486
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ውድ የቪዥን ወላጆች
የማጠናከሪያ ትምህርት አሰጣጥን ይመለከታል፦
ከቅዳሜ ጥቅምት 3 ቀን ጀምሮ በቪዥን አካዳሚ የማጠናከሪያ ትምህርትን ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍሎች በቅዳሜ መርሃ ግብር መሠጠት ይጀምራል።
ብሔራዊና ክልላዊ ተፈታኞች
👉የሚዘጋጁት በማዕከል ደረጃ
ለሚዘጋጅ ምዘና ስለሆነ፤
👉በአዲስ ስርዓተ ትምህርት የሚዘጋጁ ስለሆነና በቂ ዝግጅትና ትኩረት ሰለሚጠይቅ፤
👉የ12ኞች ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናቸው ከ9-12 ክፍል ያለውን ያካተተ ስለሚሆን
ማጠናከሪያ ፕሮግራሙን መከታተል የግድ ይላል፡፡
ከ6ኛ፣8ኛ እና 12ኞች ውጭ ያሉ የሚማሩት በፈቃደኝነት ሲሆን የሚጀምሩበትን ቀን በቅርብ እናሳውቃለን
- ለሁሉም የማጠናከሪያ ትምህርት ወርሀዊ ክፍያ ባለፈው ዓመት በነበረው በተመሳሳይ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) ይሆናል፡፡
የተቋሙ አስተዳደር!
ለወላጆችና ተማሪዎች
ዓርብ፣ በ25/01/2016ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ መንገድ ስለሚዘጋጋ ትምህርት የማይኖር መሆኑን እናሳዉቃለን።
ት/ቤቱ!
📩ዉድ ወላጆች እና ተማሪዎች📩
ነገ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት የሚቀጥል ሲሆን ልጆችዎን ጧት ከ 2:00 በፈት በሚማሩበት ግቢ እንድያደርሱ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
📩ዉድ ወላጆች እና ተማሪዎች📩
ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በመውሊድ በዓል ምክንያት እንዲሁም ሐሙስ መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም የመስቀል በዓል ስለሚከበር ት/ቤት ዝግ ይሆናል፡፡
በትምህርት ቀናት ተማሪዎች ት/ቤት የሚደርሱበት ሰዓት ጠዋት 🕰2፡00 ሰዓት ወይንም ከዚያ በፊት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ልጅዎ በዚህ በተጠቀሰው ሰዓት ወይንም ከዚያ በፊት ት/ቤት እንእንዲደርሰ እናሳስብዎታለን።
እናመሰግናለን!
የቪዥን አካዳሚ ቴሌግራም ቻናሎችን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም መቀላቀል ይችላሉ።
Vision Academy https://t.me/joinchat/Fm01fl0TN-w0MmRk
KG https://t.me/joinchat/Jvmg3DoyxjBiNGI0
Grade 1 https://t.me/+qgb80VEbE3xlYmM0
Grade 2 https://t.me/joinchat/WU1pChWkFT8xNDI8
Grade 3 https://t.me/joinchat/8IS5DCL-dR0wMjJk
Grade 4 https://t.me/joinchat/55dBfXx-MAI5ZGU0
Grade 5 https://t.me/joinchat/RUS_TOdoAXQzMjQ0
Grade 6 https://t.me/joinchat/o9Tj2X_42_I1MTA0
Grade 7 https://t.me/joinchat/PRaJodGrWVFiMWJk
Grade 8 https://t.me/joinchat/6_zLE-bV7fs1NzY0
Grade 9 https://t.me/joinchat/uVzhxr3HlJA4YWE0
Grade 10 https://t.me/joinchat/yH23QcV965RlNThk
Grade 11 https://t.me/joinchat/EuLpWQSAdEljZWY0
Grade 12 https://t.me/joinchat/yGNk78goGzg5ZTJk
እናመሰግናለን!
📩ለቪዥን አካዳሚ ወላጆችና ተማሪዎች📩
ዛሬ ሰኞ፥ መስከረም 7፥2016 ዓም የ2016 ት/ት ዘመን መጀመራችንን በታላቅ ደስታ እየገለጽን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት በሚመጡበት ወቅት
👔 የደንብ ልብስ /uniform/ አሟልተው መልበስ ይኖርባቸዋል፡፡
🏫 🕰 ትምህርት ከጠዋቱ 2 ሰአት ላይ ስለሚጀመር ቀደም ብለው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
💇♂ ወንድ ተማሪዎች እግረ ጠባብ ሱሪ /በተለምዶ እስኪኒ/፣ በተጨማሪ ፀጉርን አሳድጎ ወይም በዲዛይን ተቆርጦ መምጣት፣ እንዲሁም ጥፍርን አሳድጎ ወደ ትምህርት ቤት መምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡ ተማሪዎች በዚህ አይነት ሆነው ከመጡ ወዲያውኑ ወደ ቤት እንዲመለሱ ይደረጋል።
👩🦰 ሴት ተማሪዎች ፀጉርን መልቀቅ፤ አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል፤ ቀለም ወይም ሂና መቀባት፣ የጥፍር ቀለም መቀባት፤ ማንኛውም ጌጣጌጥ ማድረግ፣ ሱሪና የሰውነት ቅርፅ የሚያሳይ የደንብ ልብስ ማድረግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡
📵ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ይዞ ወደ ትምህርት ቤት መምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው፡፡
🦺👚 ምንም አይነት ልብስ ዩኒፎርም ላይ ደርቦ መልበስ የተከለከለ ነው።
🍱🥖በቁርስ እና ምሳ ሰአት ላይ ተማሪዎች የራሳቸውን ምግብ እና ውሃ ይዞ በመምጣት መመገብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ት/ት ቤቱ።
