en
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Open in Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

Channel ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 19 831 subscribers, ranking 1 164 in the Medicine category and 1 700 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 19 831 subscribers.

According to the latest data from 07 July, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -473 over the last 30 days and by -8 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 15.95%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 6.77% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 168 views. Within the first day, a publication typically gains 1 344 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 5.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 08 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Medicine category.

19 831
Subscribers
-824 hours
-637 days
-47330 days
Posts Archive
ፈስቡክ ምንም ዳታ ሳይበላብን ለመጠቀም አዲስ አፕ በጣም ፈጣን ሞክሩት እኔ ተመችኛል @telecomBirr

የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ ይከታተሉን። ✴✳ የስኳር በሽታ ምልክቶች እነዚህን ይመስላሉ፦ ✅ በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት፡፡ ✅ ከመጠን ያለፈ የውሃ ጥም፡፡ ✅ የፍላጎት እና ትኩረት ማጣት፡፡ ✅ የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት፡፡ ✅ የረሃብ ስሜት መጨመር፡፡ ✅ የክብደት መቀነስ፡፡ ✅ ድካም በእጅና እግር አካባቢ፡፡ ✅ የአይን እይታ መጋረድ/ብዢታ፡፡ ✅ በተደጋጋሚ በኢንፌክሽን መጠቃት፡፡ ✅ የቁስል ማገገሚያ ጊዜ መርዘም፡፡ ✅ ማስመለስ እና የሆድ ህመም ናቸው፡፡ ✴✳ የማንጎ ቅጠል ለስኳር ታማሚዎች የሚሰጠው ጠቀሜታ 👉🌀 በደም ውስጥ ያለ የስኳር መጠንን መቆጣጣር የስኳር ህመምን ለመቆጣጣር ከሚረዱን መንገዶች ውስጥ አንዱ የደም ውስጥ ያለን የስኳር መጠን መቆጣጣር ነው። የማንጎ ቅጠል ሰውነታችን ኢንሱሊን የማምረት አቅም እና የግሉኮስ ስርጭት እንዲጨምር የሚያደርግ ሲሆን፥ ይህ ደግሞ በደማችን ውስጥ ያለን የስኳር መጠን ለመቆጣጣር ይረዳል ነው የተባለው። 👉🌀 የኮሌስትሮል መጠንን ለመቆጣጣር የስኳር በሽታ ታማሚ ከሆንን በሰውነታችን ውስጥ ያለ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን የልባችን ጤንነት ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ሆኖም ግን የማንጎ ቅጠል በፔሲተን፣ ቪታሚን C እና ፋይበር ንጥረ ነገሮች የበለፀገ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ ይረዳል። 👉🌀 በስኳር ህመም ምክንያት የሚከሰት የአይን ህመም የማንጎ ቅጠል ቪታሚን A የበለጸገ በመሆኑ ለአይን ጤንነት የሚሰጠው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም የማንጎ ቅጠል የስኳር ህመም ምልክቶች የሆኑትን በእንቅልፍ ሰዓት ቶሎ ቶሎ የመሽናት፣ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ክብደት መቀነስ እና የአይን እይታ መደብዘዝ ችግሮችን ለመቀነስም ይረዳል ተብሏል። የማንጎ ቅጠልን እንዴት መጠቀም አለብን…? ✴ ከማንጎ ዛፍ ላይ የተቆረጠ ከ10 እስከ 15 ቅጠል ማዘጋጀት ✴ ውሃ ማፍላት፤ በሚፈላው ውሃ ውስጥ የማንጎ ቅጠሉን በመጨመር አንድ ላይ እንዲፈላ በማድረግ ማሳደር ✴ ጠዋት ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ሌላ ምግብም ይሁን መጠጥ ከመውሰዳችን በፊት የማንጎ ቅጠል ሻዩን መጠጣት ✴ ይህንን ለሁለት ወይም ሶስት ወራት ያለማቋረጥ የእለት ከለት ተግባራችን ውስጥ በማካተት በቀላሉ የስኳር ህመምን መቆጣጣር ያስችለናል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

መሰላቸትን ለራስህ ፍቀድ ================ የአብዛኞቻችን ሕይወት ስራችንን ብንተው እንኳን ትኩረታችንን በሚሰርቁ ድርጊቶች የተሞላ ከመሆኑ የተነሣ ለትንሽ ደቂቃ እንኳን ምንም ሣንሰራ ዘና ብለን መቀመጥ አንችልም። አንድ ጓደኞዬ “ሰዎች ሰብአዊ ፍጡራን መሆን አቁመው ሰራተኛ ፍጡራን ሆነዋል” ብሏል። አልፎ አልፎ መሰላቸት የሚኖረውን ጥቅም የተረዳሁት ከዋሽንግተን ወጣ ብላ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ውስጥ የንግግር የስነ ልቦና ሕክምና በምማርበት ጊዜ ነው። ከተማዋ ትንሽ ስለነበረች ብዙ የሚደረግ ነገር አልነበረም። የመጀመሪያ የትምህርት ጊዜ እንዳለቀ አስተማሪዬን “እዚህ አካባቢ ማታ ማታ ምን ማድረግ እችላለሁ?” አልኩት። እሱም “ራስህን እንድትሰላች ፍቀድለት። ምንም አታድርግ። በዛ ላይ መሰላቸትን መልመድ የትምህርትህ አንድ አካል ነው።” አለኝ። በመጀመሪያ እየቀለደ መስሎኝ ነበር። “ለምንድነው በገዛ እጄ እንድሰላች የማደርገው?” ብዬ ጠየቁት። እሱም እራሴን ለአንድ ሰዓት ያህል እንኳን እንድሰላች ከፈቀድኩለት እና የሆነ ጊዜ ማሣለፊያ ነገር ከማድረግ ከተቆጠብኩኝ የመሰላቸቱ ስሜት ወደ ሰላማዊ ስሜት እንደሚለወጥ አስረዳኝ። ሳይዋጥልኝ ተቀበልኩት። ከሞከርኩት በኋላ እሱ እንዳለኝ መሆኑን ሣይ በጣም ተገረምኩ። መጀመሪያ መሰላቸቱን መቋቋም ከባድ ነበር። ጊዜ ማሣለፊያ የሆነ ነገር ማድረግ ስለለመድኩ መጀመሪያ ላይ ዘና ለማለት ተቸግሬ ነበር። ከትንሽ ጊዜ በኋላ እየለመድኩት መጣሁ። ከዛ እንደውም በጣም እያዝናናኝ መጣ። እየተናገርኩ ያለሁት ለሰዓታት ያለ ስራ በስንፍና ስለመቀመጥ ሣይሆን ዘና የማለትን ጥበብ ስለመማር ነው። ምንም ነገር ሣያደርጉ እራስን ሆኖ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዘና ማለት። የተለየ ዘዴ አያስፈልገውም በቃ አስበንበት ለተወሰነ ጊዜ ምንም አለመስራት ብቻ ነው። ረጋ ብሎ ተቀምጦ ሀሣባችንንና ስሜታችንን ማጤን። መጀመሪያ ላይ የተወሰነ ሊጨንቀን ይችላል። በተለማመድነው ቁጥር እየቀነሰልን ይመጣል። የምናገኘው እርጋታ ደግሞ ከፍተኛ ነው። አብዛኛው ጭንቀቶች የሚፈጠሩት አዕምሯችን በጣም እየሰራ፣ የሚያተኩርበት ነገር ፍለጋ ሲባዝን ነው። አንድ ስራ እየሰራ ስለሌላ ስራ ያወጣል ያወርዳል። “ከዛስ?” ሲለን ምሣ እየበላን ቡና የት እንደምንጠጣ እናስባለን። ቡና እየጠጣን ስንጨርስ የት እንደምንሄድ እናውጠነጥናለን። ሳምንቱ ሊያልቅ ሲል ቅዳሜና እሁድ ምን እንደምንሰራ እናቅዳለን። ቤታችን እንደገባን በቀጥታ ቲቪ ወይም ፌስ ቡክ እንከፍታለን፤ ወይ ስልክ እንደውላለን፤ ወይ መፅሀፍ እንገልፃለን፤ ወይ የሆነ ነገር መስራት እንጀምራለን። ለደቂቃ እንኳን ምንም ነገር ሣንሰራ መቀመጥ የሚያስፈራን ነው የሚመስለው። ምንም ነገር ሣይሰሩ መቀመጥ እንዴት ዘና ማለት እንደምንችልና አዕምሯችን አንዴት ተረጋግቶ ማሰብ እንደሚችል ያስተምረናል። መሰላቸት ማለት ለአዕምሯችን “ቆይ አሁን አይደለም” ብለን ዘና የምንልበት ነፃነት እንደመስጠት ነው። ልክ እንደአካላችን አዕምሮአችንም ከጥድፊያ ኑሮ ጋብ የሚልበት እረፍት ያስፈልገዋል። አዕምሮአችን እረፍት ስንሰጠው በጣም ጠንካራ፣ ፈጣንና ትኩረት ማድረግ የሚችል ሆኖ እናገኘዋለን። እንድንሰላች ለራሣችን ስንፈቅድ በያንዳንዱ ቀን በየአንዳንዱ ደቂቃ መስራት ያሉብን ነገሮች ከሚያሳድሩብን ከፍተኛ ጫና አእምሯችን ለተወሰነ ጊዜ “እፎይ” እንዲል እናደርገዋለን። ከሁለቱ ልጆቼ አንዳቸው እኔ ጋር መጥተው “አባዬ ሰለቸኝ።” ሲሉኝ “በጣም ጥሩ ለትንሽ ጊዜ እንደዚሁ ቀጥሉ ይጠቅማችኋል” እላቸዋለሁ። እንደዚህ ማለት ከጀመርኩ በኋላ እየመጡ የሆነ ነገር እንዳደርግ መጠየቃቸውን አቁመዋል። የሆነ ሰው “እራስን እንድትሰላች ፍቀድ” ይለኛል ብላችሁ አስባችሁ አታውቁ ይሆናል። ያ የሂደቱ መጀመሪያ ይመስለኛል። ከ"ቀላሉን ነገር አታካብድ" መፅሀፍ የተወሰደ

የታይሮይድ ሆርሞኖች ምርመራ ምንነት ታይሮይድ የፊትለፊት የአንገት ክፍል የሚገኝ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑትን T3 እና T4 የተባሉ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ እጢ(gland) ነው። በደም ምርመራ የሚታ
የታይሮይድ ሆርሞኖች ምርመራ ምንነት ታይሮይድ የፊትለፊት የአንገት ክፍል የሚገኝ ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑትን T3 እና T4 የተባሉ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ እጢ(gland) ነው። በደም ምርመራ የሚታወቁት T3 እና T4 ሆርሞኖች መጠን ከፈም ዝቅም ማለት በሰውነታችን ብዙ ውስብስብ ችግሮችን ይፈጥራል። የነዚህ ሆርሞኖች ማነስ በህክምና አጠራሩ ሀይፖታይሮይዲዝም ይባላል። ምልክቶችም ከመጠን በላይ መወፈር፣ከፍተኛ የድካም ስሜትና ድብርት ዋናዎቹ ናቸው።የተለያዩ በሽታዎች የሆርሞቹ መጠን እንዲቀንሱ ቢያደርጉም የእጢው በኦፕሬሽን መወገድ ግን ዋነኛው መንሴ ነው። ታይሮክሲን የተባለ የሚዋጥ መድኃኒት በመውሰድ ይታከሙታል። የT4 እና T3 ከመጠን በላይ ከፍ ማለት ሀይፐርታይሮዲዝም ይባላል።ያልታሰበበት የክብደት መቀነስ ፣በቀላሉ መጨናነቅና መንቀዥቀዥ፣የእጅ መንቀጥቀጥ እና የሰገራ መቅጠን ዋና ዋና ምልክቶች ናቸዉ። የተለያዩ የህክምና አማራጮች ሲኖሩት መድኃኒት መውሰድ እና ኦፕሬሽን መደረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የT3 እና T4 ሆርሞኖች ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት ሳይታከሙት ለረጅም ጊዜ ከቆየ የልብ ድካም እና ሌሎች ችግሮችን በመፍጠር የጤና እክል ያስከትላል። ለዚህም ሲባል ባደጉ ሀገሮች ማንኛውም ህፃን ሲወለድ የነዚህ ምርመራዎች ይደረግለታል። የነዚህ ሆርሞኖች ትክክል አለመሆን በህፃናት እድገት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። ሌላው ከT3 እና T4 አብሮ የሚታዘዘው ምርመራ TSH ሲሆን የዚህ ሆርሞን ዝቅ ማለት የT4 እና T3 ሆርሞኖች ከፍ ማለትን ሲያሳይ TSH ከፍ ካለ ደሞ T3 እና T4 መጠን ዝቅ ማለታቸውን ያመለክታል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias

በኦፕሬሽን መውለድ ጥቅሙና ጉዳቱ ህጻናት ይህችን ዓለም በሁለት መንገድ ይቀላቀላሉ፡ በምጥ ወይም ደግሞ በኦፕሬሽን (surgical delivery by Caesarean section)፡፡ በአሁን ወቅት የህክምና አማራጭ ያላቸው እናቶች አምጦ ከመውለድ ይልቅ በኦፕሬሽን መውለድን እንደተሻለ አማራጭ ሲወስዱት ይታያል፡፡ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችም በሁለቱም መንገድ መውለድ ያለውን ጠቀሜታና የጎንዮሽ ጉዳት አስረድተው ውሳኔውን ለእናቶች ከመተው ይልቅ በኦፕሬሽን እንዲወልዱ እናቶችን ሲገፋፉ ይታያል፡፡ ለመሆኑ በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መፈቀድ አለበት? ያለው ጥቅምና ጉዳቱስ ምንድን ነው? በኦፕሬሽን መውለድ መቼ መወሰን አለበት? 1. አምጦ መውለዱ ለእናትየው ወይም ደግሞ ለህፃኑ ህይወት አደጋ ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ሲታመንበት 2. ጽንሱ በጣም የፋፋ/የወፈረ/ ከሆነ እና የእናትየው ማህጸን ጠባብ ከሆነ 3. የጽንሱ አቀማመጥ በትክክል ካልሆነ ማለትም በእርግዝና የመጨረሻዎች ቀናት ጭንቅላቱ ወደታች ካልመጣ 4. በምጥ ወቅት ጽንሱ በቂ ኦክስጅን ካላገኘና የመተንፈስ ችግር ካጋጠመው 5. መንታና ከዚያ በላይ ጽንስ ሲኖር 6. የተራዘመ ምጥ ሲኖር እና 7. እናትየው ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባት፤ የስኳር በሽተኛ ከሆነች፡ የHIV ቫይረስ ካለባት ጥቅሙ፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እናቶችን እና የጽንስን ህይወት ይታደጋል፡፡ እናቶች በምጥ ወቅት ሊሰማቸው የሚችለውን የተራዘመ ስቃይ ያስቀራል ጉዳቱ፡ 1. ጽንሱን ለማውጣት የሚቀደደው የሰውነት ከፍል ለመዳን ጊዜ ይወስዳል፤ በሰውነት ላይ ጥሎት የሚያልፈው ጠባሳም በቀላሉ የሚድን አይደለም 2. የእናቶችን የሆስፒታል ቆይታ ያራዝማል፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በፍጥነት አገግመው ልጆቻቸውን ለማጥባትም ሆነ ለመንከባከብ ይቸገራሉ 3. የመጀመሪያ ልጃቸውን በኦፕሬሽን የወለዱ እናቶች ቀጣይ ልጆችን በተመሳሳይ ሂደት እንዲወልዱ ሊገደዱ ይችላሉ፡፡ ይህም በማህጸን ግድግዳ ላይ ተደጋጋሚ ጠባሳዎች ያስከትላል፤ ቁስሉ በቶሎ ካልዳነ ደግሞ የማህጸን ግድግዳ ከሌላ የሰውነት ከፍል ጋር ሊጣበቅ ይችላል 4. በምጥ ከሚወልዱ እናቶች ይልቅ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች ለከፍተኛ ደም መፍሰስና እንፌክሽን ይጋለጣሉ፡፡ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በምጥ ከሚወልዱ እናቶች የመሞት ዕድላቸው ሶስት አጥፍ የሰፋ ነው 5. በኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ የሽንትና የሰገራ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ሊጎዱ ይችላሉ ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በቀር እናቶች አምጠው መውለድን ቢመርጡ ይመከራል፡፡ አምጠው የሚወልዱ እናቶችም የተሻለ የመንፈስ እርካታ እንዳለቸው ይናገራሉ፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

የጥርስ ህመም ሲሰማዎት እንዲህ ያድርጉ ምናልባት ሰውነትዎ ላይ ከሚሰሙት የህመም ስሜቶች ምቾት የሚነሳው ጥርስ አካባቢ የሚከሰት ህመም ሳይሆን አይቀርም። መጠዝጠዝ ሲመገቡ፣ ውሃ ሲጠጡ አልያም ንፋስ ሲነካው ከፍተኛ የህመም ስሜት ማስተናገድ የዚህ ችግር መገለጫዎች ናቸው። ብዙ ጊዜ ማስታገሻ በመውሰድ ከሚከሰተው የህመም ስሜት ለመገላገል የሚወሰድ የመፍትሄ እርምጃ ነው። አልፎ አልፎም ህክምና ተቋም በመሄድ የተበለሻውን ጥርስ ማስነቀል እና ማስወገድም የዚህ መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከዚህ ባለፈ ግን ጥርስ ሳይቦረቦርና ሂደቱ ሲጀምረው የሚሰማን ከፍተኛ የጥርስ ህመም ለማስታገስ ነጭ ሽንኩርት እና ቅርንፉድን በመጠቀም ማከም ይቻላል። ሁለቱም ባላቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ ምክንያት ለዚህ መሰል ችግር እጅጉን ተመራጭ እና የሚመከሩ ናቸው። ይህን ለማግኘት ደግሞ በቀላሉ ህመም የሚሰማዎት ቦታ ላይ ቅርንፉዱን ወይም ነጭ ሽንኩርቱን ማስቀመጥ እና ለተወሰነ ደቂቃ መያዝ። ከዚያም ረጠብ ሲሉ በተጎዳው ጥርስ ማኘክ እና የተወሰነ ጊዜ ይዞ ማቆየትና ማስወገድ። ወይም ደግሞ ሁለቱን እጽዋት ረጠብ አድርጎ በመጭመቅ እና በዘይት መልክ በማዘጋጀት በንጹህ ጥጥ የተጎዳው ቦታ ላይ ማፍሰስ። ከዚያም ለተወሰኑ ደቂቃዎች ማቆየትና ሳይጉመጠመጡ መትፋት፤ ከ15 ደቂቃ እስከ ግማሽ ሰአት ያክል የዞ ማቆየት ያስፈልጋል። ይህንን በማድረግ ከሚሰማዎት የጥርስ ህመም ስሜት መገላገል ይችላሉ። እነዚህ ሁለት እጽዋት ከጥንት ጀምሮ ለተለያዩ ህመምች መፍትሄነት የሚወሰዱ ሲሆን፥ በተለይም ደግሞ ከአፍ ጋር ለተያያዘ የጤና ችግር መፍትሄዎች ናቸው። ለምሳሌ ነጭ ሽንኩርት ለተስተካከለ የደም ዝውውር ስርአት የሚረዳውን ኢውግነል የተባለ ውህድን በውስጡ ይዟል። ይህ ደግሞ ለመላው የሆድ እና የአፍ ጤንነት እጅጉን የሚረዳ አስፈላጊ ንጥረ ነገር ሲሆን፥ ከዚህ ባለፈም ለአጥንት ጥንካሬ የሚረዱ በርካታ ውህዶችን ይዟል። ባክቴሪያዎችንና አላስፈላጊ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድና ለማጥፋትም ይህ እጽ እጅጉን ይረዳል። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

ራስ ምታት መቼ ያሰጋል? AFRODOCTORS ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: ራስ ምታት በአብዛኛው በራሱ በሽታ ከመሆን ይልቅ የሌላ በሽታ መገለጫ ነው፡፡ ብዙ የራስ ምታት አይነቶች ቢኖሩም ሁሉም አንድ የሆነ መለያ አላቸው፡፡ይኸውም ህመም ማስከተላቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹ በራስ ህመም ብቻ ሲያቆሙ ሌሎቹ ደግሞ እንደ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ የመሳሰሉትን ያስከትላሉ፡፡ ራስ ምታት በብዛት አደጋ የሌለውና በቀላሉ ልትከላከለው የምትችለው ነገር ነው፡፡ የራስ ምታት መነሻ ምክንያቶች እና የተወሰኑ ምክንቶች • መጠጥ/አልኮል፡- በተለይ ቀይ ወይን • የእንቅልፍ መለዋወጥ/ የእንቅልፍ ማጣት • ጭንቀትና የመሳሰሉት ካለዎ የህመሙ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ • ድንገተኛ የሳይነስ ኢንፌክሽን • በጭንቅላት ዉስጥ ደም መርጋት • በጭንቅላት ዉስጥ የደም ቧንቧ መወጠር/መስፋት መከሰት • የጭንቅላት ዉስጥ ዕጢ • በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ፡- ለምሳሌ የከሰል ጭስ • የፈሳሽ ዕጥረት(ዲሃይድሬሽን) • የጥርስ ችግር • የጆሮ ኢንፌክሽን.....ወዘተ…. ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ? የራስ ምታት እንደ ስትሮክና የማጅራት ገትር ለመሳሰሉ በጣም አደገኛ/ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር ሊያመጡ ለሚችሉ ህመሞች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለሆነም በህይወትዎ አይተዉት የማያዉቁት የራስ ምታት ስሜት፣ በድንገት የመጣና ከፍተኛ የራስምታት አይነት ካለዎና የሚከተሉት ምልክቶች ከራስምታቱ ጋር ተያይዞ ካለዎ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ድንገተኛ የህክምና መስጫ ተቛም ባስቸኳይ መሄድ ይገዎታል፡፡ ራስ ምታት መቼ ሊያሰጋኝ ይገባል? ከአንድ ሳምንት በላይ ከቆየ፣ ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ማስታገሻ ብትወስድም ከመሻል ይልቅ እየባሰ ከሄደ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃይለኛ ራስ ምታት ሲያምህ ከሃምሳ አመት በላይ ከሆንክ፣ ከዚህ በፊት የነበረውን አይነት ቀይሮ አዲስ ፀባይ ካመጣ፣ ህመሙ ከየእለት ኑሮህ የሚያስተጓጉልህ ከሆነ፣ ለምሳሌ ስራ ለመስራት የማያስችል አይነት ህመም ካለህ፣ ከራስ ምታቱ በተጨማሪ የተለያዩ የበሽታ ምልክቶች ለምሳሌ.... ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ፣ ሳል • እራስን መሳት • የመቀበጣጠር ወይም የሰዎችን ንግግር መረዳት ያለመቻል • ከፍተኛ ትኩሳት • ባንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ የመደንዘዝ፣ የመስነፍ ወይም ሽባ ከሆነ • የአንገት ያለመታጠፍ ችግር ካለዎ ( Stiff neck) • የዕይታ ችግር • የመናገር ችግር • የመራመድ ችግር • ማቅለሽለሽና ትዉከት የመሳሰሉት …ከታዩብህ ወደሆስፒታል ሄደህ ዶክተርህን ማማከር አለብህ፡፡ ማስታገሻውስ? • በቂ እንቅልፍ ማግኘት፡- በእያንዳንዱ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ለማግኘት መቻል ነዉ እንጂ ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ መተኛት የለብዎትም፡፡ ሁሌም ቢሆን ወደ አልጋ ለእንቅልፍ የሚሄዱበትና ሲነጋ የሚነሱበት ሰዓት ተመሳሳይ ቢሆን ይመረጣል፡፡ • እረፍት ማድረግና ዘና ማለት፡- ያለው ራስምታት ሚግሬይን ከሆነ ከተቻለ ፀጥ ያለና ጨለማ ክፍል ቢያርፉ ይመረጣል፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

የተለመደውን ምክሬን ተግባራዊ ያድርጉ ስኳር ቀንሱ ወድ ቤተሰቦቼ የምንመገበውን የስኳር መጠን መቀነስ ለምን ያስፈልጋል? 25-08 ✓ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ በብዛት ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ለሰው
የተለመደውን ምክሬን ተግባራዊ ያድርጉ ስኳር ቀንሱ ወድ ቤተሰቦቼ የምንመገበውን የስኳር መጠን መቀነስ ለምን ያስፈልጋል? 25-08 ✓ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ በብዛት ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ለሰውነት ክብደት መጨመር ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ሲሆን ፍሩክቶስ የስብ ክምችት እንዲኖር ስለሚያደርግ እና ጣፈጭን አብዝቶ መመግብ የረሃብ ስሜት እንዲሰማን እንዲሁም በብዛት እንድንመገብም ያደርጋል ስለዚህ የሰውነት ክብደትዎን ለማስተካከል የሚወስዱትን የስኳር መጠን ቢቀንሱ ይመከራል። ✓ ለጤናማ ጥርስ ነጭና የሚያንፀባርቁ ጥርሶችን እንዲኖርዎ ከፈለጉ የሚወስዱትን የስኳር መጠን ይቀንሱ። ጣፋጭ የምናዘወትር ከሆነ በአፍ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች እንዲበራከቱ ስለሚያደርግ ለጥርስ እና ድ ድ ህመም እንድንጋለጥ ያደርጉናል። ለጤናማ ጥርስ ስኳርን ማዘውተር አይመክርም! ✓ ለቆዳ ጥራት ስኳር ለቆዳችን መሰንጣጠቅ እና ጥራት ማጣት ይዳርጋል። በሴሎች ውስጥ የሚገኘውን ውሃ ስለሚያስወጣ ለቆዳ ድርቀት ይዳርጋናል። ✓ ቋሚ የሆነ ሃይል እንዲኖረን ስኳር እንደተመገብነው ከፍተኛ የሆነ ሃይልን የሚሰጥ ስለሆነ ንቁ ያደርገናል ነገር ግን ወድያውኑ መጠኑ በሚወርድ ጊዜ የድካምና የመራብ ስሜት እንዲሰማን ምክንያት ይሆናል ስለዚህም ባያዘወትሩ ይመከራል። ✓ ለጤናማ ልብ ሰውንታችን ያልተጠቀመውን ስኳር ወደ ስብነት ለውጦ የሚያስቀምጥ ሲሆን ይህ የስብ መጠን በሚጨምር ጊዜም ለተለያዩ የልብ ህመሞች እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልዎን ስለሚጨምር ቢጠነቀቁ መልካም ነው። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

✍#የሰውነት #መጥፎ #ጠረን 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ላብ በራሱ የሰውነት ሽታን አያመጣም ፣ የሰው ላብ ሽታ የለውም ማለት ይቻላል።በአንድ ሰው ቆዳ ላይ በባክቴሪያ ምክንያት የሰውነት ሽታ የሚከሰተው በላብ ውስጥ የፕሮቲን ሞለኪውሎችን በማፍረስ እና በዚህም ምክንያት ሽታ በማምረት ነው። ⏩ #የሰውነት ሽታ የተለመደ ችግር ነው ። ምንም እንኳን የእሱ መንስኤዎች ብዙውን ጊዜ በአንድ ሰው ንፅህና አጠባበቅ ልምዶች ላይ ቢሆኑም ፣ የሰውነት ሽታ በአንዳንድ አጋጣሚዎች የበለጠ ከባድ የጤና ሁኔታን ሊያመለክት ይችላል። ⏩ #ይህ ችግር ሊከሰት የሚችለው በላብ ውስጥ የበሽታ አምጭ ረቂቅ ህዋሳት ሽታ በሚፈጠሩበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ መጥፎ ሽታ በምግብ ፣ በንህጽና ፣በጤና ፣ በጾታ እና በአንዳንድ የመድሃኒት ዓይነቶች አወሳሰድ ላይ ይወሰናል፡፡ ችግሩ የሚነሳው ከእጅ ፣ከእጅ ንፍፊት ፣ ከሃፍረት ስጋ ፣ ከብብት እና ከፊንጢጣ አካባቢዎች ነው፡፡ ⏩ #መንስኤዎች 🔺 የሆድ ድርቀት፣ በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ 🔺 ሁል ጊዜ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር 🔺 አልኮል ፣ሲጋራና ጫት መጠቀም 🔺 የቫይታሚን እጥረት መኖር 🔺 ጥሩ ጠረን የሌለው ዶድራንት መጠቀም 🔺 ስኳር የሚበዛባቸውን ምግቦች እና መጠጦች አዘውትሮ መጠቀም ⏩ #አጋላጭ #ሁኔታዎች 🔺 ከመጠን በላይ ውፍረት 🔺 ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ 🔺 የተወሰኑ የሕክምና ሁኔታዎች - የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ፣ ከመጠን በላይ እንቅስቃሴ በተለመደው የሰውነትዎ ሽታ ላይ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ። 🔺 በአንዳንድ አጋጣሚዎች አንድ ያልተለመደ የሰውነት ሽታ የከፋ ነገር ምልክት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ሽንት መሰል ሽታ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ማለት ሊሆን ይችላል። 🔺 ውጥረት ወይም መጨናነቅ - ውጥረት የአፖክሪን ዕጢዎችዎ (apocrine glands) የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። ያስታውሱ ፣ እነዚህ ሽታ ያለው ላብ የሚያመጡ እጢዎች ናቸው። 🔺 ጄኔቲክስ - አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ የሰውነት ሽታ ለማዳበር በጣም የተጋለጡ ናቸው። 🔺 ጾታ ይህ ችግር ሴቶች ላይ ቢከሰትም ወንዶች ላይ ግን በይበልጥ ይከሰታል፡፡ ⏩ #የሰውነት ጠረንን ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች 🔺 አዘውትሮ ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ። በተለይ በሞቃታማ ፣ እርጥበት አዘል በሆኑ አካባቢዎች ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ገላ መታጠብ 🔺 ፀረ-ባክቴሪያ ሳሙና ይጠቀሙ 🔺 የብብትን ንህጽህና መጠበቅ 🔺 ትክክለኛውን የዲዎደረንት ምርቶችን ይምረጡ 🔺 አየር የሚዘዋውሩ ልብሶችን እና ሰውነት ላይ የማይጣበቁ ልብሶችን ይልበሱ 🔺 ላብ በቆዳ ላይ የሚይዙ ጨርቆችን ያስወግዱ። እነዚህ የሰውነት ሽታ እንዲዳብር የተሻለ የመራቢያ ቦታን ይፈቅዳሉ። 🔺 ቅመማ ቅመሞችን ወይም ሚያቃጥሉ ምግቦችን ከአመጋገብዎ ያስወግዱ ወይም ይቀንሱ። እንደ ቃሪያ ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ ቁንዶ በርበሬ ፣ ብሮኮሊ እና ሽንኩርት ያሉ ጠንካራ የሚሸቱ ምግቦች የበለጠ የበዛ ላብ ሊያስከትሉ ይችላሉ። 🔺 የአልኮል መጠጥ በላብዎ ሽታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። 🔺 በቀን 8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት 🔺 በብብት እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ያለ ፀጉር መላጨት ። ፀጉሩ ላብ ይይዛል እና ባክቴሪያዎች ሊበቅሉ የሚችሉበት ጥሩ አከባቢን ይፈጥራል። ፀጉርን ማስወገድ የሰውነት ሽታ ለመቆጣጠር ይረዳል። ⏩ #ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮቻችን በተለመደው የሰውነት ሽታዎ ላይ ያልተለመደ ለውጥ ካስተዋሉ ወይም የሆነ ነገር ትክክል እንዳልሆነ ከተሰማዎት ሐኪምዎን ያነጋግሩ።ማንኛውም ከጤና ጋር ተያይዞ ጥያቄ ካሎት ወደ ጥሪ ማዕከላችን በመደወል ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ! ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ማክዳ)

✍#የዘር #ፍሬ #ማቀፊያ #እብጠት 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #መንስኤ 🔺 የልብ ችግር 🔺 አንጀትን ሰብስቦ የሚይዘው ሽፍን ላይ ክፍተት ሲፈጠር አንጀት የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎን ወደሚይዘው ከረጢት ውስጥ በመግባት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል። 🔺 የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎችን የሚይዘው ከረጢት በተለያዩ ፍሳሾች ሲሞላ በየጊዜው መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ እብጠትን ያመጣል። 🔺 በቫይረስ፣ በፈንገስና በባክቴሪያ አማካኝነት የተለያዩ ኢንፌክሽኖች በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ ሲከሰት እብጠት ይፈጠራል። 🔺 የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ መመታትን ከደረሰ እብጠት ሊከሰት ይችላል። 🔺 ለብዙ ሰዓት የሚቆሙ ወይም እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች ላይ በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ውስጥ ያሉ ደም መላሽ ደም ስሮች ተቋጥረው እብጠትን ያመጣሉ፡፡ 🔺 በኢንፌክሽን ምክንያት የዘር ፍሬዎች መሸፈኛ ከረጢት ሊያብጥ ወይም መግል ሊይዝ ይችላል፡፡ 🔺 የዘር ፍሬው መንጭቶ ወደ ማጠራቀሚያው እስኪደርስ ድረስ ያለው ቱቦ (ቧንቧ) ካንሰር ያልሆኑ ዕጢዎች ሊበቅሉበት ይችላል። ⏩ #ምልክቱ 🔺 የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች እብጠት፣ ሲነካ ማመም እና መቅላት 🔺 ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ህመም መኖር 🔺 የዘር ፍሬ ከረጢቱ በየጊዜው በመጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ውሃ መቋጠር 🔺 የዘር ፍሬ ከረጢቱ ላይ የክብደት ስሜት መሰማት 🔺 ሽንት ሲሸና የህመም ስሜት 🔺 ሳል ሲኖር ወይም ሆድ ላይ ጫና ሚፈጥሩ ነገሮች ሲኖሩ እብጠቱ መጨመር ⏩#ህክምና ፡-የዚህ ችግር መፍትሄዎች እንደየመንሰኤዎቹ ስለሚለያይ ይህ ችግር ካጋጠመው ግለሰቡ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ⏩#የቤት #ውስጥ 🔺እባጩ በታየ በ24 ሰአት ውስጥ በረዶ በከረጢት አድርጎ መያዝ 🔺ማስታገሻ መድሃኒት መውሰድ 🔺ደጋፊ የውስጥ ፓንት ማድረግ 🔺ጫና ያላቸውን እንቅስቃሴ መቀነስ 👉👉 #ከጤና ጋር ስለተያዙ የትኛውም ችግሮች ላይ ለመመካከር ካሻዎ 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2 ሰዓት እስከ 2፡00 ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ )

ማስቲካን በማኘክ የሚገኙ የጤና ጥቅሞች ********************************** ሁላችንም ልጅ እያለን ማስቲካ ሳናኝክና እየነፋን ሳንጫወት አላደግንም ይህ ልጅ እያለን እያኘክን ብሎም እየነፋን ስንደሰትበት የነበረው ማስቲካ ለሰውነታችን 10 የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ይሰጠናል፤ እነዚህን ጥቅሞች ሳናውቅ ማስቲካን ያኘክንበት አያሌ ዘመናትን ወደኋላ ትተን አሁን ለእኛ ያለውን ጥቅም አውቀን ማስቲካ ማኘክ እንድንጀምር ጥቅሞቹን ልናሳውቅዎ ወደናል። ✔ የምናገኛቸው ጥቅሞች እነሆ፦ 1. ጭንቀትን ያስወግዳል! በተለያዩ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ከማያኝኩት/ከማይጠቀሙት በተሻለ ሁኔታ ከገቡበት ጭንቀት በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ 2. ክብደትን ይቀንሳል! የተለያዩ ጣዕም ያላቸው ማስቲካዎችን ለማኝክ ከፍተኛ ካሎሪ/ጉልበት እንድናወጣ ስለሚያደርገን ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡ 3. የምግብ ስልቀጣን ያፋጥናል! ማስቲካ ማኝክ በአፋችን ውስጥ የምራቅ መጠን እንዲጨምር/እንዲበዛ ያደርጋል ይህ ሁኔታ የምግብ ስልቀጣን/መፈጨትን የማፋጠን ከፍተኛ ሀይል አለው፡፡ 4. ሀሳብን ለመሰብሰብ ይረዳል! ማስቲካ ማኝክ ከማንኛውም ጊዜ በላይ እንድንነቃቃ እና ሃሳባችንን እንድንሰበስብ ያደርጋል፡፡ በተለይ በስብሰባ እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ (ምንም እንኳን መምህሮች ፈቃደኛ ባይሆኑም) ማስቲካ ማኝክ ነቃ ብለንና ሃሳባችንን ሰብሰብ አድርገን እንድንከታተል ይረዳናል፡፡ 5. የትውስታ አቅምን ይጨምራል! ማስቲካ በምናኝክበት ጊዜ አማካይ የልብ ምታችን ይጨምራል ይህ ሁኔታ ወደ አእምሮአችን የሚገናውን የኦክስጂን መጠን ይጨምረዋል፡፡ ስለዚህ አእምሮአችን በብቃትና በትኩረት ስራውን እንዲወጣ/እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ 6. መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል! ማስቲካ ማኝክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ከመከላከሉም በላይ ጥርሳችን እንዳይበሰብስ ይረዳል፡፡ በምናኝክበት ወቅት ከፍተኛ ምራቅ ስለምናመነጭ በአፋችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ለአፍ ጠረንና ለጥርስ መቦርቦር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡ 7. የሲጋራ ሱስን ለማቆም ይረዳል! የተለያዩ የሲጋራን ሱስ ለማቆም የሚረዱ ማስቲካዎች በውስጣቸው ኒኮቲን የያዙ በገበያ ላይ ይገኛሉ እነዚህን ማስቲካዎችን በማኝክ የሲጋራ ሱስን ማቆም ይቻላል፡፡ 8. ካሎሪን ለማቃጠል ይረዳል! ማስቲካ በምናኝክበት ወቅት በመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ይሰራሉ፡፡ እንደሚታወቀው ስራ ለመስራት ሀይል ያስፈልጋል ስለዚህ የመንጋጋ ጡንቻዎች በሠዓት 10 ካሎሪ ያህል ይቀንሳሉ ይህ ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡ 9. የገርድ በሽታን ይከላከላል! ይህ የበሽታ አይነት በጨጓራችን ውስጥ ያለው አሲድ(HCL) በጉሮሮ/የምግብ ቧንቧዎች ወደ ላይ ሲመለስ ልባችን አካባቢ የማቃጠል ስሜት የሚፈጥርብን በሽታ ነው፡፡ ይህን በሽታ በቀላሉ ለመከላከል ማስቲካ በማኝክ በምራቅ አማካኝነት ወደ ላይ የሚመጣውን አሲድ ጨጓራ ውስጥ ማስቀረት ይቻላል፡፡ 10. የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ለማግኝት! ማስቲካ በውስጡ የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ቫይታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ በተጨማሪም የአፍ ውስጥ ባክቴሪያን የሚያጠፉ እንደ ዛይሊቶል አይነት ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ መልካም ጤንነት!! ============================ ሼር እና ላይክ ያድርጉ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias