𝙞𝙨𝙡𝙖𝙢𝙞𝙘 𝙠𝙣𝙤𝙬𝙡𝙚𝙙𝙜
Open in Telegram
#የቴሌግራም_ቻናላችን_ሊንክ👇 https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA የፌስቡክ ግሩፓችን 👇 #ፊዳካ_ኣቢ_ወዑሚ_ያረሱልለህ 👇 https://facebook.com/groups/3118579678388903/ #የፌስቡክ_ፔጅ👇 Facebook peg link https://www.facebook.com/323366755034719?referrer=whatsapp
Show more1 035
Subscribers
No data24 hours
-67 days
-2030 days
Posts Archive
1 035
አንተ በመሞትህ የሌሎች ህይወት አይቋረጥም ፤ ሁሉም እንደ ወትሮው ህይወቱን መግፋቱን ይቀጥላል ፤ አንተ ግን የማይረሳ ሰው የለምና ትረሳለህ ፣ እናም ለአኺራህ ጥረህ ስራ በመጪው አለም ዘላቂ ህይወትህ የሚጠቅምህ መልካም ስራህ ብቻ ነውና።
1 035
ፈታዋ
የፈጅር አዛን ካለ ፆመኛ የሆነ ሰዉ መጠጣት እና መመገብ ሊያቆም ይገባዋል
አዛን እያ መጠጣት የሚቻልባቸዉ መንገዶች አሉ እነሱም
ዉሀ ሊጠጣ ብርጭቆዉን አንስቶ ከሆነ 1,መጣጣት ይችላል መመለስ የለበትም
2, የተመገበዉ ምግብ ካፉ ዉስጥ እያለ አዛን ቢል ካፉ ዉስጥ ያለዉን ማዉጣት የለበትም መዋጥ ይችላል
3, ከምግብ ቡሀላ መድሀኒት የሚዉጥ ሰዉ እረስቶ አዛን ሲል ቢያስታዉስ ተላጃዉን ከፍቶ መድሀኒቱን መዋጥ እና ዉሀ መጠጣት ይችላል
ወሏሁ አእለም
1 035
🚨🌙 በሳውዲ አረቢያ ጨረቃ መታየቷን ተከተሎ የታላቁ የረመዳን ፆም ነገ ይጀመራል።
ለመላው ሙስሊሞች ከወዲሁ መልካም ፆም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን 🙏
ረመዳን ከሪም 🌙
#RAMADAN1446
1 035
ጠዋት ከእንቅልፍህ የምትነቃው መንቃት ስለምትችል አይደለም ነገር ግን #አላህ (ሱ.ወ) መንቃት እንድትችል ስለአስቻለህ ነው ሌላ አዲስ ቀን እንድትኖር ስለፈቀደልህ ነው...ስለዚህ '#አልሃምዱሊላህ' በል!!!
🙏አልሀምዱሊላህ!🙏
1 035
🌼ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ የምትወደው ዋና ባህሪ ጥንካሬዉን እና ታማኝነቱን ሲሆን ወንዶች ከሴቶች ከሚወድት ባህሪ ቀዳሚው ነገር ጥብቅነት እና ቁጥብነትን ነው ።
ሸይኽ ዐብዱልመሊክ ቃሲም
1 035
የጁምአ ቀን
ነብዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል፦
{አርብ(ጁመዓ) ቀን ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሽ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ከዚያም የቻለውን ያህል (ሱና) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡}
ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም፦
1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣
4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል።
በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ኹጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል።
በሌላም የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ።
ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ።
የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦
{የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።}
(አልባኒ ሶሂህ ብለውታል)
አላህ ሱ.ወ እንዲህ ብሏል፦
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።(9)፤ ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡(10)" ((62:9_10)
የጁመአ ቀን ሱናወች ~
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِي
#የቴሌግራም_ቻናላችን_ሊንክ👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA
የፌስቡክ ግሩፓችን 👇
#ፊዳካ_ኣቢ_ወዑሚ_ያረሱልለህ
👇
https://facebook.com/groups/3118579678388903/
#የፌስቡክ_ፔጅ👇
Facebook peg link
https://www.facebook.com/323366755034719?referrer=whatsapp
1 035
Repost from 📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚
۞إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُم۞
۞ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ ۞(ቁርአን 49:13)
ያ አላህ! አንተን ከሚፈሩ ባሮችህ አድርገን።💚
1 035
Repost from 📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚
◾️ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።
✅ ሶብር አድርጊ። ምንዳሽንም ከአላህ ፈልጊ። ያለሽበት በሆነው ሸሪአዊ ሂጃብ (ኒቃብ) ላይ ፅኚ። የሰዎች ንግግር፦ አክራሪ ናት፣ አጥባቂ ናት ቢሉሽ ምንም አይጎዳሽም።🧡
📚فتاوى نور على الدرب
1 035
Repost from 📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚
#10አስር በጀነት የተመሰከረላቸው ሰሃቦች!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿أبو بَكْرٍ في الجنَّةِ، وعمرُ في الجنَّةِ، وعُثمانُ في الجنَّةِ، وعليٌّ في الجنَّةِ، وطَلحةُ في الجنَّةِ والزُّبَيْرُ في الجنَّةِ، وعبدُ الرَّحمنِ بنُ عوفٍ في الجنَّةِ، وسعدُ بنُ أبي وقّاصٍ في الجنَّةِ، وسَعيدُ بنُ زيدٍ في الجنَّةِ، وأبو عُبَيْدةَ بنُ الجرّاحِ في الجنَّةِ.﴾
“አቡበከር የጀነት ነው። ዑመር የጀነት ነው። ዑስማን የጀነት ነው። ዐሊይ የጀነት ነው። ጦለሃ የጀነት ነው። ዙበይር የጀነት ነው። አብዱራህማን ቢን ዐውፍ የጀነት ነው። ሰዐድ ቢን አቢ ወቃስ የጀነት ነው። ሰዒድ ቢን ዘይድ የጀነት ነው። አቡ ዑበይዳህ ቢን አልጀራህ የጀነት ነው።”
ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 3747
1 035
Repost from 📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚
እኔ ጌታችሁ ነኝ:- አምልኩኝ ይላል አላህ
{ إِنَّ هَـٰذِهِۦۤ أُمَّتُكُمۡ أُمَّةࣰ وَ ٰحِدَةࣰ وَأَنَا۠ رَبُّكُمۡ فَٱعۡبُدُونِ }
[سُورَةُ الأَنبِيَاءِ: ٩٢]
1 035
Repost from 📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚
قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ : ( إِنَّ أَحَبَّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبَكُمْ مِنِّي فِي الْآخِرَةِ مَحَاسِنُكُمْ أَخْلَاقًا
✍በአኼራ ከሁሉም ይበልጥ ለኔ ተወዳጆቻችሁና ለኔ ከሁሉም ይበልጥ
ቅርቦቻችሁ ከሁሉም ይበልጥ
#መልካም_ስነምግባር ያላቸው ናቸው(ረሱልﷺ)
