cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

@Tewahdo27 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮች 🌠በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። መራግብራችን :-👇 ✅መዝሙሮች✅ የንስሐ መዝሙሮች✅ ያሬዳዊ ዜማ✅ የማርያም ውዳሴዎች✅ መፅሐፍ ሀይማኖት........ ወ.ዘ.ተ 🔵 YouTube 🔴ለሃሳብ እና አስታያየት @Tewahdo27

Show more
Advertising posts
3 535
Subscribers
-224 hours
+87 days
+1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#የግንቦት_ልደታ_በዓል_አከባበር በቤተ ክርስቲያናችን ትዉፊት መሰረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነዉ፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነዉ፣ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸዉ፡፡ እኛም ከእንደነዚህ ዓይነት አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረዉ እና ራሳችንን መልዕክቴ ነው፡፡ ለዚህም የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡
Show all...
🕊                  እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🕊  ልደታ ለማርያም ድንግል    🕊 🍒 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ † ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ: ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ:: † [ ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን: ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) ] የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን:: ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል:: እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: [ኢሳ.፩፥፱] ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ፳፻፳፪ [2,022] ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: "ሙሽራዬ ሆይ ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" [መኃልይ.፬፥፰] ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ [አሮን] የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ፵ [40] ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ፵ [40] ኛው ቀን ፪ [2] ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ :- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ፯ [7] ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: በ፯ [7] ኛው ቀን [ማለትም ነሐሴ ፯ (7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . . ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: [ቅዳሴ ማርያም] "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ." "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል [ያለ ጥፋት] ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." [መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ.፩፥፱] እመቤታችን ነሐሴ ፯ [ 7 ] ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: የእመቤታችን የዘር ሐረግ :- - አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ= - በእናቷ :- ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና:: - በአባቷ በኩል :- -ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል:: ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች:: የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን:: 🕊 [  † ግንቦት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም [ልደታ] ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቴክታና በጥሪቃ ፬. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ [የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት] [    †  ወርኀዊ በዓላት    ] ፩. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት ፪. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ ፫. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር " መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጧም ሰው ተወለደ:: እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: " [መዝ.፹፮፥፩-፮] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ] @ortodox_27          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...
#ልደታ_ለማርያም  (#ግንቦት_1) በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና። እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ። ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው። በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE   https://t.me/Ortodox_27 https://t.me/Ortodox_27 https://t.me/Ortodox_27
Show all...
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

@Tewahdo27 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮች 🌠በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። መራግብራችን :-👇 ✅መዝሙሮች✅ የንስሐ መዝሙሮች✅ ያሬዳዊ ዜማ✅ የማርያም ውዳሴዎች✅ መፅሐፍ ሀይማኖት........ ወ.ዘ.ተ 🔵 YouTube 🔴ለሃሳብ እና አስታያየት @Tewahdo27

✞ዮም ፍስሐ ኮነ✞ ዮም /ፍስሐ ኮነ/(፪) በእንተ ልደታ ለማርያም በባርነት ሳለን - - -  ፍስሐ ኮነ ኃጢአት በአለም ነግሳ - - - ፍስሐ ኮነ በድንግል መወለድ - - - ፍስሐ ኮነ ቀረልን አበሳ - - - ፍስሐ ኮነ እግዚአብሔር መረጠሸ - - - ፍስሐ ኮነ ልትሆኚው እናቱ - - -  ፍስሐ ኮነ ይኸው ተፈፀመ - - - ፍስሐ ኮነ የዳዊት ትንቢቱ - - - ፍስሐ ኮነ አዝ = = = = = የሰው ልጆች ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ የአዳም ሕይወት - - - ፍስሐ ኮነ የኢያቄም የሐና - - - ፍስሐ ኮነ ፍሬ በረከት - - - ፍስሐ ኮነ ምክንያተ ድኂን - - - ፍስሐ ኮነ ኪዳነምህረት - - - ፍስሐ ኮነ ድንግል ተወለደች - - - ፍስሐ ኮነ የጌታዬ እናት - - - ፍስሐ ኮነ አዝ = = = = = በሔዋን ምክንያት - - - ፍስሐ ኮነ ያጣነውን ሰላም - - - ፍስሐ ኮነ ዛሬ አገኘነው - - - ፍስሐ ኮነ በድንግል ማርያም - - - ፍስሐ ኮነ የምስራች እንበል - - - ፍስሐ ኮነ ሀዘናችን ይጥፋ - - - ፍስሐ ኮነ ተወልዳለችና - - - ፍስሐ ኮነ የዓለም ሁሉ ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ መዝሙር ፍቃዱ አማረ "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤"                  መዝ፹፮፥፩ ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @yamazemur_getemoche ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
Show all...
ሼር 💛
#ልደታ_ለማርያም  (#ግንቦት_1) በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና። እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ። ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው። በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE   https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido https://t.me/Ortodokstewahido
Show all...
ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነትና ሥነምግባር

ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። ይሁዳ 1÷3 ስለ ሃይማኖታችን ማንኛውንም ጥያቄ እናስተናግዳለን ተጫኑት @Thomas_Mekonnen ወጣቶች ሆይ እናንተ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ናችሁ። 🙏 ❤ወጣትነታችን ❤ለሃይማኖታችን❤

#ልደታ_ለማርያም  (#ግንቦት_1) በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና። እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ። ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው። በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት) ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE   https://t.me/Ortodox_27 https://t.me/Ortodox_27 https://t.me/Ortodox_27
Show all...
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹

@Tewahdo27 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮች 🌠በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው። መራግብራችን :-👇 ✅መዝሙሮች✅ የንስሐ መዝሙሮች✅ ያሬዳዊ ዜማ✅ የማርያም ውዳሴዎች✅ መፅሐፍ ሀይማኖት........ ወ.ዘ.ተ 🔵 YouTube 🔴ለሃሳብ እና አስታያየት @Tewahdo27

✞ ለልደትሽ ምስጋና ይገባል ✞ ለልደትሽ ምስጋና ይገባል ለዓለም መዳን ምክንያት ሆነሻል ልደትሽም የእኛም ልደት ነው ባ'ንች እኮ ነው ፀሐይ ያገኘነው[፪]      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► በሊባኖስ ሰማን አዲስ ዜና ንጽሕት ስር ተወልዳለችና የዓለም ስቃይ ሰቆቃ ሊያበቃ ተወለደች እንደ ፀሐይ ደምቃ      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ለዚህ ክብር ይገባል እልልታ በልደትሽ አይሆንም ዝምታ የአንቺ ልደት ለዓለም ደስታ ነው አንቺ ምስራቅ ልጅሽም ፀሐይ ነው      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ብርሃን ሆነ በሊባኖስ ዛሬ በልደትሽ በመላዕክት ዝማሬ አይቋረጥ ምስጋና ካ'ፋችን በሊባኖስ ይሰማ ዜማችን      አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸► ስለ ክብር ክብር አለን እኛ ከሊባኖስ ነይልን ወደኛ ከአብ ሕሊና ቀድሞዎን የታሰብሽ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት የሚልሽ             መዝሙር| ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem https://t.me/yemezmur_gexem ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
🧡 ሼር 🧡
ለልደትሽ ምስጋና ይገባል ለዓለም መዳን ምክንያት ሆነሻል ልደትሽም የእኛም ልደት ነው ባንች እኮ ነው ፀሐይ ያገኘነው እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ልደታ ለማርያም በአለ ልደት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ መልካም በአል ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE      🔸 @Z_TEWODROS 🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS      🔸 @Z_TEWODROS ✍️Comment @Channel_admin09
Show all...
#ለልደታ_ለማርያም እርሷን ድንግል ማርያምን ታኦዶኮስ እንደምንላት ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ደግሞ አብሲዳማኮስ እንለዋለን። ታኦዶኮስ ማለት ወላዲተ አምላክ በሥጋ ማለት ሲሆን አብሲዳማኮስ ማለት ደግሞ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ማለት ነው። @ortodox_27
Show all...
⛪️✍ የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር_ዘርን ባያስቀርልን :ኖሮ እንደ #ሰዶም_በሆን እንደ #ገሞራም_በመሰሌን ነበር (ኢሳ ፩÷፱)❤🙏❤ #እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች #ግንቦት (፩🕯)❤️ ልደታ ማርያም 🥀 #እመቤታችን_ተወለደች ማለት ጌታ ሊወለድ ፲፭ ዓመት ቀረው ፣ #የዘመኑ_ፍጻሜ_ደረሰ ማለት ነበር። እግዚአብሔር ሃና እና ኢያቄምን ሳይወልዱ ያዘገያቸውም ለዚህ ታላቅ ክብር እንዲበቁ ነበር። ክርስቶስ ፀሐይ ከሆነ የዛሬው ዕለት ሰማይዋ የተዘረጋችበት ዕለት ነው። #ክርስቶስ_የሕይወት_ውኃ ከሆነ ዛሬ ምንጯ የፈለቀችበት ዕለት ነው። ወንጌል በመጥምቁ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ይላል። #በእመቤታችን_መወለድ ምን ያህል ሰዎች ደስ ይላቸው ይሆን? #የእመቤታችን_ልደት በብዙ ሀገራት ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበራል። እኛም በሊባኖስ ተራሮች ( #አድባረ_ሊባኖስ) መወለዷን በማሰብ ከደጅ ወጥተን ቅድም አያቶቿ በጨረቃ ተመስላ በህልማቸው ያዩአትን የጨረቃችንን (#በግሪኩ_ሶልያና) ልደት ጨረቃን እያየን እናከብራለን #ተወለደች_ማርያም ❤ #ይጠብቃል ተስፋ አዳም ተጨናንቆ የሕይወት መገናኛ መሆንሽን አውቆ ብረሃኑ ተገልጦ ሞት በሰው #እንዲያቆም ድንግል ትመጣለች ትንቢቱ እንዲፈፀም ለሀና #ለኢያቄም ብቻ አይደለም ደስታው ለዓለሙ ሀሴት ነው የመገኛሽ ቦታው ዮም ፍሥሐ ኮነ ተወልዳ ማርያም አምላክን እንድናይ ከላይ #ከአርያም በህግ በትዕዛዝ ተገለጠች በዓለም ልደቷ ግሩም ነው ለዓለም የሚያበራ ሕይወቷም ስብከት ነው ጽድቅን የሚመራ #አንደበቴ አያውቅ ክብርን ለሰው ማውጋት ልቤም ቅኔ አይችል ያንቺን ገድል ማውራት ፍስሐ ወሀሴት ተወለደች ማርያም ጌታ የተናገረው ድህነት #እንዲፈፀም #ሰላም_ለኪ አምላክን የወደለድሽ በስጋም በነፍስም ድንግል የሆንሽ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢልን #ምህረትና ይቅርታ እናገኝ ዘንድ ለምኚልን •• ልደታ ማርያም በዕለተ ቀኗ ጨለማውን ብርሃን ሃዘናችንን በደስታ ትቀይርልን ወሩ ሰላምና ፍቅር የበዛበት ይሁንልን ረድኤት በረከቷ ይድረሰን 🤲 🤲 🤲 #አሜን......... 🧡 ......... #አሜን ⊹ #አሜን🙏³ @Ortodox_27
Show all...