cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Eyerusalem (Jerri) Negiya official channel

" ምላሴ ጽድቅህን ሁልጊዜም ምስጋናህን ይናገራል።" (መዝሙረ ዳዊት 35:28) ይሄ የዘማሪት ኢየሩሳሌም ነጊያ telegram channel ነው። በዚህ ቻናል ፣ ነባርና አዳዲስ፣ እንዲሁም አልበም ላይ ያልተካተቱ ዝማሬዎቼን፣ ጽሑፎቼን ያገኛሉ። በተጨማሪም ከታች ባለው ሊንክ አዳዲስ ቪዲዮዎ ያገኛሉ https://www.youtube.com/channel/UCfDm9KT5NCiY9X_scwSqP_A

Show more
Advertising posts
1 243
Subscribers
+224 hours
+107 days
+2630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
አወይ ዘመን Awey Zemen 2024 Eyerusalem Negiya (Jerri) Official music video

ይህ ዝማሬ በዘመን ፍፃሜ እንደሚኖር ሰው ስለዘመኑ የተረዳሁትንና የሚሰማኝል ሀሳብ ጠቅለል አድርጌ ያቀረብኩበት ዝማሬ ነው:: ~መፅሐፍ እንደሚናገር ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን። ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና። በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን። ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ። ተሰ 4:13-18 #ኢየሱስይመጣል #ማራናታ #Maranata #jesusiscomingsoon #christianmusic #2024 #newgosplemusicvideo ግጥምና ዜማ እየሩሳሌም ነጊያ 08/06/2015 Etc ዘመኑም እንደሰዉ ትላንቱን ናፈቀ ማብቂያው እንደደረሰ በድኑም አወቀ ቀንና ወራቱ ዘመንና ዓመታት ሊሻር በዘላለም ቀን ሲቀረው ጥቂት ተጣደፈ ሁሉ በዛ ትርምሱ በላይ በላዩ ላይ ፋታ እየነሱ ሀዘንና ደስታ ነጭና ጥቁሩ ሲፈራረቁበት ጥላና ሀሩሩ አወይ ዘመን አወይ ጊዜ አዚም ጥሎ ድንዛዜ ማብቂያውን አውቆ ሲያዘናጋን ላኑር ብሎ እያባበለ 1 መርቅዞ ድኖ አቁስሎ አክሞ በርቶ እየጠፋ አግዞ አድክሞ መላቅጥ አጥቶ ሲያደናግረን ይህ ነው ሰንለው ወዲያ ሲጥለን መጣ ስንለው ደግሞ ይሄዳል አረፍን ባልን ፋታ ይነሳናል! አወይ ዘመን አወይ ጊዜ እንዳናልፈው በትካዜ አሳስበን ከፍቶ ከዚያ ምን ሊበጀው ከዚህ ወዲያ 2 እንባ ሳይደርቅ እልል ሲያስብለን ጮቤ አስረግጦ ደረት ሲያስደቃን ቅርቡን አርቆ ሲያኖረን ማዶ እውነት በሀሰት ሙላት በባዶ ግርምት በፍዘት ተገላቢጦሽ የማይጨበጥ ማብራሪያ የለሽ! አወይ ጊዜ አወይ ዘመን ሰው ታውሮ ቀን ሲዘምን በድን ቆሞ ፍጡር ሲዘምም ግዑዝ ድኖ ነፍስ ሲታመም 3 ፃድቅ ታፍኖ ሀጥህ ሲለፍፍ ጠቢቡ ቆሞ ሰነፉ ሲያልፍ ታታሪው በርዶት ቀማኛ ሲሞቅ ነውር አደባባይ ሜዳ ላይ ሲደምቅ ግርምት በፍዘት ተገላቢጦሽ የማይጨበጥ ማብራሪያ የለሽ! አወይ ዘመን አወይ ጊዜ እንዳናልፈው በትካዜ አሳስበን ከፍቶ ከዚያ ምን ሊበጀው ከዚህ ወዲያ 4 በዓመፃ ብዛት ፍቅር ቀዝቅዞ ራስን በመውደድ ሰዉ ነውዞ በእኔነት ገመድ ነፍሱ ተይዞ በእንቶ ፈንቶ አእምሮ ደንዝዞ ስል ሰሚ ጆሮ ዳባ ሲለብስ በመንታ ምላስ ሀገር ሲታመስ አወይ ዘመን አወይ ጊዜ እንዳናልፈው በትካዜ አሳስበን ከፍቶ ከዚያ ልብ አንጥልም ከዚህ ወዲያ::

14👍 4🥰 2🤩 1
15 ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። 16 እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
Show all...
16🙏 3
15 ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም። 16 እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።
Show all...
ሰላም ለእናንተይሁን የቴሌግራም ቤተስቦቼ🥰 ጌታ ፀጋ አብዝቶልኝ ና በር ከፍቶልኝ ቶሮንቶ ውስጥ ትልቅ በሚባል የነጮች ቤ/ክን ውስጥ አንድ የራሴንና አንድ እንግሊዝኛ መዝሙር ዘምሬለው ከ1;10 (አንድ ሰዐት ከ10 ደቂቃ) በኃላ ታገኙታላቹ በዚህች ቤ/ክን ሳገለገል ለሶስተኛ ጊዜ ቢሆንም በዚህ ትልቅ ኮንፍራንስ ላይ ማገልገል የመጀመሪያዬ ነው የሁሉ ነገር- ዝግጅት ቅንጅት -ብቃት -መሰጠታቸው አጀብ ያሰኛል 😲እንደዚህ አይነት አቅም በምድሬ ኢትዮጵያውያ ቤ/ክን መድረክ ላይ ማየት እናፍቃለው 🙌🏻እኔና ቤተሰቤ ወደ እራሳችን ቤት እስክንገባ ድረስ ሁሉ ነገር በተሟላበት በዚህች ቤ/ክን ቤት ውስጥ ጥቂት ከተለያየ ሀገር ከመጡ ሰዎች ጋር እንኖራለን እግዚአብሄር በመንገዳችን ሁሉ እየረዳን በ4 ውስጥ ነገሮች ተከናውኖልና ይህች ቤተክርስቲያን ለምድሪቱ በረከት ብቻ ሳትሆን ለስደተኞችም ጭምር በረከት ናት ስለዚህች ቤ/ክንና አግልግሎቷ እግዚአብሔር ይባርካት🙌🏻🙌🏻🙌🏻
Show all...
🥰 17 14👏 4🙏 1
Pls watch after 1:10 minutes later 😉
Show all...
Show all...
GMC 2024 Worship Night Livestream

JOIN OUR LIVE ONLINE WORSHIP EXPERIENCE:

https://tpctoronto.online.church/

6🥰 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.