cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መረጃ 24 ሰአት

ቶሎ ቶሎ ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶት ላይክ እና ሼር አርጉ ፈጠን ፈጠን ብለን መረጃን አንለቃለን ላይክ ያርጉ ፈጠን በሉ

Show more
Advertising posts
2 032
Subscribers
+324 hours
+47 days
-2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የ12ኛ ክፍል የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ‼️ የትምህርት ሚኒስቴር በብሔራዊ ደረጃ በወረቀትና በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና፣ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ መወሰኑ ጥያቄ አስነሳ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ዓመት በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ ተማሪዎች እንዲዘጋጁ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ የግል ትምህርት ቤቶች የትምህርት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ላፕቶፕም ሆነ ሌሎች ግብዓቶችን አዘጋጅተው በፈተና ወቅት ኢንተርኔት ከተጠለፈ ወይም ከተቋረጠ እነሱም ሆኑ ሚኒስቴሩ ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚወድቁ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል ያሉት፣ የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር ተወካይ ወ/ሮ ሐረገወይን ገረሱ ናቸው፡፡ የግል ትምህርት ቤቶች እንዲህ ዓይነት መሠረተ ልማት ያሟላሉ ወይ የሚለውን ራሱ ሚኒስቴሩ መፈተሽ እንዳለበት የተናገሩት ወ/ሮ ሐረገወይን፣ በአገር ደረጃ በትምህርት ቤቶች የኢንተርኔት አቅርቦት ተደራሽ ሆኖ ሲስተሙ በምንም ዓይነት ምክንያት ሳይቋረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ የማድረግ ተሞክሮ ስለሌለ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን ለሪፖርተር ተናግረዋ
Show all...
👍 2
የአሜሪካ ፍትህ ባለሥልጣናት፣ በኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ በቦይንግ 737 ማክስ የመንገደኞች አውሮፕላኖች ለደረሱ አደጋዎች በቦይንግ ኩባንያ ላይ ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ መግለጣቸውን የአሜሪካ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የአሜሪካ ፍትህ ሚንስቴር፣ ቦይንግ የወንጀል ክስ እንዳይመሠረትበት ከሦስት ዓመት የገባቸውን ግዴታዎች ስለመጣሱ ለኩባንያው ማሳወቁን ዘገባዎቹ አመልክተዋል። ቦይንግ ክስ ሊመሠረትበት እንደሚችል የተገለጠው፣ በቅርቡ የአላስካ አየር መንገድ ንብረት የኾነ ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ በሩ መገንጠሉንና በሌሎች አየር መንገዶችም ላይ ችግሮች መከሰታቸውን ተከትሎ ነው። ባለሥልጣናቱ ክሱን ከመመስረታቸው በፊት፣ ቦይንግ ለፍትህ መስሪያ ቤቱ የገባቸውን ግዴታዎች በምን መልኩ እንዳከበረና ምን ዓይነት የማስተካከያ ርምጃዎች እንደወሰደ እስከ ሰኔ መጀመሪያ ምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጧል። የአውሮፕላን አደጋዎቹ የተጎጂ ቤተሰቦችና ጠበቆቻቸው፣ ኩባንያው ግዴታዎቹን ጥሷል በማለት የወንጀል ክስ እንዲመሠረትበት ሲወተውቱ እንደቆዩ አይዘነጋም።
Show all...
👍 1
ባለፈው ሳምንት እሁድ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አራት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለው ሌሎች አምስት ሰዎች እንደቆሰሉ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ነዋሪዎችን ጠቅሰው ዘግበዋል። ኹለቱ ሟቾች ተሬ ቀበሌ ጉሎ በተባለ ትምህርት ቤት ከመምህራን ጋር በወላጆች ስብሰባ ላይ የነበሩ ሲኾን፣ ሌሎቹ ኹለቱ ግን በአካባቢው የነበሩ አርሶ አደሮች እንደኾኑ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በጥቃቱ፣ ኹለት ሴት መምህራን እና አንድ ወንድ መምህር እንደቆሰሉ እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተገልጧል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት፣ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል ግጭት እንዳልነበር እና የፋኖ ታጣቂዎችም ባካባቢው ሲንቀሳቀሱ እንዳልታዩ ነዋሪዎች ተናግረዋል ተብሏል።
Show all...
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ'ለት የተወያየበት የመንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ፣ የሠራተኞች የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቁም የሚጠይቅ ድንጋጌ መያዙን ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ የሚቋቋመው የደመወዝ ቦርድ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ከዘጠኝ በላይ አባላት እንደሚኖሩት በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተጠቀሰ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን፣ መንግሥት የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን ቦርድ እንዲያቋቁም በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደቆየ አይዘነጋም።
Show all...
👍 1
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጥተዋል። የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ አምባሳደሮች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህ መሰረትም ፦ 1. አምባሳደር ፍስሐ ሻውል ገብሬ 2. አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን ወልደየስ 3. አምባሳደር ለገሰ ገረመው ሃይሌ 4. አምባሳደር ደሊል ከድር ቡሽራ 5. አቶ እስክንድር ይርጋ አስፋው 6. አቶ ልዑልሰገድ ታደሰ አበበ 7. ወይዘሮ ናርዶስ አያሌው በላይ 8. አቶ ብሩክ መኮንን ደምሴ 9. አቶ ቴዎድሮስ ግርማ አበበ 10. አቶ መኩሪያ ጌታቸው ወርቁ ን በባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት እንዲሁም፦ 1 አቶ በትረ መንግስቱ ብርሃኑ 2 አቶ ዮሃንስ ፈንታ ወልደጊዮርጊስ 3 አቶ ኃይለሥላሴ ሱባ ገብሩ 4 አቶ ንጉስ ከበደ ካሳው 5 አቶ ዘሪሁን አበበ ይግዛው 6 አቶ ተሾመ ሹንዴ ሀሚጦ 7 አቶ ሌሊሳ ብርሃኑ ገለታ 8 አቶ ደረጀ በየነ ደምሴ 9 አቶ ሰብስቤ ባዴ አድባብ 10 አቶ ነብዩ ተድላ ነጋሽ 11 አቶ አንተነህ አለሙ ሰንበቴ 12 ወይዘሪት ለምለም ፍስሃ ምናለ 13 አቶ አንዋር ሙክታር መሀመድ 14 አቶ አብርሃም መንግስቱ ገመቹ ን በአምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። Via:ኢትዮ ኤፍ ኤም
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የፕላስቲክ አምራቾች የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶችን በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ስስ ፕላስቲኮችን የሚያመርቱ ድርጅቶች የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶች በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡ ፕላስቲክ በማምረት የተሰማሩ ድርጅቶችና ባለቤቶች ከተፈቀደላቸው 0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሲያመርቱ ከተገኙ፣ ከመዝጋታቸው ባሻገር፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት የእስር ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው ሪፖርተር አስነብቧል። በተጨማሪም ለኅብረተሰቡ ዳቦ የሚያከፋፍሉና ሌሎች ሸቀጦችን በፕላስቲክ ምርቶች ጠቅልለው የሚሸጡ ቸርቻሪዎችም ሆኑ አከፋፋዮች፣ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይደረጋል ተብሏል። ሸማቾች ማንኛውንም ዕቃ ሲሸምቱ የፕላስቲክ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ፣ ከወረቀትና ከጨርቅ የተሠሩትን መጠቀም ይገባል በማለት ባለስልጣኑ አመልክቷል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች የአሳ ምርት ወደ ሱዳን መላክ አልቻሉም ተባለ፡፡ ወደ ሱዳን ደረቅ አሳ ይልኩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች በግጭት ምክንያት መላክ ማቆማቸው ተነግሯል፡፡ ይህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ሚኒስትር እና የተጠሪ ተቋማት 9 ራት እቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ይገኛል፡፡ በግምገማው በሱዳን ባለው ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች የአሳ ምርታቸውን ወደ ሃገሪቱ እየላኩ አይደልም ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አምባሳደር ድሪባ ኩማ እንደተናገሩት ደረቅ አሳ ወደ ሱዳን በመላክ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች አሁን ላይ ምርቱን ወደ ሃገሪቱ መላክ አቁመዋል ብለዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ሃገሪቱ ከአሳ ምርት የምታገኝውን ገቢ እንዳታገኝ አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስራቤቱ ባለሃብቶቹ ሌሎች አማራጭ ምንገዶች እንዲጠቀሙ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
Show all...
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ! የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል። Via:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
Show all...
🔥 1
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ! የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል። የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል። አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል። Via:ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
Show all...