆንዎ እነዚህን ነገሮች ያገኛሉ፡
➧የሞባይል አፕልኬሽን
➧የኮምፒውተር ሶፍትዌር
➧የሞባይልና የፒሲ ጌሞች
➧የቴሌግራም ሮቦት አሰራር
➧የስልክ አፕሊኬሽን አሰራር
➧የቴሌግራም ስቲከር አሰራር
➧በYouTube ገንዘብ አሰራር
➧Online Business አሰራር
➧Website/ዌብሳይት አሰራር
➧የኮምፒውተር ሶፍትዌር አሰራር
💮 በተጨማሪም በካርድ ወጪ ለተቸገራቹ ቤተሰቦች አሪፍ መፍትሄ አዘጋጅተናል ፤ ብቻ ምን አለፋዎት ማንኛውም ቴክኖሎጂ ነክ መረጃ አያመልጦትም አሁኑኑ JOIN የሚለውን ተጭነው ይቀላቀሉን።
███▓▒░░░JOIN░░░▒▓███
███▓▒░░░JOIN░░░▒▓███
4 848
━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━
━🔹ናፍቆት🔹━
"የሃምሌ ዶፍ መጣ
ብርድ ተከናንቦ
ውርጭ አዝሎ ባንቀልባ፣
ሙቀቴ አንች ነበርሽ
ዘንድሮስ ምን ልሁን-የት አባቴ ልግባ?"
ብሎ ሰው ቢቀኝም፣
እንደዚህ ማርገድ ግን
እኔስ አያምረኝም።
እኔማ...
በጠራራ ፀሃይ-ገላ በሚያቃጥል፣
የለበሱትን ጨርቅ-የትሙን በሚያስጥል፣
እጠብቅሻለሁ-ካቦርቴን ደርቤ፣
በሳሳ አካላቴ-ናፍቆት ተኮንቤ።
እጠብቅሻለሁ...
ቁሩ ቢወበራም
መስኮቴን ከፍቼ ሳንቃየን ሳልዘጋ፣
አንቺ የሌለሽበት
መች ይበርዳል ክረምት
መች ይሞቃል በጋ?
🔘በዘነበ ወላ 🔘
➲ @yefkr_gtm
🟩🟨🟥🇪🇹🟩🟨🟥🇪🇹🟩🟨🟥
