cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የ ቃል ደብዳቤዎች💌

በዚህ ቻናል ላይ 👇 ደብዳቤዎችን💌 ወጎችን📃 ግጥሞችን📝 የተለያዩ መፅሐቶችን📚 ያገኛሉ፡፡ ሀሳብ, አስተያየት እንዲሁውም እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉት ደብዳቤ ካለ @Hebestina ይላኩልን፡፡ ቻናሉ ላይ እንለቃለን...

Show more
Advertising posts
500
Subscribers
No data24 hours
-47 days
-1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

00:36
Video unavailableShow in Telegram
ጠብቄሽ ነበረ በቲክቶክ አካዉንቴ @✍️dawit በ✍️dawit wegayew @betagitim
Show all...
00:26
Video unavailableShow in Telegram
🔥ተስፋ 🙏 በ ✍️dawit_wegayew ወዳጄ ያለ ተስፋ መኖር ባዶነት ነዉ።‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️ @betagitim
Show all...
መሄድ ከከጀልሽ ሂጂ በሩ ያው...ለህልምሽ ሳንካ ከሆንኩ....ያ ህልምሽ ካልሆንኩ ግድ የለም ሂጂ.... የኔ ለማለት ካልሞላው በወዳጆችሽ ፊት ልበ ሙሉነት ካልፈጠርኩ ካልፈለግሺኝ ግድ የለም ሂጂ ... ግን.... ስትሄጂ ቻው አትበይኝ አንቺን መጠበቅ ውስጥ ያለውን ደስታ እሱን ብቻ አትንጠቂኝ!           ©Adhanom Mitiku @yekaldebdabewoch
Show all...
00:38
Video unavailableShow in Telegram
🗣ነግሬሽ አልነበር‼️ @betagitim @betagitim
Show all...
00:39
Video unavailableShow in Telegram
Show all...
ዙፋን ሁነሽዋል የንግስናሽ ጸሃይ ሁነሽዋል በብርሃንሽ ድል በፍቅር አለም ለመኖሩ ካለ የሚጠራጠር አላዩም ማለት ነዉ አንቺ እኔ ላይ የከመርሺብኝን ፍቅር ከድልም ያልፋል ያንቺ ነገር በየቀኑ ምርኮ በየቀኑ መታሰር የልቤ ንግስናን ስትቆጣጣሪ በልቤ ሃገር ላይ እንደጸሃይ ስታበሪ የልቤ ንግስት አልኩሽ.... አየሽ እኔ እንዳንቺ አላኮርፍም ስስቅ ታጋሽ ቋሟ መለዋወጥን ማታቅ ሁነሽ ደሞ ሳገኝሽ ዳግም ሌላ ስም ላወጣልሽ አይ የኔ ስቃይ .....❤️ እጅግ የሚገርመዉ አንቺን ሳፈቅርሽ ጎላ ጎላ ሚሉ አይኖችሽ ለአይን ምያሳሳዉ ሞላ ያለ አካልሽ እንጆሪ ሚተፋ ሚመስለዉ ከንፈርሽ ቢማርከኝም.                  :ግን አይበልጥ አይወዳደር ካገኘዉት ካንቺ ዉስጥ ከልብሽ መንደር። ፈልገሽ ካጣሺኝ ከጠፋዉብሽ ምድር ላይ ቃል ስለጨረስኩልሽ ፍለጋ ወጣሁኝ ላንቺ የሚስማማ ቃል ሃጥያት ይሆንብኝ ይሆን ብፈልግ ከወንጌል😂❤️ ✍️dawit @betagitim @betagitim
Show all...
በጣም አሞኛል ለወትሮው የተለመደ ህመም ነበር ግን ይሄኛው ምነው ለየት አለ 💔
Show all...
እጄን ክንዴ አካባቢ የቆረጠኝን ወይ የሟጨረኝን ሳላውቀው ...እጄን ውሃ ሲነካው ብቻ ሲያንጣጣኝ የህመም ስሜት ተሰማኝ ። ከበስተ ጀርባ ነበር እና ብዙ ፈልጌ ሁላ ነው ህመሙ ከምን እንደሚመነጭ ያወኩት ። ..... የደማውን ቁስሌን እያየሁ ብዙ አሰብኩ ... ትላንቴን ወደ ኋላ ማየት ጀመርኩ ...ደርሶ እፍን የሚያደርገኝ እልህ ..ለምን እንደሁ ሳላውቀው ቁዝም የሚያደርገኝ ሁነት በምን እንደሁ ሳላስተውል ድብርር ብሎኝ የምውልበት ቀናት ሁላ ታሰበኝ ።ምን ሁነሻል ስባል ምንም ...ደህና ነሽ አወ ደህና ነኝ ..ችግር አለ ..ኧረ የለም ብየ የመለስኩባቸው ቀኖቼም አስታወስኩ ......ምን ወግቶኝ ነበር እንደዛ እና እንደነዛ አይነት ስሜት የተሰማኝ ..መናገር እስኪያቅተኝ ልቤን አፍኖ መተንፈስ የከበደብኝን ብዙ ብዙ ቀናቶቼን ዳሰስኩ ።ወደ ኋላ ወደ ትላንት መጓዝ ቢከብድም በትዝብት መነፀር ማየት ግን ፈለኩ ። .......ትላንት በኖርናቸው ኑረታችን የሚወዱንን ላለማስቀየም ይምንወዳቸውን ላለማጣት ስንል ችልን ማለፍን ዝምታን የመረጥንባቸው ቀናቶች ......ሰው ከሰው ሲኖር እኮ አይቶም ሰምቶም ያልፋል ለሚያልፍ ቀን ከመናገር ብለን ድንበራችንን ያላስከበርንበት ቀይ መስመራችንን ሲራመዱ በቃ ያላልንበት ....ብዙ ሁነቶች አሉን ። ............. ከበስተ ጀርባ የወጉን ያቆሰሉን ሰዎኛም እኛኛም የሆኑ ሁነቶች ከውስጣችን ተከማችተው በየት እና እንዴት እንደሚወጡ ሳናውቃቸው በሆነ ቅፅበት ግንፍል ብለው ሲወጡ ይታወቀናል ። መቼ እንደተመታነው የማናውቀው የውስጥ ስብራታችን በሆነ አጋጣሚ ለመነሳት እስኪያቅተን ያደቀናል ...ከበስተ ጀርባ የነበሩ የጥሩም የክፉም ድምሮች በዛሬ የቀን ፍትል ላይ ከውስጣችን ህመምን እናደምጣለን ። መቼ ነበር የተሰበርኩት? መቼ ነበር የወደኩት? የት ነበር ያነከስኩት? እንዴት ነበር የታመምኩት ?ምን ነበር ህመሜ? ብለን እንጠይቃለን ።<<በሰአቱ እና በጊዜው በቅጡ ታመን ያልዳነው ስብራት በቀናት ሂደት ስር ሰዶ ስቃይ ሆኖ እንደ ማብራት ቦግ እልም ሲል ብቻ ይታየናል>>። ....በትንሽ በትልቁ ክፍት ሲለን ደርሰን አልቃሻ ወይ ሳቂታ ሲያደርገን ምን ሆኔ ነው ብለን እንጠይቃለን ። የሚመለከተውም የማይመለከተውም ላይ ስናባርቅ ባለን በሌለንም ስንቆዝም ....... እንድህ እኮ አልነበርኩም ይችን እኔን አላውቃትም እስከማለት እንደርሳለን ። በወቅቱ ያላከምነው ህመማችን ሌላ እኛን ሰርቶ እንዳድስ አድስ እኔኔነትን ያስተዋውቀናል ። አንዳንዴም በበጎም በክፉም የፈገግንባቸውን ቀናት እናስባለን ትላንት ከትላንት በስቲያ ላይ ሆነን የቋጠርነውን የሳቅ ቋጠሮ ዛሬ ላይ እየመነዘርን .............. ለካ እንደዚህም ስቄ ነበር? ዳሩ እንድህም ተደስቼ ነበር? ....ብዙ የነበር ጉዞን ወደ ኋላ እንራመዳለን ። <<ከስተጀርባ ያሉ የማይታዩ ቢታዩም አይተን ያላስተዋልናቸው ወይ በያልፋል ብሂል የዋጥናቸው ብዙ ትላንቶች የታፈኑ ስሜቶቻችን ይገኛሉ ።>> <<በማወቅም ባለማወቅም ያኖርናቸው ጥሩም መጥፎም የታፈኑ ጩኸቶች በሰአቱ ያላነባንባቸው በወቅቱ ያልቦረቅንባቸው ...ብዙ ብዙ መውጣት ያለባቸው ስሜቶች መታከም ያለባቸው ስብራቶች መዳን ያለባቸው ቁስሎች አዝለን እንዞራለን ።>> ባለ መፈለግ የገፋናቸው መዋደዶች .... በግደለሽነት የተውናቸው ወዳጆች መቼ እና የት እንደተውናቸው ከምኔው እንደራቅናቸው በምን ቅፅበት እንደረሳናቸው ሳናስተውል አልፎ አልፎ የፀፀትም የመናፈቅም አይነት ስሜት ሲሰማን በአብሮነት የኖርነውን የሆነውን እንደ አድስ በትዝታ ...መስኮት እንታዘባለን ። የተገፋንባቸውንም የተጠላንባቸውንም ይሁን የወደቅንባቸውን ከማከም ይልቅ የደበቅናቸው ከመዳን ይልቅ በስቃይ ታስረን የቀርንባቸው ስንት እና ስንት ቁስሎች ይኖሩን ይሆን ? <<እንደ ቀልድ ብለን ከሌሎች ላይ የወረወርናቸው ቃላቶች ከሌለኛው ላይ አርፈው እስከ ምን እንዳቆሰሉት እስከ የት እንዳሰቃዩትስ በምን እናውቅ ይሆን ? ከበስተ ጀርባ ያሉ ያላየናቸው ያልሰማናቸው ያላስተዋልናቸው እልፍ ጩኸቶች ብዙ ስቃዩች አሉብን>> ። <<ለመናገር የሚያዳግቱ በመኖር ብቻ የምንደክምባቸው ለእኛ ብቻ የሚሰሙን ህመሞች ብዙም ናቸው ። ለማስረዳት በሚከብድ ልክ ውስጣችንን የሚያመሰቃቅሉ በምን እንደተነሱ ለምን እንደሚሰሙን እንኳ የማንረዳቸው የማናስረዳቸውም ብዙ የሚያንጣጡን ስሜቶች እንዳሉም አሰብኩ >>። ዛሬ ላይ እእ የሚያስብሉኝ ህመሞቼ ሁላ ከትላንት የቋጠርኳቸው የህመም ቋጠሮዎቼ እንደሆኑ አስተዋልኩ ። ከትላንት ከትናንት በስቲያም ማገገሚያው ምንድን ነው ????? ........ Hayat አንዳንዴ ነፍስ😑
Show all...
አንቺ በዚህ ትልቅ መድረክ በዚህ ግዙፍ አለም: ሳላውቀው ያወኩት እንዳንቺኮ የለም: የለም ከዳናዬ ኸረ የለም ከምናብ: የተውሶዬ ነሽ የምኞት እጣዬ የብርኮቴ ክታብ: ማያ መታያዬ ስጋት ሰቀቀን ነሽ እንዳጣሽ ማልሻ: ከዘፍጥረት ቁጥር ከስትንፋሳት ዋሻ: ሀ ለ እንዴት ነበረ ቃሉ የተሳለኩበት አስመርቆ የተፋኝ: ከጎንሽ መቆሜ ድክመት ፈጠረና ይኸው ስሜም ጠፋኝ: ማን ብትይ ማን ብለሽ ቆይ አቤት ምንድነው: የሚገርምሽ ነገር አቤት ስል ከሰማሽ አንቺን ሲጠሩ ነው: ከ ማስሬ በ ዉስጥ የደርሰኝ ግጥም @betagitim @betagitim
Show all...
መረሳት አያስፈራም ? በቃ መተው "ነበር" ማለት አያስፈራም ? እኩዮቻችን ቁም ነገርን ከ 2 ሠዓት በላይ መስማት ማውራት አለመቻላቸው አያስፈራም ? እንደቀልድ ህይወታችን ውስጥ መጥተው የነበሩ ሠዎች በመጥፎ ተለይተናቸውም ሳይሆን በቃ ጊዜ የለየን ሠዎችስ እነሱን መርሳት አያስፈራም ? በልጅነት አንብቤው እንደወደድኩት ግጥም ሠምቼ እንደተማረኩበት መዝሙር አሽትቼ እንዳልረሳሁት ጠረን በልቼ እንዳልጠገብኩት ምግብ የሆነ ጊዜ ላይ እጅህ ባዶ ሲሆን ጠረኑ ትዝታ ብቻ ሲሆን ምግቡ ርሀብ ብቻ መዝሙሩ ከሩቅ ብቻ መሆኑ እሱ አያስፈራም ? እኔ "ነገ" የሚያስፈራኝ " ትላንት " ስላለ ነው ፡፡ 🫶 @yekaldebdabewoch
Show all...