en
Feedback
UNION FELLOWSHIP©✝

UNION FELLOWSHIP©✝

Open in Telegram

#we deal about the strength and weakness of our fellowship #we advertise what programmes we have and had in the week. #we address you an information about such things whole over Ethiopia. #PRAYER IS THE ONLY MEANS OF RECEIVING SPIRITUAL POWER!!!!! @UACSFF

Show more
553
Subscribers
+124 hours
+17 days
No data30 days
Posts Archive
Like👍👆👆👆

#35 #የተዘነጋ_እውነት #Forward_to_Friends! Personal link- https://t.me/siwur_kulfoch/3340 @siwur_kulfoch
#35 #የተዘነጋ_እውነት #Forward_to_Friends! Personal link- https://t.me/siwur_kulfoch/3340 @siwur_kulfoch

ወጣቱን ትውልድ የሚያጨነግፉ ተግባራትን እቃወማለሁ!! ትውልድ የብዙ ሰበዞች ስብጥር ውጤት ነው። የእራሱ፣ የቤተሰቡ፣ የማሕበረሰቡ የቤተ-እምነቶችና የመንግስት ሥርዓት ድምር ነው። በዋናነት የእነዚህ መሠረታዊ ባለድርሻ አካላት የመተሳሰር በጋራ ለአዎንታዊ የትውልድ ግንባታ የመስራታቸውና ያለመስራታቸው ፍሬ በትውልዱ መንፈሳዊ፣ አእምሯዊና ሥነ ልቦናዊ ዝንባሌ ውስጥ ይታያል። ወጣትነት ነገን በመስራት ሊጠመድ የሚገባው እድሜ ነው። አንድም ሀገር ገንቢ ሌላም ሀገር ተረካቢ ነው። ዘርፈ ብዙ ተግዳሮትም ያለበት ነው። ወጣቱ ላለበት ችግር የሚጣጣም መፍትሔ ሊበጅ ያስፈልጋል። ያለው ስንክሳርና የሚቀርበው አማራጭ ከተቃረና የውሸት ዋሻ ውስጥ እንደመደበቅ ነው። በምንም መመዘኛ የወጣቱ የሥራ እጦት ለቁማርና ለአደንዛዥ ሱሶች መጋለጥ ምክንያት አይሆንም። እንዲህ ያሉ ስህተትን በስህተት ለማረም የመዳከር ልማድ በስፋት ይታያል። በሀገራችን ከተሞች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስፋፉ የመጡ ቁማር ቤቶች የብዙ ወጣቶች ወጥመድ ሆነዋል። እነዚህ ቁማር ቤቶች በየጥቂት ርቀት ሕጋዊ እውቅና አግኝተው መበራከታቸውና በትምህርት ቤቶች ዙሪያ መስፋፋታቸው የወጣቱ ትውልድ ማነቆ እየሆኑ መጥተዋል። ወጣቱ ለተደቀነበት ልዩ ልዩ መሰናክልና ለውጥ ለሚሻባቸው ፈተናዎች ለውጥን ጠባቂ ብቻ መሆኑ ትርጉም ያለውን ፍሬ አላሳየንም። ስለሆነም የራስን አስተዋጽኦና ትግል በማድረግ ነገን ፈጣሪ መሆን ግድ ይላል። ይህ እንዲሆን ወጣቱ ዓላማን ያነገበ፣ ራዕይን የሰነቀና እውን ሊያደርግ የሚሻው ህልም እንዲኖረው መትጋትና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ እገዛ ያሻዋል። ከሌለው ላይ ገንዘቡን የሚያራቁት፣ የወጣትነቱን ሀብትና ግዜ አለአግባብ የሚያባክን ከሆነ ለራሱም፣ ለማሕበረሰቡም፣ ለሀገሩም ሸክም እንዲሁም የጥፋት መሳሪያ መሆኑ አይቀርም። ቁማር መዘዙ ብዙ ነው። ለስርቆት፣ ከቤተሰብ ጋር ላለመግባባት፣ ለሱስና ለጸብ ደጅ የሚከፍት ነው። በዚህ ሱስ ተይዘው ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው። ከዚህም ለከፋ ነገር ተጋልጠዋል። ራሳቸውንም ለማጥፋት ምክንያት ሆኗቸው ያጣናቸው ወንድሞችም አሉን። ዝምታው ቀስ በቀስ ለትውልድ ውድቀትና ለሀገር እድገት ጠንቅ መሆኑ አይቀርምና ሁላችንም ይህንን የቁማር መስፋፋት እናውግዝ፤ እንከላከል፤ ወጣቱንም እንታደግ። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ:- ባህል ቱርዚም ሚኒስቴር፣ ሴቶች ሕጻናትና ማሕበራዊ ሚኒስቴር፣ ትምህር ሚኒስቴር፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የማሕበረሰብ ተወካዮች ትኩረት እንዲሰጡና መፍትሔ እንዲያበጁ በአክብሮት እጠይቃለሁ። የምኖርበት የሃዋሳ ከተማ አስተዳደርም በከተማችን ያለውን አሳሳቢ የቁማር ቤቶች መስፋፋትን ከትምህር ቤቶች አከባቢ እንዲያርቅና መፍትሔ እንዲሰጥ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ። ይህንን መልዕክት ያጋሩ!! ምንተስኖት መኩሪያ ሰኔ 12/2015 ዓ.ም ሃዋሳ-ኢትዮጵያ

❤️ቤተሰብ + የቀድሞ #የመሪዎች #ህብረት #ቤተሰብ + ላለፉት 2ዓመታት ከህብረታችን ጀርባ በብዙ ለዚህ አገልግሎት ቀኛቸውን ሰተው እያገለገለሉ የነበሩ መሪዎች ናቸው ትህትና ፍፁም የተሰጠ ልብ ጠንካ
❤️ቤተሰብ + የቀድሞ #የመሪዎች #ህብረት #ቤተሰብ + ላለፉት 2ዓመታት ከህብረታችን ጀርባ በብዙ ለዚህ አገልግሎት ቀኛቸውን ሰተው እያገለገለሉ የነበሩ መሪዎች ናቸው ትህትና ፍፁም የተሰጠ ልብ ጠንካራ መንፈሳዊ ህይወት የተቀጣጠለ የፀሎት አቅም ብቻ ተወርቶ አያልቅ የኛ ድንቅ መሪዎች በዩኒየን ፊሎሽፕ ታሪክ ላይ አድምቃቹ ፅፍችኋል ከልባችን አትጠፋም ምህረት ይብዛላችሁ ፀጋ ይጨመርላቹ የአንደበታቹ ቃል የከበደ ይሁን ትውልድ ይቀበላቹ ድመቁልን የልብ ሰው ያርጋቹ ከደረቱ ያስጠጋቹ እንወዳችኋለን የኛ ምርጥ መሪዎች ❤️

😍ቤተሰብ + #ዳኒ እና #ሊዱ 😍ሰላም ሰላም ሰላም እንደምድር አሸዋ ሰላማችሁ የበዛ ይሁን እንደሰማይ ከዋክብት እረፍታቹ የተትረፈረፈ ይሁን ዛሬም ለምስጋና ተከስቻለው በእነዚህ 2 ዓመታት በርካታ
+1
😍ቤተሰብ + #ዳኒ እና #ሊዱ 😍ሰላም ሰላም ሰላም እንደምድር አሸዋ ሰላማችሁ የበዛ ይሁን እንደሰማይ ከዋክብት እረፍታቹ የተትረፈረፈ ይሁን ዛሬም ለምስጋና ተከስቻለው በእነዚህ 2 ዓመታት በርካታ ወራት 610 ወርቃማ ቀናት እግዚአብሔር ስለወደደን እኚህን ድንቅ መሪዎች ሰጠን ብዙ ብንል ደስታችን ነበር #ዲኒ ትሁት ትጉ ለእግዚአብሔር የቀና ልብ ያለው ፈሪሀ እግዚአብሔር የሞላበት ለትውልድ የሚጨነቅ ጉልበቱ ለመምበርከክ የማይለጉም አገልጋይ ነው #ሊዱ ለእግዚአብሔር ህይወቷን የማትሳሳ ለክርስቶስ ወንጌል የጀገነች የማትሰለች መካሪ ተቆጪ አስተዋይ ለበርካታ እህቶች ምሳሌ የምትሆን ምርጥ አገልጋይ ናት❤ በመጨረሻም ያለመሰልቸት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተሹማቹ ስላገለገላቹን በብዙ እየተቸገራቹ ዋጋ ከፍላቹ ህብታችንን የልጁ የኢየሱስን ህብረት እንዲመስል በብዙ ስለደከማቹ ምን እንላለን ጌታ ብድራታቹን ይክፈላቹ ለምልሙልን የነካቹት ህይወት ይዝራ የሰራቹት ስኬትን ያፍልቅ ጎዳቹ የረሰረሰ ይሁን ፀሎታቹ ከጣሪቹ በላይ ሰማያት ይሁን ከምርቃት ሁሉ የሚልቀውን ምርት ከልባችን መረቅናቹ ጌታ መንፈስቅዱስ ልጁ ኢየሱስን ያስረዳቹ 😍የኛ ምርጥ መሪዎች እንወዳችዋለን

photo content

photo content
+1

photo content
+6

photo content
+9

photo content
+9

#ቤተሰብ + #እየሩሳሌም #ወራሾች 😍😍❤️❤️ 👋ፀጋ እና ምህረት ይብዛላችሁ ወዳጆቻችን ይኸው ትላንት በቀጠርነው መሰረት ይኸው ተገኝተናል ትላንት በነበረን ታሪካዊ ቀን ጌታ #በእየሩሳሌም #ወራሾ
+4
#ቤተሰብ + #እየሩሳሌም #ወራሾች 😍😍❤️❤️ 👋ፀጋ እና ምህረት ይብዛላችሁ ወዳጆቻችን ይኸው ትላንት በቀጠርነው መሰረት ይኸው ተገኝተናል ትላንት በነበረን ታሪካዊ ቀን ጌታ #በእየሩሳሌም #ወራሾች ድንቅ ስነፅሁፍዊ አገልግሎት ለልባችን ብዙ አወጋን በህይወት ዳገት ላይ ያለች ነፍሳችን በይበልጥ ለሩጫ ፀናች ፅናት በቃላት ተቀርፆ በድምፅ ተገንብቶ በትወና ተገልጣ በእናንተ ታየን ስለ ሁሉ ጌታ ይመስገን ድመቁልን ለምልሙልን መልዕክት ይሙላባቹ እንወዳችዋለን #ቤተሰብ +

photo content
+1

photo content
+1

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+5

#ቤተሰብ + #ሪፈራል #ቃለህይወት #ቤተክርስቲያን 👋ሰላም ፀጋ ይብዛላችሁ በማለት የከበረ ሰላምታዪን ለእናንተ ከወንበሬ ብድግ ብዬ አቀረብኩ ዋጋችሁ ከቀይ እንቁ የከበረ ፍቅራችሁ የማይጠገብ እና አ
#ቤተሰብ + #ሪፈራል #ቃለህይወት #ቤተክርስቲያን 👋ሰላም ፀጋ ይብዛላችሁ በማለት የከበረ ሰላምታዪን ለእናንተ ከወንበሬ ብድግ ብዬ አቀረብኩ ዋጋችሁ ከቀይ እንቁ የከበረ ፍቅራችሁ የማይጠገብ እና አመላችሁ በአምላካችሁ የቀና #ቤተሰብ + ዛሬ ስለነበረን ፕሮግራም በአጭሩ መፅሐፍ ብንጀምር መለስተኛ መፃህፍት ይወጣዋል እርሱ ለነገ ይቆየን እና ዛሬ በአንደበት ምስጋና ተዘክሮ የማያልቅ ውለታ የዋለችንን የኛዋን ቤተክርስቲያን #ሪፈራል #ቃለህይወትን ለማመስገን ተከሰትኩ ብዙ ስለአንተ አውርተን አንጠግብም ስላሳያችሁን በጓ ልብ ከልብ እናመሰግናለን በተለይ መጋቢ ታድዮስ እና መጋቢ ኢሳያስ እናንተን ስናስብ ልባችን ሀሴት ያደርጋል ውስጠትን የሚያሳርፍ አባታዊ ምክራችሁ ብሎም ከስህተት ጓዳና ስለሚያፈናቅል ቁጣችሁ ልብን ስለሚያርድ ጥንቃቄያችሁ አሻግሮ ሽቅብ ስለሚያሳይ ጥቆማችው እንደው በቤተክርስቲያን ያለ የትውልድ ክፍተት እናንተ ጋር ሲመጣ ቃላቶቹ አቅም አተዋል አባትን መመረቅ ወጋችን ባይሆንም እንደው ደፍረት ካልሆነብን እንባርካቹ ድመቁልን ለእግዚአብሔር ወንጌል ቀኛቹን እንደሰጣቹ ቀኙን ይሳጣቹ ምክራቹ ለደረቀ አረስራሽ ቁጣቹ ማስተዋልን ለጋሽ ፍቅራቹ እንደ ንጉስ ብርቱ እንቢልታ ከሀገርን ጠሪ መያያዛቹ ማንንም የማያወጣ ጌታ ያርግላቹ ❤️ የፀጋ ጌታ ኢየሱስ አይደል አባቶቻችን ፀጋውን ያብዛችሁ እኛ ብዙ ብንል ከአንደበት ንግግር አይዘል እርሱ መድሀኒአለም ይበላችሁ እንወዳችዋለን❤️ የእናንተው ታናሽ ልጆች

photo content
+1