Azam Media
Open in Telegram
"እንኳን ወደ አዛም ሚዲያ ቻናላችን በደህና መጡ፣ የአዳዲስ ዜናዎች፣ ማስታወቂያዎች እና የመዝናኛ ይዘቶች መዳረሻ! ወቅታዊ ሁነቶችን፣ ባህልን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በሚሸፍኑ ጽሁፎች፣ ቪዲዮዎች እና ምስሎች በተመረጡ መረጃዎች ይዝናኑ። ቴክኖሎጂ ፣የአኗኗር ዘይቤ እና ሌሎችም የኛን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ። ይቀላቀሉ ለመረጃ ጥቆማ 👉@jach17
Show more810
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Data loading in progress...
Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
July '24
July '24
+3
in 0 channels
June '24
+5
in 0 channels
Get PRO
May '24
+13
in 1 channels
Get PRO
April '24
+96
in 2 channels
Get PRO
March '24
+425
in 3 channels
Get PRO
February '240
in 0 channels
Get PRO
January '240
in 0 channels
Get PRO
December '230
in 0 channels
Get PRO
November '230
in 0 channels
Get PRO
October '230
in 0 channels
Get PRO
September '230
in 0 channels
Get PRO
August '230
in 0 channels
Get PRO
July '230
in 0 channels
Get PRO
June '230
in 0 channels
Get PRO
May '230
in 0 channels
Get PRO
April '230
in 0 channels
Get PRO
March '230
in 0 channels
Get PRO
February '230
in 0 channels
Get PRO
January '230
in 0 channels
Get PRO
December '220
in 0 channels
Get PRO
November '22
+1
in 0 channels
Get PRO
October '22
+2
in 0 channels
Get PRO
September '22
+1
in 0 channels
Get PRO
August '22
+4
in 0 channels
Get PRO
July '22
+11
in 0 channels
Get PRO
June '22
+15
in 0 channels
Get PRO
May '22
+12
in 0 channels
Get PRO
April '22
+32
in 0 channels
Get PRO
March '22
+49
in 0 channels
Get PRO
February '22
+326
in 0 channels
Get PRO
January '22
+96
in 0 channels
Get PRO
December '21
+8
in 0 channels
Get PRO
November '21
+10
in 0 channels
Get PRO
October '21
+38
in 0 channels
Get PRO
September '21
+13
in 0 channels
Get PRO
August '21
+15
in 0 channels
Get PRO
July '21
+144
in 0 channels
Get PRO
June '21
+207
in 0 channels
Get PRO
May '21
+266
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 20 July | 0 | |||
| 19 July | 0 | |||
| 18 July | 0 | |||
| 17 July | +1 | |||
| 16 July | 0 | |||
| 15 July | 0 | |||
| 14 July | 0 | |||
| 13 July | 0 | |||
| 12 July | 0 | |||
| 11 July | 0 | |||
| 10 July | 0 | |||
| 09 July | 0 | |||
| 08 July | +1 | |||
| 07 July | 0 | |||
| 06 July | 0 | |||
| 05 July | 0 | |||
| 04 July | 0 | |||
| 03 July | 0 | |||
| 02 July | +1 | |||
| 01 July | 0 |
Channel Posts
በመላው ሀገሪቱ በመጪዎቹ 10 ቀናት ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
ለዝናብ መፈጠር ምክንያት የሚሆኑ የደመና ክምችቶች በመኖራቸው አዲስ አበባን ጨምሮ በመካከለኛና በምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ከበድ ያለ ዝናብ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በአማራ፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአብዛኛው ኦሮሚያ፣ በደቡብ ምዕራብና በምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡
ከባድ ዝናብ ይኖራል የተባለባቸውን አካባቢዎችም የነገሩ በኢንስቲትዩቱ በኤጀንሲው የሚቲዎሮሎጂ ትንቤና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር አሳምነው ተሾመ ናቸው፡፡
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በብዙ የሃገራችን አካባቢዎች እየጣለ ያለውና ክረምቱ መጣሁ መጣሁ ማለቱን እያሳየ ያለው ዝናብ ክረምቱን ለሚያመርቱ አካባቢዎች የተመቸ ነውም ብለዋል፡፡
ከባድ ዝናብ ይኖራል በተባሉ አካባቢዎች ያላችሁ ጎርፍ ሊከተል ስለሚችል በአከባቢ የሚገኙ በቆሻሻ የተደፈኑ ቱቦዎችን ክፍት ማርግ ጨምሮ መሰለ አደጋ ከሚፈጥሩ ሁነቶች ጠንቀቅ በሉ ተብሏል፡፡(ሀገሪኛ ሚዳያ)
| 2 | ተወዳጅዋ ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ተካ አዲስ አልበም…
የመጀመርያ የበኩር አልበሟን በነሀሴ ወርሀ 17/2016 እንደሚለቀቅ ገልፃለች፡፡ የአልበሙ መጠርያ ርዕስ '' መጠርያዬ ''ይሰኛል በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን ተሳትፈዋል አቀናባሪ አዲስ ፍቃዱን ጨምሮ ይህ አልበም ሶስት አመት የለፋችበት አልበም መሆኑንም ጠቁማለች፡፡
ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ በማህበራዊ የፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳስታወቀችሁ ''ከዚህ በኃላ የምለቃቸው ፎቶዎች ላይ ስለ አልበሙ አንድ አንድ ነገሮች እላቹኃለሁ በተጨማሪም አዳዲስ ነገሮችም አሉ"ስትል ገልፃለች፡፡ | 259 |
| 3 | በአንጋፋው ወመዘክር አዳራሽ "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር ነው
በአንጋፋው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር አዳራሽ) "የወር ወንበር" የተሰኘ ወርሃዊ ዝግጅት መካሄድ ሊጀምር እንደሆነ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ"የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ነባሩ የሐሳብ ክምችታችን ነው። በዚሁ ክምችት አጠገብ ተቀምጠን አንዳንድ ሐሳቦችን በወር ለአንድ ቀን ከአንድ ቀንም ለአንድ ሠዓት ተኩል ረግተን ብንወያይ ደህና ነው " ብሏል።
በመጀመሪያው ወር “የወር ወንበር” ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 15 2016 ቀን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ምልከታ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህ ውይይት ላይ መነሻ ሀሳብ በይኩኖ አምላክ መዝገቡ የሚቀረብ ሲሆንበኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ ውስጥም ውይይቱ ይካሄዳል ተብሏል።
©event addis | 233 |
| 4 | #አዛም_መረጃ
ዋልታ እና ፋና ሊዋሃዱ ነው!
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከዋልታ ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት ጋር የሚያደርጉት ውሕደት ከ20 ቀናት በኃላ ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ኹለቱ የፓርቲ መገናኛ ብዙኃን ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ ፋና በሚል መጠሪያ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ ዘ-ጆርናሊስት ከታማኝ ምንጮች ሰምቷል።
የኹለቱን መገናኛ ብዙኃን ውሕደት ተከትሎ አዳዲስ የሠራተኞች የሥራ ድልድል በጊዜው ይፋ እንደሚደረግ ታውቋል።
ጣቢያዎቹ በአንድ ሥም ይጠሩ እንጂ አሁን ያሉበትን መሥሪያ ቤት ሳይለቁ፣ የተለያዩ ዝግጅቶችን ለታዳሚዎቻቸው እንደሚያሰራጩም ተገልጿል።
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም በዋልታ ይፋዊ የትሥሥር ገጾች ላይ በወጣ ልጥፍ ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ሞሐመድ ሐሰን “ጠቅላይም ተጠቅላይም” አለመኖሩን መግለጻቸው ይታወሳል።
©ዘ-ጆርናሊስት | 241 |
| 5 | #አዛም_ጥቆማ
በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር የተዘጋጀው የሥነጽሑፍ ሥልጠና በሚመጣው የክረምት ወቅት ይካሄዳል
በኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር በየዓመቱ የሚዘጋጀው የክረምት የሥነጽሑፍ ስልጠና ዘንድም ለዘጠኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሏል።
ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስምንት ዙሮች በርካታ የሥነጽሑፍ ወዳጆች ስልጠናውን እንደወሰዱ ተነግሯል።
በልቦለድ ክሂል ፣በልቦለድና ኢ ልቦለድ፣ በግጥም ፣ በፎክሎር ፣ በሥነጽሑፋዊ ታሪክ ፣በሥነሂስ በሌሎችም የሥነጽሑፍ ዓይነቶች ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ ምዝገባ እንደተጀመረ ኤቨንት አዲስ ድረገፅ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ለበለጠ መረጃ በተከታዩ ስልክ ቁጥር ደውሉ 0911448297 ተብላችኋል። | 239 |
| 6 | አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ...!
በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ሃያ ስምንተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት ረቡዕ ሰኔ 12 /2016 ዓ.ም ያካሂዳል። በዕለቱም ተወዳጇ አርቲስት መስከረም አበራ የክብር እንግዳችን ሆና በመካከላችን ትገኛለች። እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ለእናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ተሰናድተው ይጠብቃችኃል ።
ሼር ያድርጉ !
#ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ። | 243 |
| 7 | የሰው ልጅ እንጀራ እየተቀማ ይሆን?
በደቡብ ኮሪያ የንግድ ማእከል ውስጥ የሚገኘው ይህ የስታርባክ ቡና መሸጫ 100 ሮቦቶች እና 2 ሰዎች ብቻ ቀጥረዋል።
ሮቦቶቹ ትእዛዝ ተቀብለው ለደንበኞች ያደርሳሉ። ተቋሙ ሁለት የታጠቁ ሮቦቶችንም እየሞከረ ነው - ወደፊት የሰው ልጆችን ሙሉ በሙሉ መተካት ይችላሉ። | 372 |
| 8 | #አዛም_መረጃ
ካሜራ የሸሚዝ ቁልፍ በማስመሰል ሲኮርጅ የተያዘው ቱርካዊ ተማሪ
ቱርካዊው ተማሪ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስን (ኤአይ) በመጠቀም ሲኮርጅ ተይዟል።
ይህ ተማሪ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት አጠራጣሪ እንቅሰቃሴዎች በማሳየቱ በፓሊስ ሊያዝ እንደቻለ ሮይተርስ ዘግቧል።
በደቡባዊ ስፓርታ ግዛት ፓሊስ የተለቀቀው ቨዲዮ ተማሪው እንዴት ካሜራን የሸሚዝ ቁልፍ በማስመሰል በጫማው ሶሎ ውስጥ በተደበቀ ራውተር አማካኝነት ከኤአይ ጋር እንዳያያዘው ያሳያል።
ቢዚህ ቪዲዮ የፓሊስ ባልደረባው ሲስተሙ መስራቱን ለማረጋገጥ ጥያቄዎችን ስካን ሲያደርግ እና ከኤአይ ትክክለኛውምን መልስ በጆሮ ማዳመጫ ሲሰማ ይታያል።
የቱርክ ባለስልጣናት በዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወቅት መሳሪያ ከአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) ጋር በማገናኘት ጥያቄዎችን ሲመልስ የደረሱበትን ተማሪ አስረዋል። | 333 |
| 9 | #አዛም_ቴክኖሎጂ
YouTube shorts አዲስ በAI የታገዘ feature ሊያስተዋውቅ ነው
YouTube shorts የተጠቃሚዎችን ኮመንት መሰረት ያደረገ የቪዲዮ አደራደር ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።
ተመሳሳይ አይነት አስተያየት የተሰጣቸው ቪዲዮዎች በተቀራራቢ ሰአት የሚታዩ ሲሆን የቪዲዮው ባለቤት የማይፈልጋቸውን የcomment ርዕሶች ማጥፋትም ይችላል ተብሏል።
በተጨማሪም Google አዲስ Dream Screen የተባለ AI-generated green screen background እየሞከረ እንዳለ ታውቋል። | 304 |
| 10 | #አዛም_መረጃ
በስም የሚጠራሩት የአፍሪካ ዝሆኖች
በአፍሪካ የሚገኙ ዝሆኖች በስም እየተጠራሩ እንደሚግባቡ አዲስ የጥናት ውጤት አመላክቷል፡፡
በኮሎራዶ ስቴት ዩኒቨርስቲ የስነ- ምህዳር ተመራማሪዎች ይፋ የተደረገው አዲስ ግኝት ዝሆኖቹ በአስገራሚ ሁኔታ በተለያየ ስያሜ እንደሚጠራሩ እና ለጥሪው የሚሰጡት ምላሽም አንዱ ከሌላው የተለየ ስም እንዳለው አመላካች መሆኑን ነው የጠቆመው።
ተመራማሪዎቹ ዝሆኖቹ የሚግባቡበትን መንገድ ለማጥናት ባደረጉት ክትትል ለሰዎች መስማት አዳጋች በሆነ ድምጽ መልዕክት ሲለዋወጡ እና ለዚህም ምላሽ ሲሰጡ ማስተዋላቸውን አመላክተዋል፡፡
ዝሆኑቹ ለእነርሱ በተሰጠ ስያሜ ሲጠሩ ኩምቢያቸውን እና ጆሯችውን በማንቀሳቀስ ምላሽ የሚሰጡ ሲሆን ቀጥሎም ወደ ጠራቸው ዝሆን በመቅረብ እንደሚግባቡ ነው አጥኚዎቹ የገለጹት፡፡
ዝሆኖቹ ለጥሪ የሚጠቀሙት ድምጽ ስም መሆኑን ለማረጋገጥ የተለያዩ የድምጽ መመርመሪያ ማሽኖችን ሳይንቲስቶቹ ጥቅም ላይ ያዋሉ ሲሆን ማሽኖቹ 28 በመቶ የሚሆነውን ጊዜ የትኛው ስያሜ ለየትኛው ዝሆን የተሰጠ መሆኑን በትክክል ገምተዋል ነው የተባለው፡፡
በኬንያ አምቦሲሊ ፓርክ በተደረገው ጥናት ዝሆኖች እንደሰው ልጅ ስሞችን እንደሚጠቀሙ ብናረጋግጥም ሁሉም ዝሆኖች በስያሜ ይግባባሉ የሚለው ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገናል ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡
©al_ain | 236 |
| 11 | #አዛም_ቴክኖሎጂ
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ብዙዎችን ባለሀብት ያደርግ ይሆን?
እንደሚታወቀው ቲክቶክ በፈጠረው የቲክቶክ ኮይን ጊፍት አማካኝነት ብዙዎቹ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ረድቷል።
ቴሌግራምም የቲክቶክን ፈለግ በመከተል የቻናል ባለቤቶች ጊፍት የሚያገኙበትን አማራጭ እንደሚያስተዋውቅ ይፋ አድርጓል።
ጊፍቱ የሚሰጠው አዲስ ባስተዋወቀው Telegram stars አማካኝነት ሲሆን ክሬተሮች የተሰጣቸውን ጊፊት ወደ ገንዘብ መቀየር ይችላሉ ብሏል።
ይህ አሰራር በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆን ቴሌግራም ባሰራጨው ዜና አስታውቋል።
አንድ ሰዉ ጊፍቱን የሚያገኘው በምን መስፈርትና ሁኔታ እንደሆነ የተገለፀ ነገር የለም። | 240 |
| 12 | #አዛም_መረጃ
ቴሌግራም ልክ እንደ ቲክቶክ ቴሌግራም ላይ ለግብይት የሚያገለግል ኮይን አስተዋውቋል
Telegram stars ሲል የተሰየመው ዲጅታል መገበያያ በGoogle እና Apple pay አማካኝነት የተለያዩ የቴሌግራም አገልግሎቶችን ለመግዛት ያስችላል።
ዝርዝር መረጃ በቀጣይ አናቀርብላችኋለን። | 295 |
| 13 | "ቢሊየነር መሆኔን አታወቅም ነበር ፈገግታዬ ማርኳት ነው ያፈቀረችኝ"
የ69 አመቱ አሜሪካዊ ቢሊየነር የሬይደርስ ሶከር ባለቤት ማርክ ዴቪስ የ25 አመት ፍቅረኛቸው "ቢሊየነር መሆኔን አታውቅም ነበር ። ፈገግታዬ ማርኳት ነው ያፈቀረችኝ" ሲሉ ተደምጠዋል። | 355 |
| 14 | #አዛም_ቴአትር
"እያዩ ፈንገስ" ለሁለት ቀናት ብቻ ሊታይ ነው
በበረከት በላይነህ ተደርሶ በግሩም ዘነበ የሚተውነው "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት መድረክ ላይ መቅረብ ከጀመረ ዘንድሮ አስር ዓመት እንደሚሞላው አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ይህንን የአስርኛ ዓመት ክብረበዓል በማሰብ ረቡዕ ሰኔ 5 እና አርብ ሰኔ 7 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በራስ ሆቴል ለሁለት ቀናት ብቻ "እያዩ ፈንገስ" የአንድ ሰው ተውኔት ለታዳሚያን እንደሚቀረብ ኤቨንት አዲስ ድረገጽ ሰምቷል። | 261 |
| 15 | #አዛም_ቴክኖሎጂ
የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የቁንጅና ውድድር 10 ተፎካካሪዎች ተለዩ
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሚዳኘው ውድድር ለአሸነፊዎች 20 ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል ስለመባሉም በመረጃው ላይ ተፅፏል።
የሚሊየኖችን ስራ ይነጥቃሉ የሚል ስጋት የፈጠሩት አጅሬዎቹ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ደግሞ ከኛ በላይ ቆንጆስ የታለ ለማለት መሰናዳታቸው ነው የተሰማው ።
ከ10 ተወዳዳሪዎችም ሶስቱ ተለይተው በያዝነው ሰኔ ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በሚመራ የሽልማት ስነስርአት ይፋ ይደረጋሉ ተብሏል።
ለአሸናፊዎቹ በአጠቃላይ 20 ሺህ ዶላር ለሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፥ አሸናፊዋ 5 ሺህ ዶላር እና 3 ሺህ ዶላር ዋጋ ያለው የስልጠና እድል ታገኛለች ብለዋል አዘጋጆቹ።
የቁንጅና ውድድሩን በወር ከ10 ሺህ ዶላር በላይ የምታስገኘው ኢታና ሎፔዝና ኢሚሊ ፔሌግሪኒ ላለፉት 10 አመታት የወይዘሪት ብሪታንያ ዳኛ ከሆኑት ሳሊ አን ፋውሴት ጋር ተጣምረው ይዳኙታል ተብሏል። | 313 |
| 16 | #አዛም_ሙዚቃ
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ "የልቤን" አልበም ተለቀቀ
የድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሣ "የልቤን "የተሰኘ የመጀመሪያ አዲስ አልበም ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 1 2016 ዓ.ም በራሱ Mesay Tefera የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለማቀፍ መተግበሪያዎች ላይ ተለቋል።
አልበሙ በውስጡ ቻል ቻል ፣የብቻዬ ፣ቆንጆ ነሽ፤ደህና ይግጠምሽ፤ ማካሪና ፤ ከአባይ ማዶ ፤ውረጅ ካናቴ ፤ የልቤን ፤ግድ የለሽም፤ ኸረ ተይ፤አይ አለማወቋ፤ አወሰድማዬ፤ እሳቱ የተሰኙ ርዕሰ ያላቸው የተለያዩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ 12 የሙዚቃ ስራዎችን ይዟል። | 327 |
| 17 | #አዛም_መረጃ
ከህዋ ላይ የመሬትን ገጽታ የሚያሳየውን ታዋቂ ምስል ያነሱት አሜሪካዊ ህይወታቸው አለፈ
ከህዋ ላይ የመሬትን ገጽታ የሚያሳዩ ምስሎችን በማንሳት እውቅናን ያተረፉት አሜሪካዊው ዊሊያም አንደርስ ህይወታቸው አለፏል።
የአሜሪካውን የጠፈር ድርጅት (ናሳ) በ1963 የተቀላቀሉት ዊሊያንም አንደርስ በ1968 ወደ ጨረቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎችን ይዛ የተወነጨፈችው መንኮራኩር አብራሪ ነበሩ።
የ”አፖሎ 8” ተልዕኮ እነ አንደርስ ጨረቃ ላይ ሳያርፉ 10 ጊዜ ዞረዋት ወደ መሬት እንዲመለሱ ማስቻሉ ይታወሳል።
ይህ ታሪካዊ ጉዞ ዊሊያም አንደርስ የመሬትን ውብ ገጽታዎች በካሜራዎቹ እንዲያስቀር አድርጎት አሁንም ድረስ ምስሎቹ ለመሬት ጥናትና ተያያዥ ጉዳዮች ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ታድያ አሁን አንደርስ ብቻቸውን ሲያበሯት የነበረች “ቲ-34” አነስተኛ አውሮፕላን በሰሜናዊ ሲያትል መከስከሷ ተሰምቷል።
ልጃቸው ግሬግም “ጎበዝ አብራሪ” የነበሩት አንደርስ በ90 አመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ማረጋገጡን ሬውተርስ ዘግቧል። | 272 |
| 18 | #አዛም_ሙዚቃ
ወጣቷ ድምጻዊት ሀና ግርማ ''ባንተ ላይ'' በተሰኘ ስራዋ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች
ድምፃዊት ሀና ግርማ ከ9 ወራት በፊት በሰራችው ስራ ከሰሞኑ የናሆም ሪከርድስን ሪከርድ ሰብራለች ።
''ባንተ ላይ''ሙዚቃው በናሆም ሪከርድስ በተለቀቀ 9 ወሩ 20 ሚሊዮን እይታ አግኝቷል።ይህም ኩባንያው ቪድዮዎችን መልቀቅ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተመልካች በማግኘት ቀዳሚ ሆኗል።
ናሆም ሪከርድስ በዩቲዩብ ከለቀቃቸው ስራዎች በቀዳሚነት ላይ የሚገኘው የታሪኩ ጋንኪሳ ዲሽታ ጊና ሲሆን 35 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። ይህ ስራ በዚህ ቁጥር የታየው በ3 አመት ውስጥ ነው። የሃና ግን በ9 ወራት ነው 20,000,000 የታየው። የቬሮኒካ አዳነ "ጥፍጥ አለኝ" ከሁለት አመት በፊት ተለቆ 18 ሚሊየን ጊዜ ታይቶ ናሆም ከለቀቃቸው ስራዎች ብዙ እይታ በማግኘት 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
©ሁሉ አዲስ | 311 |
| 19 | #አዛም_መረጃ
ጃፓን የሚያገቡ ዜጎችን ለማበረታታት የመጠባበሻ መተግበሪያ ሰርቻለሁ አለች
በአዛውንቶች ህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ጃፓን የሚወለዱ ህጻናት ቁጥርን ለመጨመር በሚል የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመዘርጋት ላይ ትገኛለች፡፡
የጃፓን መዲና እና ከ22 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ቶኪዮ ደግሞ የውልደት መጠን ዝቅተኛ ነው፡፡
የከተማዋ አስተዳድር ይህን ለመፍታት በሚል ዜጎች እንዲጋቡ እና ልጆችን እንዲወልዱ በሚል አጋራቸውን በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ መተግበሪያ ሰርቷል፡፡
ይህን አፕሊኬሽን ወይም መጠባበሻ መተግበሪያ ለመጠቀም ገቢ ያለው መሆን፣ ያላገባ ማስረጃ መኖር፣ ግብር መክፈሉን እና ማንነቱን የሚያሳዩ መረጃዎችን ማቅረብ እንደ ግዴታ አስቀምጧል፡፡
ይሁንና ይህን የአጋር መፈለጊያ መተግበሪያ እንዲጠቀሙ ከሚጠበቁ ጃፓናዊያን መካከል 70 በመቶዎቹ ፍላጎት አላሳዩም ሲል ኤአፍፒ ዘግቧል፡፡ | 284 |
| 20 | #አዛም_መረጃ
በአሜሪካ አላባማ ግዛት በተካሄደ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ የሆነችው እንስት አነጋጋሪ ሆናለች
የ23 አመቷ ሳራ ሚሊከን ከልክ ያለፈ ውፍረቷ ነው በውድድሩ አሸናፊ ሆናለች ስትባል ትችት ያስከተለባት።
የአሜሪካ ብሄራዊ የቁንጅና ውድድር አዘጋጁ አካልም በማህበራዊ ሚዲያዎች ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።
ቁንጂና እንደተመልካቹ አይን ቢሆንም የአለባማዋ ቆንጆ ወፍራም መሆኗ የውድድሩን አዘጋጅ “ከልክ ላለፈ ውፍረት ድጋፍና እውቅና መስጠት ነው” ያሉ ሰዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።
የአሜሪካ ብሄራዊ የቁንጅና ውድድር አዘጋጅ (ኤንኤኤም) ተወዳዳሪዎች ራሳቸውን ሆነውና የተፈጥሮ ውበታቸውን እንዳያፍሩበት እንደሚያበረታታ በድረገጹ አስፍሯል።
የረጅም ጊዜ ህልሟ መሳካቷ የፈጠረባት ደስታን የሚያደበዝዙ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የተከፈተባት ሳራ ሚሊከን፥ “ደስታዬ ከአምስት ደቂቃ አልበለጠም፤ የሚሰብሩ ቃላት ይወረወሩብኝ ነበር” ብላለች። | 270 |
