cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፍቅሩ ምርኮኞች

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል መከራ ፥ወይስ ጭንቀት ፥ ወይስ ሰደት ፥ ወይስ ራብ ፥ወይስ ራቁትነት ፥ ወይሰ ፍርሃት ፥ ወይስ ሰይፍ ነዉን? ሮሜ 8፥35 እሱ መቼ በፈረስ አንገት በጦር አንደበት ሰዉ ይማርክና ሰይፍ ሳይመዝ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ዉድ ህይወቱን ከፍሎ የፍቅሩ ምርኮኞች አደረገን እንጂ ማርኮናል ምርኮኞቹ ነን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
186Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1.ደስታን ፍለጋ ለዚህ ጥያቄ ግልፅ የሆነውና የመጀመሪያው ምላሽ ሰዎች ማንኛውንም አይነት ፊልም እራሳቸውን ለማዝናናት እንደሚመለከቱት ሁሉ ፖርኖግራፊንም የሚያነቃቃቸው እና ደስ የሚያሰኛቸው ነገር ከመፈለግ አንፃር ማየታቸው ነው። ከሰው መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ አንዱ ወሲብ እንደመሆኑ ሰዎች ይህንን ፍላጎት በተገቢው ሆነ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ለማሟላት፤ በገሀዱ አለም እራሳቸው ያላደረጉትን ወይም የማያረጉትን ነገር ግን ስሜታቸው የሚፈልገውን ነገር አይተው በምናባቸው ተሳታፊ ለመሆን ፖርኖግራፊን ይመለከታሉ። 2. ጭንቀት/ድብርት ብዙውን ጊዜ በድብርት እና በጭንቀት ውስጥ ያሉ ሰዎች በፖርኖግራፊ ሱስ የሚጠቁ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። በአብዛኛው በፖርኖግራፊ ብቻ ሳይሆን በሌላም የዕፅ ሱሶች የሚያዙ ሰዎች ሱስ የሆነባቸውን ድርጊት ደጋግመው እንዲያረጉ ሚገፋፋቸው ወሲባዊን ደስታን ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት ሳይሆን ውስጣቸው ከሚሰማቸው የስሜት መዋዥቅ ማለትም ጭንቀት፣ ድብርት፣ ሀዘን፣ ፍርሃት እና ሀፍረት ለማምለጥ ነው። ስለዚህ በሕይወታቸው ከባድ ጭንቀት ያለባቸውና ያልፈቱት አስጨናቂ ነገር በልባቸው ያለባቸው ሰዎች ሃዘናቸውን ለመርሳትና ጊዜያዊ ደስታ ለማግኘት ይጠቀሙበታል። በስራ ቦታቸው ላይ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ስራቸውን እየጠሉት የሚሰሩ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል። #ነገም_ይቀጥላል....... #share #share #share ሀሳብ አስተያዬት ካላችሁ 👉 @yefkeumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን: #ፖርኖግራፊ_ምንድን_ነው ? ከፓርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል! #ክፍል_ አንድ ፖርኖግራፊ ምንድን ነው? በአንድ ወቅት ‘ጉግል’ አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር። ይህ የሚያሳየን በሐገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው። ይህ ሱስ እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል። በቅድሚያ ግን ፖርኖግራፊ ምንድን ነው? ፖርኖግራፊ ቃሉ የተገኘው ‘πορνογραφία’ (pornographia) ከሚል የግሪክ ቃል ሲሆን በጥንት ጊዜ የቃሉ ትርጉም ስለ ሴተኛ አዳሪ ግልጽ በሆነ መንገድ የሚያትት ማናቸውም አይነት የስነ ፁህፍ ወይም የስነ ጥበብ ስራ ማለት ነው። ነገር ግን በአሁኑ ዘመን ይህ ከጽሁፍ እና ስዕል ወደ ቪዲዮ ምስል ማደጉን እናያለን። ማንኛውም የወሲብን ስሜት የሚቀሰቅሱ ወሲባዊ ታሪኮች፣ ፊልሞች፤ ፎቶግራፎች እንዲሁም የቃላት ልውውጥ ፖርኖግራፊ ይባላል። በአሁኑ ወቅት ሰዎች ፖርኖግራፊ ለማየት ለዚህ ከተዘጋጁ ልዩ ድህረ ገፆች ባሻገር ለዚህ አላማ ባልተዘጋጁ የማህበረሰብ መገናኛ ድህረ ገፆች ማለትም ቴሌግራም፤ ትዊተር፤ ፌስቡክ የመሳሰሉትን በመጠቀም ለፖርኖግራፊ ሱስ ተጋላጭ ይሆናሉ። በዘመናችንም ፖርኖግራፊ በቀላሉ ሊገኝ የሚችል መሆኑም ሱሱ እንደወረሽኝ እንዲዛመት አድርጎታል። ፖርኖግራፊ ሰዎችን በቀላሉ ሱሰኛ የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን ሲጋራ፣ ጫት እና የተለያዩ ዕፆች ሊያደርሱት ከሚችሉት ጉዳት በላይ ከባድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል በግልጽ ለማየት ተችሏል... #ነገም_ይቀጥላል... ከማርሲል የተወሰደ #share #share #share @yefkrumrkognoch @yefkrumekognoch
Show all...
#ስለ_ፖርኖግራፊ_ጥናቶች_ምን_ይላሉ? ስለፖርኖግራፊ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ለፖርኖግራፊ ተጋላጭ የሚሆኑት ከ11 ዓመታቸው ጀምሮ ነው። በኢንተርኔት ውስጥ ከሚገኘው ወደ ግማሽ የሚሆነው መረጃ ፖርኖግራፊ ወይም ከፖርኖግራፊ ጋር ተያያዥ የሆነ መረጃ ነው። በየቀኑ ኢንተርኔት ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 25% የሚሆኑት ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ናቸው። ከኢንተርኔት ላይ ከሚወርዱ ቪዲዮዎች መካከል 35% የሚሆነው ከፖርኖግራፊ ጋር የሚገናኙ ናቸው ። 34% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሳይፈልጉት በማስታወቂያዎች በራሳቸው ብቅ በሚሉ ሌሎች መረጃዎች ምክንያት ለፖርኖግራፊ ይጋለጣሉ። አለም ላይ ካሉ ድህረ ገጾች መካከል 12% የሚሆነው የፖርኖግራፊ ገጾች ነው። በአለማችን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያገኙ ሰዎች መካከል በፖርኖግራፊ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይገኙበታል። በሰሜን ኮሪያ በሐገሪቱ ውስጥ ፖርኖግራፊ ነክ የሆኑ ነገሮችን ማሰራጨትም ሆነ ማየት በሞት የሚያስቀጣ ነው። ለምሳሌነት የጠቀስኩላችሁ እነዚህ ሃቆች ጉዳዩ ምን ያህል ትኩረት የሚያሻው መሆኑን ያሳያሉ። ይህ በሀገራችን ብዙ የማይደፈር ርዕስ ቢሆንም ትውልድን ራሳችንንም ለማዳን ስንል ደፍረን ልንነጋገርበት ወስነናል። ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊ ይመለከታሉ? ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊን አዘውትረው ይመለከታሉ? ችግሩን መለየት በራሱ የመፍትሄው አንድ አካል ነው የሚለውን መርህ ይዘን ከብዙዎቹ ምክንያቶች ጥቂቶቹን ለመመልከት እንሞክር። #ነገ_ይቀጥላል....... #share #share #share ሀሳብ አስተያዬት ካላችሁ 👉 @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
መፍትሄ የሌለው ችግር የለም! ሁለት ጓደኛሞች ቀለል ባለ የቁምጣና የቲሸርት አለባበስ ሆነው በአንድ ጫካ ውስጥ ዘና እያሉና እየተጫወቱ ይሄዳሉ፡፡ በድንገት አንዱ ጠያቂ ሌላኛው መላሽ የሆኑበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ ጠያቂ፡- “አሁን አንበሳ ቢመጣብህ ምን ታደርጋለህ?” መላሽ፡- “ሽጉጤን አውጥቼ ግንባሩን ነዋ የምለው”፡፡ ጠያቂ፡- “እንዴ! ሽጉጡን ደሞ ከየት አመጣኸው?” መላሽ፡- “አንተስ አንበሳውን ከየት አመጣኸው?” የዚህ በልጅነታችን እንሰማቸው የነበሩትን ታሪኮች የሚመሰለው ታሪክ አስተማሪ ነጥብ፡- ለሚመጣው ለማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው! አንዳንድ ሰዎች አመለካከታቸው ሁሉ አሁን “አንበሳ ቢመጣብኝስ” የሚል ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሁል ጊዜ የሚታያቸው የሚመጣው “አንበሳ” ነው፡፡ ስለሆነም ሁል ጊዜ በፍርሃት፣ በስጋትና ገና ለገና አንድ ችግር ይመጣ ይሆናል በሚል ጠርጣራነት ነው የሚኖሩት፡፡ የዚህ ተቃራኒ ሰዎች በማንኛውም ሰዓት ችግር ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ ለሚመጣው ችግር መፍትሄ የማምጣት ብቃትም እንዳላቸው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ገና ለገና ችግር ይመጣል ብለው ከመዝናናት፣ ከመግባባት፣ ከመስራት፣ ከመውጣት፣ አዳዲሲ ነገር ከመጀመር . . . አይመለሱም፡፡ አለማችን በየጊዜው የምትጋፈጠውን እንደወቅቱ ወረርሽ ያሉ ችግርችን እንመልከታቸው፡፡ ሁል ጊዜ ግን መፍትሄ ይገኝላቸዋል፡፡ ይህ አመለካከት ከሚነሳው ችግር ጋር አብሮ የሚነሳ ብርቱነትንና “እችለዋለው” የሚል አቋምን አመልካች ነው፡፡ ገደል ካለ፣ ድልድይ አለ! በሽታ ካለ፣ መድሃኒት አለ! ጠላት ካለ፣ ወዳጅ አለ! መውደቅ ካለ፣ መነሳት አለ! ሁል ጊዜ ራእይህንና ተልእኮህ መንገድ ላይ ሊቆም የሚመጣ ችግር ካለ መፍትሄም አለ! ስለዚህ፣ ገና ለገና ችግር ይመጣል ብለህ ከመንገድህ አትገታ! @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
እውነታን የመቀበል ምርጫ አንደኛው ምርጫህ በየጊዜው በመንገድህ ላይ የሚደነቀሩ በፍጹም ልታስወግዳቸው የማትችላቸውን እንቅፋቶች ሲታገሉ መኖር ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን እውነታን ተቀብለህ፣ ዝንባሌህንና መንገድህን በመቀየር መገስገስ ነው፡፡ ታሪኩ ከተከሰተ ትንሽ ሰንበት ብሏል፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1989 ዓ/ም በጸሐፊነቱና በቀስቃሽ ተናጋሪነቱ የታወቀው ዴኒስ (Dennis Waitley) ከሺካጎ ከተማ ወደ ሎስ አንጀለስ የሚሄደውን የበረራ መስመር ቁጥር 191 ለመያዝ በመንገድ ላይ እንዳለ ትንሽ በመዘግየቱ ምክንያት በረራው ለጥቂት ያመልጠዋል፡፡ በአየር ማረፊያው ደርሶ ለመግባት ሲጣደፍ አይኑ እያየ የመቀበያውን ደጆች ሲዘጉት ተመለከተ፡፡ የዘገየው ለጥቂት በመሆኑ ምክንያት ወደ በረራው ለመግባት እንዲፈቀድለት ቢማጸንም እንኳን ስላልተፈቀደለት በጣም ይበሳጫል፡፡ በዚያው ቀን ከምሳ በኋላ ዋና ተናጋሪ ሆኖ ሊቀርብበት የሚገባው ስብሰባ ቀጠሮ በዚህ ምክንያት ተበላሸበት፡፡ ከአካባቢው ዘወር በማለት በመነጫነጭ ላይ እያለ፣ ከሃያ ደቂቃዎች በኋላ አንድ ሰበር ዜና ቀልቡን ይስበዋል፡፡ ለጥቂት ያመለጠው በረራ ገና በመነሳት ላይ አያለ በመከስከሱ በውስጡ ያሉት ሰዎች በሙሉ መሞታቸውን ተመለከተ፡፡ ንዴቱና ቅሬታው ወደ ድንጋጤ፣ ወደ ኃዘንና በኋላም “በረራው እንኳን አመለጠኝ” ወደሚል ሃሳብ ተለወጠ፡፡ ከአየር ማረፊያው ወትቶ ሆቴል በመያዝ ወደ ክፍሉ ገብቶ አረፍ ለማለት ሞከረ፡፡ በእጁ ላይ ያለውን የበረራ ትኬት በመመለስ ገንዘቡን ከመቀበል ይልቅ ትኬቱን ለማስታወሻነት ለማስቀመጥ ወሰነ፡፡ ይህ ትኬት የዘወትር አስታዋሹ ሆነለት፡፡ በአንድ ነገር በሚበሳጭበት ጊዜ ሁሉ ባለቤቱ እጁት ትይዘውና ወደዚያ ለማስታወሻነት ወደተቀመጠ የበረራ መስመር ቁጥት 191 ትኬት በመውሰድ ሁሉም ነገር ለመልካም እንደሆነ ታስታውሰዋለች፡፡ ዴኒስ፣ “እያንዳንዱ ቀን በሙሉ ኃይላችን ልንኖረው የሚገባን ስጦታ ነው” ሲል ይደመጣል፡፡ በዚህም መልእክቱ፣ መለወጥ የማንችለውን እውነታ ከመታገል ይልቅ ለመኖር ስለተፈቀደልን ደስተኞች ልንሆን እንደሚገባን ያስታውሰናል፡፡ ልክ እንደ ዴኒስ ምንም ብታደርግ ልትለውጣቸው የማትችላቸው “አናዳጅ” ገጠመኞች ዘወትር ከመንገድህ ላይ አይጠፉም፡፡ እነዚህ በየጊዜው መንገድህ ላይ የሚደነቀሩና ካሰብከው ሩጫ የሚገቱህ ገጠመኞች የሚሰጡህ ያለመመቸት ስሜት ወደ ስሜታዊነትና በዚያም ስሜታዊነት ተነድቶ ውሳኔን ወደመቀያየር ቀጠና የሚያስገባህ ከሆነ የጥሩ ምርጫ ሰው አይደለህም፡፡ ይህ አይነቱ የየእለት ገጠመኝና “እንቅፋት” በተገቢው ሁኔታ ካልተያዘ ለዋና ዋና የሕይወት አቅጣጫዎችህ እንቅፋት የሚሆንን ምላሽ እንድትሰጥ ሊጋብዝህ ይችላል፡፡ አንተ ከተረጋጋህና ከአቅምህ በላይ የሆኑትን ነገሮች ለፈጣሪ መልቀቅ ከተማርክ አንዳንድ እድል እንኳን አመለጠኝ . . . አንዳንድ ሰው እንኳን ከድቶኝ ሄደ . . . አንዳንድ የጀመርኩት ነገር እንኳን አልተሳካ . . . አንዳንድ ፍቅረኛ እንኳን እምቢ ብሎኝ ሄደ . . . የምትልበት ቀን ሊመጣ እንደሚችል ላስታውስህ! (“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ Share♻️share♻️share @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
ተጠያቂው አንተ ነህ! “ሁሉም ነገር የሚነሳውም ሆነ የሚወድቀው ከአመራር የተነሳ ነው” – John Maxwell አንተ የምትመራው የግል ሕይወትህ ዓላማ-ቢስ ከሆነ፣ ዘወትር የማይሻሻል ከሆነ፣ ዲሲፕሊን ከሌለው፣ መስመር ከለቀቀና ከተበላሸ፣ የሰው መጫወቻ ከሆነ . . . ተጠያቂው አንተ ነህ! አንተ የምትመራው ቤትና ቤተሰብ ውስጥ ምግባረ-ብልሹነት ከነገሰ፣ ጸበኝነት ከቁጥጥር ውጪ ከሆነ፣ መከባበር ከሌለ፣ የቤቱ ሁኔታና ንጽህና ቅጡን ካጣ . . . ተጠያቂው አንተ ነህ! አንተ የምትመራው መስሪያ ቤት ከተዝረከረከ፣ ስራ በትክክል ካልተሰራ፣ ሰራተኞች እንደፈለጉ ከሆኑ፣ ደንበኛ የሚጉላላ ከሆነ፣ ስራውን በትክክል የሚመራ የአሰራር ሂደት ከሌለ፣ ተገቢ ቁጥጥር ከሌለ . . . ተጠያቂው አንተ ነህ! አንተ በምትመራው አትራፊ ተቋም ውስጥ ትኩረቱ ሁሉ ገንዘብ ማግኘት ላይ ብቻ ከሆነ፣ የአቅርቦት ጥራት ከወረደ፣ ሰዎች ለሚከፍሉት ገንዘብ የሚመጥን አገልግሎት ካላገኙ . . . ተጠያቂው አንተ ነህ! አንተ በምትመራው የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ውስጥ ሁሉም የራሱን ጥቅም አሳዳጅ ከሆነ፣ ባለጉዳይ ከተጉላላ፣ ለሕዝብ የሚጠቅምና የሚጎዳ ነገር እየተለቀመና እየተለየ እርምጃ ካልተወሰደበት፣ የተጠያቂነት መዋቅር ከሌለ . . . ተጠያቂው አንተ ነህ! ከላይ በተጠቀሱትም ሆነ በሌሎች እዚህ ጋር ዘርዝረን መጨረስ በሚያስቸግሩን የግልና ማሕበራዊ ሂደቶች መሪው አንተ ከሆንክ ለሚሆነው ነገር ሁሉ ተጠያቂው አንተ ነህ፡፡ ተጠያቂነት ማለት፣ መለወጥ የምትችለውን ለመለወጥ የምትችለውን ማድረግ፣ ለመለወጥ አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ሰዎች በሚያውቁትና በሚታይ መልኩ ለመታገል መቁረጥና በሚታይ መልኩ መታገል፣ ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለበላይ አካል ወይም ለሚመለከታቸው ሁሉ ማሳወቅና ስጋትህን መግለጽ . . . ማለት ነው፡፡ አንተ ሳትወርድ የምትመራው ነገር ሊወርድ አይችልም፣ አንተ ቸልተኛ ሳትሆን የምትመራው ነገር ችላ ሊባል አይችልም፣ አንተ ዝም ካላልከው የምትመራው ነገር ሊበሰብስ አይችልም . . . ስለዚህ ሃላፊነትን ውሰድ! @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
📚ሃይማኖት ወይስ ሕይወት...???📚 👇👇👇 🔷 በዓለም ላይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች አሉ። እግዚአብሔር የለም ብለው የሚያምኑ ሰዎች እንኳን ክብደታቸው ራሱ ሃይማኖታቸው ነው። እግዚአብሔር የለም ቢሉም እንኳን ራሳቸውን ወይም አንድ ሌላ ነገር ተተኪ አድርገው ልዩ አክብሮት መስጠታቸው አይቀርም። ስለዚህ በዓለም ላይ ሃይማኖት አልባ የሆነ ሰው የለም ማለት እንችላለን። 🔶ቁም ነገሩ ግን በምን አይነት የሀይማኖት ካባ መሸፈናችን ሳይሆን ሃይማኖቴ ብለን የያዝነው እምነት ከሞት ባሻገር ለሚጠብቀን ዘላለማዊ ጉዞ ዋስትና መስጠት አለመስጠቱን ነው። የእግዚአብሔር ቃል #ለሰዎች_አንድ_ጊዜ_መሞት_ተወስኖባቸዋል_ይለናል (ዕብ 9፥27) ..በተጨማሪም “ሰው_ዓለሙን_ሁሉ_ቢያተርፍ_ነፍሱንም_ቢያጐድል_ምን_ይጠቅመዋል? #ወይስ_ሰው_ስለ_ነፍሱ_ቤዛ_ምን_ይሰጣል?” (ማቴዎስ 16፥26) 🔷ስለዚህ ሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የያዝነው ሃይማኖት የት እንደሚያደርሰን መጠየቅ አስተዋይነት ነው። ሰው ወደደም ጠላም ከሞት በኋላ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት (መንግሥተ ሰማይ) ወይም ወደ ዘላለማዊ ጥፋት (ገሃነመ እሳት) እንደሚሄድ የእግዚአብሔር ቃል ያሳስበናል። 🔶በሃይማኖት ካባ መሸፈን ብቻ በቂ እንዳልሆነ ሊያሳስበን እግዚአብሔር በነብዩ ኢሳይያስ በኩል እንዲህ ይላል “ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፥ #ልቡ_ግን_ከእኔ_የራቀ_ነውና_በሰዎች_ሥርዓትና_ትምህርት_ብቻ_ይፈራኛልና” — (ኢሳይያስ 29፥13) 🔷አንዳንድ ሃይማኖቶች የዘላለም ሕይወት ለማግኘት:- ይህን አድርግ ያንን አታድርግ በማለት የሚዘረዝሯቸው ነገሮች አሉ። ይህም ሆኖ እንኳን #የዘላለም_ዋስትና አይሰጥም። መደረግ ያለበት ነገር ሁሉ ከተደረገ በኋላ እንኳን የሚሰጡት ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ብቻ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ግን፥ #የዘላለም_ሕይወት_እንዳላችሁ_ታውቁ_ዘንድ_በእግዚአብሔር_ልጅ_ስም_ለምታምኑ_ይህን_ጽፌላችኋለሁ።” (1ኛ ዮሐንስ 5፥13) በማለት ወደ እግዚአብሔር መንግስት የመግባት ዋስትና እንዴት ማግኘት እንደምንችል ይነግረናል። ይህም ዋስትና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ተጽፎአልናል። 🔶ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ አለም የመጣው አለም የሃይማኖት እጥረት ስለነበረባት የሰው ልጅ በነበረበት በሺህ የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ላይ አንድ ተጨማሪ ሃይማኖት ለመጨመር አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚች ዓለም ስለመጣ ዋና አላማ ሲናገር ፤ #እኔ_ሕይወት_እንዲሆንላቸው_እንዲበዛላቸውም_መጣሁ።”(ዮሐንስ 10፥10) ይህም ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚች ዓለም የመጣው የዘላለም ሕይወት ዋስትና በሌላው የሃይማኖት ካባ ተሸፋፍነው ለነበሩ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ዋስትና ለመስጠት ነው። “በእርሱ ( በክርስቶስ) የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” — ዮሐንስ 3፥16 🔷ሃይማኖት ሰው ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ የሚያደርገው ጥረትና መፍጨርጨር ሲሆን፥ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ያዘጋጀልን የዘላለም ሕይወት ግን፥ በእኛ ጥረት ወይም ጽድቅ ሳይሆን ኋጢአተኝነታችንን ተረድተን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ የምናገኘው የነጻ ስጦታ ነው። ይህንን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘውን ደህንነት የተቀበሉትን አማኞች ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይላቸዋል #ጸጋው_በእምነት_አድኖአችኋልና_ይህም_የእግዚአብሔር_ስጦታ_ነው_እንጂ_ከእናንተ_አይደለም፤ #ማንም_እንዳይመካ_ከሥራ_አይደለም።(ኤፌ 2፥8-9) 🔶የዘላለም ሕይወት #ዋስትና ማግኘት የምንችለው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ብቻ ነዉ። “ኢየሱስም፦ #እኔ_መንገድና_እውነት_ሕይወትም_ነኝ_በእኔ_በቀር_ወደ_አብ_የሚመጣ_የለም።”( ዮሐንስ 14፥6)። #እነሆ_በደጅ_ቆሜ_አንኳኳለሁ_ማንም_ድምፄን_ቢሰማ_ደጁንም_ቢከፍትልኝ_ወደ_እርሱ_እገባለሁ_ከእርሱም_ጋር_እራት_እበላለሁ_እርሱም_ከእኔ_ጋር_ይበላል።( ራእይ 3፥20) በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ልብዎን ከፍተው ወደ ሕይወት እንዲያስቡ ይጠይቅዎታል። ይህንን ጥሪ መቀበሉና አለመቀበሉ የእርስዎ ምርጫ ነው። 🙏🙏🙏ፈቃደኛ ከሆኑ ይህንን ጸሎት ከልብ ይጸልዩ🙏🙏🙏 "እግዚአብሔር ሆይ! ኋጢአተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ። ሃይማኖተኛ መሆን ብቻ የዘላለም ሕይወትን ዋስትና እንደማይሰጥ ተረድቻለሁ። የሰው ልጅ በራሱ ጥረትና ጽድቅ ማግኘት ያልቻለውን የዘላለም ሕይወት ልትሰጠኝ በመስቀል ላይ መስዋዕት ስለሆንክልኝ አመሰግናለሁ። ከልጅነት ጀምሮ የሰራሁትን ኋጥአት ሁሉ ይቅር በለኝ። ወደ መንግስት ሰማይ መግቢያው መንገድ አንተ ብቻ እንደሆንክ አምናለሁ። የልቤን በር ከፍቼ፥ የሕይወት አዳኝና ጌታ አድርጌ እቀበልሃለሁ። አንተም ወደ ዘላለማዊ መንግስትህ ስለተቀበልከኝ አመሰግናለሁ። #አሜን🙏🙏🙏 ከ @okabizi 👇👇👇join and share👇👇👇 @life_of_true @life_of_true @life_of_true
Show all...
ወንጌል ስለማን ነው???? ================= ልናስተውለው የሚገባን ነገር፦ 👉ወንጌል ባለጠግነትም ድሀ መሆንም አይደለም 👉ወንጌል ልሳንም ጥምቀትም አይደለም 👉ወንጌል ከሰው ልጆች ተግባር ጋር የሚገናኝ አይደለም ❤️ወንጌል ነገር ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ጌታ ኢየሱስ ስለ ሀጥያታችን እና ስለበደላችን መሞቱን,መቀበሩን እና መነሳቱን የሚያውጅ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ የእግዚአብሔር የማዳን ሀይል ነው። ሮሜ 1 (Romans) 3-4፤ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሮሜ 1 (Romans) 16፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። 📌የወንጌል ዋነኛው መልዕክት ================== የእግዚአብሔርን የማይለዋወጥ ፍቅር ለሀጥያተኞች የሚያውጅ እና በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ሰዎች ከ እግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ እና የዘላለምን ሕይወት በነጻ በእምነት እንዲቀበሉ ኃጢአት የሚያስከፍለውን ክፍያ ለመክፈል ማለትም ከሁሉ የከፋውን ሞትን ለመሻር ክርስቶስ ከ ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ ሰው ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን የሚናገር መልካም የምስራች ነው። ( ሐዋ13:28-40,ሐዋ13:38-41፣ ሮሜ.3:21-28፣ 1ቆሮ.15:3-4)። የአብ ፍቅር የወልድ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን። ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Show all...
       በልባችን ይፍሰስ     እኛ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን መሰረታዊው ነገር ምንድነው?  ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን የስራ ሽርክና አይደለም፣ የሚያገናኘን ጉዳይ ለማስፈፀም አይደለም፣ ብድር ጥየቃም አይደለም። ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ኔትዎርኩ ፍቅር ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ፍቅር የሆነውን እግዚአብሔርን ልንገናኘው ልንቆራኘው የምንችለው በፀብ አይደለም፣ በትዕቢት አይደለም በፍቅር ብቻ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ከምድር ጋር የሚያጣብቅ ሳይሆን ወደ ሰማይ የሚስብ የሰማይ ስበት ነው።       በእግዚአብሔር ፍቅር ስንሰክር የሚባላው አንበሳ የምንጋልበው በግ ይሆንልናል፤ ስጋን ከአጥንት የሚለይ ከሰውነት ወደ አመድነት የሚለውጠው እሳት መናፈሻችን ይሆናል። ዛሬ ላይ አንበሳን አላምደው አብረውት ይሆናሉ ያላላመዱትን አንበሳ በግ የሚያደርግ ግን በእግዚአብሔር ፍቅር መነደፍ ነው። ት.ዳን 6:16 ከፍጥረት ጀምሮ እስካሁን እሳትን ተላምዶ በእሳት ባህር ውስጥ የሚመላለስ እስካሁንም አልተሰማም የእግዚአብሔር ፍቅር እሳቱን መናፈሻ አድርጎት ሶስቱ ብላቴናዎች ተንሸራሽረውበታል። ት.ዳን 3:22-25       ዛሬ እንደበረዶ የሚቀዘቅዝ፣ እንደ እሳት የሚለበልብ ዓለም ላይ እየኖርን ኑሮ ወዲህና ወዲያ ሲያላውዘን፣ ችግር እንደ ንፋስ ሲገፋን፣ መከራ እንደማዕበል ሲያዳፋን፣ ተስፋ ሳንቆርጥ ችለንና አልፈን የማንቆመው የእግዚአብሔር ፍቅር ከልባችን ላይ ስለተሟጠጠ ነው። ፍቅሩ ሲሰወርብን የእምነት ምርኩዛችን ይሰበራል። እንደሸንበቆ ተሰብሮ በማይወጋን፣ እንደ አሸዋ ቤት የማያረገርግብን ፍቅሩን አብዘተን እንታመንበት የማይጥለውን ክንዱን ምርኩዝ እናድርገው። ዓለምን የምናሽቀነጥራት ድል የነሳትን ጌታ ክርስቶስን ፍቅር የሆነውን ጌታ ክርስቶስን ስንይዝ ብቻ ነው። በውስጣችን ሃሞታችን አይፍሰስ፣ ተስፋ መቁረጥ አይፍሰስ፣ ተሸናፊነት አይግሰስ፣ ጥላቻ አይፍሰስ፣ ምቀኝነት አይፍሰስ። በልባችን የእግዚአብሔር ፍቅር ይፍሰስ። " በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።" ወደ ሮሜ ሰዎች 5 :                      ---------//---------                     ቻናሉን ይቀላቀሉ                          👇 👇 👇 @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር ✍️ እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ነው። ኢየሱስ ይወደኛል! የማውቀው ይህንን ነው! ዛሬም እግዚአብሔር እንደሚወድህ ታምናለህ? ዘላለማዊ በሆነ ፍቅር ይወድሃል! ✍️ አሁን እያለፍክበት ያለው ችግር ሳይዝህ ራስህን በተከፈተ ሰማይ ሥር፣ ከሁኔታዎች ጋር ባልተገናኘ በእርሱ ሞገስ ተከበህ ስትራመድ እንድትመለከት አበረታታለሁ።ነለወደፊትህ መልካም ነገሮች ጠብቅ። ✍️ እርሱ ለአንተ ባለው ፍቅር እመን፤ የአይኑ ብሌንና የልቡ ሀሴት እንደሆንክ በሙሉ ልብህ እመን። ከፍተኛ ሞገስ ያለህ እጅግ የተባረክና በጥልቅ የተወደድክ እንደሆንክ አስብ። ✍️ እግዚአብሔር ለአንተ ያለው ፍቅር በሁኔታዎች የማይለዋወጥ፣ እጅግ ንፁህና አስደናቂ ነው። ሁሉም ነገር ከአንተ ብቃት ጋር የተገናኘ ሳይሆን አንተ በእግዚአብሔር ዓይኖች ማን ከመሆንህ ጋር የተገናኘ ነው። ✍️ አሮጌው የሕግ ኪዳን አፅንኦት የሚሰጠው አንተ ለእግዚአብሔር ስላለህ ፍቅር ነው። አዲሱ የጸጋ ኪዳን አፅንኦት የሚሰጠው ግን እግዚአብሔር ለአንተ ስላለው ፍቅር ነው። የአብ ፍቅር የወልድ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን። ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት ♻️Share ♻️share♻️ @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Show all...
አስበኝ ዘማሪት ሰላም ደስታ 🕐7:02min 💾 6.9MB ♻️share♻️share♻️ @yefkrumrkognochu @yefkrumrkognochu
Show all...
ላይህ ናፍቃለሁ ዘማሪ አብራሃም 🕐6:17min 💾3.6MB Share share share @yefkrumrkognoch
Show all...
#የሚያስጨንቃቹን_በእርሱ_ላይ_ጣሉት። - ምንድነው የሚያስጨንቅሽ? ምንድነው የሚያስጨንቅህ? የሚያሳስባቹስ ነገር ምንድነው? የትኛውም የግልህ ጉዳይ ሊሆን ይችላል ፣ "#ማንም_አይረዳኝም" ልትዪ ትችያለሽ። ነገር ግን አንድ እውነት አውቃለሁ ፣ #ላንቺ_ካንቺ_በላይ_የሚያስብ_እግዚአብሔር_አባት_አለሽ ፤ #ላንተ_ካንተ_በላይ_የሚያስብ_እግዚአብሔር_አባት_አለህ። አባት ለልጁ እንደሚንሰፈሰፍ እና የሚያስፈልገውን ነገር እንደሚያደርግለት ፣ እንደሚጠብቀው ፣ ላንተም ከምድራዊ አባት ይልቅ የሚያስብ የሰማዩ አባት አለህ። ✅ እስቲ ካጣኸው ነገር ፣ ከሚያሳስብህ እና ከሚያስጨንቅህ ነገር ጋር ትግል #አትታገል! ፤ #ለሰማዩ_አባትህ_እድሉን_ስጠው! #ለራስህ_የምትታገል_ከሆነ_እርሱ_ለመስራት_ይቸገራል ፣ ቀለል አድርገው! ፣ ጭንቀትህን ልቀቀው! አባትህ ላይ ጣለው! ያኔ እርሱ ስለአንተ ይሰራል በሚያስፈልግህ ነገር ይሞላሃል። — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” 🧐 እስቲ የሰማይ ወፎችን ተመልከት!....... #አይዘሩም! #አያጭዱም!...... "ነገ ምን እንበላለን?" ብለው #በጎተራም_አይከቱም!። ልብስ ለብሰው መኪና ኑሮዋቸው ለቅንጦት ኑሮ አይደለም ፣ #ለዋነኛው_ለምግባቸው እንኳ ፈጽሞ አይጨነቁም! እስቲ አስተውል!....... አንዳንዴ "እንዴት ያስቀናሉ!" እስከምትል ድረስ ትገረምባቸዋለህ። አንድ ነገር ልንገርህ ፣ እንዲህ ጭንቀት የሌለበት ኑሮ የሚያኖራቸው #ያንተው_አባት እኮ ነው። — ማቴዎስ 6፥26 “ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ #የሰማዩ_አባታችሁም_ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?” ጥቅሱን በደንብ ተመልከት! <<".....#የሰማዩ_አባታችሁም ይመግባቸዋል...." ነው የሚለው እንጂ #አባታቸው አይልም። እስቲ አስበው.... አባትህ ልጆቹ ላልሆኑት ያውም እዚሁ ምድር ላይ ከዓለም ጋር ለሚጠፉ ፣ ሳይጨነቁ እንዲኖሩ ካደረገ...... ላንተ ደሞ ምን ያህል እንደሚጨነቅልህ Imagine! የሚገርመው እኮ ፣ አባትህ የሚመግባቸው እዚሁ ምድር ላይ ለሚጠፉ ፍጡራን ነው። አንተኮ ዘላለማዊ ነህ! ፈጽሞ ከእነርሱ ትበልጣለህ። ⏩ተጨንቀህ ያስጨነቀህን ነገር አታስተካክለውም! “ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?” (ማቴ 6 ፣ 27) ነገር ግን አንተ ከሁሉ አስቀድመህ #እግዚአብሔርን_ብቻ_ፈልግ! #እርሱን_ብቻ_አስቀድም! ሌላው ነገር በሙሉ እግዚአብሔር ያስተካክለዋል። የሚያስፈልግህን የሚያውቀው የሰራህ አካል እንጂ አንተ አይደለህም። እርሱን ደግሞ አባትህ ይሰጥሃል። ማቴዎስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³²..... ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ³³ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ³⁴ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል የአብ ፍቅር የወልድ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን። ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት @yefkrumrkognoch
Show all...
🔹አንድ ጊዜ አንድ ወንጌላዊ ቆሞ ሲናገር አንድ ወጣት የሀጢአት ሸክም የሀጢአት ሸክም ትላለህ ምንም የሚሰማኝ ነገር የለም ክብደቱስ ምን ያክል ነዉ? 4 ኪሎ ወይስ 36 ኪሎ ብሎ ጠየቀዉ 🔹ሰባኪዉም ክብደቱ 400ኪሎ የሆነ ጭነትን በሬሳ ላይ ብታደረግ ይሰማዋልን ? በማለት በጠየቀዉ 🔹 ወጣቱ ስለ ሞተ አይሰማዉም ሲል መለሰ ሰባኪዉም 🔹 እንግዲያውስ የሀጢአት ሸክም ያልከበዳት ነፍስ እንደዚህ የማተች ናት አለዉ @yefkrumrkognoch @yefkrumrkognoch
Show all...
የረሳነዉ እዉነት ✍ ዛሬ ዛሬ በቤተክርስቲያን ለአማኞች መሰበክ/መነገር የነበረባቸው ነገር ግን የተረሱ እዉነቶች አሉ ከእነዚህ ሊቀየሩ ከማይችሉት እዉነቶች አንዱ የገሀነም እሳት እንዳለ ነዉ። ✍ አብዛኞቻችን እረስተነዋል የገሀነም እሳት እንዳለ እንኩዋን። ቤተክርስቲያንም ማስተማር የተወችው ይመስላል። ምክንያቱም ስብከቶቻችን ሁሉ ትወጣለ ትሻገራለ ከፍታዉ ያንተ ነዉ የሚሉ ከሆኑ አመታት ተቆጥረዋል። ✍ ተመለሱ እንመለስ የዘላለም ሞት አለ ገሀነም እሳት አለ የሚል ስብከት የሰማችሀበትን ቀን እስቲ አስታውስ ✍ ስለ መመለስ ስለ ንስሀ የሚሰብኩ ሰባኪያን እየተጠሉ በፋንታዉ ስለ ምድራዊ ብልፅግና የሚሰብኩ እየተወደዱ የመጡበት ጊዜ ነዉ ብል ማካበድ አይሆንም ✍ በቤተክርስቲያን የሚሰበኩ አብዛኛውን ስለ ገሀነም እሳት ቢሆን ከቤቶቻችን ከሰፈሮቻችን ከሀገራችን ብዙዎች በዳኑ ✍ ዛሬ በሀገራችን የምንመለከተዉ ዘረኝነትም ጫፍ ባልወጣ ነበር ምክንያቱም ዘረኛ መሆን በጋነም እንደ ሚያስጥል ስለ ሚያዉቁ ✍ ወዳጄ ሆይ በመጽሐፍ ቅዱስ ገሀነም እሳት እንዳለ ስለ ሚያረጋግጥ ላስጠነቅቅ እወደለሁ ያንተ አለማመን እዉነቱን ሊለዉጥ አይችልም ወደዚያም ከመጣል ሊያስቀር አይችልም። ✍ ሰይጣን የእግዚአብሔርን ፀጋና ምህረት እንዳታይ ሊጋርድብክህ እንደ ሚችል እረዳለሁ ✍ ገሀነም የለም እያለ እንዳትፈራ ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን እንቢ አለሰማክም ልትለዉ ይገባል ✍ ለሰይጣን ለጭፍሮቹ ከተዘጋጀዉ ቦታ ነፍስክን ልታስመልጣት ይገባል። ዛሬ በመመለስ ወደ እግዚአብሔር። ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️️♻️♻️ ♻️ @yefkrumrkognoch ♻️ ♻️ ♻️ ♻️ share share share ♻️ ♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
Show all...
✝✝✝ #ተፈፀመ !!! ✝✝✝ “ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ #ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።” — ዮሐንስ 19፥30 ⚜ #ጌታ ኢየሱስ #ክርስቶስ #በቀራንዮ መስቀል #ላይ ያንቺንና #ያንተን ነገር #ፈፅሞታል ። ⚜ #በመስቀሉ ስራ #የፈፀመልን አንዳንዱን #ሳይሆን ሁሉን #ነዉ ገና #ለመፈፀም የምትሞክሩ #ወዳጆቼ ጊዜያችሁን #አታባክኑ #ያለቀን ነገር #ለመጨረስ #መሞከር ትርፉ #ድካም ነዉ ። ⚜ #ፅድቅ በስራ #ቢሆን እኛ #የእግዚአብሔር ፅድቅ #እንድንሆን ልጁን #ሀጢያት #ባላረገዉ ⚜ #በበሽታ እንድንሰቃይ #ቢሆን በመገረፉ #ቁስል #ተፈዉሳችኋል ባላለን ። ⚜ #እንድትባረክ መልካምና #በጎ #ፍቃዱ ባይሆን #እባርክሃለሁ ባላለህ ⚜ #ሀያላን ቆምጣጣዉን #መራራዉን እርሱ #የወሰደዉ የጣፈጠዉን #ያማረዉን ለእኛ #ሊሰጥ ወዶ #ነዉ ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።” — ኤርምያስ 29፥11 የሰላም ሀሳቡ ዉስጥ ዉድቀት ኪሳራ ጭንገፋ ድህነት በሽታ ......የሉም @Yefkrumrkognoch
Show all...
HE IS COMING BACK Amazing gospel song 🕐7:19min 💾 5.0MB Share share share ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
ማልዬ ማሊ ለኢየሱስ ግጥም በታገል ሰይፉ 🕐 5.16 min 💾 3.6MB Share share share ❤️❤️ የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
❤️#መልከጼዴቅ_የክርስቶስ_ምሳሌ❤️ ===================== ✍️ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን (Christ in Old Testament ) ♦️የብሉይ(የአሮጌው) ኪዳን መፅሐፍት ስለ ክርስቶስ የሚያወሩ እና ወደ ክርስቶስ የሚተረጎሙ ናቸው፡፡ ✍️ጌታ ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ስለ እርሱ እንደሚያወሩ ተናግሯል ዮሐ 5:39,45-47 ✍️በሕግ(በ5ቱ የሕግ መጽሐፍት) እና በነብያት ሁሉ ስለ እርሱ የተፃፈውን ተረጎመላቸው። ሉቃ 24:19- ✍️ መልከጼዴቅ በአብርሃም ዘመን ይኖር የነበረ እና የክርስቶስ ክህነት እና ንግስና በምሳሌ እንዲገልጥ እግዚአብሔር የተጠቀመበት ሰው ነው። ዘፍ14:17- ✍️ በእግዚአብሔር ልጅ(በኢየሱስ ክርስቶስ) ተመስሎ(ምሳሌ)ሆኖ ለዘላለም ይኖራል እንጂ ራሱ ለአብራሃም የተገለጠው ክርስቶስ አይደለም። ✍️መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ካጠናን መልከጼዴቅ በታሪክ ውስጥ የነበረ ሰው እንደሆነና የክርስቶስን ክህነታዊ እና ንጉሳዊ (ካህንም ንጉስም) አገልግሎትን ምሳሌ(ጥላ) እንዲሆን እግዚአብሔር የተጠቀመው ሰው ነበር። ✍️እናትና አባትና የለውም ሲል መጽሐፍ ቅዱስ መልከጼዴቅ የተገኘበት ወይም የተወለደበት መነሻ የለውም ማለት አይደለም። ይልቅ ግን በቀላሉ ካየን ስለ መልከጼዴቅ መነሻና ስለቤተሰቡ(ወላጆቹ) የተጻፈ ወይም የተመዘገበ ታሪክ በብሉይ ኪዳን የለም ማለት ነው። የመልከጼዴቅ ክህነት እንደ ሌዊ ልጆች ክህነት ከመነሻ ጋር ምንም ግንኙነት የለም። ✍️ዕብ ምዕ. 7፥3፤ አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። ( ይህን ሲል የመልከጼዴቅ ክህነት የተጀመረበት ጊዜና ያበቃበት በብሉይ ኪዳን ታርክ አልተመዘገበም ለማለት ነው።) "ለዘላለምም ካህን ሆኖ ይኖራል"፦ ሲል በሕይወት መኖርን ቀጥሏል ለማለት ሳይሆን መልከጼዴቅ ያገለገለው ክህነታዊ አገልግሎት ቀጥሏል ለማለት ነው። (ይህ ደግሞ የመልከጼዴቅ ሞት በመጽሓፍ ቅዱስ አለመገለጹን እንጂ መልከጼዴቅ የማይሞት መሆኑን ለማመልከት አይደለም።) ዕብራውያን 7 (Hebrews) 24፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤..... 26፤ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤ ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
Show all...
ሰላም ✍️ ሰላም ማለት በሕይወትህ ውስጥ ችግር አለመኖር አይደለም። በሕይወትህ ውስጥ ትልቅ ውድቀት ውስጥ ሆነህም ሰላምን መለማመድ ይቻላል። ✍️ ከኢየሱስ ጋር የምትለማመደው እውነተኛ ሰላምም ያ መረዳትህን የሚያልፈው ሰላም ነው። ✍️ በተፈጥሯዊው መንገድ ስናየው፣ መጥፎ ነገሮች ውስጥ ሆነህ ሰላምና እረፍት ይሰማሃል ማለት ትርጉም የሚሰጥ ነገር አይደለም፣ በመለኮታዊ መንገድ ግን በተመሰቃቀሉ ነገሮች መሃል ሆነህም በሰላም መሞላት ትችላለህ። ✍️ ዓለም ሰላም፣ ህብርና ጸጥታን የሚተረጉመው በሚሰማን ስሜት ላይ በመመሥረት ነው። ወዳጄ፣ በውስጥህ የሚሰማህን ግራ መጋባት በቋሚነት ለማረጋጋት ውጫዊ አካባቢዎችን መጠቀም አትችልም። ✍️ በውስጥህ የሚሰማህን የሚነካና ግራ መጋባትህን ወደ ሰላም የሚመልሰው ኢየሱስ ብቻ ነው። ጌታ ከአጠገብህ በመሆኑና በውስጥህ ባለው ዘላቂ ሰላም ውጫዊ አካባቢህን ማረጋጋት ትችላለህ። ✍️ ምክንያቱም በኢየሱስ ለውጥ ሁልጊዜም ከውስጥ ወደ ውጪ ነው።
Show all...
ዛረ ሆኖ ነጌን አይቶ አቀነቀነ ዘማርው እንድ ብሎ እንጌናኝ ነጌ እንገናኝ ደህና ዛሬን ለማደሩ መቸ አወቀውና ሰው ኬንቱ ሰው መንጌዱን ስያሬዝም እቅዱን ስያሴፋ ዜንግቶት ይሆናል ታይቶ እንዴምጤፋ ሰው ከንቱ ሰው ኬንቱ ( እዝ ) ሰው ኬንቱ (፮x) ጌታ ብቻ ብርቱ (፪x) ጄግና ወቶ ስቀር ጎቤዙ ስቀጤፍ ነጌን እያሰቡ ከዛሬ አለማሌፍ ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ ብይ ጤጭ እያለ ነፍሱን ስያዝናና ሞት እንዴ ዴራሽ ወንዝ ድንጌት ይመጣና ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ
Show all...
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️ ሠላማችሁ ይብዛ 〰〰〰〰〰 ዛሬ እንግዲህ ጠቃሚ የሆነ ፅሑፍ ላኩላችሁ እባካችሁ ባታስተላልፉት እንኳን አንብቡት ስለዚህ ነገር አስብ በፀሎት ሰዓት ለምን የእንቅልፍ ስሜት ይሰማናል??? ለ 3 ሰዓት የሚቆይ ፊልም ለማየት ግን ንቁ ነን መፅሐፍ ቅዱስን ስናነብ ለምን ይደብረናል??? ሌላ መፃህፍትን ስናነብ ግን የሚያስደስተን ስለ እግዚአብሔር የሚያወሩ መልእክቶችን እንዳላየ ማለፍ ለምን ቀለለብን??? ሆኖም የቀልድ ሲሆን የምናሠራጨው ⏩ ለምን የፀሎት ስፍራዎች አነሱ?? መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች ሲበዙ የተለያዩ ዝግጅቶችን መታደም እያስደሰተን ??? ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ማድረግ የሚከብደን??? ይሔንን ለሁሉም ጓደኞቻቹ አሠራጩ⏩ 80% የምትሆኑት በእርግጠኝነት ይሔን አታሠራጩም እግዚአብሔር አለ በምድር የካዳቹኝን በፍርድ ቀን እክዳችኀለሁ ልክ አንድ በር ሲዘጋ ጌታ ሁለት ይከፍታል እግዚአብሔር ሁለት በር ከከፈተላቹ ደሞ ይሄንን መልዕክት ለሁሉም ሰው ላኩ እኔን ጨምሮ... እግዚአብሔር አይፎን ባይኖረውም የእኔ ተመራጭ ቁጥር ነው.......!! ፌስቡክ አይጠቀምም ግን ምርጥ ጓደኛዬ ነው.......!! ትዊተር ® ባይጠቀምም እኔ እስካሁን እከተለዋለው.......!! እና ያለምንም ኢንተርኔት ኔትዎርክ እኔ ግን ከርሱ ጋር ተገናኝቻለሁ......!! ቴሌግራም ♻ላይ ባይኖርም ግን ሁልጊዜ በመስመር ላይ ነው........!! ይሄንን መልዕክት አስተላልፉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ✝✝ 5 ሴኮንዶችን በመጠቀም ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ለ-12 ሠዎች ንገሩና የ 12 ወራት በረከትን ተቀበሉ እኔ የራሴን ከእናንተ ጀምሬያለሁ 💚💛❤️እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ Add ✝ ✝ Share♻️♻️ በማድርግ ለሌሎች እንድደርስ 🙏🙏አርጉ🙏🙏 ❤️❤️ የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
በመተማመን ቅረብ ✍️ በታላቅ መተማመንና በደፋርነት የመኖር ቁልፍ ኃጢአትህ በሙሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደተሰረየልህ መረዳትና የእግዚአብሔር ተወዳጅ ልጅ በመሆንህ የሰማይ አባትህ ባንተ እንደማይቆጣ ማወቅ ነው። ✍️ ኃጢአቶችህ በሙሉ በመስቀል ላይ በኢየሱስ ሥጋ ላይ ተፈርዶባቸው ተቀጥተዋል፣ ይህ እውነት ነው ግን በአንተ የሆነ አይደለም። ✍️ ኃጢአታቸው ሁሉ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይቅር እንደተባለ የማይተማመኑ ብዙ አማኞች አሁንም ከጥፋተኝነት፣ ከፍርሃትና ከመኮነን ጋር እየታገሉ ነው። ✍️ እነዚህ ሰዎች በወደቁ ቁጥር ምሕረትን ለመቀበልና በሚያስፈልጋቸው ጊዜ የሚረዳቸውን ጸጋ ለማግኘት ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት ከመቅረብ ይልቅ ልክ አዳምና ሔዋን በኤደን ገነት እንደተደበቁት ሁሉ እነሱም ከሰማያዊ አባታቸው ይደበቃሉ። በማፈርና በፍርሃትም አንገታቸውን ይደፋሉ። (ዕብ4፡16)። ✍️ ግን አንተስ ኃጢአቶችህ በሙሉ ይቅር የተባሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ አለህ? ኢየሱስን ጌታህንና አዳኝህ አድርገህ በተቀበልክበት ቅፅበት ያለፈው፣ የአሁን እና የወደፊት ኃጢአትህ በሙሉ ይቅር ተብሏል። ✍️ የእግዚአብሔር ቃል በኤፌ 1፡7 ላይ “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።” ይለናል። ✍️ ዳግም ስትወለድ አንዴ በክርስቶስ ውስጥ ስለሆንክ የበደል ሥርየት ለማግኘት መሞከር አይጠበቅብህም። ✍️ ይህ የኃጢአት ሥርየት የተገኘው አንተ በሠራኽው ሥራ ሳይሆን እርሱ በጸጋው ባለጠግነት የሰጠህ አንተ ያልከፈልክበትና ያልተገባህ ሞገስ ነው! የአብ ፍቅር የወልድ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን። ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
Show all...
 ደሙ ከኩነኔ ይጠብቅሃል ✍️ ኢየሱስ ተላልፎ በተሰጠበት ምሽት ስለ ደሙ ምን እንዳለ ታውቃለህ? በመጨረሻው ራት ወቅት ኢየሱስ ፅዋውን አንስቶ “ይህ ለእናንተ ጥበቃ የፈሰሰው የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው" ብሏል? በጭራሽ! ✍️ እርሱ ያለው “ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴዎስ 26÷28) ነው። ደሙ የፈሰሰው ለኃጢአትህ ይቅርታ ነው። የኢየሱስ ደም ይጠብቀናል? ✍️ አዎን፣ በእርግጥ ይጠብቀናል! ደሙ ከዲያብሎስ ጥቃቶች ቢጠብቀንም የኢየሱስ ደም የፈሰሰበት ዋነኛ ምክንያት ግን ይህ አይደለም። ✍️ ወዳጄ የአዳኛችን ደም የፈሰሰበት ዋናው ምክንያት ስለ ኃጢአታችን ይቅርታ ነው። ይህ ማለት የኢየሱስ ደም በተጨማሪም ከየትኛውም አይነት ኩነኔ ጥበቃ ያደርግልናል። ✍️ የኢየሱስ ደም ጻድቅ እንዳደረገህና ኃጢአትህ ሁሉ ይቅር እንደተባለ መገለጥ ካለህ፣ ከከሳሹ ከሚመጣብህ ኩነኔ ሁሉ ተጠብቀሃል ማለት ነው። ይህንን መረዳት ይገባሃል። ✍️ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዙፋን በድፍረት ለመቅረብና እርሱን እንደ አፍቃሪ አባት ለማየት መተማመን ይሰጥሀል። ✍️ ከኩነኔ መጠበቅህን ማወቅ በኃጢአት፣ በሱስ፣ ወይም ዛሬ በእስራት በያዘህ ነገር ላይ ሁሉ እንድትነግሥ ያደርግሃል። የአብ ፍቅር የወልድ ጸጋ የመንፈስ ቅዱስ ሕብረት ከእናንተ ጋር ይሁን። ሀሳቡን ከወደዱት ሼር ያርጉት
Show all...
ትንሽ አረፍ በል እስቲ !!! በሕይወትህ ልትሰራቸው ከምትችላቸው ስህተቶች መካከል አንዱ ካለማቋረጥ በማሕበራዊ ግንኑነትና በስራ የመጠመድ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ልምምድ ያላቸው ሰዎች ብዙ ስለሰሩ፣ ከብዙ ሰው ጋር ስለተገናኙ፣ ያለእረፍት እዚህና እዚያ ስለተሯሯጡ ሙሉ ሕይወት የኖሩ ይመስላቸዋል፡፡ የዚህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤ መጨረሻው ዝለት ነው፡፡ የዝለት ምልክቶች በቀናት ወይም በወራት ውስጥ የሚከሰቱ አይደሉም፡፡ ቀስ በቀስና ሳናውቀው ስር የሚሰዱና በመጨረሻ ወደ ፊት መቀጠል ሲያቅተው የሚታወቁን ስሜቶች ናቸው፡፡ የመዛል ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡፡ • ቀድሞ እንጓጓበት በነበረ ነገር አለመጓጓት፡፡ • አቅም የማጣት ስሜት፡፡ • ተስፋ ቢስ ስሜት፡፡ • የባዶነት ስሜት፡፡ • ከሰዎች የመለየት ስሜት፡፡ • የድብርት ስሜት፡፡ • የአሉታዊ (ጨለምተኛ) ስሜት፡፡ • የጭንቀት ስሜት፡፡ • የመነጫነጭና የቁጣ ስሜት፡፡ • እንቅልፍ ማጣት፡፡ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የስሜት ቀውሶች አንድ ሰው ለራሱ እረፍት ሳይሰጥ ካለማቋረጥ ወዲህና ወዲያ ሲል የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ምን ላድርግ? • በቀን መካከል ከስራህና ከማሕበራዊ ግንኑነት ውጪ የምታሳልፍበት የብቻ ጊዜ (Reflection Time) ያስፈልግሃልና በተቻለህ መጠን ያንን አድርግ፡፡ • አንዳንድ ጓደኝነት ወይም የፍቅር ግንኙነትህ (ትዳርን አይጨምርም) መልስ ያጣ ጥያቄ፣ አለመግባባትና ግርግር ሲበዛው እረፍት ያስፈልግሃልና ብቻህን የምታሳልፍባቸው ቀናትን፣ አስፈላጊ ከሆነ ሳምንታትን አመቻችና ከነሱ ነጠል ብለህ እረፍ፡፡ • በአመት ውስጥ ቢያስን አንድ ጊዜ ከስራም ሆነ ከማንኛውም የማሕበራዊ ሕይወት ዑደት ዘወር የምትልበት እረፍት ያስፈልግሃልና በተቻለህ መጠን ያንን አድርግ፡፡ • አልፎ አልፎ ከቴሌቭዢን፣ ከሶሻልሚዲያ በመኪና ውስጥ ከሚደመጡ ሙዚቃዎች፣ ጫጫታና ከፍ ያለ የሙቃ ድምጽ ካለባቸው ካፌና ምግብ ቤቶች . . . ራስህን ገለል አድረግና ለጆረህ እርፍት፣ ለአእምሮህ ሰላም ስጠው፡፡ • አልፎ አልፎ በሰዎች ላይ፣ በመሪዎች ላይ፣ በተቋሞች ላይ ካለህ ጠንካራና የተቃውሞ አመለካከት ረገብ በልና የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ስለመስጠትና ስለደጋፊነት አስብ፣ ተግብር፡፡ ትንሽ አረፍ በል እስቲ !!!
Show all...
ሁኔታውን መቆጣጠር ካልቻልክ ትኩረትህን ተቆጣጠር መቆጣጠር የማትችለው ነገር ላይ ትኩረትህን ማድረግ እጅግ አድካሚ ነገር እንደሆነ በማስታወስ ልጀምር፡፡ በቤተሰብ ግንኙነት፣ በስራ ቦታ፣ በትምህርት ቤትና በመሳሰሉት ማሕበራዊ ሂደቶችህ ውስጥ ፈጽሞ መቆጣጠር የማትችላቸው ነገሮች ያጋጥሙሃል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ሁኔታውን መቆጣጠርና መለወጥ ከቻልክ ያንን አድርግ፣ ካልቻልክ ግን ጊዜ ሳታባክንና የሕይወት ቀውስ ሳታተርፍ ትኩረትህን መቆጣጠርና መለወጥ አስፈላጊ ነው፡፡ በፍጹም ልትለውጣቸው የማትችላቸው ቤተሰቦች ካሉህ፣ ትኩረትህን ለውጥ፡፡ ምናልባት ለአንተ ትኩረት መለወጥ ማለት ቤተሰቦችህን ማክበር ሳትተው ከእነሱ ከምትጠብቀው ነገር ላይ ትኩረትህን ማንሳት ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ አነሱን ለመለወጥና ለመቆጣጠር ከመሞከር የራስህን ስሜት ለመለወጥና ለመቆጣጠር ሊሆን ይችላል፡፡ መቆጣጠርም ሆነ መለወጥ የማትችለው ማንኛውም አይተነት ጓደኛ ካለህ፣ ትኩረትህን ለውጥ፡፡ ምናልባት ለአንተ ትኩረት መለወጥ ማለት አንድን ነገር ከጓደኛህ እየጠበክ ባለማግኘትህ ከመቁሰል ይልቅ ፍላጎትህን ከሌላ አቅጣጫ ለማሟላት የትኩረት ለውጥ ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ እውነት በስራም ሆነ በሌሎች ማሕበራዊ ግንኙነቶቻችን ውስጥ ልንጠቀምበት የምንችለው አስገራሚ መርህ ነው፡፡ ደግሜ ላስታውስህ፣ መቆጣጠርና መለወጥ በማትችለው ሰውና ሁኔታ ላይ ችክ ብለህ ዘመንህን ከምታቃጥል ትኩረትህን ተቆጣጠር፣ ትኩረትህን ለውጥ፡፡ ይህንን አለማድረግ ማለት ምንም ያህል ደጋግመን ብንተኩስ የማንመታው ኢላማ ላይ ማነጣጠርና መተኮስ ማለት ነው፡፡ መቆጣጠርና መለወጥ የማንችለው ነገር ላይ ትኩረትን ማድረግ . . . • ጊዜንና ጉልበትን ያባክንብናል • የስሜት ቀውስ ያስከትልብናል • ሁል ጊዜ፣ “ለምን?” ከሚለው ጥያቄ ሳንወጣ እንደተወጠርን እንኖራለን • ጉዳያችንን ከራሳችን ጋር ማድረግ ትተን ከሰዎች ጋር በማያዘዝ ስንጓተት እንድንኖር ያደርገናል
Show all...
ሶስቱ በፍጹም ልትንቃቸው የማይገቡህ ውብ ስጦታዎች “አንድን ነገር ባካበድከው ቁጥር ፈላጊው ይበዛል፤ ቀለል ባደረከው ቁጥር ደግሞ ችላ ይባላል” ሲባል ሰምተህ ይሆናል፡፡ “ሰውን በቀላሉ ስትገኝለት አቅልሎ ያይህና ይንቅሃል፣ ራስህን ስታካብድና አልገኝ ስትል ደግሞ በብርቱ ይፈልግሃል፣ ያከብርሃል” የሚባልም አባባል አለ፡፡ ይህንን የተለመደውን የሕብረተሰቡን አመለካከት ስለሚያውቁ ይሆን ሰዎች ላለመናቅ ሲሉ ራሳቸውን በማካበድ ሩቅ የሚደርጉት? ምንም ያህል ቀለል ብለው ቢቀርቡልህ በፍጹም እንደቀልድ፣ እንደቀላልና አንደ ነጻ ልትወስዳቸው የማይገቡሁ ሶስት ስጦታዎች አሉ፡፡ 1. ሰው ጊዜውን ሲሰጥህ አንድ ሰው እንዳከበረህ ከምታውቅበት መንገድ አንዱ ጊዜውን ሲሰጥህ ነው፡፡ በሰው ሕይወት ውስጥ ውድ ከተባሉ ነገሮች መካከል ጊዜው አንዱ ነው፡፡ ሰው ጊዜውን በነጻ ሲሰጥህ ሰውየውን አክብረው፣ አመስግነው፣ ለሰጠህ ጊዜ ተጠንቀቅለት፣ ለሰጠህ ጊዜ የሚመጥን ነገር ይዘህ ቅረብ፣ በሰዓቱ ተገኝ . . . እንጂ ጊዜ ስለተረፈው እንዳገኘህ አትቁጠር፡፡ ይህ ሰው የሰጠህን ጊዜና በዚያች ሰዓት የሚያልፍበትን የእድሜ ደረጃ እድሜ ልኩን ተመልሳ ስለማትመጣ አያገኛትም፡፡ ምን ያህል እጅግ ውድ የሆነ ነገር እንደሰዋለህ አስብ፡፡ 2. ሰው ገንዘቡን ሲሰጥህ አንድ ሰው እንዳከበረህ ከምታውቅበት መንገድ ሌላኛው ገንዘቡን ሲሰጥህ ነው፡፡ ሰው በእጁ የገባውን ገንዘብ ያገኘው ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን፣ አንዳንዴም ጤንነቱን ሰውቶ ስለሆነ ገንዘብ በሰው ሕይወት ውስጥ ሌላው ውድ የተባለው ነገር ነው፡፡ ማንኛውም አይነት ሰው፣ ሃብታምም ሆነ ሃብት የሌለው፣ ምንም ያህል የገንዘብ መጠን በስጦታም ሆነ በግብዣ መልክ አንተ ላይ ሲያፈስስ እንደቀላል አትቁጠረው፡፡ ለምን ከዚያ የበለጠ አልሰጠኝም በማለት አትነጫነጭ፣ ሳታመሰግነውም አትለፍ፡፡ 3. ሰው ራሱን ሲሰጥህ አንድ ሰው እንዳከበረህና እንደወደደህ ከምታውቅበት መንገድ እጅግ የላቀው ደረጃ ራሱን ሲሰጥህ ነው፡፡ አንድ ሰው ራሱን የሰጠህ በጓደኝነት፣ በፍቅረኛነትም ሆነ በእውነተኛ የስራ አጋርነት፣ ይህ ሰው ሊሰጥህ ከሚችላቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ የከበረውን ነገር እንደሰጠህ ልታስታውስ ይገባሃል፡፡ አንድ ሰው ራሱን ለአንተ ከመስጠቱ የተነሳ ያለፈ ታሪኩን፣ የዛሬ ኑሮውንና የወደፊቱን እቅዱን እርግፍ አድርጎ ስለነገረህ ሞኝና ርካሸ አድርገህ ከቆጠርከው ተሳስተሃል፡፡ በምንም አይነት የቅርበት ደረጃ ራሱን ክፍት አድርጎ የሰጠህን ሰው የክብርን ሁሉ ክብር ልትሰጠው ይገባሃ፡፡
Show all...
የተንጠለጠለ ሕይወት አንድ ሰው እንዲህ አለ፣ “ነገ አለም ያበቃላታል ብባል እንኳን ዛሬ ዘርን ከመዝራት አላቆምም”!!! ገና ለገና ነገ አንድ ነገር ይሆንልኛል ወይም ይሆንብኛል በማለት ዛሬን መኖር የሚገባቸውን ኑሮ በማቆየት የሚንጠለጠሉ ሰዎች አሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ ነገ ይሆናል ብለው በሚጠባበቁት ነገር ምክንያት ተንጠንልጥለው የዛሬን ሕይወት ከመኖር ይገታሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎቸ ፈጽሞ ያላረፈና የተንጠለጠለ ሕይወት ነው ያላቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱ አይነት ሰዎች በአውቶቡስ ተሳፍረው ሲሄዱ ገና ለገና በቅርቡ እወርዳለሁ በማለት የማይቀመጡ፣ የማያርፉና ከማንም ተሳፋሪ ጋር የማይግባቡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ እስኪወርዱ ምናለበት ቢያርፉ? መውረጃቸው እስኪደርስ ምናለ ቢጫወቱና ቢግባቡ? ገና ለገና ነገ ይመጣልናል ወይም ይመጣብናል ብለን ለምንጠብቀው ነገር የዛሬን ሕይወት ማቆምና መሰዋት የሞኝነት ሁሉ ሞኝነት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና በቅርቡ ውጪ ሃገር እሄዳለሁ በሚል ተስፋ ምክንያት ትምህርትና ስራን መከታተልን ትተው ቁጭ ብለው የመሄጃ ቀናቸውን ይጠብቃሉ፡፡ እንዴት ያለ የባከነና ሕይወት??!! አንተ ግን ነገ ውጪ ሃገር ትሄዳለህ ብትባልም እንኳን ዛሬ መስራት ያለብህን ከመስራት አታቁም፡፡ በመጨረሻ ጉዞው ከተሳካ ትጋትህንና ትርፉን ይዘህ ትሄዳለህ፤ ካልተሳካ ደግሞ ትጋትህንና ትርፍህን ይዘህ እዚሁ ትቀጥላለህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና አንድ ሰው አንድን ነገር አደርግልሃለሁ ስላላቸው ብቻ የግል ጥረታቸውን ትተው ቁጭ ብለው ያንን ተስፋ ይጠብቃሉ፡፡ እንዴት ያለ የተንጠለጠለ ሕይወት??!! አንተ ግን አንድ ሰው አንድን ነገር አደርግልሃለሁ ቢልህም እንኳን ያንን ነገር በራስህ ጥረት ለማምጣት ያለህን እንቅስቃሴ አታቁም፡፡ በመጨረሻ ሰዎቹ ካደረጉልህ ድርብ ውጤት ይሆንልሃል፤ ካላደረጉልህ ደግሞ የጀመርከውን ጥረት ይዘህ ትቀጥላለህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች አንድ ሰው አፈቅርሃለሁ/አፈቅርሻለው ስላላቸው ብቻ ትኩረታቸውን ሁሉ ቀድሞ ከነበራቸው ዓላማና ግብ ላይ አንስተው ቁጭ ብለው ያንን ሰው ይጠበብቃሉ፡፡ እንዴት ያለ አንዱን ጥሎ አንዱን የማንሳት ስህተት??!! አንተ ግን እንደተፈቀርክ ቢነገረህም እንኳን ዓላማህን ከመከታተል ወደኋላ አትበል፡፡ ፍቅሩ እውን ከሆነና ከጸና ዓላማህም ይዘህ ወደፍቅር ሕይወት ትገባለህ፤ ፍቅሩ ካልጸና ደግሞ ዓላማህን ይዘህ ወደፊት ትቀጥላለህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና አንድ ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ አለብኝ ብለው በማሰብ ዓላማን ከመያዝ፣ ከመስራት፣ ከመማርና ከማሕበራዊ ግንኙነት ራሳቸውን በመግታት ቁጭ ብለው አንድ ድንገተኛ ነገር እስከሚመጣ ይጠብቃሉ፡፡ እንዴት ያለ የታሰረ ሕይወት??!! አንተ ግን ነገ አንድ ነገር ቢደርስብኝና ሕይወቴ ቢያልፍስ በሚል ስጋት ዛሬን መኖርንና ማጣጣምን አታቁም፡፡ የፈራኸው አይደርስም እንጂ፣ ከደረሰ የነበረህን ጊዜ በመጠቀምህ ደስተኛ ትሆናለህ፤ ካልደረሰ ደግሞ የነበረህን ሕይወት በማጣጣም ትቀጥላለህ፡፡ የነገው ቢሆንም ባይሆንም፣ ቢመጣም ባይመጣም ያንን ሲጠብቁ ዛሬን ተንጠልጥሎ በከንቱ ከማሳለፍ ይልቅ አረፍ ብሎ ሕይወትን እየኖሩና እያጣጣሙ መቀጠል ይሻላል፡፡
Show all...
“ለምን?” ብለህ ጠይቅ! አንዲት ሴት ሁል ጊዜ ድፎ ዳቦን ከጋገረች በኋላ ዳቦው በስሎ ሲወጣ ሙሉ ዳቦ ሳይሆን የግማሽ ድፎ ዳቦ ቅርጽ ይዞ ነው የሚወጣው፡፡ እቤቷ ደጋግመው በመጋበዝ የሄዱ ወዳጆቿ ሁኔታውን እየታዘቡ ከከረሙ በኋላ፣ ምናልባት የመጋገሪያ ሳህኗ በግማሽ የተቆረጠ ሰባራ ይሆናል ብለው በመመካከር የተጋገረውን ዳቦ ገና ከምድጃ ሲወጣ ሲያዩት ሊጥ ተደርጎበት ወደምድጃ የገባው ሳህን ምንም ጉድለት እንደሌለውና ዳቦው በስሎ ሲወጣ ግን ግማሽ ሆኖ አዩ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር፣ “ለምንድን ነው ሙሉ ሳህን እያለሽ ሁል ጊዜ ግማሽ ዳቦ የምትጋግሪው?” ብለው የጠየቋት፡ ስትመልስም፣ “ከልጅነቴ ጀምሮ እናቴ እንደዚያ ሰትጋግር ስላየሁኝ ነው” አለቻቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ወደ እናቷ በመሄድ ለምን ግማሽ ዳቦ ይጋግሩ እንደነበረ ሲጠይቋቸው እሳቸውም እናታቸው (የልጅቷ አያት) እንደዚያ ይጋግሩ ስለነበረ መሆኑን ተናገሩ፡፡ አያትየው በሕይወት ስለሌሉ እሳቸው በሕይወት ሳሉ የቅርብ ወዳጃቸው የነበሩ አንዲት በእድሜ ጠና ያሉ ሴት ተገኙና የዚህች ልጅ አያት ግማሽ ዳቦ ይጋግሩ እንደበረና ከጋገሩስ ለምን ያንን ያደርጉ እንደነበረ ሲጠየቁ፣ “ለረጅም ጊዜ ዳቦ ትጋግርበት የነበረው ሳህን ተሰብሮባት ስለነበረ ሌላ ለመግዛት ስላልፈለገች በሰባራው ሳህን ዳቦ ትጋግር ስለነበረ ነው ግማሽ ዳቦ ይወጣ የነበረው” አሉ፡፡ አያት በተሰበረ ሳህን ምክንያት የጀመሩትን በግማሽ ዳቦ የመጋገር ልማድ እናት ምንም እንኳን ያልተሰበረ ሳህን ቢኖራቸውም “ለምን?” ብለው ባለመጠየቃቸው ምክንያት በሙሉ ሳህን ግማሽ ዳቦን ሲጋግሩ ኖረው ለልጅ አስተላለፉት፡፡ ልጅም፣ “ለምን?” ብላ ሳትጠይቅ በሙሉ ሳህን ግማሽ ዳቦን በመጋገር ቀጠለች፡፡ እነዚህ ወዳጆቿ “ለምን?” ብለው በመጠየቃቸው ምክንያት መነሻውን ላይ በመድረስ ከነገሯት በኋላ በነበራት “ለምን?” ብሎ ያለመጠየቅ ሞኝነት በመበሳጨት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሙሉ ሳህን ሙሉ ዳቦን መጋገር ጀመረች፡፡ ቤተሰብህን አክብር፣ የተለመደውን የኑሮ ዘይቤ ግን “ለምን?” ብለህ ጠይቅና አሻሽል! የመስሪያ ቤት አለቆችህን አክብር፣ የተለመደውን የአሰራር ሂደት ግን በትህትና “ለምን?” ብለህ ጠይቅና የተሻለን አሰራር ቅደድ፡፡ ለሕብረተሰቡም ሆነ ለሃገርህ መሪዎች ተገቢውን ክብር ስጥ፣ የተለመደውን አሰራር ዜይቤ ግን “ለምን?” ብለህ በመጠየቅ እንዲያሻሽሉ ግፊትን አድርግባቸው፣ አንተ ተራህ ደርሶ መሪ ስትሆን ደግሞ የተለመደው አሮጌ አሰራር “ለምን?” ብለህ በመቀየቅ ወደተሻለው ቀያይረው፡፡ በተሰማራህበት የንግድ ዘርፍ የተሰማሩትን ሌሎች ነጋዴዎች አክብር፣ የተለመደውን የአነጋገድ ልማድ ግን “ለምን?” ብለህ ጠይቅና አዲስ አሰራር ቅደድ፡፡ እንደኛው ሃገር አይነት ለሺዎቹ አመታት የተመረገ አመለካከት ባለበት ሕብረተሰብ ውስጥ ያንን የተለመደውንና የተመሰረተውን አሮጌና ውጤተ-ቢስ አሰራርና አመለካከት ለመቀየር መሞከር ግፊያንና ሙግትን እንደሚያስነሳ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም፣ ምንም ለውጥ የማያመጣን የተለመደ፣ ያረጀና ያፈጀ ልማድ ይዞ ኋላ ቀር ሆኖ ከመቅረት፣ ለምን?” ብሎ በመጠየቅ ወደ አዲስ ቀጠና መግባት ይሻላል፡፡ አንድ ነገር ለብዙ ጊዜ ስለተደረገ ብቻ አላደርገውም! “ለምን?” ብዬ እጠይቃለሁ! አንድን ነገር ብዙ ሰው ስላደረገው ብቻ አላደርገውም! “ለምን?” ብዬ እጠይቃለሁ! አንድን ነገር ቀላል ስለሆነ ብቻ አላደርገውም! “ለምን?” ብዬ እጠይቃለሁ!
Show all...
አንተ ካልወሰንክ ሌላ ሰው ይወስንልሃል! የአሜሪካ 40ኛው ፕሬዘዳንት ሆኖ ያገለገለው ሮናለድ ሬገን (Ronald Reagan) ውሳኔ የማስተላለፍን አስፈላጊነት ገና በልጅነቱ እንደተማረ ይናገራል፡፡ ገና በልጅነቱ አንድ ጊዜ አክስቱ አዲስ ጫማ ልታሰራለት ወደ ጫማ ሰሪ ቤት ወሰደችው፡፡ ጫማ ሰሪው እግሩን ከለካው በኋላ “እንዲሰራልህ የምትፈልገው ጫማ ቅርጹ ከእግር ጣቶች ጋር ክብ እንዲሆን ነው ወይስ አራት ማዕዘን እንዲሆን ነው የምትወደው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሮናልድ ሬገን መወሰን አቅቶት ሲወላውል ጫማ ሰሪው፣ “ችግር የለውም ትንሽ ቀናት አስብበትና ትነግረኛለህ” አለው፡፡ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ጫማ ሰሪው ሬገንን መንገድ ላይ አገኘውና፣ “የጫማውን ቅርጽ ጉዳይ ወሰንክ?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሬገንን፣ “ገና አልወሰንኩም” ብሎ መለሰለት፡፡ ጫማ ሰሪው “እሺ” ብሎ መንገዱን ከቀጠለ በኋላ በሚቀጥለው ቀን ጫማውን ሰርቶ እቤቱ ድረስ ላከለት፡፡ ሬገን ጫማውን ሲያየው የቀኝ እግር ጫማው ቅርጽ ክብ፣ የግራ እግር ጫማው ቅርጽ ደግሞ አራት ማዕዘን መሆኑን በመመልከት በጣም ደነገጠ፡፡ “ከዚያን ጊዜ ጀምሮ” ይላል ሬገን፣ “እነዚያን የግራና የቀኝ እግር ጨማዎች ባየኋቸው ቁጥር ስለ ውሳኔ ትልቅ ትምህርትን ያስታውሱኝ ነበር፡- “አንተ የራስህን ውሳኔ ካልወሰንክ፣ ሌላ ሰው ለአንተ ይወስንልሃል፡፡ የውሳኔውን ውጤት የምትኖረው ግን አንተው ነህ”፡፡ በሕይወትህ በፍጹም ለሰው የማትተዋቸው “ወሳኝ ውሳኔዎች” እንዳሉ ታውቃለህ? በተለይም የሕይወትህን አቅጣጫ እስከወዲያኛው በሚያስቀይሩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔህን ችላ ባልከውና ሰው እንደፈለገ እንዲያደርገው በፈቀድክ ቁጥር ሌላ ሰው ይወስንልሃል፡፡ በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ሌላ ሰው የወሰነልህን ውሳኔ መራራ ፍሬ እየበሉ እንደመኖር አስቀያሚ ነገር የለም፡፡ በሕይወታችን “ሁለት አይነት ጫማ አድርገን” ወዲህና ወዲያ የምንንገላታው የምንፈልገውን ነገር ቁርጥ አድርገን አውቀን ውሳኔያችንን እኛው ስላልወሰንን ነው፡፡ በጥንቃቄ፣ በጥበብና በሚዛናዊነት ከሰው ምክርንና ጥበብን ለመቀበል ክፍት የመሆንህን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ . . . • የሕይወትህን ዓላማ አስመልክቶ ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡ • የቀረውን ሕይወትህን ከማን ጋር በፍቅር እንደምትኖር ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡ • የምትማረውን የትምህርት ዘርፍ አስመልክቶ ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡ • ከፈጣሪ የተቀበልከውን ማንነትህን የመኖርና ራስህን የመሆንህን ጉዳይ አስመልክቶ ውሳኔህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ፡፡ ሰዎች በአንተ ውስጥ ሆነው የመኖራቸውና የመወሰናቸው ዘመን ያብቃ!
Show all...
ካለምክ አይቀር ትልቅ ሕልም ይኑርህ!!! “ቺክን ሱፕ ፎር ዘ ሶል” ("Chicken Soup For the Soul") ዝነኛ መጽሃፉ ላይ ጃክ ካንፊልድ (Jack Canfield) አንድን አስገራሚ እውነተኛ ታሪክ አስፍሯል፡፡ በካሊፎንያ ግዛት ውስጥ ሳን ሲድሮ በተሰኘ ስፍራ አንድ ሞንቴ ሮበርትስ (Monty Roberts) የተባለ ሰው ትልቅ ፈረስ የሚያረባበትና የሚያሰለጥንበት እርሻ አለው፡፡ የዚህ ባለሃብት ጅማሬ ድንቅ ታሪክን ያዘለ ነው፡፡ የሞንቴ አባት ከስፍራ ወደ ስፍራ እየተዘዋወረ ፈረሶችን በማሰልጠን የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡ የሞንቴም ሕይወት ወዲህና ወዲያ ከሚዘዋወር አባቱ ጋር የተቆራኘ ስለነበር ትምህርት ቤቱን በማቋረጥ ደጋግሞ ከአባቱ ጋር ይዘዋወር ነበር፡፡ አንድ ጊዜ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ ሳለ አስተማሪያቸው ወደፊት መሆን የሚፈልጉትን ሕልማቸውን በጽሑፍ አቀናብረው እንዲመጡ የቤት ስራ ሰጣቸው፡፡ ሞንቴ ማታ እቤቱ በመግባት ሰባት ገጽ ሙሉ ወደፊት ማድረግና መሆን ስለሚፈልገው ነገር ጻፈ፡፡ ወደፊት የፈረስ እርባታና ማሰልጠኛ ያቀፈ ትልቅ እርሻ እንዲኖረው እንደሚፈልግና ያንንም ግቡን የሚገልጽ ጽሑፍ ነበር፡፡ ከዚህ ግቡ ጋር የእርሻውን ንድፍ በስእል መልክ በማስፈር ለተመልካቹ ግልጽ በሆነ መልኩ አስፍሮት ነበር፡፡ ከ80 ሄክታር ያላነሰ ስፍራን አልሞ ነበር፡፡ ይህ ሕልም ቀድሞውኑ በውስጡ ሲብላላ የነበረ ጉዳይ ስለነበረ ጊዜን ሰጥቶትና በጥራት በመስራት በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪ አስረከበው፡፡ ከሁለት ቀናት በኋላ ውጤት የያዘውን ወረቀቱን አገኘ፡፡ በወረቀቱ ፊት ለፊት ገጽ ላይ በቀይ “F” ተጽፎበታል፡፡ ከውጤቱ በታች ደግሞ፣ “ክፍለ ጊዜው ሲያልቅ ወደ ኋላ ቀርተህ አነጋግረኝ” ይላል፡፡ ሕልመኛው ሞንቴ ከክፍለ ጊዜው በኋላ አስተማሪውን ለማግኘት ሄደ፡፡ ገና አስተማሪውን እንዳገኘው፣ “F ያገኘሁት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቀው፡፡ አስተማሪውም በመመለስ፣ “እንዳንተ ላለ ወጣት ይህ ሕልም ትንሽ ቅጥ ያጣ ነው፡፡ ገንዘብ የለህም፣ ኑሮን ለመግፋት ወዲህና ወዲያ በመዞር የሚሰራ ቤተሰብ ነው ያለህ፡፡ ባጭሩ ምንም ነገር የለህም፡፡ የፈረስ ማርቢያ እርሻ ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ መሬት መግዛት አለብህ፣ እርባታውን ለመጀመር ቅድመ ክፍያ ያስፈልግሃል፣ ለእርባታ የሚሆኑ ፈረሶችን ለማግኘት ገንዘብ ይጠይቅሃል” በማለት ሕልሙ ላይ መድረስ የማይችልበትን የምክንያት አይነት ደረደረለት፡፡ በመጨመርም፣ “ይህንን ምኞትህን እውን ልታደርግበት የምትችልበት ምንም መንገድ ሊኖር አይችልም፡፡ ቀለል ያለ ግብን ጽፈህ ከመጣህ የሰጠሁህን ውጠት አሻሽልልሃለሁ” በማለት ወረቀቱን ሰጠው፡፡ ሞንቴ እቤቱ በመሄድ አስተማሪው የነገረውን ነገር ለረጅም ጊዜ ቁጭ ብሉ በጣም አሰበበት፡፡ አባቱንም ሃሳብ እንዲሰጠው ጠየቀው፡፡ የአባቱ መልስ፣ “ልጄ ሆይ፣ በጉዳዩ ላይ የራስህን አመለካከት መወሰን አለብህ፡፡ ሆኖም፣ ይህ የምትወስነው ውሳኔ በጣም አስፈላጊ ውሳኔ እንደሆነ አስባለሁ” የሚል ነበር፡፡ ሞንቴ በነገሩ ላይ ለአንድ ሳምንት ብዙ ካሰበበት በኋላ ያንኑ ወረቀት ለአስተማሪው መለሰለት፡፡ በወረቀቱ ላይ እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር፣ “ለቤት ስራዬ የሰጠኸኝን የ F ውጤት ከአንተ ጋር አቆየው፣ እኔ ከሕልሜ ጋር እቆያለሁ”፡፡ ይህ ታሪክ ከተከሰተ ከብዙ አመታት በኋላ በአሁን ጊዜ ሞንቴ ሮበርትስ በ80 ሄክታር ላይ ያረፈ ትልቅ የፈረስ ማርቢያ እርሻ አለው፡፡ በዚያም እርሻ ውስጥ 370 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የግል መኖሪያ አለው፡፡ ያንን F ያገኘበትንና ሕልሙ የተጻፈበትን ወረቀት በፍሬም አድርጎ በሳሎን ቤቱ ግድግዳ ላይ ሰቅሎታል፡፡ ሞንቴ በውስጡ የነበረውንና ከልቡ ያመነበትን ሕልም ከአስተማሪው የግል አመለካከት የተነሳ ለመጣል እምቢ ያለ ሰው ነበር፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ሞንቴ እና በአለማችን የሚገኙ ሌሎች በርካታ እሱን መሰል ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎችና ሰዎች፣ “ከዚህ ማለፍ አትችሉም” በመባል የተሰመረባቸውን የገደብ መስመር አልፎ ለመሄድ የቆረጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች ከራሳቸው እይታ በመነሳት ማድረግ ወይም መሆን የምንችለውንና የማንችለውን የመገመት መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ በዚያ ገደብ ውስጥ የመቆየትና ያለመቆየት ውሳኔው ያለው ግን እኛው ጋር ነው፡፡ “አይቻልም” ሲሉን በውስጣችን “ይቻላል” በማለት፤ “ያንተ ነገር አከተመ” ሲሉን ለራሳችን “የእኔ ነገር አላከተመም” እያልን በመንገር ወደፊት የመገስገስ ሙሉ መብትና ብቃቱም አለን፡፡ በሌላ አባባል፣ ሊገታን የሚችል ገደብ እኛው ያበጀነው ገደብ ነው፡፡ የይቻላል እይታ ማለት በአንድ ሙከራ ሳንገታና ሰዎችና ሁኔታዎች በሚሰጡን “አትችልም” የሚል መልእክት ሳንገደብ ወደ ፊት ለመገስገስና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ አላማችን ጋር ለመድረስ መትጋት ማለት ነው፡፡ ሆኖም፣ አብዛኛውን ጊዜ አንድን ነገር ለማከናወን ሁሉ ነገር የተሟላልን አይነት ሰዎች መሆን እንዳለብን እንድናስብና ቀድሞውኑ ተስፋ ቆርጠን እንቀመጣለን፡፡ በሕይወታችን ግን ስኬታማ ለመሆን ሁሉ ነገር የተሟላ መሆን የለበትም፤ ያመንንበትን መልካም ዓላማ ለመከተል ውስጣችን ሙሉ መሆን ነው ያለበት፡፡ ይቻላል!!! (እይታ ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)፡፡
Show all...
እድለኛ ነህ ወይስ እድለ-ቢስ? “መልካም እድል ማለት ዝግጁነትና ጥሩ ገጠመኝ ሲገናኙ ማለት ነው፡፡ መጥፎ እድል ማለት ደግሞ ዝግጁ አለመሆን ከእውነታ ጋር ሲገናኝ ማለት ነው” - Eliyahu Goldratt “ፎርብስ” የተሰኘው ታዋቂ መጽሔት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በጃንዋሪ 2/2018 እትሙ ላይ “እድል ምንድን ነው? በስኬታማነትህ ላይስ ምን አይነት ተጽእኖ አለው? የሚልን ሃሳብ አስፍሯል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ላይ ጎልቶ የተቀመጠው ሃሳብ፣ ብዙ ሰዎች እድል ብለው የሚጠሩት ጉዳይ አንድ መልካም ገጠመኝ ሲመጣ ለዚያ ገጠመኝ የመዘጋጀታቸውንና ክፍት የመሆናቸውን ሁኔታ ነው፡፡ እድልንና በእድል ላይ ያለንን አመለካከት አስመልክቶ የጠለቀ ጥናት ያደረገው የስነ-ልቦና አዋቂ ሪቻርድ (Richard Wiseman) ከብዙ አመት ጥናት በኋላ የደረሰበትን ውጤት ሲጨምቀው፣ “እድል ማለት በግል ሕይወታችን ላይ ካለን አመለካከት ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ነው” ይለናል፡፡ እድለኛ ነኝ ብለው የሚያምኑ ሰዎች በሕይወታቸው የሚያጋጥማቸው መልካም ነገር ላይ የሚያተኩሩና ሕይወታቸውንና በዙሪያቸው ያለውን አለም በዚያ መነጽር የሚያዩ ሰዎች ናቸው፡፡ በአዎንታዊ የተሞሉ ሰዎች ትኩረታቸው መልካም ገጠመኞች ላይ ስለሆነና ለማየትና ለማስተናገድ የተዘጋጁት መልካም መልካሙን ገጠመኞች ስለሆነ ያንን እየቆጠሩ ራሳቸውን እንደ እድለኛ ይቆጥሩታል፡፡ አሉታዊ ሰዎች ግን በተቃራኒው ትኩረታቸው ጤና-ቢስ ገጠመኞች ላይ ስለሆነና ለማየትና ለማስተናገድ የተዘጋጁት ክፉ ክፉውን ገጠመኞች ስለሆነ ያንን እየቆጠሩ ራሳቸውን እንደ እድለ-ቢስ ይቆጥሩታል፡፡ ማንኛውም የሕይወት ገጠመኝ እንደ መነሻ ነጥብ ወይም እንደ መስፈንጠሪያ ስፕሪንግ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ለማተኮር የመረጥናቸው ገጠመኞች ላይ በመርገጥ ስንዘል ወደየት እንደምንሄድ የሚወስንልን ለመነሻነት የመረጥነው ገጠመኝ ነው፡፡ በአንድ አይነት ቤት ሁኔታ ውስጥ ያደጉ ሁለት መንትያዎችን እንደምሳሌ ልንወስድ እንችላለን፡፡ እነዚህ ሁለት መንትያዎች አባታቸው እጅግ ጨካኝና ቁጡ የሆነ ሰው ስለነበረ በጣም እየደበደባቸው ነው ያደጉት እንበል፡፡ ይህ ሰው ብዙ ገንዘብ ያለው ነጋዴ ነው፡፡ እናታቸው ደግሞ ብልህ ስለነበረች ጥሩ ባህሪይ ያለው አባት ባይኖራቸውም እንኳን ቢያንስ ጥሩ ትምህርት ያግኙ በማለት ተመራጭ ትምህርት ቤት ነው ያስተማረቻቸው፡፡ የአስራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ አንደኛው ልጅ ስለአባቱ ክፋት በማሰብ እጅግ መራራ ወደመሆን መጣ፡፡ “ለምን እንደዚህ አይነት አባት ኖረኝ?” “ለምን እንደጓደኞቼ ጥሩ አባት አልኖረኝም?” በሚሉና በመሳሰሉት አይነት ጥያቄዎች በመሞላት ትምህርቱን ላለመቀጠልና ሱስ ወደተሞላበት ወደተራ ሕይወት ለመውረድ ወሰነ፡፡ የዚህ ልጅ መንታ ወንድም ግን ያተኮረው ሌላ ነገር ላይ ነበር፡፡ ምንም እንኳን አባቱ ክፉ ቢሆንበትም ጥሩ ትምህርት ቤት ለመማር እድል ማግኘቱን በማሰብ፣ በተጨማሪም የእናቱን ሩህሩህነትና ብልህነት በማመስገን ትምህርቱን ለመቀጠልና የተሻለ ደረጃ ለመድረስ ወሰነ፡፡ በእነዚህ በአንድ አይነት “እድሎች” ውስጥ ባደጉ ሁለት ልጆች መካከል ያለው የጎላ ልዩነት ምን እንደሆነ ለአንባቢዬ ታይቶታል ብዬ አምናለሁ፡፡ አንዱ መልካሙ ላይ በማተኮር “እድለኛ” ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ክፉው ላይ በማተኮር “እድለ-ቢስ” ሆነ፡፡ ከዚህ የተለየ ሌላ ምንም አይነት ምስጢር የለውም፡፡ ምናልባት ከዚህ በፊት የነበረህን ልምምድ ባላውቅም፣ ከዛሬ ጀምረህ ግን ይህንን አይነቱን አመለካከት የማዳበሩ ታላቅ እድል አለህ፡፡ ሕይወትህ በእድልና በገጠመኝ እንደተሞላች በማስታወስ፣ እነዚህ በየእለቱ ወደአንተ የሚመጡ እድሎችና ገጠመኞች ደግሞ አንዳንዴ መልካም፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ክፉ ልምምዶችን ይዘው እንደሚመጡ ማሰብ ይገባሃል፡፡ ከዚህ አመለካከት በመነሳት ከየትኞቹ ላይ ረግጠህ ለመነሳት እንደምትፈልግ ምርጫው የአንተ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ክፉ እድል የሚባለውን ከእውነታ የራቀ አመለካከት በመተው፣ ረግጠህ የምትነሳበትን የሕይወት ገጠመኝና ልምምድ የመምረጥ መብትህን ተጠቀምበት እንጂ የገጠመኞች መጫወቻና ሰለባ አትሁን፡፡ (“የጥበብ መንገድ” ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ)
Show all...
✅ የኢየሱስ መለኮታዊ ማንነት ✍ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነዉ። በዚህ ልጅነቱም በሁሉ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ነዉ። ስለዚህም የእግዚአብሔር አብ መገለጫ የሆኑ መለኮታዊ ባህሪያት ሁሉ የእርሱም መገለጫዎች ናቸዉ።ከዚህ ቀጥለን የኢየሱስ እግዚአብሔርነት በጌትነት አምላክነት የእግዚአብሔር ልጅነትልጅነት እና ለማይታየዉ አምላክ ምሳሌነት እንመለከታለን። 🔷 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ✔️ የሐዋርያዉ ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጀምር፦ በመጀመሪያ ቃል ነበረ ብሎ ሲፅፍ ቃል ለሚለው የተጠቀመበት የግሪክ ቃል ሎጎስ የሚል ነዉ። ግሪኮች ሎጎስ የሚሉት የተነገረውን ቃል ብቻ ሳይሆን ገና ያልተነገረዉንም በልብ ያለዉንም ሀሳብ ጭምር ነዉ። ✔️መፅሐፍ ቅዱስቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረትን የፈጠረዉ በቃሉ እንደሆነ ያስተምራል (መዝ 33 : 6)። የዕብራውያን መልእክት ፀሐፊፀሐፊ ዓለማት የተዘጋጁት በእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በእምነት እናስተዉላለን ይላል ( ዕብ 11 : 3) ይህም በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ዉስጥ ክርስቶስ ዓለማትን የፈጠረ እንደ ሆነ በእምነት እናስተዉላለን ማለት ነዉ። ✔️የሐዋርያው ዮሐንስ ግሪኮች ያንን ፍጥረትን ያስገኘ ምክንያት የሚሉትን በስጋ የተገለጠዉን ቃል እንደ ነበረና ያም ቃል እግዚአብሔር እንደ ነበረ በትስጉትም (ቃል ስጋ የሆነበት ሂደት ነዉ) በስጋ እንደ ተገለጠ በማስተማር ወንጌሉን ይጀምራል። ያም ቃል ከእግዚአብሔር ጋር የነበረ ሲሆን ራሱ እግዚአብሔር ነበረ። ስለዚህ ሎጎስ ሀሳብ ወይም ንግግር ሳይሆን ማንነት ያለው የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል ነዉ። ✔️ መፅሐፍ ቅዱስ ቃልም እግዚአብሔር ነበር ይላል እንጂ ቃልም የእግዚአብሔር ንግግር ነበረ አይልም። ቃልም እግዚአብሔር ነበር የተባለዉ ቃል ሀሳብ ወይም ንግግር ሳይሆን ማንነት ያለው ስለሆነ ነዉ። ሁሉ ነገር የተፈጠረውም በእርሱ ነዉ ያለ እርሱም የተፈጠረ ምንም ነገር የለም ያ ሁሉን የፈጠረዉ ቃል ደግሞ ሰዉን ለማዳን ስጋ ሆነ። ቃል ስጋ የሆነበትም ምስጢር ቃል እግዚአብሔርነቱን ሳይለቅ ሰዉ የሆነበትና ወደ አለም በሰዉነት የገባበት ሂደት ነዉ። ✔️ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ከመገለጡ በፊት ቃል እንደ ነበረ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል ( ዮሐንስ 1 :1 -3) ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመጀመሪያ ቃል ነበረ በማለት ከጀመረ በኋላ ሁሉ በእርሱ ሆነ ብሎ የሚናገርበት መንፈስ ከዘፍጥረት 1 :1 ጋር በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ከሚለዉ ጋር አንድ አይነት ነዉ። ለዚህ ነዉ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ይህን ሁሉን የፈጠረዉን ቃል እግዚአብሔር ነበረ ያለዉ። የዘፍጥረት መፅሐፍ እግዚአብሔር ፈጠረ የሚለዉን የዮሐንስ ወንጌል ቃል ሁሉን ፈጠረ በማለት ቃል እግዚአብሔር መሆኑን አብራርቷል። የዘፍጥረት መፅሐፍ የአፈጣጠራቸዉን ቅደም ተከተል በዝርዝር የያዘ ሲሆን የዮሐንስ ወንጌል ግን በጥቅሉ ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነዉም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም በማለት አጠቃልሎ አቀርቦታል። ✔️ በዮሐንስ 1: 1 ላይ ቃል የተባለው በዘፍጥረት 1 : 1 ላይ እግዚአብሔር የተባለዉ ነዉ። ለዚህም ነዉ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ያለው። ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም የሆነ የለም የሚለው ቃል በሰማይና በምድር ያሉት የሚታዩትና የማይታዩት ሁሉ የተፈጠሩት በክርስቶስ መሆኑን አጠቃልሎ የሚያሳይ ቃል ነዉ። ዝርዝር አፈፃፀማቸው ደግሞ ዘፍጥረት ምዕራፍ አንድን ብናነብ መረዳት እንቺላለን። ስለዚህ ስጋ የሆነዉ ቃል በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ላይ ሁሉን የፈጠረዉ እግዚአብሔር ነዉ። እስራኤላውያንም መቀበል ያቃታቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠው የሁሉ ፈጣሪ የሆነዉ እግዚአብሔር መሆኑን ነዉ። ♻️ሼር በማድረግ ለሌሎች♻️ አካፍሉ ♥️♥️ የፍቅሩ ምርኮኞች ♥️♥️
Show all...
በቀጣይ ይጠብቁን ስለ ኢየሱስ መለኮታዊ ማንነት Add ✝ share ♻️ ❤️❤️ የፍቅሩ ምርኮኞች❤️❤️
Show all...
ስለ ኢየሱስ የመማር አስፈላጊነት ክፍል ሁለት * የእግዚአብሔር ልጆች የምንሆነው በእርሱ በኩል ስለሆነ ኤፌሶን 1 : 5 * በእግዚአብሔር ዘንድ ያለዉ መጠበቃችን እርሱ ስለሆነ (1ዮሐ 2 : 1) * ከሀጢአት የሚያነጻን የእርሱ ደም ስለሆነ (1ዮሐ 1 :7) * የስብከታችን ርዕስ እርሱ ስለሆነ (2ቆሮ 4 : 5) * የመለኮት ሙላት የሚኖረዉ በእርሱ ሰዉነት ስለሆነ ቆላ 2 : 9) *እግዚአብሔር ስሙት ያለዉ እርሱን ስለሆነ (ማቴ 17 : 5) *ከአዳም ጀምሮ ቅዱሳን የመኑት እርሱን ስለሆነ ( ዕብ 11 : 13) * የቤተ ክርስቲያን መስራችና መሰረት እርሱ ስለሆነ (ማቴ 16 :16 - 18 1ቆሮ 3 : 11) * በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህናችን እርሱ ስለሆነ (ዕብ 8 :1) * ያለ እርሱ ምንም ማድረግ ስለማንችል (ዮሐ 15 : 5) * የጥበብና የእዉቀት መዝገብ እርሱ ስለሆነ (ቆላ 2 : 2 - 3) * ወደ እግዚአብሔር ቤት መግቢያ በር እርሱ ስለሆነ (ዮሐ 10 : 10) *የሰይጣንን ራስ ይቀጠቅጣል የተባለው የሴቲቱ ዘር እርሱ ስለሆነ (ዘፍ 3 : 15) *ታላቁ አምላካችንና መድኃኒታችን እርሱ ስለሆነ (ቲቶ 2 : 12 -13) * የምንጠብቀው የተባረከዉ ተስፋችን እርሱ ስለሆነ ( ቲቶ 2 :12 - 13) * ሙሴ በህግ ነብያትም ስለ እርሱ የጻፉለት አዳኝ እርሱ ስለሆነ (ዮሐ 1 : 46) የአባቴ ብሩካን ከተመቻቹ ✝ Add ♻️ share ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች❤️❤️
Show all...
አልመህ ተኩስ አንድ ንጉስ ከአጃቢዎቹ ጋር በአንድ ጫካ ውስጥ ሲዘዋወር አንድ ዛፍ ላይ ያየው ነገር ትኩረቱን ሳበው፡፡ በዚህ ትልቅ ዛፍ ላይ የተለያዩ ክብ ቅርጽ ያላቸው ኢላማዎች ተስለዋል፡፡ የገረመው ነገር፣ እያንዳንዳቸው ኢላማዎች መካከል ምንም ሳይስቱ ኢላማቸውን በትክክል የመቱ ቀስቶች ተሰክተው ይገኛሉ፡፡ ንጉሱ በጣም ተገረመና፣ “እነዚህን ኢላማዎች ሁሉ በትክክል አነጣጥሮ የመታውን ሰው ለሰራዊቴ አለቃነት እፈልገዋለሁና ፈልጋችሁ አግኙልኝ” አለ፡፡ ልክ ይህንን ተናግሮ እንደጨረሰ አንድ ወጣት ልጅ ብዙ ቀስቶችን ተሸክሞ እየገሰገሰ ንጉሱ ጋር ደረሰ፡፡ ንጉሱ፣ እነዚህን ሁሉ ኢላማዎች በትክክል የመታው ሰው እሱ መሆኑን ጠይቆ የአዎንታ መልስ ካገኘ በኋላ እንዴት እንደዚህ አነጣጣሪ ሊሆን እንደቻለ ጠየቀው፡፡ የልጁ መልስ አጭርና ግልጽ ነበር፣ “በመጀመሪያ ቀስቴን ወጥሬ በዛፉ ላይ እሰካዋለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ዛፉ በመሄድ በተሰካው ቀስት ዙሪያ የክብ ምልክትን አስቀምጥበታለሁ” በማለት እንደዚያ አነጣጣሪ ያስመሰለውን እውነት ፍርጥ አደረገና ነገረው፡፡ ይህ መሰረታዊና ቀላል አፈ-ታሪክ የብዙ ሰዎችን የሕይወት ዘይቤ ያንጸባርቃል፡፡ ይህ ወጣት በመጀመሪያ ዓላማን አድርጎ አልነበረም ያንን ዓላማ ለመምታት ጥረት ያደረገው፡፡ በቅድሚያ ወዳሻው ቀስቱን ከለጠጠና ከሰነዘረ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ስፍራ ነው እንደዓላማ በመቁጠርና ልክ ዓላማውን እንደመታ ለማስመሰል በዙሪያው ክብን ያበጀለት፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ ዒላማንና ግብን አቅደው በዚያ ባቀዱት መሰረት ሊተኩሲ ሲገባቸው ከተኩሱ በኋላ ቀስቱ ያረፈበትን ነው እንደግብ የሚቆጥሩት፡፡ በሌላ አባባል፣ ያገኘነውን፣ የመሰለንንና የቀለለንን ነገር ካደረግን በኋላ በዚያ ባደረግነው ተግባር ዙሪያ ዓላማን ለመፍጠር መሞከር የሞኝነት ሁሉ ሞኝነት ነው፡፡ ዓላማ ከሌለን የምንሄድበትን አናውቅም፡፡ ግብም ከሌለን ተኩሰን የመታነው ነገር ሁሉ እንደ ግብ ስለሚቆጠር ይህንና ያንን ስናደርግ ጊዜያችን ይባክናል፡፡ ለዚህ ነው በዓላማና በግብ የምንመራ ሰዎች መሆን ያለብን፡፡ አንድ በር ተከፍቶ ስላገኘህ ብቻ ከገባህ በኋላ የገባህበትን ዓላማ ለማግኘት አትሯሯጥ፤ በመጀመሪያ በዚያ በር የመግባትህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማ ጋር መስማማቱን አረጋግጥ፡፡ አንድ ሃገር የመሄድ እድል ስለተገኘ ብቻ ከሄድክ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትሂድ፤ በመጀመሪያ ወደዚያ ሃገር የመሄድህ ጉዳይ ከሕይወትህ ዓላማህ ጋር አለመጣረሱን አረጋግጥ፡፡ አንድ ሰው ትኩረትና የመፈቀር ስሜት ስለሰጠህ ብቻ ሁለንታንህ በመስጠት ግንኙነት ውስጥ ከገባህ በኋላ ዓላማ ለመፍጠር አትታገል፤ ጓደኛንም ሆነ ፍቅረኛን ከዓላማህ አንጻር ምረጥ፡፡ ስራህንም እንደዚያው! ትምህርትህንም እንዲዚያው! የሕይወትህን ዋና ዋና ክፍሎችም እንደዚያ! ከዓላማ ተነሳ እንጂ ተነስተህ ከተጓስክ በኋላ ዓላማህን ለማግኘት አትባክን፡፡ ዓልመህ ተኩስ እንጂ የተኮስከው ነገር የመታውን ነገር ሁሉ ዓላማህ እንደሆነ በማሰብ ራስህን በማታለል ዘመንህን አታባክን፡፡
Show all...
“የዛሬ ስራዬ ነገ እኔን ይሰራኛል” - በመስራት የመሰራት ምስጢር “ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር ዛሬ በምንሰራው የስራ አይነት ላይ ብቻ ሳይሆን የዛሬው ስራችንና ድካማችን ነገ በሚያመጣው መልካም ውጤትና እንዲሁም በመስራታችን የራሳችንንና የሌሎችን ሕይወት የመለወጣችን ጉዳይ ላይም ሊሆን ይገባዋል” አስተዋዮች እንዲህ ብለው ያስባሉ፣ “ትኩረቴን ዛሬ የምሰራው የስራ አይነት ላይና የጊዜው ልፋቴ ላይ ብቻ ካደረኩ ተስፋ አስቆራጭ አመለካከት ውስጥ እገባለሁ፡፡ ትኩረቴን ግን ዛሬ በምሰራው ስራ ምክንያት ነገ የሚገነባው ነገር ላይ ማድረግ አለብኝ”፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ዛሬ የተሰማሩበት የስራ መስክ ለወደፊታቸው መሸጋገሪያ ድልድይ እንደሆነ በሚገባ የተገነዘቡ ሰዎች ናቸው፡፡ ሶስት ሰዎች ለአንድ ቤት ግንባታ መሰረት ለመጣል ይሰራሉ፡፡ አሸዋውን፣ ሲሚንቶውንና ጠጠሩን በመደባለቅ እያዋሃዱ የተለያዩ ግንባታዎችን በማድረግ ስለዋሉ ደክሟቸዋል፡፡ አንድ ሰው በመንገድ ሲያልፍ አያቸውና ምን እንደሚገነቡ ሊጠይቃቸው ቀረብ አለ፡፡ መጀመሪያ ያገኘውን ሰራተኛ፣ “ምን እየሰራችሁ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ ሰራተኛ አካፋው ላይ ደገፍ በማለት ላቡን እየጠረገ፣ “ሲሚንቶ እያቦካሁ እያየኸን ምን ትጠይቀኛለህ፤ የማያልቅ ልፋት ውስጥ ነኝ፡፡ ትናንትም ይኸው፣ ዛሬም ይኸው፣ ነገም ይኸው” በማለት በማማረር መለሰለት፡፡ ሰውየው የጠበቀውን መልስ ስላላገኘ ዘወር በማለት ራቅ ብሎ የሚሰራውን ሌላኛውን ሰው ጠጋ በማለት፣ “ምን እየሰራችሁ ነው?” በማለት ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቀው፡፡ ይህ ሰው ፈጥኖ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ለእለት ጉርሴ ነው የምሰራው፤ እዚህ ምድር ላይ ሳይሽከረከሩ መቆም የለም፡፡ ዛሬ የሰራኋትን በዚሁ ከጓደኞቼ ጋር በማዋጣት ከተገባበዝንና አንዳንድ ነገሮች ቀመስ ቀመስ ካደረግን በኋላ እቤት እገባለሁ፡፡ ነገ ደግሞ ለነገው እለት ጉርስ ለመስራት እነሳለሁ፤ ሕይወት እንዲሁ ነው”፡፡ መንገደኛው አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ሶስተኛውን ሰው ለመጠየቅ ፈለገና ጠጋ በማለት፣ “ምን እየሰራችሁ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ ሶተኛ ሰው የመለሰለት መልስ ከሁለቱ ለየት ያለ ነበር፡፡ “ሁለቱን ጓደኞቼን ስትጠይቃቸው ጆሮዬ ጥልቅ ብሏላ፡፡ እነሱ ምን እንዳሉህ አላውቅም፣ እኔ ግን የምሰራው ሁለት ነገር ነው፡፡ አንደኛው፣ በዚህ ቦታ የተሰጠንን ለህብረተሰቡ የሚውል የስልጠናና የመዝናኛ ግንባታ ማጠናቀቅ ነው፡፡ እዚህ ጋር የመማሪያ ክፍሎች አሉ፣ እዚያ ጋር ደግሞ ቤተ መጻህፍት፣ የማብሰያ ክፍልና የመሳሰሉት፣ ከጎኑ ደግሞ ለሌሎች ስራዎች የሚውሉ ሌሎች ግንባታዎች እንጨምራለን፡፡ ሁለተኛው ስራዬ ግን የራሴን ሕይወት ነው፡፡ እዚህ ከሰራሁና ገንዘብ ካገኘሁ በኋላ ባለኝ ጊዜ በመማር ራሴን አሻሽላለሁ፡፡ ከጥቂት አመታት በኋላ ኮንትራክተር ለመሆን አስባለሁ፡፡ የዛሬ ስራዬ ነገ እኔን ይሰራኛል” መንገደኛው ጥያቄውን ከጨረሰ በኋላ መንገዱን ቀጠለ፡፡ ከአእምሮው ግን ፈጽሞ ሊጠፋ ያልቻለ ሃሳብ ይመላለስበት ጀመር፣ “የመጀመሪያው ሰው ሲሚንቶ አቡኪ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ለእለት ጉርስ ለፊ ነው፣ ሶስተኛው ሰው ግን የግል ሕይወቱንና አንድ ዓላማ ያለውን ግንባታ ገንቢ ነው”፡፡ እይታቸው ዛሬ ከሚሰሩት ስራ ያላለፈ ሰዎች እጅግ አሳዛኝና ለክስረት ራሳቸውን የሚያዘጋጁ ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ዛሬ በእጃቸው የገባውን የመስራት እድል በመጠቀም ነገ ማድረግና መሆን ወደሚፈልጉት ደረጃ ለማደግ መነሳሳቱ ሊኖራቸው ሲገባ በጊዜው ያለመመቸት ሁኔታ ተውጠው ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ የዛሬው ስራቸው ሆዳቸውን ከመሙላት አልፎ የወደፊት ዓላማቸውንም ማሟላት እንዳለበት ዘንግተውታል፡፡ የዛሬውና ጊዜአዊው፣ የሩቁንና የዘለቄታዊውን ከማየት ይከለክላቸዋል፡፡ ዛሬ የሚሰሩት ስራ ለነገ ሕይወታቸው ዘር እንደሆነ ስለዘነጉ ከማማረር ያለፈ ውሎ የላቸውም፡፡ የአንድ ሰው ማንነቱ ዛሬ በሚሰራው ስራ አይመዘንም፡፡ የአንድ ሰው የወደፊቱ በዛሬው ሁኔታ አይገደብም፡፡ ዛሬ ያለበት ደረጃ የደረሰው ከትናንትናው በመነሳት እንደሆነ ሁሉ የዛሬው ሁኔታው ደግሞ ለነገው ድልድይ ነው፡፡ የሰው ገደቡ አመለካከቱ ነው እንጂ ሁኔታው አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ሁለት ሰዎች በአንድ አይነት ቤት አድገው፣ አንድ አይነት አነሳስ ተነስተውና እኩል እድል ተሰጥቷቸው አንዱ ወደላቀ የሕይወት ደረጃ ሲደርስ ሌላኛው ለተራ ነገር ሰክኖ የሚታየው፡፡ (“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተቀነጨበ
Show all...
✅ ስለ ኢየሱስ የመማር አስፈላጊነት ክፍል አንድ * እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የፈጠረዉ በእርሱ በኩል ስለ ሆነ(የሐ 1: 1-3 ቆላ 1 :15 ዕብ 1: 10 *መጀመሪያዉም መጨረሻዉም የዘላለም አምላክ እርሱ ስለሆነ ራዕይ 1 :17 * እግዚአብሔር የሚንፀባርቀዉ በእርሱ በኩል ስለ ሆነ ዕብ 1:1-3 * እግዚአብሔር የሚናገረው በእርሱ በኩል ስለሆነ ዕብ 1: 1-3 * በሰማይ ያለዉ ብቸኛው አማላጃችን እርሱ ብቻ ስለ ሆነ (ዕብ 7 : 23) * እግዚአብሔር የኃጢአት ይቅርታ የሚያደርገው በእርሱ በኩል ስለሆነ (ሮሜ 3 : 25) * እግዚአብሔር አብ የሚታወቀው በእርሱ በኩል ስለሆነ (ሉቃ 10:25 *ጽድቅም ጥበብም ቅድስናንም ቤዛነትንም ከእግዚአብሔር ዘንድ የምናገኘዉ በእርሱ በኩል ስለሆነ (1ቆሮ 1 : 30 - 31) *እግዚአብሔር የፍቅሩን የገለጠዉ በእርሱ በኩል ሰለሆነ (1የሐ 4 :9 የሐ 3 : 16) * የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ሰለሆነ (የሐ 3 : 16) * የኃጢአት ይቅርታ የሚገኘው በእርሱ ስም በማመን ብቻ ስለሆነ (የሐዋርያት ስራ 10 43) *ፀሎታችን ተሰሚነት የሚያገኘው በእርሱ በኩል ስለሆነ (ዮሐ 14 : 13- 14) * በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የለዉ መካከለኛዉ እርሱ ብቻ ስለሆነ (1ጢሞ 2 : 5) * ወደ አብ የሚያደርሰው ብቸኛ መንገድ እርሱ ስለሆነ (ዮሐ 14 : 6 * እግዚአብሔር ከዘላለም ፍርድ የሚያድነን በእርሱ በኩል ስለሆነ (ዮሐ 3 : 18 ) * ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የምንችለው በእርሱ በኩል ስለሆነ (ዕብ 10 : 19 - 20) *መንፈስ የቅዱስን መቀበል የምንችለዉ በእረሱ በማመናችን ስለሆነ ( የሐ 7 : 37 -39) *እግዚአብሔር ማምለክ የምንችለዉ በእርሱ በኩል ስለሆነ ( ቆላ 3 :17) * የነፍስ እረፍት የሚሰጥ እርሱ ብቻ ስለሆነ (ማቴ11: 28) * የነፍሳችን እረኛ እርሱ ብቻ ስለሆነ (1ጴጥ 2 : 25) *መዳን በሌላ በማንም ስለሌለ)(ሐዋ 4 : 12) * እርሱን አለማመን ፍርድ ስለሆነ (ዮሐ 3 : 18) * ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅነዉ በእርሱ ሞት ስለሆነ ሮሜ 5 : 10) ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
የዓለም ጋጋታ 👣👣👣 ================ 👉ሰዎች ለምንድነው የሚተቹህ ❓ ✔ አንተ የደረስክበትን መድረስ ሳይችሉ ሲቀሩ ✔ አንተ ያለህ ነገር እነርሱ ከሌላቸው ✔ የአንተን ነገር ሊኮርጁ ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር ... ይላሉ እንግዲህ || በክርስቶስ የሆነ ከዚህ ዓለም ጋጋታ ነጻ መሆን አለበት ምክንያቱም ያለን ጊዜ ጥቂት ነው ሙሽራው ልመጣ በደጅ ነው ። ✔መወራት ያለበት ክርስቶስ ነው ✔መሰበክ ያለበት ክርስቶስ ነው ✔መዘመር ያለበት ክርስቶስ ነው ✔መታየት ያለበት ክርስቶስ ነው በክርስቶስ የሆነ ምንም አያስፈልገውም ፣ #በክርስቶስ_ተሞልቷልና ። የሚያወራው ክርስቶስን ብቻ ነው ፣ እንደ ነብሴ ጡር ሴት ሁሌ የሚያምረው #ስም ክርስቶስ ኢየሱስ ፦ ✔ጠዋት ክርስቶስ ✔ቀትር ላይ ክርስቶስ ✔ማታም ክርስቶስ በክርስቶስ ተሞልተናል ከውስጣችን የሚወጣው ክርስቶስ ብቻ ነው ። (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2: 9-11 ) ፤ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። #ለአለቅነትና_ለሥልጣንም_ሁሉ_ራስ_በሆነ በእርሱ ሆናችሁ #ተሞልታችኋል። የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ። ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
"አሻጋሪዎች" ሰባኪው በ አንድ ቤተክርስቲያን እየተገኘ ዘወትር ያስተምራል። በየ እለቱ በርካታ ምእመናን በቦታው እየተገኙ ይሰበካሉ። ከ እነዚህ በርካታ ምእመናን ውስጥ አንደኛው ራቅ ካለ ቦታ ነው ሚመጣው። ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣም ሆነ ሲመለስ የመሻገሪያ ድልድይ የሌለውን ወንዝ እየዞረ ስለሆነ ከሌሎች ይልቅ ብዙ የሚደክመው እሱ ነው። አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ፡ ሰባኪው የሚያስተምረው ስለ ጽኑ እምነት ነበር። " የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል እምነት ቢኖራቹ ይህን ተራራ በገፋችሁት ሂድ እልፍ በል ባላችሁት ግዜ በሄደ። " የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ሃይለ ቃል ገልጾ በ እምነቱ ጽኑ ሲሆን የሚሳነው ነገር እንደሌለ ለምእመኑ አስረዳ። በሚዞረው ትልቅ ወንዝ ምክንያት ከሌሎቹ ምእመን ይልቅ ብዙ የሚደክመው ያ ሰው ከ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲያቀና እንደተለመደው እዛ ድልድይ አልባ ወንዝ ላይ ደረሰ። ወንዙን ሲያየው ሰባኪው ያስተማረው የእምነት ትምህርት ድቅን አለበት። ወዲያውኑ "እኔ እኮ በእግዜብሔር አምናለው እግዜብሔርም ይህን ለ እኔ ማድረግ አይሳነውም" በፍጹም እምነት ወደ ጥልቁ ወንዝ በመሄድ ረገጠው እንዳለውም ተሳካለት መራመድም ቻለ። ያን ዙሪያ ጥምጥም ይሆነ የቤቱን ጎዳና በጣም አጭር በሆነ ደቂቃ አጠናቆ እቤቱ ግባ። ሚስቱም በመደንገጥ " ቤተክርስቲያን አልሄድክም እንዴ? ምነው በጊዜ መጣህ?" ብላ ብትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት። እሷም በጣም ተደንቃ" ባለቤቴ ይህ ተዐምር ከተደረገለት መምህሩማ ምን ያህል ኣምላክ የመረጠው ቅዱስ ነው ብላ በል ነገ ይዘኸው ና! ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን።" ብላ ባለቤቷን ተማጸነች። በማግስቱ የዋሁ ባል ያለምንም ፍርሃት እና ጥርጣሬ በወንዙ ላይ ተረማምዶ ከተሻገረ በኋላ፡ ትምህርት ተከታትሎ ጉባኤው ሲፈጸም ሰባኪውን ሄአድርሱት ባለቤቴ እቤት እየጠበቀችን ነው፡ እባክህን አብረን እንሂድ አለው።" ሰባኪውም ግብዣውን ተቀብሎ ጉዞ ጀመሩ። ሁለቱም እዚያ ወንዝ አጠገብ ሲደርሱ፡ የዋሁ ሰውዬ እንደለመደው በውሃው ላይ እየተራመደ ጥቂት ከተጓዘ በኋላ ዞር ብሎ ሰባኪውን ሲመለከት ከወንዙ ዳር እንደቆመ ነው። በሰባኪው መቆም ተገርሞ "ና እንጂ መምህር ምን ሆነሃል?" ሲል ጠየቀው። ሰባኪውም "ፈራሁ" ሲል ይመልስለታል። ውሃውን እየረገጠ ወደኋላ ተመልሶ "ምነው መምህር? እኔን ለዚህ አብቅተህ እንዴት ትፈራለህ? ና ተሻገር እባክህን " ሲል ጠየቀው በሰውዬው ንግግር ጭንቅላቱ የተነካው መምህርም፡ "ወዳጄ እኛ እናሻግራለን እንጂ አንሻገርም!" ሲል መለሰለት። እኛስ በእውነቱ የምንናገረውን የምናስተምረውን የምንሰብከውን እየኖርን ነውን? መልሱን ለእናንተ ትቻለው። (እኔም ያነበብኩትን እንዲህ አካፈልኳችሁ እናንተም ከተመቻችሁ ለሌሎች )
Show all...