en
Feedback
Azam Media

Azam Media

Open in Telegram

"እንኳን ወደ አዛም ሚዲያ ቻናላችን በደህና መጡ፣ የአዳዲስ ዜናዎች፣ ማስታወቂያዎች እና የመዝናኛ ይዘቶች መዳረሻ! ወቅታዊ ሁነቶችን፣  ባህልን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በሚሸፍኑ ጽሁፎች፣ ቪዲዮዎች እና ምስሎች በተመረጡ መረጃዎች ይዝናኑ። ቴክኖሎጂ ፣የአኗኗር ዘይቤ እና ሌሎችም የኛን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።  ይቀላቀሉ ለመረጃ ጥቆማ 👉@jach17

Show more
810
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
#አዛም_መረጃ የ1 አመት ከ5 ወሩ ጋናዊ ህጻን የአለም በእድሜ ትንሹ ሰአሊ በመሆን በሪከርድነት ተመዘገበ ሊያም አንክራህ የተባለው ታዳጊ በጋና ዋና ከተማ አክራ ነዋሪ ነው፡፡ ወላጅ እናቱ ቻንትሌ ኩ
#አዛም_መረጃ የ1 አመት ከ5 ወሩ ጋናዊ ህጻን የአለም በእድሜ ትንሹ ሰአሊ በመሆን በሪከርድነት ተመዘገበ    ሊያም አንክራህ የተባለው ታዳጊ በጋና ዋና ከተማ አክራ ነዋሪ ነው፡፡ ወላጅ እናቱ ቻንትሌ ኩኩዋ ኤግሃን ሰአሊ እና ‘’አርትስ ኤንድ ኮክቴል’’ የተባለ የስዕል ስቱድዮ ባለቤት ነች፡፡     ልጇ ሊያም የስዕል ተሰጥኦ እንዳለው የተረዳችበትን ሁኔታ ስታስረዳ፤ ገና የ6 ወር ጨቅላ እያለ የስዕል ስራዎቿ ላይ ለማተኮር በሚል ጨርቅ ዘርግታ በቀለም እንዲጫወት ሰጠችው፤ ከዛም በእጆቹ መዳፎች የፈጠራቸው መስመሮች የተጠቀማቸው የቀለም ውህደቶች የስዕል ችሎታ ሊኖረው እንደሚችል እንድታሰብ እንዳደረጋት ትናገራለች፡፡     ይህን የመጀመርያ የሊያም ስዕል ‘’ክሮውል’’ ወይም ‘’መዳህ’’ የሚል ስያሜ ወጥቶለት በስዕል ስቱድዮዋ ውስጥ ይገኛል ብላለች::  ©Alain

#አዛም_መፅሐፍ የደራሲና ገጣሚ ምግባር ሲራጅ “እየዳነ ሄደ” መጽሐፍ ነገ አርብ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።በምርቃት ሥነሥር
#አዛም_መፅሐፍ የደራሲና ገጣሚ ምግባር ሲራጅ “እየዳነ ሄደ” መጽሐፍ ነገ አርብ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጻሕፍት ውስጥ ይመረቃል።በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ልዩ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች የሥነጽሑፍ  ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።

#አዛም_ድንቃድንቅ አሜሪካዊቷ ዲያን አርምስትሮንግ ለ27 ዓመታት ጥፍሮቿን ባለመቁረጥ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ገብታለች ለመጨረሻ ጊዜ የተከረከመቻቸው በ 1997 ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጥፍሮቿ 1
#አዛም_ድንቃድንቅ አሜሪካዊቷ ዲያን አርምስትሮንግ ለ27 ዓመታት ጥፍሮቿን ባለመቁረጥ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ገብታለች ለመጨረሻ ጊዜ የተከረከመቻቸው በ 1997 ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ   ጥፍሮቿ 1.3 ሜትር አድገዋል ጊነስ ከተመዘገበች ገባች በኋላ፣ ብዙ ሰዎች የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዴት እንደምትወጣ ለማወቅ ፍላጎት ነበራቸው።  ዲያና ረዣዥም ጥፍሮቿን እንደለመደች እና እንደ ወለል መጥረግ እና እቃ ማጠብ ካሉ የቤት ውስጥ ሥራዎች ጋር መላመድ መቻሏን ተናግራለች።  "መጸዳጃ ቤት ስሄድ ልክ እንደሌላው ሰው ነው የሚመስለው" ስትል አክላለች።

ፀሀፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 21 201
ፀሀፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ የክብር የእንግዳ የሆነበት አንጋፋው የኪነጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነጥበብ መርሃግብር ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 21 2016 ዓ.ም ይካሄዳል። በፕሮግራሙ ፀሐፊ ተውኔት ውድነህ ክፍሌ "የአንድ ግጥም፣ የአንድ ወግ" የክብር እንግዳ ሆኖ  ይገኛል። እንዲሁም ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ብለዋል አዘጋጆቹ። ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው።

#አዛም_ሙዚቃ ድምፃዊ ወንዲ ማክ አልበም ማጠናቀቁን አስታወቀ ድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) በይፋዊዉ የማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳለው በአዲስ አልበም መምጣቱን ገልፆል:: ወን
#አዛም_ሙዚቃ ድምፃዊ ወንዲ ማክ አልበም ማጠናቀቁን አስታወቀ ድምፃዊ ወንደሰን መኮንን በመድረክ ስሙ (ወንዲ ማክ) በይፋዊዉ የማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳለው በአዲስ አልበም  መምጣቱን ገልፆል:: ወንዲ ማክ "ፈጣሪ ፈቅዶ እነሆ በአዲስ ዐልበም መጥተናል በቅርብ ቀን ይጠብቁን" ብሎ ቢገልፅም መች አዲስ አልበሙ እንደሚወጣ በግልፅ አልተናገረም:: ድምፃዊዉ ከዚህ ቀደም በሰራቸው "ሺ ሰማንያ" "ታገቢኛለሽ ወይ?"  "አባ ዳማ"  "ገዳይ" ን ጨምሮ በተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎቹ ተወዳጅነትን አግኝቷል:: መረጃው የኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ነው

#አዛም_መረጃ የዘንድሮው የ"ለዛ ሽልማት" ተሸላሚዎች ዝርዝር 1.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ፊልም ☑️ ዶቃ ፊልም 2.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ ☑️ አርቲስት ግሩም ዘነበ (በዶቃ ፊልም)
#አዛም_መረጃ የዘንድሮው የ"ለዛ ሽልማት" ተሸላሚዎች ዝርዝር 1.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ፊልም ☑️ ዶቃ ፊልም  2.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ ☑️ አርቲስት ግሩም ዘነበ (በዶቃ ፊልም) 3.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት ☑️ አርቲስት መስከረም አበራ (የሱፍ አበባ ፊልም) 4.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ☑️ በስንቱ  5.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ ☑️ አርቲስት አለማየሁ ታደሰ (በስንቱ ) 6.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት ☑️ አርቲስት መስከረም አበራ (በስንቱ ) 7.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ አልበም ☑️የግርማ ተፈራ ካሣ " ግን የት ሀገር ?" አልበም 8.የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ) ☑️ ወግዳይት (አሳላፊ አልበም) 9.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን ☑️የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ "ናዕት"  ዘፈን 10.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ዘፈን ☑️የድምጻዊት ሔዋን ገ/ወልድ "ሸሙና"   11.የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ ☑️የድምጻዊት ራሔል ጌቱ "ኢትዮጵያዬ" 12.የለዛ ሽልማት የህይወት ዘመን ዘርፍ ተሸላሚ ☑️ አንጋፋው ድምጻዊ ንዋይ ደበበ © event addis

የ13ኛው የ"ለዛ ሽልማት" ሥርሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል በሸገር 102.1 በሚተላለፍ "ለዛ" የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅነት የሚከናወነው "ለዛ ሽልማት"ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም አ
የ13ኛው የ"ለዛ ሽልማት" ሥርሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል በሸገር 102.1 በሚተላለፍ "ለዛ" የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጅነት የሚከናወነው "ለዛ ሽልማት"ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም አመሸሻ ላይ በሒልተን ሆቴል ውስጥ ይከናወናል። ከሐምሌ 1 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 2015 ዓ.ም ድረስ በተሰሩ የጥበብ ስራዎች የታጩ የጥበብ ባለሞያዎች በ12 ዘርፎች ይሸለማሉ። 1.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ፊልም 2.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ 3.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ተዋናይት 4.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም 5.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይ 6.የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ፊልም ተዋናይት 7.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ አልበም 8.የአልያስ መልካ ሽልማት (ምርጥ አዲስ ድምጻዊ) 9.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዘፈን 10.የለዛ ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ዘፈን 11.የዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪዲዮ 12.የለዛ ሽልማት የህይወት ዘመን ዘርፍ የለዛ ሽልማት በቀጥታ ስርጭት በዓባይ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሁሉም የዓባይ ቲቪ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ( በፌስቡክ፣ ዩትዩብ፣ ቲክቶክ፣ ኢንስታግራም) ይሰራጫል ተብሏል።

#አዛም_ሙዚቃ የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ይለያል "የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ አርብ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል። የሙዚቃው ግጥም የወንድሰን ይሁብ ሲሆን ዜማው በ
#አዛም_ሙዚቃ የድምጻዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል "ይለያል "የተሰኘ የሙዚቃ ቪዲዮ ዛሬ አርብ ግንቦት 16 2016 ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ በኩል ይለቀቃል። የሙዚቃው ግጥም የወንድሰን ይሁብ ሲሆን ዜማው በብስራት ሱራፌል ተሰርቷል። የሙዚቃ ቪዲዮው ዳይሬክተር ወንድሰን ይሁብ ነው። ለምለም ኃ/ሚካኤል ባሳለፍነው ሳምንት "ማያዬ" የተሰኘ አልበም ለአድማጮች ማድረሷ ይታወሳል።

#አዛም_መፅሐፍ በዛጎል የመጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው “ነገረ መጻሕፍት” የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት በገጣሚ እና ደራሲ ታገል ሰይፉ “ዝንቡላ
#አዛም_መፅሐፍ በዛጎል የመጻሕፍት ባንክ የሚዘጋጀው “ነገረ መጻሕፍት” የመጽሐፍ ውይይት የፊታችን ቅዳሜ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ይካሄዳል። በዚህ ሳምንት በገጣሚ እና ደራሲ ታገል ሰይፉ “ዝንቡላ እና ካሮት“በተሰኘው መጽሐፉ ላይ  ውይይት ይካሄዳል። የዕለቱ አወያይ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። ይህ መርሐግብር ቅዳሜ ግንቦት 17 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 እስከ 10:30 ይካሄዳል።

#አዛም_ጥቆማ የአባቶች ቀን ልዩ ውድድር ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ አባቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ልጆች ለአባታቸው ያላቸውን ክብርና ምስጋና በምን መልኩ እንደሚገልፁ
+1
#አዛም_ጥቆማ የአባቶች ቀን ልዩ ውድድር ዘንድሮ በኢትዮጵያ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ አባቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ልጆች ለአባታቸው ያላቸውን ክብርና ምስጋና በምን መልኩ እንደሚገልፁ የሚያሳይ አጭር ቪዲዮ በመቅረጽ የሚካሄድ ነው። ምስሎቹ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በሚያገኙት የእይታና የላይክ መጠን ተመርጠው 1ኛ - ለሚወጣ የምስክር ወረቀት፣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡ 2ኛ - ለሚወጣ ጋቢና ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ፡፡ እንዲሁም 3ኛ ለሚወጣ ከውዱ አባብዬ ጋር በዮድ አቢሲኒያ ልዩ የምሳ ግብዣ ላይ የሚታደሙ ይታደማሉ። ተወዳዳሪዎች ቪዲዮዎቻቸውን ከታች በሚገኘው በኢትዮጵያ አባቶች ቀን በጎ አድራጎት ድርጅት ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ መልዕክት መላኪያ ላይ ያስቀመጡ። https://www.facebook.com/profile.php?id=100064190287928&mibextid=ZbWKwL ፕሮግራሙ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በዮድ አቢሲያ የባህል አዳራሽ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይከናወናል።

#አዛም_ቴክኖሎጂ በሞት ያጣናውን ሰው የሚያገናኘው መተግበሪያ "ዳድ ቦት" በሞት ያጣናቸውን  ሰዎች በህይወት ያሉ ያክል በድምጽና ፎቶግራፍ የሚያገናኝ ነው፡፡ መተግበሪያው የሚወዱትን ሰው በሞት የመለየት የህመም ስሜትን ይቀንሳል ተብሎለታል፡፡ በሰው ሰልሽ መንገድ ሟችን ወደ ሕይወት የመመለስ መሰል ተግባራት በልብ-ወለዱ ዓለም ለረጅም ጊዜ ሲሞከር የቆየ ነው፡፡ የሰው ሰልሽ አስተውህሎት መስፋፋትና መዘመን ጋር ተያይዞ ከልብ ወለድነት በዘለለ በገሃዱ ዓለም እንዲሆን እያደረገው ነው፡፡

#አዛም_ኪነጥበብ ሮፍናን የክብር እንግዳ ሆኖ የሚገኝበት አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል! በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ሃያ አራተኛ ም
#አዛም_ኪነጥበብ ሮፍናን የክብር እንግዳ ሆኖ የሚገኝበት አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዛሬ ይካሄዳል! በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ሃያ አራተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት ረቡዕ ግንቦት 14/2016 ዓ.ም ያካሂዳል። በዕለቱም ዝነኛው #ሮፍናን የክብር እንግዳችን ሆኖ በመካከላችን ይገኛል። እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ለእናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ተሰናድተው ይጠብቃችኃል  ። ሟር ያድርጉ ! #ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።

#አዛም_መፅሐፍ የዓለማየሁ ደመቀ "ዮቶር 2" መጽሐፍ ለንባብ በቃ የደራሲ ዓለማየሁ ደመቀ " ዮቶር 2" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ግንቦት 12 2016 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል። በ207 ገፆች የተቀነበበው
#አዛም_መፅሐፍ የዓለማየሁ ደመቀ "ዮቶር 2" መጽሐፍ ለንባብ በቃ የደራሲ ዓለማየሁ ደመቀ " ዮቶር 2" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ  ግንቦት 12 2016 ዓ.ም ለንባብ በቅቷል። በ207 ገፆች የተቀነበበው መጽሐፉ በ450 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል። መጽሐፉ ጃፋር መጻሕፍት መደብርን ጨምሮ በተለያዩ መጻሕፍት መደብሮች ይገኛል። ከዚህ ቀደም በደራሲ አለማየሁ ደመቀ የተጻፈው "ዮቶር ኮባላይ ካህን" 14ተኛ ዕትም መጽሐፍ በድጋሚ ለአንባቢያን መቅረቡ ይታወሳል።

#አዛም_ሙዚቃ የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ሶስተኛው አዲስ አልበም እንደተጠናቀቀ እና በቅርቡ ለአድማጮች እንደሚቀርብ ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከዚህ ቀደም
#አዛም_ሙዚቃ የድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ሶስተኛው አዲስ አልበም እንደተጠናቀቀ እና በቅርቡ ለአድማጮች እንደሚቀርብ ድምጻዊው በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ ከዚህ ቀደም "አንተ ጎዳና" እና "ናፍቆት እና ፍቅር"የተሰኙ የሙዚቃ አልበሞችን ለአድማጮች ማድረሱ ይታወሳል።

ፋና ላምሮት እና ብሌን ዮሴፍ ተለያዩ ለዓመታት በፋና ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው በ"ፋና ላምሮት" የድምጻዊውን ውድድር ላይ በመሐል ዳኝነት ስትዳኝ የቆየችው የሙዚቃ ባለሞያው ብሌን ዮሴፍ ከፋና ላ
ፋና ላምሮት እና ብሌን ዮሴፍ ተለያዩ ለዓመታት በፋና ቴሌቪዥን እየተላለፈ በሚገኘው በ"ፋና ላምሮት" የድምጻዊውን ውድድር ላይ በመሐል ዳኝነት ስትዳኝ የቆየችው የሙዚቃ ባለሞያው ብሌን ዮሴፍ ከፋና ላምሮት ጋር የነበራትን ቆይታ መጨረሷን በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች። ብሌን ዮሴፍ በማህበራዊ ትስስር ገጿ"የፋና ላምሮት የዳኝነት ቆይታዬን ጨርሻለሁ።ሲያበረታኝ የነበረዉ ልብን የሚያሞቅ ፍቅራችሁ እንደነበር ታዉቁ ይሆን እግዚአብሔር ያክብርልኝ እወዳችኋለሁ" ብላለች።

✍የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ ✅ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ) ✍የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ ✅ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ) ✍የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ ✅ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ) ✍የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ አሸናፊ ✅ችቦ (ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ ) ✍የዓመቱ ምርጥ ተውኔት ✅በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ) ✍የዓመቱ ምርጥ ግጥም ✅እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ) ✍የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት ✅ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ) ✍የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥም ✅ላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ) ✍የክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን ሽልማት ✅ኃይለመለኮት መዋዕል

#የክብር_ሽልማት የመጀመሪያው "የክብር ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ትላንት ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በግዮን ግሩቭ ጋርደን ውስጥ ተካሄዷል። የክብር ሽልማት አሸናፊዎች ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል: 🔰የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት ✅ ትዝታችን በኢቢኤስ 🔰የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት ✅ ለዛ 🔰የአመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ ✅ትዕግስት በጋሻው 🔰የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው ✅ መንሱር አብዱልቀኒ 🔰የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ ✅ አስካለ ተስፋዬ 🔰የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት á‹˜áˆ˜áŠ• ተሸላሚ ✅ አማረ አረጋዊ 🔰የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ ✅ ዶንኪ ቲዩብ

✍የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ 👉 ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ) 👉 ማሙሽ (ማይክል አዝመራው) 👉 ጠያይም መላዕክት (ቤተ ማርያም ተሾመ) 👉 ወድቆ የተገኘ ሀገር (ይፍቱሥራ ምትኩ) 👉 አሌፍ ቤት (ወንድሙ ገዳ) ✍የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ 👉 አሳንቲ (ምርት ባቦ) 👉 አዎ እሱ ጋ ያመኛል (አድሃኖም ምትኩ) 👉 ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ) 👉 አዝማሪው ልቤ (ጌታነህ ደጉ) 👉 እሰሩኝ (መሠረት ባህሩ) ✍የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ 👉 ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ) 👉 ተስፋዬን ፍለጋ (ማርቆስ ተግይበሉ) 👉 ሕይወቱ የአብራሪነት የአውሮፕላን ጠለፋ ትዝታዎቹ (ካፒቴን ልዑል አባተ) 👉 ዓለማየሁ እሸቴ (በወሰን ደበበ ማንደፍሮ) 👉 የህይወት ጎዳና (ሕይወት ጥላሁን) ✍የዓመቱ ምርጥ ተውኔት 👉 በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ) 👉 የሌሊት ሙሽሮች (ውድነህ ክፍሌ) 👉 የደፈረሱ ዓይኖች (ውድነህ ክፍሌ) 👉 ነገሩ አይቆምም (ድረስ ደሳለኝ) ✍የዓመቱ ምርጥ ግጥም 👉 እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ) 👉 ፍቅር ሰው ማኅሌት (ዮሐንስ ኃ/ማርያም) 👉 ፍለጋ (ፍቃዱ ጌታቸው) 👉 እንኳን መሃይም ሆንኩ (በለው ገበየሁ) 👉 ምርቃት (ዓለምነህ ረጋሳ) ✍የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት 👉 ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ) 👉 ጋዜጠኛዋ (ሳሙኤል ተሻገር) 👉 ወዳጅ (ግዛቸው ገብሬ) 👉 ገምዛ (ሙሉቀን አረጋ) 👉 ቅኔ (ቅድስት ሳህለ) ✍የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ 👉 ችቦ (ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ) 👉 እያል ድሬ (ሚልኬሳ ሙሜ) 👉 ኦብሲቱ (ሐሊ ሙዘይን) ✍የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥም 👉 ላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ) 👉 አትከልክሉኝ (አብነት አጎናፍር) 👉 ገላጋይ (ዮሓና) 👉 እርፍ በይ (ዘሩባቤል ሞላ) 👉 ማንነቴ (ኤልያስ መልካ) ✍የክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን እጩ 👉 ኃይለመለኮት መዋዕል 👉 ሳህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም 👉 ፀሐይ መላኩ 👉 ሲሳይ ንጉሱ 👉 አዳም ረታ

በሁሉም የሽልማት ዘርፎች ምርጥ አምስቶች  የሚከተሉት ናቸው። 🔰የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት ✅ ጦቢያ ✅ ውሎ አዳር ✅ ትዝታችን በኢቢኤስ ✅ ፋና ቀለማት ✅ ጠያቂው ሲጠየቅ 🔰የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት ✅ ሁሉ አዲስ ✅ የጥበብ መንገድ ✅ ታዛ ✅ መሰንበቻ ✅ ለዛ 🔰የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ ✅ ትዕግስት በጋሻው ✅ ወንድሙ ኃይሉ ✅ ብርሃኑ ድጋፌ ✅ ብስራት ከፈለኝ ✅ ሰለሞን ጫላ 🔰የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው ✅ እሸቴ አሰፋ ✅ ግርማ ፍስሃ ✅ ምንይችል እንግዳ ✅ ወንድዬ ካሳ ✅ መንሱር አብዱልቀኒ 🔰የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ ✅ ኤደን ገብረሕይወት ✅ ሰይፉ ፋንታሁን ✅ አስካለ ተስፋዬ ✅ ዳናዊት መክብብ ✅ ዮናስ ከበደ 🔰የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት  ዘመን ዕጩ ✅ ማዕረጉ በዛብህ ✅ ታምራት ገብረጊዮርጊስ ✅ ጸጋዬ ኃይሉ ✅ መርዕድ በቀለ ✅ አማረ አረጋዊ 🔰የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ ✅ ዶንኪ ቲዩብ ✅ ማያ ቲዩብ ✅ መሪ ፖድካስት ✅ ማራኪ ወግ ✅ ከናቲ ጋር

#አዛም_መረጃ የ"ክብር ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል የክብር ሽልማት የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በጊዮን ግሩቭ ጋርድን ውስጥ አመሻሽ ላይ ይካሄዳል ተብሏል። ይህ
#አዛም_መረጃ የ"ክብር ሽልማት" የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል የክብር ሽልማት የሽልማት ሥነሥርዓት ዛሬ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በጊዮን ግሩቭ ጋርድን ውስጥ አመሻሽ ላይ ይካሄዳል ተብሏል። ይህም የሽልማት ሥነሥርዓት በሀገሬ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ያገኛል።