ar
Feedback
ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

الذهاب إلى القناة على Telegram

ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias

تُعد قناة ዶ/ር ሶፎንያስ ኤርምያስ_Dr Sofonias Ermias (@drsofonias) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 19 949 مشتركاً، محتلاً المرتبة 1 157 في فئة الطب والمرتبة 1 681 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 19 949 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 27 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -557، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -23، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 26.07‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 6.79‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 5 203 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 354 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 10.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ጤና ነክ ጥያቄ ካለዎት፣ በጽሑፍ በቴሌግራም ብቻ ይሄንን➡️  t.me/Dr_Sofonias በመጫን ያስቀምጡልኝ ሙያዊ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ ሊወስድብኝ ስለሚችል፣ በትዕግስት ይጠብቁኝ ​📢 ለማስታወቂያ/ስፖንሰርሺፕ: ​ለስፖንሰርሺፕና ምርትዎ በሙያዊ ምክር እንዲተዋወቅ ከፈለጉ፣ ይሄንን ➡️ t.me/MASTAWKIYA በመጫን ያናግሩን

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 28 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الطب.

19 949
المشتركون
-2324 ساعات
-1257 أيام
-55730 أيام
أرشيف المشاركات
የተለመደውን ምክሬን ተግባራዊ ያድርጉ ስኳር ቀንሱ ወድ ቤተሰቦቼ የምንመገበውን የስኳር መጠን መቀነስ ለምን ያስፈልጋል? 25-08 ✓ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ በብዛት ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ለሰው
የተለመደውን ምክሬን ተግባራዊ ያድርጉ ስኳር ቀንሱ ወድ ቤተሰቦቼ የምንመገበውን የስኳር መጠን መቀነስ ለምን ያስፈልጋል? 25-08 ✓ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ በብዛት ጣፋጭ ምግቦችን መመገብ ለሰውነት ክብደት መጨመር ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንደኛው ሲሆን ፍሩክቶስ የስብ ክምችት እንዲኖር ስለሚያደርግ እና ጣፈጭን አብዝቶ መመግብ የረሃብ ስሜት እንዲሰማን እንዲሁም በብዛት እንድንመገብም ያደርጋል ስለዚህ የሰውነት ክብደትዎን ለማስተካከል የሚወስዱትን የስኳር መጠን ቢቀንሱ ይመከራል። ✓ ለጤናማ ጥርስ ነጭና የሚያንፀባርቁ ጥርሶችን እንዲኖርዎ ከፈለጉ የሚወስዱትን የስኳር መጠን ይቀንሱ። ጣፋጭ የምናዘወትር ከሆነ በአፍ ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች እንዲበራከቱ ስለሚያደርግ ለጥርስ እና ድ ድ ህመም እንድንጋለጥ ያደርጉናል። ለጤናማ ጥርስ ስኳርን ማዘውተር አይመክርም! ✓ ለቆዳ ጥራት ስኳር ለቆዳችን መሰንጣጠቅ እና ጥራት ማጣት ይዳርጋል። በሴሎች ውስጥ የሚገኘውን ውሃ ስለሚያስወጣ ለቆዳ ድርቀት ይዳርጋናል። ✓ ቋሚ የሆነ ሃይል እንዲኖረን ስኳር እንደተመገብነው ከፍተኛ የሆነ ሃይልን የሚሰጥ ስለሆነ ንቁ ያደርገናል ነገር ግን ወድያውኑ መጠኑ በሚወርድ ጊዜ የድካምና የመራብ ስሜት እንዲሰማን ምክንያት ይሆናል ስለዚህም ባያዘወትሩ ይመከራል። ✓ ለጤናማ ልብ ሰውንታችን ያልተጠቀመውን ስኳር ወደ ስብነት ለውጦ የሚያስቀምጥ ሲሆን ይህ የስብ መጠን በሚጨምር ጊዜም ለተለያዩ የልብ ህመሞች እና ለስትሮክ የመጋለጥ እድልዎን ስለሚጨምር ቢጠነቀቁ መልካም ነው። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

✍#የሰውነት #መጥፎ #ጠረን 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ላብ በራሱ የሰውነት ሽታን አያመጣም ፣ የሰው ላብ ሽታ የለውም ማለት ይቻላል።በአንድ ሰው ቆዳ ላይ በባክቴሪያ ምክንያት የሰውነት ሽታ የሚከሰተው በላብ ውስጥ የፕሮቲን ሞለኪውሎችን በማፍረስ እና በዚህም ምክንያት ሽታ በማምረት ነው። ⏩ #የሰውነት ሽታ የተለመደ ችግር ነው ። ምንም እንኳን የእሱ መንስኤዎች ብዙውን ጊዜ በአንድ ሰው ንፅህና አጠባበቅ ልምዶች ላይ ቢሆኑም ፣ የሰውነት ሽታ በአንዳንድ አጋጣሚዎች የበለጠ ከባድ የጤና ሁኔታን ሊያመለክት ይችላል። ⏩ #ይህ ችግር ሊከሰት የሚችለው በላብ ውስጥ የበሽታ አምጭ ረቂቅ ህዋሳት ሽታ በሚፈጠሩበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ መጥፎ ሽታ በምግብ ፣ በንህጽና ፣በጤና ፣ በጾታ እና በአንዳንድ የመድሃኒት ዓይነቶች አወሳሰድ ላይ ይወሰናል፡፡ ችግሩ የሚነሳው ከእጅ ፣ከእጅ ንፍፊት ፣ ከሃፍረት ስጋ ፣ ከብብት እና ከፊንጢጣ አካባቢዎች ነው፡፡ ⏩ #መንስኤዎች 🔺 የሆድ ድርቀት፣ በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ 🔺 ሁል ጊዜ ፕሮቲን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር 🔺 አልኮል ፣ሲጋራና ጫት መጠቀም 🔺 የቫይታሚን እጥረት መኖር 🔺 ጥሩ ጠረን የሌለው ዶድራንት መጠቀም 🔺 ስኳር የሚበዛባቸውን ምግቦች እና መጠጦች አዘውትሮ መጠቀም ⏩ #አጋላጭ #ሁኔታዎች 🔺 ከመጠን በላይ ውፍረት 🔺 ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ 🔺 የተወሰኑ የሕክምና ሁኔታዎች - የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ፣ ከመጠን በላይ እንቅስቃሴ በተለመደው የሰውነትዎ ሽታ ላይ ለውጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ። 🔺 በአንዳንድ አጋጣሚዎች አንድ ያልተለመደ የሰውነት ሽታ የከፋ ነገር ምልክት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ሽንት መሰል ሽታ የኩላሊት ወይም የጉበት ችግሮች ማለት ሊሆን ይችላል። 🔺 ውጥረት ወይም መጨናነቅ - ውጥረት የአፖክሪን ዕጢዎችዎ (apocrine glands) የትርፍ ሰዓት ሥራ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። ያስታውሱ ፣ እነዚህ ሽታ ያለው ላብ የሚያመጡ እጢዎች ናቸው። 🔺 ጄኔቲክስ - አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች ይልቅ የሰውነት ሽታ ለማዳበር በጣም የተጋለጡ ናቸው። 🔺 ጾታ ይህ ችግር ሴቶች ላይ ቢከሰትም ወንዶች ላይ ግን በይበልጥ ይከሰታል፡፡ ⏩ #የሰውነት ጠረንን ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች 🔺 አዘውትሮ ሞቅ ባለ ውሃ መታጠብ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ። በተለይ በሞቃታማ ፣ እርጥበት አዘል በሆኑ አካባቢዎች ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ገላ መታጠብ 🔺 ፀረ-ባክቴሪያ ሳሙና ይጠቀሙ 🔺 የብብትን ንህጽህና መጠበቅ 🔺 ትክክለኛውን የዲዎደረንት ምርቶችን ይምረጡ 🔺 አየር የሚዘዋውሩ ልብሶችን እና ሰውነት ላይ የማይጣበቁ ልብሶችን ይልበሱ 🔺 ላብ በቆዳ ላይ የሚይዙ ጨርቆችን ያስወግዱ። እነዚህ የሰውነት ሽታ እንዲዳብር የተሻለ የመራቢያ ቦታን ይፈቅዳሉ። 🔺 ቅመማ ቅመሞችን ወይም ሚያቃጥሉ ምግቦችን ከአመጋገብዎ ያስወግዱ ወይም ይቀንሱ። እንደ ቃሪያ ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ ቁንዶ በርበሬ ፣ ብሮኮሊ እና ሽንኩርት ያሉ ጠንካራ የሚሸቱ ምግቦች የበለጠ የበዛ ላብ ሊያስከትሉ ይችላሉ። 🔺 የአልኮል መጠጥ በላብዎ ሽታ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። 🔺 በቀን 8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት 🔺 በብብት እና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ያለ ፀጉር መላጨት ። ፀጉሩ ላብ ይይዛል እና ባክቴሪያዎች ሊበቅሉ የሚችሉበት ጥሩ አከባቢን ይፈጥራል። ፀጉርን ማስወገድ የሰውነት ሽታ ለመቆጣጠር ይረዳል። ⏩ #ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮቻችን በተለመደው የሰውነት ሽታዎ ላይ ያልተለመደ ለውጥ ካስተዋሉ ወይም የሆነ ነገር ትክክል እንዳልሆነ ከተሰማዎት ሐኪምዎን ያነጋግሩ።ማንኛውም ከጤና ጋር ተያይዞ ጥያቄ ካሎት ወደ ጥሪ ማዕከላችን በመደወል ከጤና ባለሙያ ጋር ይማከሩ! ለመማከር 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2፡00 ሰዓት እስከ ማታ 2፡00 ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ማክዳ)

✍#የዘር #ፍሬ #ማቀፊያ #እብጠት 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #መንስኤ 🔺 የልብ ችግር 🔺 አንጀትን ሰብስቦ የሚይዘው ሽፍን ላይ ክፍተት ሲፈጠር አንጀት የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎን ወደሚይዘው ከረጢት ውስጥ በመግባት እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል። 🔺 የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎችን የሚይዘው ከረጢት በተለያዩ ፍሳሾች ሲሞላ በየጊዜው መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ እብጠትን ያመጣል። 🔺 በቫይረስ፣ በፈንገስና በባክቴሪያ አማካኝነት የተለያዩ ኢንፌክሽኖች በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ ሲከሰት እብጠት ይፈጠራል። 🔺 የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ላይ መመታትን ከደረሰ እብጠት ሊከሰት ይችላል። 🔺 ለብዙ ሰዓት የሚቆሙ ወይም እንቅስቃሴ የማያደርጉ ሰዎች ላይ በዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች ውስጥ ያሉ ደም መላሽ ደም ስሮች ተቋጥረው እብጠትን ያመጣሉ፡፡ 🔺 በኢንፌክሽን ምክንያት የዘር ፍሬዎች መሸፈኛ ከረጢት ሊያብጥ ወይም መግል ሊይዝ ይችላል፡፡ 🔺 የዘር ፍሬው መንጭቶ ወደ ማጠራቀሚያው እስኪደርስ ድረስ ያለው ቱቦ (ቧንቧ) ካንሰር ያልሆኑ ዕጢዎች ሊበቅሉበት ይችላል። ⏩ #ምልክቱ 🔺 የዘር ፍሬ ማመንጫ ፍሬዎች እብጠት፣ ሲነካ ማመም እና መቅላት 🔺 ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ህመም መኖር 🔺 የዘር ፍሬ ከረጢቱ በየጊዜው በመጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ውሃ መቋጠር 🔺 የዘር ፍሬ ከረጢቱ ላይ የክብደት ስሜት መሰማት 🔺 ሽንት ሲሸና የህመም ስሜት 🔺 ሳል ሲኖር ወይም ሆድ ላይ ጫና ሚፈጥሩ ነገሮች ሲኖሩ እብጠቱ መጨመር ⏩#ህክምና ፡-የዚህ ችግር መፍትሄዎች እንደየመንሰኤዎቹ ስለሚለያይ ይህ ችግር ካጋጠመው ግለሰቡ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ⏩#የቤት #ውስጥ 🔺እባጩ በታየ በ24 ሰአት ውስጥ በረዶ በከረጢት አድርጎ መያዝ 🔺ማስታገሻ መድሃኒት መውሰድ 🔺ደጋፊ የውስጥ ፓንት ማድረግ 🔺ጫና ያላቸውን እንቅስቃሴ መቀነስ 👉👉 #ከጤና ጋር ስለተያዙ የትኛውም ችግሮች ላይ ለመመካከር ካሻዎ 8809 ላይ ይደውሉ! ከጧት 2 ሰዓት እስከ 2፡00 ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ቢደዉሉ የዶክተር አለ የጤና ባለሙያዎች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ )

ማስቲካን በማኘክ የሚገኙ የጤና ጥቅሞች ********************************** ሁላችንም ልጅ እያለን ማስቲካ ሳናኝክና እየነፋን ሳንጫወት አላደግንም ይህ ልጅ እያለን እያኘክን ብሎም እየነፋን ስንደሰትበት የነበረው ማስቲካ ለሰውነታችን 10 የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ይሰጠናል፤ እነዚህን ጥቅሞች ሳናውቅ ማስቲካን ያኘክንበት አያሌ ዘመናትን ወደኋላ ትተን አሁን ለእኛ ያለውን ጥቅም አውቀን ማስቲካ ማኘክ እንድንጀምር ጥቅሞቹን ልናሳውቅዎ ወደናል። ✔ የምናገኛቸው ጥቅሞች እነሆ፦ 1. ጭንቀትን ያስወግዳል! በተለያዩ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ከማያኝኩት/ከማይጠቀሙት በተሻለ ሁኔታ ከገቡበት ጭንቀት በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ 2. ክብደትን ይቀንሳል! የተለያዩ ጣዕም ያላቸው ማስቲካዎችን ለማኝክ ከፍተኛ ካሎሪ/ጉልበት እንድናወጣ ስለሚያደርገን ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡ 3. የምግብ ስልቀጣን ያፋጥናል! ማስቲካ ማኝክ በአፋችን ውስጥ የምራቅ መጠን እንዲጨምር/እንዲበዛ ያደርጋል ይህ ሁኔታ የምግብ ስልቀጣን/መፈጨትን የማፋጠን ከፍተኛ ሀይል አለው፡፡ 4. ሀሳብን ለመሰብሰብ ይረዳል! ማስቲካ ማኝክ ከማንኛውም ጊዜ በላይ እንድንነቃቃ እና ሃሳባችንን እንድንሰበስብ ያደርጋል፡፡ በተለይ በስብሰባ እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ (ምንም እንኳን መምህሮች ፈቃደኛ ባይሆኑም) ማስቲካ ማኝክ ነቃ ብለንና ሃሳባችንን ሰብሰብ አድርገን እንድንከታተል ይረዳናል፡፡ 5. የትውስታ አቅምን ይጨምራል! ማስቲካ በምናኝክበት ጊዜ አማካይ የልብ ምታችን ይጨምራል ይህ ሁኔታ ወደ አእምሮአችን የሚገናውን የኦክስጂን መጠን ይጨምረዋል፡፡ ስለዚህ አእምሮአችን በብቃትና በትኩረት ስራውን እንዲወጣ/እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ 6. መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል! ማስቲካ ማኝክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ከመከላከሉም በላይ ጥርሳችን እንዳይበሰብስ ይረዳል፡፡ በምናኝክበት ወቅት ከፍተኛ ምራቅ ስለምናመነጭ በአፋችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ለአፍ ጠረንና ለጥርስ መቦርቦር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡ 7. የሲጋራ ሱስን ለማቆም ይረዳል! የተለያዩ የሲጋራን ሱስ ለማቆም የሚረዱ ማስቲካዎች በውስጣቸው ኒኮቲን የያዙ በገበያ ላይ ይገኛሉ እነዚህን ማስቲካዎችን በማኝክ የሲጋራ ሱስን ማቆም ይቻላል፡፡ 8. ካሎሪን ለማቃጠል ይረዳል! ማስቲካ በምናኝክበት ወቅት በመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ይሰራሉ፡፡ እንደሚታወቀው ስራ ለመስራት ሀይል ያስፈልጋል ስለዚህ የመንጋጋ ጡንቻዎች በሠዓት 10 ካሎሪ ያህል ይቀንሳሉ ይህ ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡ 9. የገርድ በሽታን ይከላከላል! ይህ የበሽታ አይነት በጨጓራችን ውስጥ ያለው አሲድ(HCL) በጉሮሮ/የምግብ ቧንቧዎች ወደ ላይ ሲመለስ ልባችን አካባቢ የማቃጠል ስሜት የሚፈጥርብን በሽታ ነው፡፡ ይህን በሽታ በቀላሉ ለመከላከል ማስቲካ በማኝክ በምራቅ አማካኝነት ወደ ላይ የሚመጣውን አሲድ ጨጓራ ውስጥ ማስቀረት ይቻላል፡፡ 10. የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ለማግኝት! ማስቲካ በውስጡ የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ቫይታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ በተጨማሪም የአፍ ውስጥ ባክቴሪያን የሚያጠፉ እንደ ዛይሊቶል አይነት ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ መልካም ጤንነት!! ============================ ሼር እና ላይክ ያድርጉ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

ለእስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ የፑሽ አፕ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የፑሽ አፕ ስፖርት ከፍ ካለው ቦታ ጀምሮ የሚጀምር የተለመደ የሰውነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልምምድ ነው። እጅን ተጠቅሞ አካልን ከ
ለእስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ የፑሽ አፕ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የፑሽ አፕ ስፖርት ከፍ ካለው ቦታ ጀምሮ የሚጀምር የተለመደ የሰውነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልምምድ ነው። እጅን ተጠቅሞ አካልን ከፍ በማድረግ እና ዝቅ በማድረግ በግፊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በመጠቀም የሰውነታችን የጡንቻ ክፍሎች፣ የሴራቱራክ የፊት ፣ የቁርጭምጭሚት እና አጠቃላይ የሰውነታችን ክፍል የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ያካሂዳሉ ፡፡ ፑሽ አፕ በማንኛውም አትሌቲክስ ስልጠና ወይም በአካላዊ ትምህርት እና በተለምዶ በወታደራዊ የአካል ማጎልመሻ ስልጠና ውስጥ የሚያገለግል መሰረታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ልምምድ ነው፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ በተለመደ ሁኔታ በወታደራዊ ተቋማት፣ በትምህርት ቤት ስፖርት ፣ ወይም በአንዳንድ ማርሻል አርት ትምህርቶች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ የተለመደ የቅጣት ዓይነት ነው። የፑሽ አፕ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በምንሰራበት ወቅት በዋነኝነት የሚሰሩት የደረት፣ የክንድ እና የትከሻ ጡንቻዎች ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም ከሌላው የሰውነታችን ጡንቻዎች ክፍል ድጋፍ የሚፈለግ እንቅስቃሴ ሲሆን በስፋት የሚፈለገውን ኃይልና ውጤት ወደ ጡንቻዎች ሰፊ ክልል ያደርሳል፡፡ በአጠቃላይ የፑሽ አፕ ልምምድ በምንሰራበት ጊዜ፡- 1, የደረት ጡንቻዎች 2. የሆድ ጡንቻዎች 3. የትከሻ ጡንቻዎች 4. የኋላ አካል ክፍል 5. ትራይሴፕስ 6. ክንዶች 7. ባይሴፕስ 8. እንዲሁም መገጣጠሚያዎች እና ጅማቶችን የሚያካትት ስፖርታዊ ልምምድ ነው፡፡ እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

✍ #የጡት #ካንሰር #ግንዛቤ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #ካንሰር የብዙ አይነት የካንሰር የህመም አይነቶች አጠቃላይ መጠሪያ ስም ነው ፡፡ በሽታው ከሌሎች በሽታዎች ተለይቶ የሚታወቀው ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ማደጉና ህዋሶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመውረር በመቻሉ ነው ፡፡ የጡት ካንሰር በቅድሚያ ጡት ላይ በመከሰት በሽታው በአጭር ጊዜ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በመዛመት የከፋ ችግር ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡ ⏩ #ጡት በተፈጥሮው በውስጡ ወተት ለማመንጨት የሚያስችሉ በርካታ ከረጢት መሰል ነገሮች እንዲሁም እነዚህን ከጡት ጫፍ ጋር የሚያገናኙ ቱቦዎች አሉት፡፡ እነዚህ ቱቦዎች በእርግዝና ወቅት ወተት ለማመንጨት ትልቅ ሚናን የሚጫዎቱ ናቸው ፡፡ የጡት ካንሰር በአብዛኛው ማደግ የሚጀምረው በእነዚህ ቱቦዎች ውስጥ ነው ፡፡ ⏩ #የጡት ካንሰር ተፈጠረ የሚባለው አንድ ጤነኛ ያልሆነ ህዋስ በሰውነት ውስጥ ተፈጥሮ ከገደብ በላይ መራባት ሲጀምር ነው ፡፡ የተራባው ህዋስም በጊዜ ሂደት ጤነኛ የነበሩ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን ህበረ ህዋሳትን በማጥቃት በሽተኛ ያደርጋቸዋል ፡፡ ⏩#የጡት #ካንሰር #ምልክቶች ⏩# የጡት ካንሰር ምልክቶችን አስቀድመን ላናውቃቸው እንችላለን ነገር ግን የካንሰሩ ደረጃ ከፍ እያለ ሲመጣ ለመለየት የሚያስችለንን ምልክቶች ይኖሩታል ፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ካንሰር መሆኑን ለመለየት የሚጠቁመን ምልክቶች ናቸው ፡፡ 🔺 የጡት ቅርፅ እና መጠን መቀየር 🔺 የጡት ቆዳ ከለር መቀየር 🔺 የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባባት 🔺 በጡት እና ጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ 🔺 የጡት መቅላት ፣ ማበጥ 🔺 የህመም ስሜት መሰማት 🔺 ከጡት ውስጥ ያልተለመደ ፈሳሽ መፍሰስ 🔺 ብብት አካባቢ ያበጠ ነገር ማየት ⏩ #ለጡት #ካንሰር #ሊያጋልጡ #የሚችሉ #ነገሮች 🔺 ጡት የማያጠቡ ሴቶች 🔺 በቤተሰብ እንደዚህ አይነት ችግር ካለ 🔺 የእድሜ መጨመር 🔺 ለጨረር የመጋለጥ እድል ካለ 🔺 የሰውነት ክብደት መጨመር 🔺 የሆርሞን ህክምና ማድረግ 🔺 ልጅ ያልወለዱ ሴቶች 🔺 የወር አበባ ቀደም ብሎ መምጣት 🔺 የወር አበባ ቀድሞ ማቆም 🔺 አልኮል መጠጣት ⏩#የጡት #ካንሰርን #እንዴት #እንከላከል 🔺 በየአመቱ የጡት ካንሰር ምርመራ ማድረግ 🔺 ሁልጊዜ እራስን በራስ ጡታችንን መመርመር 🔺 አልኮል መጠጦችን አለመጠጣት 🔺 የሰውነት ክብደትን ማስተካከል 🔺 የአመጋገብ ዘይቤን ማስተካከል 👉👉#በማንኛውም የጤና ጉዳይ ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ባለሙያዎች ላይ እየደወሉ የየዕለቱን የጤና ላይ ለውጦችዎን በማማከር ነገ ከሚከሰት የጤና ችግር አስቀድመው ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጠብቁ ይንከባከቡ:: ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ከድጃ)

ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡ 1. ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ
ለብ ያለ ውሃ ውስጥ ሎሚ ጨምቀው ዘውትር ቢጠጡ እነዚህን 10 የጤና ጥቅሞች ያገኛሉ፡፡ 1. ጉበቶን ከመርዛማ ነገሮች ያፀዳሉ፡፡ለብ ባለ ውሃ ውስጥ የሎሚውን ጭማቂ (ፈሳሽ) ብቻ ሳይሆን የሎሚው ልጣጭ ጭምር ከተን የምንጠጣ ከሆነ ደረጃ 2 የጉበት ፀረ- መርዝ ማስወገድ ተግባራን ያከናውናል፡፡ 2. ጉበቶ ሐሞት እንዲያመነጭ በማበረታታት ቅባታማ ምግቦችን ሰውነቶ እንዲፈጭ ይረዳል፡፡ 3. ሎሚ ከፍተኛ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ ስላለው ሕዋሳታችን(cells) እንዳይወድሙ ይጠብቃቸዋል፡፡ 4. በሎሚ ውስጥ ያለው አንቲ- ኦክሲደንት እና ፌቶኬሚካልስ የጉበት ሕዋሳት እንዲታደሱ ይረዳል፡፡ 5. በሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የምግብ ስርዓተ ልመትን ያፋጥናል እንዲሁም የኩላሊት ጠጠርን (kidney stone) ያሟሟል፡፡ 6. ሎሚ ከሰውነት ውጭ አሲድ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ አልካላይን ነው ስለሆነም በሰውነት ውሰጥ ያለውን የፒ ኤች ደረጃ ሚዛናዊ እንዲሆን ይረዳል በተጨማሪም በሽታን ይከላከላል፡፡ 7. በሎሚ ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከል አቅም እንዲኖረን ያስችላል፡፡ 8. ሎሚ የደም ቅባትን በመሰባበር በዙ ሰዎች የሚያጋጥማቸውን የሀሞት ድንጋይዎች(gall stones) በሰውነታችን ውስጥ እንዳይፈጥር ያግዛል፡፡ 9. ሎሚ ከፍተኛ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ስላላው የዩሪክ አሲድ መጠንን በመቀነስ ሰዎች በሪህ (Gout) እና የአጥንት አንጓ 10. ብግነት (Arthritis) እንዳይጠቁ ይጠብቃቸዋል፡፡ 11. ሎሚ ከአንደንድ የካንስር በሽታዎችም ይከላከላል፡፡ መልካም ልምምድ መልካም የጤና ጊዜ ይሁንልዎ! እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

በቀን ውስጥ ሚስቶች መስማት የሚፈልጉት 12 ነገር 1ኛ/ ደና አደርሽ : ደና እደሪ 2ኛ/ ቀንሽ እንዴት ነበር 3ኛ/ እኮራብሻለሁ 4ኛ/ ደስታን ትሰጪኛለሽ 5ኛ/ ስለትዳራችን ምን ታስቢያለሽ 6ኛ/ እ
በቀን ውስጥ ሚስቶች መስማት የሚፈልጉት 12 ነገር 1ኛ/ ደና አደርሽ : ደና እደሪ 2ኛ/ ቀንሽ እንዴት ነበር 3ኛ/ እኮራብሻለሁ 4ኛ/ ደስታን ትሰጪኛለሽ 5ኛ/ ስለትዳራችን ምን ታስቢያለሽ 6ኛ/ እኔ ያላንኝቺ ሙሉ አይደለሁም 7ኛ/ በጣም ቆንጆና ተወዳጅ ነሽ 8ኛ/ ላጠፋሁት ጥፋት ይቅር በይኝ 9ኛ/ አመሰግናለሁ 10ኛ/ ትናፍቂኛለሽ 11ኛ/በጣም ጥሩ ጏደኛዬ ነሽ 12/ እወድሻለሁ ባሎች እስኪ እንሞክር ይህ በአመት አንዴ አይደለም በየቀኑ ነው። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ከ'ሴክስ' ጋር የተያያዙ ችግሮች =================== አንዳንድ ሰዎች ኮንዶም ለመግዛት ፋርማሲ ሄደው ሌሎች ተስተናጋጆች እስኪወጡ ይጠብቃሉ። አሁንም 'ወደ ገደለው' መግባት ስለሚያፍሩ የማይፈልጉትን ሌሎች መድሀኒቶች ይጠይቁና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው "ኮንዶም አለ?" ይላሉ። አንዳንድ የጤና ጥያቄዎች ለመናገር የሚከብዱ ነገር ግን ወሳኝ ስለሆኑ ለመተውም የሚያስቸግሩ ይሆናሉ። አንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን ታካሚዎች ከህክምና ክፍል ሊወጡ ሲሉ ነው የሚጠይቁት። Door handle questions ይባላሉ። ከሴክስ ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደዚህ አይነት ናቸው። የሰዎች የሴክስ ህይወት በአመለካከታቸው፣ በአስተዳደጋቸው፣ በማህበረሰባዊ እሴቶች፣ በሚዲያ (ፖርኖግራፊን ጨምሮ) እንዲሁም በሌሎች ብዙ ሁኔታዎች ይወሰናል። ጥሩ የሴክስ ህይወት ያላቸው ሰዎች ደስተኛ፣ በራሳቸው የሚተማመኑ ከአጋራቸው ጋር ጥሩ የፍቅር ግንኙነት ያላቸው ሲሆኑ ጥሩ የሴክስ ህይወት የሌላቸው ሰዎች በተቃራኒው ከፍተኛ ጭንቀት ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ ሰዎች የሴክስ ችግሮች የሚታከሙ ስለማይመስላቸው፣ ስለሚያፍሩ፣ የህክምናውን ሚስጥራዊነት ስለማያምኑ ወይም በባህል ልዩነት ምክኒያት ወደ ህክምና አይመጡም። የጤና ባለሞያዎችም ስለሴክስ ለመጠየቅ ያፍራሉ ወይም የተለያዩ ግምቶች ይወስዳሉ። ለምሳሌ፦ እድሜያቸው ገፍቷል፣ አካላዊ ህመም እያለበት ሴክስ የሚያደርግ አይመስለኝም...ወዘተ። ከሴክስ ጋር የተያያዙ ህመሞች ከ3 ሰዎች አንድ ሰው ላይ እንደሚከሰቱ ጥናቶች ያሳያሉ። እነዚህ ህመሞች የፍላጎት አለመኖር፣ የብልት አለመቆም፣ ቶሎ መጨረስ፣ በሴክስ ወቅት ህመም መሰማት፣ ከሴክስ በኋላ የሚከሰት የራስ ምታት ...ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። ከሴክስ ጋር የተያያዙ ህመሞች ውጤታማ ህክምና ያላቸው ሲሆን ጥንዶች ከተመቻቸው በጋራ ወይም በግል ሊታከሙ ይችላሉ። ሚስጥራዊነቱ ሙሉበሙሉ የተጠበቀ ነው።

እሬት \ ወደር የሌለው የፀጉር እድገት ፦ የሬት የውስጠኛው ክፍልን የሚያህል ለፀጉር እድገት ተመራጭ መላ አለ ብዬ አላስብም 👉 ~እድገቱ ለማይጨምር ፀጉር ~ ለሚነቃቀል ~ የተፈጥሮ ወዙን ላጣ ~
እሬት \ ወደር የሌለው የፀጉር እድገት ፦ የሬት የውስጠኛው ክፍልን የሚያህል ለፀጉር እድገት ተመራጭ መላ አለ ብዬ አላስብም 👉 ~እድገቱ ለማይጨምር ፀጉር ~ ለሚነቃቀል ~ የተፈጥሮ ወዙን ላጣ ~ በተለይ በብዛት ሴቶችም ወንዶችም ላይ ለሚከሰተው የፊት ፀጉር መነቃቀል ፤ በአንድ ወር ውስጥ የሚታይ ለውጥን ለማየት እሬት ተመራጭ ነው። አጠቃቀሙ 👇 የእሬቱን ጄል ቢያንስ በሳምን አንድ ጊዜ መቀባት 👉 ለ 1:00 ሰአት ያህል አቆይተን መታጠብ ። ፀጉራችን የመነቃቀል ባህሪ ካለው ትንሽ የወይራ ዘይት ጨምረን ከእሬቱ ቀላቅለን መቀባት ። የወይራ ዘይት ከሌለ ማንኛውንም ፈሳሽ ቅባት መጨምር እንችላለን ። ፀጉራችን በጣም የሳሳ ከሆነ 👉ከአንድ እንቁላል ጋር የሚበቃንን ያህል እሬት በመጠቀም መቀባት ። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias

ከንፈርዎ አካባቢ ያለውን ፂም ለማጥፋት የሚረዳ የቤት ውስጥ ውህድ 1.ወተት እና እርድ፡- 1 የሾርባ ምንኪያ የእርድ ዱቄት 1 የሾርባ ማንኪያ ወተት ወይም ውሀ በመቀጠልም ይህን ውህድ አንድ ላይ ማዋ
ከንፈርዎ አካባቢ ያለውን ፂም ለማጥፋት የሚረዳ የቤት ውስጥ ውህድ 1.ወተት እና እርድ፡- 1 የሾርባ ምንኪያ የእርድ ዱቄት 1 የሾርባ ማንኪያ ወተት ወይም ውሀ በመቀጠልም ይህን ውህድ አንድ ላይ ማዋሀድ እና ከንፈርዎን መቀባት እና ለአንድ ሰአት ያሀል ባለበት ማቆየት እና ቀስ አድርገው እያሹ መታጠብ በሳምንት ለሶስት ጊዜ ማድረግ 2.ስኳር፡- 2 የሾርባ ማንኪያ ስኳር 1 የሾርባ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ እና ሳሳ ያለ ጨርቅን ማዘጋጀት በመቀጠልም ስኳሩን መጥበሻ ላይ በማድረግ በመጠኑ ሞቅ ማድረግ እናም ሎሚውን ላዩ ላይ መጭመቅ እና በደንብ አድርጎ ማዋሀድ ይህም ቀጠን ያለ ውህድ እስኪሰራ መጠበው እና ቀዝቀዝ አድርገው ከንፈርዎ አካባቢ መቀባት እና በቀስታ ቦታው ላይ ማሸት እና መታጠብ፡፡ስኳር ማንኛውንም ፀጉር ከቆዳዎ ላይ ለማንሳት ይጠቅማል እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ @DrSofonias

ግለ ወሲብ(ሴጋ)ጉዳቱ እና መፍትሄው 👉 ክፍል አንድ(1) 👉ግለወሲብ ምንድነው? ግለወሲብ ጤናማ ካልሆኑ የወሲብ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚመደብና እራስን በራስ የማርካት እንቅስቃሴ ነው ። ግለወሲብ በኔ እምነት በጊዜአዊነት ስሜትን ከማርካት ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም ። ቢኖርውም ከጉዳቱ አይበልጥም።ለዚህም ነው ለወጣቱ ማህበረሰብ ጉዳቱን የበለጠ ለማስገንዘብ የፈለኩት ። አንድ ነገር ለማየት ይሞከራል ፤ ይደገማል ፤ይደጋገማል የተደጋገመ ነገር ደግሞ ልምድ ይሆናል ፤ ልምድ ደግሞ ወደ ሱስ ያመራል እናም ከዛ ሱስ ውስጥ ለመውጣት እጅግ በጣም ከባድ ነው ። ከወሲብ ጋር የተያያዙ የተለያዪ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 95% የሚሆነው የአለም ወጣት በግለወሲብ ሱስ የተያዘ ነው ። ያ ማለት አንድ አምራች ዜጋ የምትፈልግ ሀገር ምን ያህል በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ በግለወሲብ ምክኒያት እንደምትጎዳ ለመረዳት አዳጋች አይሆነም። 👉የሚከተሉት የግለወሲብ ጉዳቶች ናቸው :- 1.የጸጉር መሳሳት 2.እውነተኛ ወሲባዊ ግንኙነት የማድረግ ችግር 3.ቶሎ መሰልቸት, የሰውነት መዛል 4.አይነ ስውርነት 5.ጭንቀት 6.የወሲብ አካላት ለወሲብ መነሳሳት አለመቻል 7.ያለምንም እርካታ ቶሎ መጨረስ 8.ራስ ምታት 9.የእርካታ ማጣት 10.ወደ ተቃራኒ ፆታ የሚወስደው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፍላጎት ማጣት 11.ለግብረ-ሰዶማዊነት ፍላጎት መጨመር 12.የማስታወስወስ ብቃት ማነስ 13.የታችኛው የጀርባ ህመም 14.ድካም 15.ጭንቀት 16.የስሜት መለዋወጥ 17.የእንቅልፍ ማጣት 18.ትኩረትን መሰብሰብ አለመቻል 19.የብቸኝነትና, እራስን የማግለል ስሜት 20.ግለ ወሲብ ከተደረገ በኋላ የበደለኛነት ስሜት መሠማት ለምን አደረኩት የሚል ቁጭት 21.የወሲብ መነሳሳት ስሜት ማነስ 22.የራስን ሕይወት የማጥፋት ሐሳብ እና ዝንባሌ እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩት የግለወሲብ ጉዳቶች በአንዳንድ ሰዎች ላይ ቶሎ ሲታዩ በሌሎች ላይ ላይ ደግሞ ዘግይተው ሊታዩ ይችላሉ ። 👉በክፍል ሁለት ደግሞ ግለወሲብን እንዴት ማቆም እንችላለን የሚለውን እናያለን ። ይህ መረጃ እህት ወንድሞቻቸሁ ጋር እንዲደርስ ሼር አድርጉ ። እኔን ለማማከር የምተፈልጉ ቴሌግራም ላይ inbox አናግሩኝ ይኀው አድራሻዬ https://t.me/DrSofonias https://t.me/DrSofonias