cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መረጃ 24 ሰአት

ቶሎ ቶሎ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶት ላይክ እና ሼር አርጉ ፈጠን ፈጠን ብለን መረጃን አንለቃለን ላይክ ያርጉ ፈጠን በሉ

Show more
Advertising posts
2 017
Subscribers
No data24 hours
-87 days
-1230 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
Media files
380Loading...
02
Media files
430Loading...
03
በጀት‼️ ለ2017 ዓ.ም የቀረበው ወደ 1 ትሪሊየን ብር የሚጠጋ የመንግስት በጀት ለምክር ቤቱ ተላከ‼️ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2017 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ፤ የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ ተደርጓል። በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣ ለካፒታል ወጪዎች ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ነው። በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሰፊ ሥራዎች ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካላት የቆዳ ስፋት ከግማሽ በላይ የሆነው የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ለማድረግ፣ የደን ዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በአሁኑ ወቅት በተበጣጠሰ መልኩ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በክልል መንግስታት ፋይናንስ እየተደረገ እየተሰራ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተቀናጀና ተገቢውን ሀብት መመደብ በሚያስችል የፋይናንስ አሰራር ስርዓት መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
600Loading...
04
Media files
670Loading...
05
Media files
630Loading...
06
Media files
630Loading...
07
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ከዕሁድ'ለት ጀምሮ መቋረጡን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዕሁድ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከጎንደር ወደ ባሕርዳር እንዲኹም ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ እንደኾኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶቹ የተዘጉት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ባስቀመጡት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክልከላ ምክንያት መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ላለፉት አራት ቀናት ከባሕርዳር ወደ ኹሉም የጎንደር አካባቢዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልጸዋል። ከ10 ቀናት በፊት በሦስቱ የጎጃም ዞኖች ተመሳሳይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ እንደነበር ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል። አንድ ጊዜ ለአራት ወራት የተራዘመውና ባጠቃላይ ለ10 ወራት የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ለኹለተኛ ጊዜ ሳይራዘም ትናንት አብቅቷል። ኾኖም መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማብቃቱ በይፋ ያለው ነገር የለም።
650Loading...
08
Media files
1011Loading...
09
Media files
940Loading...
10
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከፍለው ለመማር የማይችሉ ተማሪዎች የባንክ ብድር እንዲያገኙ የሚረዳ ሕጋዊ አሠራር እንዲመቻች ተጠየቀ፡፡ በ2015 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባውና ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የሚያደርገው አዋጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከስምንት ወራት በፊት ወደ ሥራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝነት ለማሸጋገር ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ምንም እንኳ ተጠያቂነቱ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መንግሥት በገንዘብ የሚደግፋቸውም ቢሆኑም፣ ራሳቸውን በራሳቸው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የፋይናንስ፣ የአስተዳደር፣ የአካዴሚክ፣ የሰው ሃብት እና መሰል ነፃነት አዋጁ ያጎናፅፏቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ራስ ገዝ ሆኖ ሥራ በጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ከፍለው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ክፍያው በከፍተኛ መጠን እንደጨመረባቸው እየተናገሩ ነው፡፡ ወደፊት ራስ ገዝ የሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ሲገቡ አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ከፍለው እንዳይማሩ ይገድባል የሚል ሥጋት እየተሰማ ነው፡፡ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ለተማሪዎች የሚሰጥ ብድር መመቻቸት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በተመሳሳይ፤ መንግሥት በውጭው ዓለም የተለመደውን ለተማሪዎች ብድር የሚቀርብበት አሠራር ሊያስብበት ይገባል ብለዋል፡፡
1080Loading...
11
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ወሰነ ? ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ፦ ➡️ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው፣ ➡️ ፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃዱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ፈጽሞ #የተከለከለ፣ ➡️ በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣ በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ፣ ➡️ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ ➡️ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ #እንደሚያወግዝ ገልጿል። #የተመሳሳይ_ጾታ_ጋብቻ እና #የግብረ_ሰዶማዊነትን ኃጢአት በተመለከተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
970Loading...
12
Media files
960Loading...
13
የፈረንሳይ ባለስልጣናት የኦሎምፒክ ውድድሩ ሳይቃረብ ከዋና ከተማዋ ቤት የሌላቸውን ሰዎች ማስወጣት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የፈረንሳይ የኦሎምፒክ ዝግጅት ሊደርስ የቀረው ጊዜ ከአንድ ወር አይበልጥም፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናትም ለዝግጅቱ እንቅፋት ይሆናሉ ያሏቸውን የእፅ አዘዋዋሪዎች ህገ-ወጥ ስደተኞችና ሰፋሪዎችና ጥገኝነት ፈላጊዎችን በመለየት ከዋና ከተማዋ ፓሪስ እያስወጡ መሆኑን ከዚያው የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ከአውሮፓውያኑ 2023 እስከ ተያዘው የ2024 ሰኔ ወር ድረስ ብቻ ከፓሪስ አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አርባ አምስት ሰዎችን ማስወጣታቸውም ተገልጿል፡፡
1231Loading...
14
በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት ምክንያት ያደረገው እና ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ የጊዜ ገደብ በማለቁ በእስር የቆዩ ሰዎች የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥልም አሳስቧል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት ዛሬ መጠናቀቁን ኮሚሽኑ አሳትውሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የገለጸው ኮሚሽኑ ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ መግለጫችን ሲያወጣ የቆየ ሲሆን በዚህም የመንግስት እና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች በመብት ጥስቶች ላይ መሳተፋቸውን እንዳረጋገጠ ገልፆ ነበር በመሆኑም በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውስጥ በእስር ላይ የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎች ማኅበረሰባዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።  
1340Loading...
15
Media files
1240Loading...
16
"19 ሰዎች ከእስር ተፈተዋል"ምንጮች በአፋር ክልል በሚገኘው አዋሽ አርባ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ በእስር ላይ ከነበሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ጋዜጠኞች መካከል አስራ ዘጠኙ “የተሃድሶ ስልጠና’’ ከወሰዱ በኋላ ባለፈው ቅዳሜ መለቀቃቸውን ተሰምቷል። በተመሳሳይ ቀን ሌሎች 20 እስረኞች ከአዋሽ አርባ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የእስረኞች ማቆያ እንዲዘዋወሩ መደረጋቸውን እና ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። እስረኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት፤ በዋነኛነት በአማራ ክልል እና እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ “በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ” ተፈጻሚነት እንዲኖረው ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ነው። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ባወጣው መግለጫ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ወደሚገኝ “መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ” የተወሰዱ እስረኞች ብዛት 53 መሆናቸውን አስታውቆ ነበር። ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርቱ፤ ✔የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የቀድሞ አባል የሆኑት መምህር ናትናኤል መኮንን፣ ✔ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ እና ✔ ጋዜጠኛ አብነት ታምራት በአዋሽ አርባ በእስር ላይ እንዳሉ ማስታወቁ አይዘነጋም። ሆኖም መግለጫው ከወጣ በኋላ መምህር ናትናኤል እና ጋዜጠኛ አብነት ከእስር መለቀቃቸውን ማረጋገጡን በኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል የሪጅን ዳይሬክተር ሰላማዊት ግርማይ  ተናግረዋል። በኢሰመኮ የነሐሴ ወር ሪፖርት ተጠቅሰው የነበሩት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩት አቶ ስንታየሁ ቸኮል፤ ግንቦት 25፤ 2016 ከአዋሽ አርባ ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደተዘዋወሩ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። “የኢትዮ ኒውስ” የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች የሆነው ጋዜጠኛ በላይም በቢሮው ስር ወዳለው የእስረኞች ማቆያ መዘዋወሩንም አክለዋል።
1150Loading...
17
Media files
1080Loading...
18
የሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንትና የንግድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባቱን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። 79 አባላትን ያካተተው ልዑካን ቡድን፣ ከተለያዩ የሳዑዲ ዓረቢያ ታዋቂ ኩባንያዎች የተውጣጡ ባለሃብቶችንና የአገሪቱን ንግድ ምክር ቤት ኃላፊዎች ያቀፈ እንደኾነ ሚንስቴሩ ገልጧል። ልዑካን ቡድኑ በሦስት ቀናት ቆይታው፣ በአዲስ አበባ በሚካሄድ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ይሳተፋል፤ የተለያዩ ፕሮጀክቶችንም ይጎበኛል ተብሏል። ሚንስቴሩ፣ የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የንግድና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በኹለቱ አገራት መካከል ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋትና የኹለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር ያለመ እንደኾነ ገልጧል።
1140Loading...
19
Media files
1250Loading...
20
Media files
1200Loading...
21
የተወካዮች ምክር ቤት ህወሓት ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን ማሻሻያ አዋጅ  በዛሬው እለት አጸደቀ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አጽድቋል። በ2011 ዓ.ም. የወጣውን “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን” የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በሁለት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው። “በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ መሆኑ ተጠቅሷል። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ፤ “ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል” በሚል “ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ” የተደረገው ህወሓት በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል። “አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል” ሲል በዛሬው እለት  በጸደቀው አዋጅ ላይ ተመላክቷል።
1310Loading...
22
Media files
1260Loading...
23
Media files
1070Loading...
24
በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል   በኦሮሚያ ክልል ከግንቦት 19  እስከ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ በ11  ሰዎች ላይ ከባድ እና በ1 ሰው ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ አብዛኞቹ የሞት አደጋዎች  የተከሰቱት ምስራቅ ቦረና ፣ቄለም ወለጋ፣ምስራቅ አርሲ፣ጅማ፣ምስራቅ ጉጂ ዞኖች  እንዲሁም  ሸገር እና  ቢሾፍቱ ከተማዎች የተከሰቱ መሆናቸውን  የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ አብዛኛዎቹ አደጋዎች  የተከሰቱት በቀኑ ክፍለ ጊዜ ሲሆን   የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት ተሽከርካሪ፣በህዝብ ማመላለሻ፣ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) እና በሞተር ሳይክል የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡                       የአደጋዎቹ መንስኤዎቹ ያለ መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር፣ከፍጥነት ወሰን በላይ ማስከርከር፣ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር፣ ደርቦ ማለፍ  ምልክቶችን አለማክበር ፣የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን ኢንስፔክተር መሰለ አበራ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
1130Loading...
25
የሱዳን መንግሥት፣ ሩሲያ በሱዳን የቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር እንድታቋቁም አኹንም ቁርጠኛ አቋም እንዳለው አረጋግጧል። በሩሲያ የሱዳን አምባሳደር ሞሃመድ ሲራጅ፣ የባሕር ኃይል ጣቢያው የሎጅስቲክስ ማዕከል እንዲኾን ኹለቱ አገሮች እንደተስማሙ ለሩሲያ ዜና ምንጮች ተናግረዋል። ሱዳን፣ ሩሲያ የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር ማዕከሉን እንድትገነባ የገባችላትን ቃል እንደማታጥፍ አምባሳደሩ ገልጸዋል። ኹለቱ አገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ከአምስት ዓመታት በፊት ቢኾንም፣ እስካኹን ግን ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ አልቻሉም።
1210Loading...
26
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ በአገራዊ የምክክር ሂደቱ በግጭቶች ተሳታፊ የኾኑ አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤታማ ሊኾን አይችልም ማለቱን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። የጋራ ምክር ቤቱ፣ ግጭቶች በሙሉ ቆመው ኹሉም አካላት ወደ ሰላማዊ ንግግር እንዲመጡ በድጋሚ መጠየቁንና መንግሥትም አማጺ ኃይሎች በአገራዊ ምክክሩ አንዲሳተፉ ኹኔታዎችን እንዲያመቻች በድጋሚ ጥሪ ማድረጉንም ዘገባው ጠቅሷል። ምክር ቤቱ የምክክር ኮሚሽኑ ግጭቶች እንዲቆሙ የማድረግ ሥልጣን እንዳልተሰጠው በመግለጽ፣ ግጭቶች ባልቆሙበት ኹኔታ አገራዊ ምክክር ማድረግ ውጤት ላያመጣ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ገልጧል ተብሏል። ኮሚሽኑ ጫካ የገቡ ኃይሎች በምክክሩ የሚሳተፉ ከኾነ፣ ከለላ ለመስጠት መንግሥትን እንደሚጠይቅ መናገሩን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።
1210Loading...
27
Media files
1270Loading...
28
በህንድ በከፍተኛ ሙቀት የተነሳ በሶስት ቀናት ውስጥ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ በህንድ ውስጥ ባለፉት ሶስት ቀናት ውስጥ ከ50 የሚበልጡ ሰዎች በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በአስከፊ የሙቀት መጠን የተነሳ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሰሜናዊቷ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት ብቻ በሳምንቱ መጨረሻ በሙቀት ሳቢያ 33 ሰዎች ሞተዋል። በኦዲሻ ግዛት ደግሞ 20 የሚጠጉ ሰዎች በሙቀት መሞታቸውን አንድ ባለሥልጣኑ ለኤኤንአይ የዜና ወኪል ተናግረዋል። ህንዳውያን ለጠቅላላ ምርጫ በመጨረሻው የድምጽ መስጠት ሂደት ላይ ሆነው ይህው የሞት ሪፖርት ይፋ ተደርጓል። የምርጫው ውጤት በነገው እለት ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል። በየአምስት ዓመቱ ህንድ አጠቃላይ ምርጫዋን በሚያዝያ እና ግንቦት የበጋ ወራት ታካሂዳለች። ነገር ግን በዚህ አመት የሙቀት መጠኑ ኃይለኛና ረዘም ያለ የሙቀት ሞገዶች እያጋጠማት ይገኛል። የህንድ ፌደራል ጤና ሚኒስቴር ከመጋቢት 1 እስከ ግንቦት 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 56 የተረጋገጡ በሙቀት ስትሮክ የሰዎች ህልፈት መመዝገቡን ይፋ አድርጓል ።በዚህ ወቅት 24 ሺ 8 መቶ 49 ያህል ሰዎች በሙቀት በተፈጠረ የጤና እክል ጉዳዮች ሪፖርት ተደርጓል። ሆኖም፣ ትክክለኛው የተጎጂዎች ቁጥር በጣም ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል። በኡታር ፕራዴሽ በርካታ በጎ ፈቃደኛ የፖሊስ አባላት፣ የምርጫ አስፈፃሚዎች፣ የጥበቃ ሰራተኞች እና የንፅህና አጠባበቅ ሰራተኞች ቅዳሜና እሁድ ከሞቱት መካከል ይገኙበታል። የሀገሪቱ የምርጫ አስፈፃሚ ናቭዲፕ ሪንዋ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ለሟች የምርጫ ኮሚሽኑ ሰራተኛ ቤተሰቦች የገንዘብ ካሳ 1.5 ሚሊዮን ሩፒ ወይን 18,000 የአሜሪካን ዶላር እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል። ሪንዋ በተጨማሪም ድምጽ ለመስጠት ወረፋ ላይ የቆመ አንድ ሰው በሙቀት ምክንያት ራሱን ስቶ ወድቋል ብለዋል። መራጩ ወደ ጤና ተቋም ሲደርስ ህይወቱ ማለፉን ገልፀዋል።የኦዲሻ አውራጃ ባለስልጣናት ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ 99 ሰዎች በሙቀት ስትሮክ መሞታቸውን ሪፖርት አድርገዋል ። ከእነዚህ ውስጥ ግን 20 ብቻ ከሙቀቱ ጋር የተያያዘ ህልፈት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ የኦዴሻ ልዩ የእርዳታ ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ። ከሙቀት ጋር የሰዎች ህልፈት በቢሃር፣ማድያ ፕራዴሽ እና ጃርካሃንድ ግዛቶችም ተመዝግቧል። በሰሜን እና በመካከለኛው ህንድ እንዲሁም በአንዳንድ የምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ያለው ሙቀት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ያለማቋርጥ የቀጠለ ሲሆን ከፍተኛው የሙቀት መጠን ከ45 እስከ 46 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ደርሷል። በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 50 ከፍ ብሏል። ይሁን እንጂ የሕንድ የአየር ሁኔታ ክፍል በመጪዎቹ ቀናት የሙቀት መጠኑ ሊቀንስ እንደሚችል ገልጿል። በኤሌክትሪክ ፍጆታ መጨመር ምክንያት በርካታ ክልሎች ከፍተኛ የውሃ እና የመብራት እጥረት እያጋጠማቸው ነው። ከዋና ከተማው ዴልሂ የወጡ ቪዲዮዎች እንዳሳዩት ሰዎች ከውኃ ታንከሮች ውሃ ለማግኘት ሲጋፉ ያሳያሉ። በርካታ የመዲናዋ ክፍሎችም ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ እያጋጠማቸው ነው።
1450Loading...
29
Media files
1300Loading...
30
Media files
1400Loading...
31
Media files
1220Loading...
32
Media files
1300Loading...
33
" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው። በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦ ✔ የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣ ✔ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ #በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ #ተካቷል፡፡ ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል አለባበስን እና የተማሪዎች አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል። አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡ (Reporter Newspaper)
1330Loading...
34

1370Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
2
በጀት‼️ ለ2017 ዓ.ም የቀረበው ወደ 1 ትሪሊየን ብር የሚጠጋ የመንግስት በጀት ለምክር ቤቱ ተላከ‼️ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ። ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2017 በጀት አመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2017 ዓ.ም. የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ ፤ የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፤ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም እንዲዘጋጅ ተደርጓል። በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች ፣ ለካፒታል ወጪዎች ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ላይ ነው። በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሰፊ ሥራዎች ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሀገራችን ካላት የቆዳ ስፋት ከግማሽ በላይ የሆነው የተጎሳቆለ መሬት እንዲያገግም ለማድረግ፣ የደን ዘርፉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ለማስቻል፣ በአሁኑ ወቅት በተበጣጠሰ መልኩ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በክልል መንግስታት ፋይናንስ እየተደረገ እየተሰራ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ልማት በተቀናጀና ተገቢውን ሀብት መመደብ በሚያስችል የፋይናንስ አሰራር ስርዓት መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የአረንጓዴ አሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድን ማቋቋሚያ እና አስተዳደሩን ለመወሰን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ከዕሁድ'ለት ጀምሮ መቋረጡን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከዕሁድ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ ከጎንደር ወደ ባሕርዳር እንዲኹም ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ እንደኾኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። መንገዶቹ የተዘጉት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ባስቀመጡት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክልከላ ምክንያት መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ላለፉት አራት ቀናት ከባሕርዳር ወደ ኹሉም የጎንደር አካባቢዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልጸዋል። ከ10 ቀናት በፊት በሦስቱ የጎጃም ዞኖች ተመሳሳይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ እንደነበር ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል። አንድ ጊዜ ለአራት ወራት የተራዘመውና ባጠቃላይ ለ10 ወራት የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ለኹለተኛ ጊዜ ሳይራዘም ትናንት አብቅቷል። ኾኖም መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማብቃቱ በይፋ ያለው ነገር የለም።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2