ሰም እና ወርቅ
Open in Telegram
ሀሳብን በብዕር!! . .. ... ለሙገሳ ለወቀሳ ቢፈልጉ ለከሰሳ ካስፈለግም ለሽልማት አልሆን ካለ ለውግራት ካሻወትም በርቱ ማለት (ደና ነገር እንደሰራ ሰው ምን የሚያስሞግስ ነገር አለ?) ማለቴ በቃ ከፈለጋቹ ይኸው @Eliyashabesha123 @Mypoint010
Show more626
Subscribers
-124 hours
-27 days
-430 days
Posts Archive
626
እልፍ ህፃናት ያለዕድሜያቸው ተደፈሩ ህጋችንም እንደልማዱ እያሰረ መልቀቅ ለመደ..... የማይቀይር የማያስተምር ህግ!!!!
.
በህፃን ሄቨን ላይ የደረሰው ነገር በጣም አሰቃቂ እና አስነዋሪ ተግባር ነው አንድ ማሰቢያ አይምሮ ከተሰጠው ሰው የማይጠበቅ ተግባር ነው አረመኔው ወንጀለኛ የፈፀመባት።
.
.
ካሁን በውኋላ በሌላው እንዳይደገም ጠንከር ያለ እርምጃ በወንጀለኛው ላይ መወሰድ አለበት።
626
ፊርማ እና ድጋፍ እየተሰበሰበ ነው ለህፃን ሄቨን እንሳተፍ
Sign the petition
https://chng.it/22TWwGtXgG
Justice for Heven ⚖️🥹
626
በዛሬው እለት ፍፃሜውን ባገኘው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ክብሯን የሚመጥን ውጤት አላመጣችም ታዲያ ተጠያቂው ማነው ስንል ልንወያይ ወደድን መሳተፍ የምትፈልጉ ገባ ገባ በሉ.....።
626
እንደ ጉልባን በዐል፤ እንደ ቂጣ በዐል፤
የጥድፍ የጥድፍ ሆነና ኑሯችን፣
ትናንት የመረቅነው፤ ጠዋት የከፈትነው፤
ማታ ላይ ይናዳል አቤት ውርደታችን።
ከ፦ካሌብ
626
ተስፋ እንደሰው ጨካኝ አይለም!
.
ተስፋ እንደሰው
ጨካኝ አይደል
ክፉም አይደል፥
ያሳያል አድማስን ዛሬን አሳልፎ
ያደርሳል ከምኞት ከውድቀት ደግፎ
ከግርግር ትቢያ መሀል
ከውድቅዳቂ... አካል
በተስፋ፥እስትንፋስ ይፀናል
መኖር ዳግም ይፀድቃል
ፅልመት በወጋገን ይገፈፋል
ለመሮጥ መንፏቀቅ ይጀመራል
ከዛ.... ያልፋል!
የኔ ብጤው እማ!
ምላሱ ስል ነው መች ይሰንፋል
ብቅ ያለን ሁሉ ይሰይፋል
«አይሳካም አይሆንም» ይላል
ፍም እሳት ላይ ውሀ ይከልሳል
.. ሰርክ ቢማልድ ቢያመሽ ያቅሙን ያህል እያወራ
.. ተስፋ እንደሰው አይደል ያማረ ነገ ላይ ድሩን አያደራ።
...
#ኢልያስ #ሀበሻ
.
https://t.me/Eliyaskedir
https://t.me/Eliyaskedir
626
ሄድን.........መሄድ አስበን፣
ይሻለናል ብለን፣
ቀስቃሽ የሌለበት እረፍት የመሰለን፣
እንዴት ተጃጃልን።
ላላወቅነው አለም፣ ላላወቅነው ቅዠት፣
በገዛ እጆቻችን ራስን መሰዋት፣
ትልቁ ቂልነት።
አንሂድ ይቅርብን!
ከ፦ካሌብ
626
ሮጥን ሮጥን ሮጥን ሮጥን፣
ከማን አመለጥን?
እኛው አባራሪ እኛው ተባራሪ፣
እኛው አለቃቃሽ ዘራፍ ባይ ፎካሪ።
በርግጥ ከሰው ሸሸን፣
ሄድን ተገንጥለን፣
ሰው ፣ ቀዬ ስንቀይር ብንቀየር ብለን።
ነገር ግን አልሰራም አልሸሸም ቅላችን፣
ከራስ እንዴት እንሽሽ......አቤት መከራችን።
ከ፦ካሌብ
626
አሰረኝ ጠፍንጎ ላይፈታልኝ ምሎ፣
ፅልመት በወረሰው ከባዶ ቤት ሰቅሎ።
እኔ ላይ ጨከነ ዛተ ሊያስጨንቀኝ፣
በዛቻም አልቀረም ጀመር ያሳቅቀኝ።
መዝገብን ዘረጋ ተገለፀ ገፁ፣
ዝብርቅርቁ ወቷል ይታያል ህፀፁ።
" ሕይወትህ ነው" አለኝ፣
ገፁን እያሳየኝ፣
መልስ አጣው ጨነቀኝ፣
እውነት ነው? ውሸት ነው?
እውነት እንደሆነ መቀበል ከበደኝ።
ነገር ግን እውነት ነው።
መዝገቡ..........
ሕይወቴን ነው የሚመስለው።
ከ፦ካሌብ
