cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

ግጥም '''ስሜቶች ከተደበቁበት ወረቀት ላይ ሰፍረዉ እልፍ ትዝታዎች ከተበተኑበት ተሰብስበዉ የሚቀመጡበት የጸሃፊያን ሀሳብ ማረፊያ የአንባቢያን መጽናኛ ነች''። በዚ ቻናል @betagitim ግጥሞች🔥💌 ደብዳቤዎች✍️💌 ያገኛሉ። ሃሳብ እና አስተያየቶን በዚ 👇👇👇 ያናግሩን @dawit_wegayew

Show more
Advertising posts
1 112
Subscribers
-124 hours
+27 days
+2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ትዝታዬ ወርቁ ትዝታዬ እንቁ በትላንትና ህመም ታስሮ ከዛሬ መራቁ ወይን ሁኖ ጣሙ የጥንቱ ትዉስታ ዛሬን ሲበልጥብን ያለፈዉ ትዝታ ስንሸኘዉ ሳቃችንን ተራ ስናቀበል ሰንናፍቅ የሳለፍነዉን ሰርክ ስንብሰለሰል ዛሬ ኑረን ሳይሆን በነበርን ተዉጠን ለሞት ስንበቃ ጊዜ መች መልስ ሰጠን?። ✍️ዳዊት 4/11/2016 @betagitim @betagitim
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ፃድቅ አያደርግም፡ በገዳይ መቀደም ዝም በይ ያ'ቤል ደም! ደርሰሽ አትጩኺ፡ እንደተበደለ ለሁለት የጣሉት፡ ላንዱ እየታደለ ፍቅር መተማመን፡ በእጣ ከጎደለ የፉክክር ሜዳ፡ ከተደለደለ ከዚያ በኋላማ፡ ሞት በዘር አይደለ? ለሟች እና ገዳይ፡ ምን ይሰራል ድንበር መጮህ አስቀድሞ፡ የደረሱበት ጋር፡ ላለመድረስ ነበር። ፅጌሬዳ ቀንበጥ ፡ እሾኋ ሲወጋት ብትጮህ እሪ ብትል፡ ተካይ ምን ያድርጋት? እንዴት ትፀድቃለች? እሷ ብትለሰልስ፡ ሌላውን ባትጎዳ በዘሯ አይደለም ወይ ፡የመጣባት እዳ? ፃድቅ አያሰኝም በገዳይ መቀደም ደርሰሽ አትጩኺ፡ዝም በይ ያ'ቤል ደም እየበጠበጠ፡ ለጣለው ወላጁ አንዴ እንደ ብርሌ፡ ከተበጀ ልጁ ቢነቃም ባይነቃም፡ ለጠጅ የሚጋጭ ሟችም ያው ገዳይ ነው፡ አልቀናውም እንጂ። red-8 @betagitim @betagitim
Show all...
በፈገግታሽ ጸዳል - በጸደይ ገጽሽ ፊት - አግዝፎ ሊያፈካኝ፤ ዝንታለም ደብቆ - ሰውሮኝ የኖረ - ጨለማዬ ገፋኝ!! ገድልሽ ገደለ ፍቅር - ተጥበረበርኩልሽ - በብርሃንሽ ግፊት፤ ወትሮም አቅም የለኝ - የውበት ምልኪ ነው - ያስገኘኝ ካንቺ ፊት፤ እንግዲህ እንዳሻሽ - አንቺ እንዳፈቀደሽ - እንደ ልብሽ ሁኚ!! የክቴ ነሽና - የነፍሴን ንሸጣ - የልቤን ዝማሬ የምትታደኚ!! @ዘቢደር! @betagitim @betagitim
Show all...
ደብዳቤ ልኬልሽ ባታነቢዉ ራሱ ልነግርሽ ያሰብኩትን ላንቺ በቃላት ማድረሱ ከብዶኝ...ፅፌ የሰረዝኩት ድጋሚ ፅፌም ያጠፋዉት ጀምሮ እስኪያልቅ ቃላት ተሽቀዳድመዉ ቢቀመጡም አንዳቸዉም ናፍቆትና ፍቅሬን    በልክ አያመላክቱም ደብዳቤዉን ጽፌዉ ሳየዉ.... ልነግርሽ ያሰብኩት ከፃፍኩት ይበልጣል ቃል ላስፍር  ብል ቃል ከየት ይመጣል ምንም ብጽፍልሽ አንስቼ ወረቀት በቃላት ሰፍቼሽ ልቤን አልችልም ማስደሰት። ✍️ዳዊት @betagitim @betagitim
Show all...
ነግሬሽ ነበረ... (በላይ በቀለ ወያ) . . ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል ነግሬሽ ነበረ፡፡ ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል ምን ተራራ ቢያህል... ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡ ነግሬሽ ነበረ ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡ ነግሬሽ ነበረ የናትነት ስሟ ፣ ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡ ነግሬሽ ነበረ አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ ልክ ነሽ አንዳንዴ እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡ @astawesegnregasa @betagitimነግሬሽ ነበረ... (በላይ በቀለ ወያ) . . ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል ነግሬሽ ነበረ፡፡ ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል ምን ተራራ ቢያህል... ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡ ነግሬሽ ነበረ ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡ ነግሬሽ ነበረ የናትነት ስሟ ፣ ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡ ነግሬሽ ነበረ አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ ልክ ነሽ አንዳንዴ እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡ @betagitim @betagitim
Show all...
6👍 1
#ህልሜ_የአንድ_ቀን_ነች💔 ሰማይን ብጠጋ ጨረቃን ብቃኛት ሕልሜን ስኖር ኮከብ ስመለከት ያለዉ አንድ ዜማ       ያለሺዉም አንቺ የሞላሺዉም አንቺ የቱ ጋር ልሁና ....ልጠብቅሽ የቱ ጋር ትረጊያለሽ እንደ ንብ ሁሉንም ለምን ትቀስሚያለሽ የትም ከተገኘሽ የትም ትቀሪያለሽ ከሁሉም ብትቀስሚ ከሁሉም ብቶኚም ከአንዱም ልብ የለሽ አትገኚም ያንቺ ነገር   በአንድ ቀን ጀምሮ  ህይወትሽ ያበቃል   ሰዉ ሲበርደዉ ደራርቦ ሲሞቀዉ ያወልቃል ገላ ከገላ ተሰቃቅሎ ሞቆ ያንቺ ነገር እንግዲህ ...ያበቃል      በአንድ ቀን ጀምሮ በአንድ ቀን አልቆ በለስ ቀናኝ ብዬ ህልሜን እያስፈታዉ የህልሜ ሴት... የአንድ ቀን ሁና ፍቅሯን እንደተመኘዉ አጣዉ። 💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔 ✍️ዳዊት 🌬🌬🌬🌬🌬___🌬🌬🌬🌬🌬🌬 @betagitim @betagitim @betagitim
Show all...
1
ሲጋራ አጨሳለዉ ላንቺ ስል ላንቺ ስል በጭሱ መሀከል አገኝሽ ይመስል ብሎ ቢል አጫሹ እኔ ጠጪ ደግሞ መጠጥ እጠጣለዉ ላንቺ ስል ላንቺ ስል አልኮል እጋታለዉ ላንቺ ስል ላንቺ ስል ሌሊት ሲያስመልሰኝ ከአንጀቴ አዉጥቼ እጥልሽ ይመስል። @betagitim @betagitim
Show all...
😁 5👍 2
#ሰማዩ_ያንቺ_ነዉ ሰማይ ክራር ሁኖኝ የትዝታ ቅኝት የልቤን መስመር ተስፋዉን ለማየት የልቤን ዜማ ስልተ ምቱን ስዉር ፈቺ ቅኔ ቤቱን ስቃኘዉ ሚታየኝ ጭራሽ ሳላስብሽ ስማዩን ሳይ ሚታየኝ ያ መልክሽ ቀና ዋልኩኝ ብዬ ለማመስገን ቀና ስል ሰማዩ ተዉቧል ባንቺ ገፀ ምስል ኪዳን ኑሮበት ሲማስን አይኔ ቀና እያለ ፊትሽ ያይና ንጋትን ከሌት ለሱ ተመሳሰለ ፍቅር... የተጻፈለት ..የተባለለት ሁሉ አንዱም መች ገለጸዉ የቀንን ብረሃን ወደ ሌት የቀየረዉ ደሞም ሲመጻደቅ መች ደርሰዉ ይልና ልብ ና አፍ አራርቆ ሲኦል ሲልክ ነፍስን ነጥቆ ሲያሻዉ የከንፈር ድግስ አስድግሶ ጽዋ አርጎ ገነት ሲጥል አመንኩሶ ወደ እሷ በሚል መንፈስ በመስቀል ተመቶ በጸበል አያስፈዉስ በአላ በረቢ በዱዓ በእጣን የማይለቅ ፍቅር ማለት ሰይጣን ፍቅር ቃሉን ትርጉሙን ሰዉሮ በቁም ያለ ሰዉን ያሳያል ልብ ዉስጥ ቀብሮ ነፍስን ጠፍሮ አስሮ ይከርምና ቃላት ይለግሳል ስለ እርሱ ለሚያጠና በእንቺነትሽ በኩል በእኔነቴ ግድም ተሰምሮ አልተቀመጠም የፍቅር ትርጉም አለም ፍቅርን በሺህ ትርጉም ቢገልፀዉ እኔ ግን ምገልጸዉ ሰማዩ አንቺን ሲያሳየኝ ነዉ። ✍️ዳዊት ✌️ @betagitim @betagitim @betagitim
Show all...
👍 2 2
.. አልታረቅነም ታርቀናል ፡ከራሳችን ጠፍተን ከደላሎች ገብያ ተጥለናል ፡ለቃል ገብያ ተደላድለናል ፡በቃል ገብያ ሀብታም  ሁነናል ፡በምላስ  ብቻ ከልብ ባልሆነ ሀሳብ ገምተናል ፡፡የሀሰትን  ጭቅቅት ፡በተረት አለቅልቀን ተግተናል፡፡...    ✍መንገደኛው ባለቅኔ        ከድር ሰተቴ❤️ 📚 @betagitim @betagitim
Show all...
4
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.