cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የፍቅሩ ምርኮኞች

ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል መከራ ፥ወይስ ጭንቀት ፥ ወይስ ሰደት ፥ ወይስ ራብ ፥ወይስ ራቁትነት ፥ ወይሰ ፍርሃት ፥ ወይስ ሰይፍ ነዉን? ሮሜ 8፥35 እሱ መቼ በፈረስ አንገት በጦር አንደበት ሰዉ ይማርክና ሰይፍ ሳይመዝ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ዉድ ህይወቱን ከፍሎ የፍቅሩ ምርኮኞች አደረገን እንጂ ማርኮናል ምርኮኞቹ ነን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
186
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
መውደቅንና ውዳቂነትን ታምታታለህ? ራስህን መዝነው 1. የተሳሳቱ ሰዎችን (ራስህን ጨምሮ) የመውቀስ ልማድ አለብህ? 2. በሌሎች ሰዎች እንዳልተሳካለት ሰው ሆኜ እታያለሁ የሚል ስጋት አለብህ? 3. እንደሚሳካልህ እርግጠኛ የሆንክባቸውን ነገሮች ብቻ እየመረጥክ ማድረግ ትወዳለህ? 4. አንድን ነገር አንድ ጊዜ ሞክረኸው ካልተሳካ ደግሞ የመሞከር ፍላጎት የለህም? 5. ስኬታማ ሰዎች የስኬታማነትን ብቃት በጥረት ሳይሆን በውርስ ወይም በእድል እንዳገኙት ታስባለህ? 6. ምንም ያህል ብትሞክር እንኳ ማድረግ የማትችላቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ታስባለህ? 7. የማንነትህ ዋጋ ከተሳካልህና ካልተሳካልህ ነገር አንጻር የተያያዘ እንደሆነ ታስባለህ? 8. ያለመሳካትን ሃሳብ ስታስብ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይጫጫንሃል? 9. ስላልተሳኩልህ ሁኔታዎች ሙሉ ሃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ምክንያት ማብዛት ትወዳለህ? 10. አዳዲስ ችሎታዎችን ከማዳበር ይልቅ ያለህን ችሎታ ማሳየትና ስለእሱ ማውራት ይቀናሃል? ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ከዚህ በታች ላሉት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡ አመለካከትህን ለውጥ ውድቀት ምንድን ነው? ለወደፊቱ ደግመን እንዳንወድቅ እንቅፋትን ለይቶ የማወቂያ ሂደት ወይስ እንዳከተመልን ጠቋሚ ነገር? አለመሳካት ምንድን ነው? የመሞከራችንና ወደፊትም ከመሞከር እንደማናቆም አመልካች ነገር ወይስ ያለመቻል ምልክት? ስህተትስ ምንድን ነው? ሁሉም ሰው የሚያልፍበት ጤናማ የሕይወት ሂደት ወይስ የማንነት ቀውስ? የመውደቅ ፍርሃትህን ተጋፈጠው በጥቅሉ ሲታይ በአንድ ጉዳይ ላይ የመውደቅና የመሳሳት ስሜት ሲጋፋን ያንን ፍርሃታችንን የመጋፈጡ ምርጫ ውጤታማ ነው፡፡ ይህም ማለት የምንፈራቸውን ነገሮች ቀስ በቀስ በመዳፈር መነካካትና ማድረግ ማለት ነው፡፡ ስትወድቅ እንደገና ተነሳ ራሳቸውን ላሸነፉ ጎበዞች መውደቅን እንደመጨረሻ ክስተት መቀበል የማይታሰብ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ከአንድ ውድቀትና ስህተት በኋላ የመነሳትን ሁኔታ ሳያስመዘግቡ በፍጹም አያርፉም፡፡ አንተም ይህንን አመለካከት እንደ ራስህ አድርገህ ልትወስደውና ከውድቀት ባሻገር ዘልቀህ ልትጠቀምበት ትችላለህ፡፡ መውደቅና መነሳት የሕይወትህ አንዱ አካል እንደሆነ በመቀበል በወደክ ጊዜ ሁሉ በመነሳት ወደፊት መገስገስ ትችላለህ፡፡ ከውድቀታችን አጉል ተጽእኖ ማምለጥ እንችላለን እንጂ መውደቅ እንዳይከሰት ማድረግ አንችልም፡፡ ትወድቃለህ እንጂ ውዳቂ አይደለህም!
Show all...
ራስን ማሸነፍ፡- ይህንና ያንን ለማሸነፍ ከመሞከራችን በፊት ማሸነፍ ያለብን ራሳችንን ነው፡፡ አለቀ! በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሁሉንም ነገር ለማሸነፍ የሚኖረን ጥረት የሚሰጠንን ጊዜያዊ ድል፣ በተቃራኒው ደግሞ ራሳችንን በማሸነፍ ዘላቂ ድል ውስጥ መግባት እንደምንችል ጥርት ባለ መልኩ እንማራለን፡፡ ከሁሉም በፊት ማሸነፍ ያለብን ችግራችንን ወይም ሰዎችን ሳይሆን ራሳችንን ነው! ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . . “ከዚህ በኋላ አንድን ጦርነት ባሸንፍ ያልቅልኛል” የዚህ አባባል ባለቤት ነው ተብሎ የሚነገርለት የጥንት ንጉስ በአካባቢው የሚገኙትን ሃገራት ሁሉ አሸንፎ በግዛቱ ስር ለማድረግ በጀመረው ጉዞ ብዙዎቹን አሸንፎ በቁጥጥር ስር ካደረገ በኋላ ከድካሙ አረፍ ብሎ በፊቱ ስላሉ ቀሪ ግዛቶች ሲያስብ የተናገረው ንግግር ነበር፡፡ ሌላውን አሸንፈን እኛ ሲያልቅልን! ሌላውን ድል ነስተን እኛ ሲያከትምልን! በሁሉም ነገር አሸንፎ የመገኘት ፍላጎት የሰው ዘር ሁሉ የሚጋራው የውስጥ ፍላጎት ነው፡፡ ይህ ፍላጎት ገና ከልጅነት የሚጀምርና ጊዜያችን ደርሶ ከዚህች አለም እስክንሰናበት ድረስ የሚከተለን እውነታ ነው፡፡ ይህ የማሸነፍ ፍላጎት በራሱ ክፋት ባይኖርበትም፣ ለማሸነፍ ያነሳሳን የመነሻ ሃሳባችንና የምንከተለው ሂደት ግን መልካም ላልሆነ ፍጻሜ ሊዳርገን ይችላል፡፡ በውስጣችን ያለው የአሸናፊነት ጥማት ከብዙ ጉዳዮች ጋር ስለሚገናኝ እረፍት እስከምናጣ ድረስና ዓላማችን እርሱ ብቻ እስኪመስል ድረስ ከአንዱ ፍልሚያ ወደሌላኛው ፍልሚያ እየዘለልን ዘመናችንን ልናሳልፍ እንችላለን፡፡ ካላሸነፍናቸው ወደኋላ ሊያስቀሩን፣ አልፎም ሊያጠፉን የሚችሉ ሁኔታዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ስለሆነም፣ እንዳይጥሉን የምንታገላቸው ሁኔታዎች በርካታ ናቸው፡፡ በተጨማሪም፣ ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነትም ከማሸነፍና ከመሸነፍ ሁኔታ የማያልፍበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ አንድ ሰው እንዴት ነው ከባባድ ሁኔታዎችን ማሸነፍ የሚችለው? ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረው የማያቋርጥ ትግል በምን መልኩ ካለሽንፈት መወጣት ይችላል? እነዚህን ቁልፍና ወሳኝ ጥያቄዎች ለመመለስ “ማሸነፍ” በሚለው ሃሳብ ላይ ያለንን አመለካከት ልንሞግተውና ልንቃኘው ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚጠቅሙንን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ነጥቦች እናሰላስላቸው፡፡ • ራሱን ያላሸነፈ ሰው ምንም አይነት ሁኔታንም ሆነ ማንንም ሰው ማሸነፍ አይችልም፡፡ • ራሱን ያሸነፈ ሰው የትኛውንም አስቸጋሪ ሰውም ሆነ ሁኔታ ማሸነፍ ይችላል፡፡ • ራስን በማሸነፍ የሚመጣ አሸናፊነት ማለት ከከባድ ሁኔታዎችና ከአስቸጋሪ ሰዎች አጉል ተጽኖ ውጪ ወይም በላይ መኖር ማለት ነው፡፡ • ብርቱ ሰው ሌላውን ሰው ወይም ሁኔታዎችን ሳይሆን በመጀመሪያ ራሱን ያሸነፈ ሰው ነው፡፡ • አስቸጋሪ ሰዎችንና ሁኔታዎች በማድከም ለማሸነፍ መሞከር መልካም እርምጃ ሊሆን ይችላል፤ ከዚያ የላቀው ተመራጭ መንገድ ግን ውስጥን በማጠንከር ራስን ማሸነፍ ነዉ።
Show all...
አትፍራ! ተራመድ! “ጀግንነት ማለት የፍርሃት አለመኖር ማለት ሳይሆን ፍርሃትን አጥብቆ በመቋቋም የመቆጣጠርና ወደፊት የመራመድ ብቃት ማለት ነው” - Mark Twain ሳይወድቁ እንዴት መራመድን መልመድ ይቻላል? ሳይኮላተፉስ እንዴት መናገር ይለመዳል? የብዙ ሰዎች አጥር የተገነባው ፍርሃት በሚባል ወጥመድ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እንቅፋት እንደሌለ እርግጠኛ ካልሆኑ በስተቀር አይራመዱም፡፡ መክሰር የሚባለው “አስፈሪ” ነገር አለመኖሩን እርግጠኛ ካልሆኑ በስተቀር ንግድን አይጀምሩም፡፡ መገፋት የሚባለው ነገር እንደማይመጣ ማረጋገጫ ካልተሰጣቸው በስተቀር ለፍቅር ልባቸውን አይሰጡም፡፡ እነዚህ አሉታዊ ሁኔታዎች ግን ማንነታችንን ለስኬት የሚያዘጋጁ የተፈጥሮ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ከተጋፈጥካቸው ያሳድጉሃል፤ ከፈራሃቸው ግን ተራ ሆነህ እንድትቀር ያደርጉሃል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሌላው የማያደርገውንና ድፍረት የሚጠይቅን ነገር ማድረግ ብዙም አይከብዳቸውም፡፡ ከፍታው አስፈሪ ከሆነ ተራራ ላይ በጀርባቸው ባዘሉት ፓራሹት ተማምኖ መዝለል፣ በሞተር ባይስክል እየበረሩ መገለባበጥ፣ … ድፍረቱና ድርጊቱ ብዙ ነው፡፡ ከእነዚህ የድፍረት ድርጊቶች መካከል በሁለት እጅግ ከፍ ባሉ ህንጻዎች መካከል በተወጠረ ቀጭን ገመድ ላይ ካለምንም ድጋፍ ተራምዶ ማለፍ አንዱ ነው፡፡ በአለም ከታወቀው የቀጭን ገመድ ተራማጅ (Funambulist) አንዱ ካርል ዋሊዳ (Karl Wallenda) ነው፡፡ ካርል ብዙ ድፍረት የሚጠይቁ ነገሮች በማድረግ የታወቀ ሰው ነው - የፍርሃት ቃል አውጥቶ አያውቅም፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1978 ዓ.ም በሳንዋን፣ ፖርቶሪኮ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የባለ አስር ፎቅ ህንጻዎች ላይ በተወጠረ ገመድ ላይ ለመራመድ ሙከራ አደረገ፡፡ ያቺ ሙከራ የዚህ ሰው የሕይወት መጨረሻው ነበረች - ተከስክሶ የሞተበት ቀን፡፡ ከሞተ በኋላ ሚስቱ ስትናገር እንዲህ አለች፣ “ይህንን ከመሞቱ በፊት ያደረገውን የመጨረሻ የገመድ ላይ ርምጃ ከማድረጉ በፊት ለሶስት ወራት ሙሉ አለወትሮው ወሬው ሁሉ የመውደቅ ፍርሃት ነበር፡፡ የፍርሃትን ሃሳብ ሲያስብ የመጀመሪያው ጊዜ ነው፡፡ እንደ እኔ አመለካከት ሃሳቡን ሁሉ የጣለው በገመዱ ላይ በመራመድ ላይ ሳይሆን ባለመውደቅ ላይ ነበር፡፡” የምትፈራው ጤና ቢስ ነገር ተስፋ ከምታደርገው መልም ነገር ይልቅ ፈጥኖ የመምጣት ባህሪይ እንዳለው አስተውለህ ታውቃለህ? ይህ የሚሆነው እድልህ እንደዚያ ስለሆነ አይደለም፤ በዙሪያህ ያለው ነገር መልካሙን ህልምህን ሳይሆን ፍርሃትህን የሚመግቡ መረጃዎችን የማቅረብ ዝንባሌ ስላለው ነው፡፡ ፍርሃትህን መጋቢው ብዙ ነው፡፡ የፈሪውና “የአጉል ጠንቃቃው” ወሬ፣ የሶሻል ሚዲው ወሬ፣ የዜና አገልግሎት የዝገባ ትኩረት … የፍርሃት ምግቡ ብዙ ነው፡፡ ማንኛውም አዲስ እርምጃ ፍርሃትና ማስከተሉ አይቀርም፡፡ ሆኖም ትኩረታችን ፍርሃቱ ላይ ከሆነ ወይ ሳንራመድ እዚያው እንቀራለን፣ ወይ እየፈራን ተራምደን እንወድቃለን፡፡ ፍርሃት እንዲህ ይልሃል … - አትመልከት - አንድ ነገር እንዳታይ! - አታድምጥ - አንድን ነገር እንዳትሰማ! - አታስብ - አንድ ድምዳሜ ላይ እንዳትደረስ! - አትወስን - ስህተት እንዳትሰራ! - አትራመድ - እንዳትወድቅ! - አትኑር - እንዳትሞት! - አትማር - ፈተና እንዳትወድቅ! - አትውደድ - እንዳትጎዳ! በሕይወትህ ልታነግስ የምትችለው ስሜት አንዱን ብቻ ነው - የፍርሃትን ወይም የመኖር ድፍረትን፡፡ አንዱ እንዲነግስ ስትፈቅድለት ለሌላኛው የባርነት ትእዛዝን እያስተላለፍክ ነው፡፡ ፍርሃት ሲነግስ የመኖር ጣእም ይጠፋል፡፡ ስለዚህ አትፍራ! ተራመድ! ውጣና ሞክር!
Show all...
💁‍♂የትዳር ጓደኛ እንዴት እንምረጥ?💁 የሕይወት ጓደኛ ምርጫ መስፈርቶች ትዳር ምስረታ ማሰብ ሲጀመር፣ ትዳር እንዲጸና ማድረግ የሚያስችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሰብዓዊ መስፈርቶች መኖራቸው ቸል ሊባል የሚገባው ነጥብ አይደለም፡፡ ጋብቻ መለኮታዊም ሰብዓዊም ተቋም እንደ መሆኑ መጠን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርኆዎችና፣ ሰብዓዊ ተሞክሮዎች፣ ቋሚና ዘላቂ መመሪያዎች እንዲሁም አላፊና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተገናዝበው የሚተገበሩበት ሲሆን፣ ምንጊዜም ቢሆን ለመለኮታዊው፣ ዘላቂና ቋሚ ለሆነው መስፈርት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል፡፡ 👉1. ምርጫው በውስጣዊ ማንነት እንጂ ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ እንዳይመሰረት መጠንቀቅ፣ ምንም እንኳ ውጫዊ ውበት ወይም ነገሮች በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ያላቸው መሆኑ ባይካድም፣ ውስጣዊ ውበት፣ የአስተሳሰብ ቁንጅና፣ በእምነት የተሞላ ቅንና ሩህሩህ ልብ፣ እንዲሁም ሙያ የላቀ ትኩረት ሊሰጣቸው ወይም ተመዛዝነው ሊታዩ ይገባል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊ ውበታቸውን መንከባከብ ላይ ብቻ ለሚያተኩሩ አማኝ እህቶች ሲመክር “…ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣…” ካላቸው በኋላ የላቀውን ነገር ሲያመለክታቸው “…ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ …” በማለት የትኩረት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ያሳባቸዋል (1ጴጥ.3፡3-4፤ )። ይህ ምክር ለወንዶችም ጠቃሚ ነው፡፡ 👉2. ለጋብቻ የታሰበው ወንድ ወይም የተመረጠችው ሴት አማኝ መሆኑን/ኗን ማረጋገጥ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ቃል ኪዳናዊ ግንኙነት እንደ መሆኑ መጠን መከናወን ያለበት አማኝ በሆኑ ተቃራኒ ጾታ ባላቸው ሁለት ግለሰቦች መካከል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት የሰጠ ሲሆን፣ “… ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? …” በማለት የሚያቀርበው ሙግት በተለይ ከጋብቻ አንጻር በጥልቀትና በጥሞና ሊታይ የሚገባው እውነታ ነው (2ቆሮ.6፡14-16) ፡፡ 👉3. የወደፊት ተጣማጆች ልብ ዝንባሌ መሰረቱ እውነተኛ ፍቅር እንጂ የሌሎች ነገሮች ግፊት እንዳይሆን መጠንቀቅ፣ በተቃራኒ ጾታዎች መካከል መሳሳብ፣ መፈላለግ መኖሩ ተፈጥሯዊ ጉዳይ በመሆኑ አንዱ ሰው ሌላውን ማፍቀር ኃጢአት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከሁሉ አስቀድሞ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለጋብቻ ሲታሰብ መነሳት ያለበት ጥያቄ፣ በእርግጥ ይህን/ይህቺን ሰው እወደዋሁ/እወዳታለሁ? የሚለው እንጂ፣ ምን አለው? ከማን ወገን ነው? …ወዘተ ሊሆን አይገባም፡፡ ይህን ጉዳይ አውጥቶ አውርዶ የመወሰን ግላዊ ነጻነትን የሚጋፉ አያሌ ልምዶች ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መኖራቸው እሙን ሲሆን፣ ውጤታቸውም አስከፊ ነው፡፡ ከነዚህም ምክንያቶች መካከል የፍቅር ግንኙነቱን ከሚፈልጉት አንዱ “እግዚአብሔር አንቺን/አንተን ሰጥቶኛል” ብሎ ጥያቄ ማቅረብ፣ አንዳንድ ነቢያት ነን ባዮች “አከሌን/እከሊትን እንድታገቢ/እንድታገባ እግዚአብሔር ተናግሮኛል” ሲሉ የሚያመጡት አሳሪ መልዕክት፣ እንዲሁም ማንም ሰው የፍቅር ስሜት የሌለውን ሌላ ሰው አግብቶ ሰላም ያለበት፣ የተረጋጋና የእግዚአብሔር በረከቶች የሚከተሉት ኑሮ መሥርቶ መኖር ስለሚቸገር ራስን እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሥራ መጥመድ ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ግንኙነት ውስጥ ዘሎ ከተገባ በኋላ ችግሮች ውሎ አድሮ መከሰት ሲጀምሩ “እግዚአብሔር እንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ስገባ ለምን ዝም አለኝ?” ብሎ ለማማረር መሞከር ስሜት ሊሰጥ የማይችል ቂልነት መሆኑን መገንዘብና ኃላፊነቱን መውሰድ ግድ ይላል፡፡ 👉4. ብስለትና ዝግጁነትን መመዘን ጋብቻ ቤተሰባዊ ኑሮን ለመመሥረት ሕጋዊ የመግቢያ በር ስለሆነ ቀጣዩን ኃላፊነት ወስዶ ለመኖር ከሚያስችለን ሁለንተናዊ ብስለት ደረጃ ላይ እንገኛለን? ብሎ ራስን መጠየቅና ሁኔታዎችን መመዘን ብልህነት ነው፡፡ ብስለት አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ገጽታዎችን ሊያጠቃልል የሚችል ሲሆን፣ ሁለት ከተለያዩ ጾታዎች፣ ጀርባ ታሪኮች፣ አመለካከቶች፣ እውቀት ደረጃ፣ የአስተዳደግ ባሕል የመጡ ሰዎች የጋራ ጎጆ ቀልሰው አንድ ሥጋ ሆነው አብረው ለመኖር ሲጣመሩ ያስተሳሰራቸውን ጽኑ ፍቅርና እነዚህን ልዩነቶች አጣጥመው ወደፊት ለመራመድ ብስለት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እርስ በእርስ እየተናበቡ ፍቅርን ለመለዋወጥ፣ የአንዱ ብርታት የሌላውን ድካም እየሸፈነ የሚመች ረዳት የመሆን ሚናውን ለመወጣት ዝግጁ መሆን ከእያንዳንዱ የትዳር አጋር ይጠበቃል፡፡ እንዲህ ሲባል ግን ፍጹምነትን መጠበቅ ይኖርብናል ማለት አይደለም፡፡ ይቀጥላል ...... ✍ ፓ/ር ሙሴ በላይነህ
Show all...
መንፈስ ቅዱስ 😇ክርስትና ማለት መንፈስ ቅዱስ በሰው ልጆች ህይወት ራሱን የሚገለጥበት ህይወት ማለት ነው። 😒አንድ ሰው በህይወቱ ስኬታማ አይደለም ማለት ያለ መንፈስ ቅዱስ ህይወቱን እየመራ ማለት ነው። 💭መንፈስ ቅዱስ ህይወታችሁ ላይ ሲገለጥ፣ ➡️ወደ እውነት ይመራቹኋል ➡️ያስተምራቹኋል፣ ➡️እየሱስ ያለውንም ሁሉ ያስታዉሳቹኋል። ➡️መሪያችሁ ይሆናል ➡️ያጽናናቹኋል፣ ➡️በራሳችሁ መስራት ማትችሉትን ነገሮች መስራት እንድትችሉ ሃይል ይሆናቹኋል። ➡️ወዳጃችሁ ይሆናል፣ ከእግዚአብሄር የራቃችሁ ያህል ሲሰማችሁ ወደ እርሱ ይመልሳቹኋል፣ ➡️ወደ ሃጥያት እንዳትገቡ በልባችሁ የንሰሃ መንፈስ ይከታል። 🎁የሚያስፈልጋችሁ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ተጠቃሎ አለ:: ደስታ ቢሆን, ሰላም ቢሆን, ቅባት ቢሆን...
Show all...
ክፍል6:- በምድራችን ላይ በክፉ መንፈስ ተነድተው ሕዝብን ያሳሳቱ ሀሰተኛ ክርስቶሶችና ነብያት! አን ኤልዛቤጥ ሊ(1736-1784) በእንግሊዝ ሀገር የተነሳችና "ተንቀጥቃጮች የተሰኘ" ሀይማኖት የፈለሰፈች ተከታዮቿም <<እናታችን>> እያሉ የሚጠሯት ሀሳዊ ክርስቶስ ሆና ተነስታ ነበር። ስታስተምርም ራሷን የምትገልጸው እኔ በሴት መልክ የተገለጥኩ ሁለተኛው ኢየሱስ ነኝ እያለች ብትሰብክም እንኳን ለሌላው ልትተርፍ ይቅርና ራሷን ማዳን ሳትችል ቀርታ እስከ ምጽአት የመጨረሻው ፍርድ ድረስ ላትነሳ ሞታ በድንጋይ ታትማለች የፍቅሩ ምርኮኞች
Show all...
🛎🛎🛎ዓለም ወዴት እየሄደች ነው?🛎🛎🛎 1. መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል * በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም *በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ *ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡ *የmiami ከተማ በመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ .*ካናዳ ከእንስሳት ጋር የ sex ግንኙነትን መፍቀዶአ * በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ። ⚠️⚠️⚠️የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ደርስዋልና ንስሃ እንግባ ⚠️⚠️⚠️ ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ? ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? ኢየሱስ “በጓደኞችህ ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድሃለሁ” አለ ፡፡ ኢየሱስን ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት ኣሜን !!! ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች❤️❤️
Show all...
ክፍል5:- ሱን ሚዩንግ ሙን (1920-2012) በሰሜን ኮሪያ ተወልዶ በደቡብ ኮሪያ ያደገው ሙን የግሉ ቤተክርስቲያን መስራች ሲሆን ራሱን ሁለተኛ ኢየሱስ እንደሆነና ከዚህ ቀደም በስጋ ተገልጦ ሳለ ሳይጨርሳቸው የሄደውን ጉዳይ የሱ መገለጽ ማስፈለጉን በአደባባይ የሚናገር ሰው ነበር። ሚስተር ሙን ባለቤቱን <ሃክ ጃን ሀን> የሚጠራት አዳምና ሄዋን ያበላሹትን ዓለም በማጽዳት መልካም ቤተሰብን በዓለም ላይ ለመመስረት የተፈጠረች ናት በማለት ሲያሞካሻት ነበር። ሙን የተባረከ የሕብረት ጋብቻ በሚል ዘመቻ በአንድ ቀን እስከ ብዙህ ሺህ የሚቆጠሩ ጥንዶችን አሜሪካ ባለችው በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ጋብቻ በማስፈጸም ዝናው ይታወቃል። ሙን በአሜሪካን ሀገር ሳለ በፈጸመው የታክስ ማጭበርበር ወንጀል ተከሶ 18 ወራት ተወስኖበት፤ ከዚህ ውስጥ የ13 ወራት እስራቱን ቅሞ በአመክሮ ሊለቀቅ ችሏል። ሱን ሙን ከ3 ቢሊዬን በላይ ሀብት ያለው ሲሆን የተለያዪ ኮርፕሬሾችንና የክሲዮን ማሕበራት አሉት። ሃሳዊዉ ሙን በተወለደ በ92 ዓመቱ በኒሞንያ በሽታ ሞቶ ላይነሳ ተቀብሯል። እሱ ቢሞትም በሱ የሀሰት ትምህርት የተታለሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላት በተለያዪ የዓለም ሀገራት ለማፍራት ችሏል። ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች❤️❤️
Show all...
               .✡.#️በርታ#.✡️. 📚“እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ #በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው #ጸጋ #በርታ#።”    2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1-7 ✡️.#በውስጡ#ሰውነትህ በመንፈስህ#ጥንካሬ#በርታ። ✡️.#በቃሉ የጠለቀ #እውቀትና #በጸሎት በርታ። ✡️.እግዚአብሔርን #የጠራህን #በማወቅ #በርታ። ✡️.#የክርስቶስን #ፍቅር #በማወቅና #በፍቅሩ ላይ በመመላለስ #በርታ#። ✡️.#ራዕይህ ላይ #በማተኮር #በመትጋት#ተስፋ #ባለመቁረጥ #በርታ#። ✡️.#የእግዚአብሔር #ጸጋ #በመታመን #በርታ#። ✡️.የነገን #ክብር የፍጻሜውን #ድል እያሰብክ #በርታ። ✡️.በብዙ #መከራ #ተቃውሞ ፈተና#የጸናውን ኢየሱስን ጀማሪና #ፈጻሚ የሆነውን #እየተመለከትክ#በርታ። ✍️👉በፍጹም #ተስፋ #አትቁረጥ፦ ✡️.#የጠላትን#ሀሳብ#ባለመሳት#ጸንቶ   #በመዋጋት#በርታ። ✍️👉የሚያበረታ#ፀጋ አለ#ብቻህን አይደለህም#ቅረብ #በእምነት ወደ#ፀጋው ዙፋን እሱ#ያበረታሀል💪💪 🎯#በርታ #ጌታ #የታመነ እና #ኪዳኑን የማያጥፍ መሀሪ መሆኑን #በማሰብ#በርታ ጠንከር ። 🎯#ራዕይህን #ህልምህን#ጌታን ደግሞ#እንዳንተ በብዙ #መከራ#ፈተና#ፀንተው #ድል የነሱትን በማሰብና ለድልነሺዎች የተዘጋጀውን የክብር አክሊል እያሰብክ በርታ።  
Show all...
❤️#ወንጌል❤️ ============= ✍️ወንጌል የሚለው ቃል (ከላቲን evangelium / ኢቫንጄሊየም, ከጥንት የግሪክ ቃል εὐαγγέλιον / ኧውጄሊዮን (ዮአንጄልኦን) = አስደሳች መልዕክት፣ የምስራች ፣ መልካም ዜና ከሚለው የተገኘ ቃል ነው። Greek: εὐαγγέλιον Transliteration: euangélion Pronunciation: yoo-ang-ghel'-ee-on 📌ወንጌል ማለት፦ ============= ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ አስደሳች መልዕክት ፣ መልካም ዜና መልካም የምሥራች ነው፡፡ የንስሐ፣ የመፍትሄ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የተስፋ፣ የደኅንነት፣ የእርቅ፣ ከፍርድ የመዳን፣እና የዘላለም ሕይወትን የሚያውጅ መልካም የምስራች ነው። 📌ወንጌል ስለማን ነው???? ================= ልናስተውለው የሚገባን ነገር፦ 👉ወንጌል ባለጠግነትም ድሀ መሆንም አይደለም 👉ወንጌል ልሳንም ጥምቀትም አይደለም 👉ወንጌል ከሰው ልጆች ተግባር ጋር የሚገናኝ አይደለም ❤️ወንጌል ነገር ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ጌታ ኢየሱስ ስለ ሀጥያታችን እና ስለበደላችን መሞቱን,መቀበሩን እና መነሳቱን የሚያውጅ ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ የእግዚአብሔር የማዳን ሀይል ነው። ሮሜ 1 (Romans) 3-4፤ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሮሜ 1 (Romans) 16፤ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። 📌የወንጌል ዋነኛው መልዕክት ================== የእግዚአብሔርን የማይለዋወጥ ፍቅር ለሀጥያተኞች የሚያውጅ እና በክርስቶስ የቤዛነት ስራ ሰዎች ከ እግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ እና የዘላለምን ሕይወት በነጻ በእምነት እንዲቀበሉ ኃጢአት የሚያስከፍለውን ክፍያ ለመክፈል ማለትም ከሁሉ የከፋውን ሞትን ለመሻር ክርስቶስ ከ ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ ሰው ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን የሚናገር መልካም የምስራች ነው። ( ሐዋ13:28-40,ሐዋ13:38-41፣ ሮሜ.3:21-28፣ 1ቆሮ.15:3-4)። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው ወንጌል በመስቀል ላይ የተከናወነ አስደናቂ የድኅነት ስራ ነው፣ “መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ..” (1ቆሮ.15፡1-4)። የክርስቶስ ሞት እና ትንሳዔ የወንጌል ማዕከል ነው። 📌ወንጌል ለማን ይሰበክ?? ================ ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሚታወጅ መስቀል ላይ የተሰራ የእግዚአብሔር የማዳን ሀይል ነው። ማቴዎስ 28 (Matthew) 19-20፤ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው…” (1ጢሞ.1፡15)። ወንጌል ሰዎች ከኃጢአታቸው ንስሃ በመግባት የበደላቸውን ስርየት እንዲቀበሉ ይናገራል፣ “..በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከ ኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል” (ሉቃ.24:47) ። ሀጥያተኛ የሆነው የሰው ልጅ በመስቀል ላይ በተሰራው የክርስቶስ የማዳን ሥራ በማመን ዘላለሙን በነጻ ማሳመር ይችላል። ዮሐንስ 3 (John) 14-15፤ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። 16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። 17፤ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። 18፤ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። “በልጁ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው” (ዮሐ.3:36)። በኃጢአት ምክንያት ከሚመጣ የዘላለምም ፍርድ ያመልጣል፣ “በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም..”(ዮሐ.3፡18)። ዮሐ 3:16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ወንጌል አደራ እንጂ እንጀራ አይደለም!!! ይቀጥላል.......
Show all...
የፍቅሩ ምርኮኞች አምስቱ የንስሀ ደረጃዎች 1)ሀጢአትን ማወቅ 2)ሀጢአትን መናዘዝ 3)ሀጢአትን መተዉ 4)ወደ ቀድሞ ቅድስና መመለስ 5)ትዕዛዛቱን መጠበቅ
Show all...
🌴 #ሥራችሁ_ምንድነው❓🌴 🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴 🔆#ጥያቄው_ለምታነቡት_ሁሉ ይመለከታል ሥራችሁ ምንድነው❓ ለምንድነው በዚህ ምድር ያላችሁት❓ ለምንድነው የምትኖሩት❓ ምንድነው የህይወት ግባችሁ❓ ብዝዎቻችሁ መልሳችሁ ተመሳሳይ ነው❗️ 🔆#ክርስትያኖች_ለምን እንደሚኖሩ ሲጠየቁ መልሳቸው ተመሳሳይ ነው #እግዚአብሔርን_ለማምለክ_እና_ለማመስገን! በማለት ብቻ ይመልሳሉ፡፡ ነገር ግን እናስተውል ለምንድነው በምድር ላይ ያለነው⁉️ኛ እዚህ ምድር የምንኖረው አምልኮ እና መስጋና ለመስጠት ብቻ አይደለም! አምልኮ ማለት ለእግዚአብሔር ስግደት ማቅረብ ክብር መስጠት ነው፡፡ ታድያ እግዚአብሔር እኛን በዚህ ምድር ላይ ያስቀመጠን ለሳምንታዊ አምልኮ ብቻ ቢሆን ኖሮ ልክ ጌታን የተቀበልን ዕለት ወደ ጌታ እንወሰድ ነበር ወይም እንሞት ነበር፡፡ ምክንያቱም ፍፁምና ጣፋጭ የሆነ መዓዛ ያለው በዕልፍ ዐዕላፍ መላዕክት የታጀበ ፣ ቀን እና ለሊት ሳይገድበን በቡጉ ስር 24 ሰዕት" ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" ለታረደው በግ ክብር በአርያም እያልን እያልን የምንዘምርበት አምልኮ ያለው በሰማይ ነው፡፡ እናስ ምድር ምን እንሰራለን ሌላ አላማ አለ! 🔆#ጌታ_ኢየሱስ በሰይጣን ሲፈተን ለሶስተኛ ግዜ በፈተነው ግዜ ኢየሱስ የሰጠው መልስ እንዲህ የሚል #ለአምላክህ_ለእግዚአብሔር_ብቻ_ስገድ_እርሱን_ብቻ_አምልክ_ተብሎ_ተፅፏል 🙏#በዚው_አጋጣሚ ሰይጣንን የምታሸንፉት መጽሐፍ ላይ በተፃፈው ቃል ነው፡፡ እናም ኢየሱስ ለሰይጣን እንደዛ ከመለሰ በኃላ በምድር ያለሁት እግዚአብሔርን ለማምለክ#ለመስገድ ነው ብሎ ወደ ስግደት አልገባም! ይልቁንስ ወደምድር የመጣበት ሌላ ምክንያት ስለሚያውቅ ወደ ተልዕኮ ሄደ፡እናንተስ በምድር ያላችሁት ለማምለክ እና ለመስገድ ብቻ ነው? አይደለም! ያለነው በሳምንት አንዴ ቸርች ለመመላለስ ብቻ አይደለም! 🔰#በመጽሐፍ_ቅደሳችን ውስጥ በብሉይ ኪዳን የተጻፈ ትንቢተ ዮናስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰?#ነቢዩ_ዮናስ_እግዚአብሔርን_አልታዘ_ብሎ_ተርሴስ_ወደ_ምትባል_መንደር_በመርከብ_ከእግዚአብሔር_ኮብልሎ_ለመሄድ_ተነሳ_በመርከብዋም_ሂሳብ_ከፍሎ_ተሳፈረ_እግዚአብሔርም_በባህሩ_ላይ_ታላቅ_ነፋስን_ላከ_ከባድ_ማዕበልም_ተነስቶ_መርከቢቱን_አንገላታት_ልትሰበርም_ተቃረበች፡፡ 🔰#በመርከብዋ_ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎችም ፈሩ፡፡ ዮናስ ግን ወደ መርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ ተኛ ፤ በከባድ እንቅልፍ ላይም ነበር፡፡ መርከበኞቹም እርስ በርሳቸው "ይህ ክፉ በማን ምክንያት እንደመጣብን ለማወቅ ኑ ዕጣ እነጣጣል" ተባባለው ዕጣ ጣሉ፡፡ ዕጣውም ዮናስ ላይ ወደቀ፡፡#ዮናስ_1_7 ከዚያን እንዲህ ብለው ጠየቁት #ሥራህ_ምንድነው❓#ዮናስ_1_8 ብለው ነው የጠየቁት፡፡ 🔰#የሚገርምው_የእርሱም መልስ ከእኛ የተለየ አልነበረም፤ የብስንና ባህርን የፈጠረውን፤ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ" ነበር ያለው#ዮናስ_1_9፡፡ ዮናስ ስራው የሆነውን የተልዕኮውን ሕይወት ረስቶ #እግዚአብሔርን_ማምለክ በሚል ሰበብ ብቻ እየኖረ ነበር ማለት ነው፡፡ 🔰#ስራው_ግን ለነነዌ ሕዝብ እንዲደርስ ነበር፡፡ ስራው ጥፋት የተዘጋጀለትን ትውልድ እንዲታደግ ፣ መልእክት እንዲያደርስ ነበር፡፡ ደግሜ ልጠይቃችሁ ምን እየሰራችሁ ነው? ሥራችሁ ምንድነው? ለአምልኮ ወይስ ለተልዕኮ? ጌታ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ ብኃላ 🔰#በሜቴዎስ_ወንጌል_ላይ ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፣ ጥቂቶች ግን ተጠራጠሩ፡፡ ኢየሱስም ቀርቦ እንዲህ አላቸው🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 #እንግዲህ_ሂዱና_አሕዛብን_ሁሉ_በአ_በወልድና_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም_እያ_መቃችኋቸው_ያዘዝኋችሁንም_ሁሉ_እንዲጠብቁ_እያስተማራችኋቸው_ደቀ_መዛሙርት_አድርጓቸው❗️ ✝በዚው አጋጣሚ የክርስታያን(የአማኝ) ጥጉ ነቢይ መሆን ፖስተር ወይም ጼንጤ መሆን ዲያቆን ፣ ዘማሪ መሆን ሳይሆን ደቀ መዝሙር መሆን ነው፡፡ 📚#ማቴ_28_19_20 እና ልክ ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ ሰገዱለት(አምልኮ ሰጡት) ይላል! ጌታም ከዚህ ብኃላ በአብ ቀኝ እቀመጣለው እናንተም ልክ እንደአሁኑ ስገዱሉኝ አምልኩኝ አላላቸውም፤ ይልቁንስ ሂዱና ህዝቦችን ሁሉ በአብ ፣ በወልድ ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠቀማችሁ ይህ ደግሞ ተልእኮ ነው፡፡ 🔰#አያችሁ_ጌታ ኢየሱስ በምድር የኖረው ለተልዕኮ ነው፡፡ የተወለደው እራሱ ወንጌልን ሊሰብክ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ ተልዕኮ ነው፡፡ እናስ እናንተ ለምን እየኖራችሁ ነው? እግዚአብሔርን ለማምለክ እንዳትሸወዱ እርሱ ምድር ላይ ያለንበት ቀዳሚ ተልእኮአችን አይደለም! በምድር ላይ ያለነው ስለ እውነት ልንመሰክር ነው፡፡ 🔰#የሚገርማችሁ_እናንተ ወንጌልን የመስበክ እድልን አግኝታችሁ ግን እድላችሁን አትጠቀሙም መልአክት ለመስበክ እድሉን ቢያገኙ እንዴት ደስተኛ እንደሚሆኑ ብታውቁ!ግን ጌታ እኛን ከመውደዱ ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ እድሉን ለኛ ሰጠን፡፡ ወንጌልን መመስከር ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ ተነሱና ከአሁን ጀምሮ መስክሩ! እወዳችዋለው....... ♻ join ♻ learn ♻ share
Show all...
#እኔነት እኔነት የትሕትና መንገድ ተጻራሪ፣ የትሕትና ጸር ነው። እኔነት ለአህያዊ አስተሳስብ ዳርጎ እኔ ከሞትኩ የሚያሰኝ እዳ ነው። እኔነት መተካከልን ብቻ እያሳየ፣ በመተው ፈንታ ይገባኛል የሚያሰኝ ስግብግብ የአልጠግብ ባይነት መንፈስ ነው። እኔነት ባልንጀሬን በማለት ፈንታ፣ እኔ እብስ የሚያሰኝ ቁራኛ ነው። እኔነት የክርስትያናዊ ሕይወት ፍጹም ተጻራሪ ነው። እኔነት በክርስቶስ ኢየሱስ ያልነበረ የዓለማዊነት ርዝራዥ ነው። እኔነት ትእቢትን አድርቶ ለስብራት የሚዳርግ ደመኛ ነው። ዘማሪው "መጎንበስ የጠላ ድንገት ይሰበራል፣ እኔነት ሲበዛ ትእቢትን ያደራል" ብሎ ዘምሯል። እኔነት ራስን ብቻ እንጂ ሌላውን የሚከልል መጋረጃ ነው። እኔነት በሌላው ሥራ ሳይቀር ራስን ለማሳየት ከፍ ያለ ማማ ላይ መውጣት ነው። እኔነት ከእርሱ ነው፣ በእርሱ ነው፣ለእርሱ ነው በማሰኘት ፈንታ፤ ከእኔ፣ በእኔ፣ ለእኔ የሚያሰኝ እብሪት ነው። እኔነት ለራስ ብቻ በማግበስበስ ሌላውን መርሳት፣ ሲብስም መጨፍለቅ ነው። እኔነት ዘማሪዋ "ዛሬም እኔ ነገም እኔ ወሬዬ እኔ፣ ልመናዬ እኔ... አወይ አልጠግብ ባይነቴ፤" እንዳለችው እኔ እኔ እያለ የሚያስለፈልፍ ዛር ነው። እኔነት ለጌታ ያልተሰጠ ሕይወት ንጽብርቆሽ ነው። የቤተ ክርስቲያን ዝብርቅርቆሽ ሁሉ ከእኔነታችን የተወለደ ነው። እኔነት ራስን አሞግሶ ሌላውን የማንኳሰስ እብደት ነው። ተከባብሮ እና ተቻችሎ መኖር ያቃተን እኔነታችን ማሸነፍ ስላቃተን ነው። ከወንድም ጋር ከመክበር ብቻ መድመቅ ውዴታችን ስለሆነ ነው። በማይለያይ እንደውም በአንድ አይነት ነገር ሁሉ ሳይቀር እየተለያየን እዚህም እዛም ያስደኮነን ሌላ ሳይሆን የእኔነት እርሾ ነው። በክርስትና ጉዟችን ውስጥ እርግጠኛ መሆን ያለብን አንድ ነገር ባልተካደ ሕይወት ጌታን እንዳንከተል ነው። ይህ ትግል ተወጣሁት የምንለው ሳይሆን፣ የዝንትዓለም ትግላችን ነው። እያደባ የሚከተለንን እኔነት እየተዋጋን ወደ ፊት እንቀጥል። #መጋቢ_ስንታየሁ_በቀለ
Show all...
ክፍል 3;- ዮሐንስ ከሚፍለቀለቀው ዘይት ውስጥ በህይወት በመትረፉ የሮማ ባለስልጣናት እርሱን በምንም መንገድ መግደል አይቻልም በማለት ተስፋ ቆረጡ። ከዚያም አለታማ ወደ ሆነው <<ፍጥሞ>> ወደ ምትባል ደሴት በግዞት ለሁለት ዓመታት እንዲኖር ተፈረደበት። ሐዋርያው ዮሐንስ በብቸኝነት ፍጥሞ በምትባለው ደሴት ባሳለፈው የመከራ ጊዜያት ሁሉ እግዚአብሔር ከጎኑ ነበር። አስደናቂ የሆኑ ሰማያዊ ራዕዮችን በማየት [[የዮሐንስ ራዕይን]] የጻፈውም በዚህ ጊዜ ነው። ዮሐንስ ንጉሰ ነገስቱ ዶሚታን በ99 ዓ'ም ሲሞት ከግዞት ነጻ ተለቆ ቀድሞ የቤተክርስቲያን መሪ ወደ ነበረበት ወደ ኤፌሶን ቤተክርስቲያን ሄዶ አገልግሎቱን ቀጠለ። በዚያ ቤተክርስቲያን ሳለ በተመረዘ ምግብ እንዲገደል ሙከራ ቢደረግበትም የሚገድል ነገር ቢበሉ እንኳ አይገድላቸውም /ማር 16:18/ ብሎ ጌታ በገባው የተስፋ መሠረት ከሞት ተረፈ። በኤፌሶን የኢስያን ቤተክርስቲያን በመምራት በጊዜው የተጻፉትን የማቴዎስ የማርቆስና የሉቃስ ወንጌላትን በማንበብ ለእውነተኛነታቸው ማረጋገጫ ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዮሐንስ መልዕክቶችን በመባል የሚታወቁ ሶስት መልዕክቶችን በመባል የሚታወቁ ሶስት መልዕክቶችን በመፃፍ ሐዋርያው አስተዋጽኦ አበርክቷል። ሐዋርያው ዮሐንስ ሌሎች ሐዋርያዎቶች ሁሉ ከሞቱ በኋላ ለሰላሳ ዓመታት በታማኝነት እግዚአብሔርን አገልግሎ በ101 ዓመቱ ወደ ጌታው እቅፍ ተሰብስቧል። ❤️❤️ የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
ክፍል 2 _________________________________ ዮሐንስ ለኢየሱስ በጣም ቅርብ ናቸው ከሚባሉ ሶስት ሐዋርያት አንዱ ነው። ያቆብ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሌሎቹ ዘጠኙ ሐዋርያት ያላዩትን ብዙ ተአምራት አይተዋል። ኢየሱስን ከነሙሉ ግርማው እና ክብሩ እንዲሁም ፊቱና ልብሱ እንደ ጸሐይ ሲያበራ ለመመልከት የታደሉትም እነርሱ ናቸው። የሮማው ንጉሰ ነገስት ወደ ዮሐንስ በመመልከት ስማ አንተ የአንተ ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እስቲ አሁን ከእጄ እንዲያድንህ ጠይቀው? አለ። ወደ ጠባቂውም በመዞር ውሰዱት ሲል አዘዘ። የሚፍለቀለቀው ዘይት ተዘጋጅቷል ዮሐንስ ወደ ዘይቱ ሲቃረብ ሕዝቡ በደስታ ይጮህና ያጨበጭብ ጀመር። ሐዋርያው የሚፍለቀለቀው ዘይት ውስጥ እንደገባ እጁን ወደ ሰማይ አባቱ ዘርግቶ መጸለይ ጀመረ። ደቂቃዎች ተቆጠሩ ዮሐንስ አሁንም እየጸለየ ነው። የሕዝቡ የደስታ ጩኧት ወደ ድንጋጤና ፍጹም ፀጥታ ተለወጠ አከባቢው ፀጥ ረጭ ብሏል ተአምር ነው ሐዋርያው ፀሎቱን ቀጥሏል አንድአንዶቹ ይህንን ጉድ ተመልከቱ፤ አምላኩ ኢየሱስ ከሞት አዳነው እያሉ ይናገራሉ። የሮማው ንጉሰ ነገስት ሳያስበው ከመቀመጫው በድንጋጤ ቆሞ ትዕይንቱን ይከታተላል። ክርስትና ከሮማ ግዛቶች የማጥፋት የሁሉ መቀጣጫ ይሆናል ብሎ የሰራው ስራ ለክርስትና ማበብና መስፋፋት ምክንያት ሆነ። የሮማ ገዢው በድንጋጤ ወደ ተዋጡት ባለስልጣናቱ በመዞር ይህንን ሰው ለማጥፋት ሌላ ምንም መንገድ የለም ማለት ነው ሲል ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ ድምጹ እየተቆራረጠ ጠየቃቸው። የሕዝቡ ጩኧት የባለስልጣናቱን ቀልብ ስቧል ሐዋርያው እንደቀድሞ ሳይሆን ድምፁን ከፍ በማድረግ ለአምላኩ ክብር እየዘመረ ነው። በዚህ ጊዜ በሁኔታው ትዕግስቱ የተሟጠጠው ንጉሰ ነገስት ይህንን ሰው ከእንግዲህ አይኔ እንዳያየው በማለት በብስጭት ጮኧ። ❤️❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️❤️
Show all...
የማይሸበረው ዮሐንስ፤ ሮማን ኢምፓየር/95 ዓ'ም/ ክፍል 1:- ይህ ሐዋርያው ዮሐንስ ነው! ይህ ሐዋርያው ዮሐንስ ነው! በማለት ነበር የሮማ ገዥው ሰው ሁሉ እንዲሰበስብ ጥሪ ያስተላለፈው። ይህንንም መልዕክት መስማትና ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያቱ በሕይወት ያለውን የዮሐንስን አሟሟት ለማየት ህዝቡ ወደ አንፊ ትያትር/ግልጽ መድረክ ጎረፈ። የሮማ ኖጉሰ ነገስትም "እሺ ዮሐንስ የፍቅር ሐዋርያ የተባልከው አንተ ነህ? ለመሞትስ ተዘጋጅተሃል? ሲል በፊት ለፊቱ የቆመውን የእድሜ ባለጸጋ በንቀት እያየ ጠየቀው። ዮሐንስም መልስን ሳይመልስ ተደርድረው ከቆሙት ባለስልጣኖች መሐከል አንዱ ጣልቃ ገብቶ ክቡር ሆይ! ምን አልባት ሰምተው ይሆናል እነዚህ ሰዎች እኮ አምላካችን የሚሉት ኢየሱስ ሳይመለስ ዮሐንስ አይሞትም ሚሉት ትምህርት አላቸው አለ። ንጉሰ ነገስቱም በታላቁ የሮም ግዛቶች ውስጥ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ ሰምተውታል። እነዚህ ክርስቲያኖች ልበ ጠንካሮችና አጉል መንፈሳዊነት የተጠናወታቸው ናቸው። አይሞትም የሚሉት ይህ ሰው ዛሬ እንደሚሞት አሳያቸዋለሁ በማለት ዛተ። አንበሶች አንድአንድ ጊዜ ክርስቲያኖችን አይገድሉም እሳትም የማያቃጥላቸው ወቅት አለ። ለእንደነዚህ ዓይነቱ በሰይፍ አንገቱን ቆርጦ መገላገል ነው አለ ከንጉሱ አገልጋዮች አንዱ። የሮማ ንጉሰ ነገስትም ብዙ ስቃይ እንዳይደርስባቸው በሰይፍ የሚቀጡት እኮ የሮም ዜግነት ያላቸው ዜጎቻችን ብቻ ናቸው በማለት ሲናገር ሌላው ቀበል አደረገና በተቀቀለ ዘይት ውስጥ መጨመርስ መቼም ማንም ቢሆን ከዚህ አያመልጥም አለ። ንጉሱ በመስማማት ይህ ጥሩህ ሀሳብ ነው። በፍጥነት ዘይቱን አዘጋጁ ብሎ አዘዘ። ❤️የፍቅሩ ምርኮኞች❤️
Show all...
#ለኮሮና_አስደናቂ_መድኋኒት_ተገኝቷል!! ■ ዜናዉን የዘገበዉ #መልዐክ አሁን የተገኘዉ መድኋኒት ኮሮናን ጨምሮ ካንሰርን እስከ ዛሬ በህክምናዉ ሳይንስ መድኋኒት ላልተገኘላቸዉ በሽታዎች ሁሉ መፍትሄ ነዉ። ይህ መድኋኒት አሁን ላይ ዓለምን እያስጨነቀ ላለዉ የኮሮና በሽታ ብቻ ሳይሆን ወደፊት እንኳን የሰዉ ልጆችን ይገድላሉ ተብለዉ ለሚፈሩት በሽታዎች ሁሉ መፍትሄ መሆኑ ተረጋግጧል። ■ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠይቅ ሲሆን፤ መድኋኒቱን ለመዉሰድ ፍቃደኝነት ብቻ ነዉ የሚያስፈልገዉ። የትኛዉም ሆስፒታል መሄድ አይጠበቅባችሁም ነገር ግን እናንተ ፍቃደኛ ከሆናችሁ መድኋኒቱ ዋጋ ስለተከፈለበት በነፃ መዉሰድ ትችላላችሁ። መድኋኒቱን ልዩ የሚያደርገዉ አንድ ጊዜ ከተወሰደ እስከ መጨረሻዉ በሽታዉ ዳግም እንዳይከሰት ማድረጉ ከሁሉም መድኋኒቶች ለየት ያደርገዋል። ■ እግዚአብሔር አለምን እንዲሁ አለ ምንም ምክንያት ስለወደደ አንድያ ልጁን ሰጥቶናል። በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ከኮሮና ከካንሰር ከHIV ከተለያዩ በሽታዎች ሁሉ ያድናል፤ ከነፍስም ከስጋም በሽታና ሞት ያድናል። የመድኋኒቱ ስም ኢየሱስ ይባላል። እናንተን ለማዳን ማመንና መቀበል እንጂ ኋይማኖት፣ዘር፣ ቋንቋ፣ የሃብትና የዕዉቀት እንዲሁም የስልጣን ደረጃ አይጠይቅም። ኮሮና ብዙ የሚያወራለት አግኝቶ እንጂ ኋይለኛ የመሰለዉ ከዚህ መድኋኒት ጋር በፍፁም አይወዳደርም። ከዚህ በኋላ የተለየ መድኋኒት የለም ይሄ መድኋኒት አንድ ጊዜ ከተወሰደ የትኛዉንም ገዳይ በሽታ ማሸነፍ ትችላላችሁ። በሽታዉን ከእናንተ ላይ ያቃጥለዋል። #መድኋኒቱ #መድኋኒቱ #መድኋኒቱ ● ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፤ ሉቃስ. 2:11 ● የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና፤ ሮሜ. 10:13 ✍በጌታ በእየሱስ ስም የትኛውም በሽታ ከእናንተ እና ከቤተሰቦቻችው ይነሳል ይህን ድንቅ መልዕክት ለሁሉም #ሼር #share አድርጉ -ለበለጠ መረጃ ❤️ የፍቅሩ ምርኮኞች❤️
Show all...
#ልጅ ፡ አባቴ ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል? #አባት ፡ እንደነዚህ ሁን ልጄ #ልጅ ፡ እንዴት? #አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ጊዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን እንዲገኝ ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና፤ እንደ ጨውም ሁን ለሁሉም ምግብ ቢፈለግም በቀላሉ ይገኝ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ አይደለምና፤ ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተዉት ጊዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ ይመጣል እንጂ አይበላሽምና - በተገፋም ጊዜ ከፍ ከፍ ይላልና፡፡ #ልጅ ፡ እሺ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም? #አባት ፡ አለ ልጄ፤ እንደነዚህ አትሁን #ልጅ ፡ እንዴት? #አባት ፡ ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን የሌሎችን ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤ እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና፤ ከሁሉ ከሁሉ ግን እንደ ደወል አትሁን! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን አያስቀድስምና፡፡ ❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️
Show all...
❤️#በክርስቶስ_አማኞች_ሁለ_ተቀብተዋል❤️ ======================== ✍️ራስ(#ክርስቶስ) የተቀባ ከሆነ አካልም(#አማኞች ሀሉ) የተቀቡ ናቸው። ስለዚህ #ትኩስ_ቅባት የለም #እጥፍ_ቅባት የለም #ልዩ_ቅባት የለም #የሚበዛም_ሆነ_የሚቀንስ_ቅባት የለም ✍️ እናንተም #ከቅዱሱ( ከ ኢየሱስ from the #Holy One ) ቅባት ተቀብላችኋል# ....1 ዮሐንስ 2፡20፤ ♦️ በብሉይ ኪዳን #ቅባት በዋናነት ለመለኮታዊ አጀንዳ #መሾምን እና ኃይል መካፈልን ያመለክታል፥ የሚቀባውም እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አልነበሩም ። በብሉይ ኪዳን ነገስታትን ፣ ካህናትን እና ነብያትን በተለያየ ጊዜ ይቀቡ ነበር መንፈስም በላያቸው ይሆናል ስራውን ሲጨርስ ጥሎአቸው ሊሄድ ይችላል ዳግመኛ ስላልተወለዱም ለዘላለም በውስጣቸው መኖር አይችልም ነበር። ✍️ ለምሳሌ ዳዊት ለንግስና በእግዚአብሔር ሲሾም ሳሙኤል ቅባት አፍስሶበታል፥ከተቀባበትም ሰዓት ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል በዳዊት ላይ ነበር። 1ኛ ሳሙኤል 16:13። ✍️በብሉይ ኪዳን ንጉስ ዳዊት ሲቀባ ቅባቱ ራሱ ላይ ነው የፈሰሰው የተቀባው ራሱ እንጂ የአካል ክፍሉ ጨጓራው ፣እጁ፣እግሩ ለብቻው ተቀባ የሚል ቃል የለም እንደዚሁ ከክርስቶስ አካል ውስጥ አንድ አማኝ ራስ ከሆነው ከክርስቶስ ተለይቶ ሊቀባ አይችልም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረትም የለም። ♥️♥️ኢየሱስ #ክርስቶስ ነው። #ክርስቶስ_ማለት_የተቀባ_ወይም_መሲሕ_ማለት ነው።ኢየሱስ የእግዚአብሔር የዘላለም ዕቅድ በእርሱ ይከናወን ዘንድ የተቀባ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው (የሐዋርያት ሥራ 10:38) ክርስቶስ በእግዚአብሐር የተቀባ ከሆነ አማኝም #በክርስቶስ በመሆኑ የተቀባ ነው፥ ራስ የተቀባ ከሆነ አካልም የተቀባ ነው። ስዎች እንደሚሉት፦ #ትኩስ_ቅባት የለም #እጥፍ_ቅባት የለም #ልዩ_ቅባት የለም #የሚበዛም_ሆነ_የሚቀንስ_ቅባት የለም 1 ዮሐንስ 2፡20፤ እናንተም ከቅዱሱ(.ከ ኢየሱስ from the Holy One, . ) ቅባት ተቀብላችኋል ፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።. #በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚ ያፀናንና #የቀባን እግዚአብሔር ነው ደግሞም #ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው (2ኛ ቆሮ 1:21-) 1 ዮሐንስ 2 (1 John) 27፤ እናንተስ #ከእርሱ የተቀበላችሁት #ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ #ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። ♦️በአዲሱ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ የሚኖረው #በሁሉም አማኞች ውስጥ ነው ደግሞም #ለዘላለም ነው። አማኞች ብርቱ በነበሩበት ጊዜ አልመጣምና ሲደክሙ ጥሎአቸው ሊሄድ አይችልም እንዴውም ለደከመው ብርታትን እየሰጠ ያፅናናቸዋል። ✍️በአዲስ ኪዳንም መንፈስ ቅዱስን መጋበዝ እና ና ማለት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ። ዮሐንስ 14 ፡15-16፤ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ #ለዘላለምም# ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ዮሐንስ 14 (John) 17፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር #በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። በክርስቶስ ላላችሁ ፀጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ። ❤️የፍቅሩ ምርኮኞች❤️
Show all...
ሰላም የፍቅሩ ምርኮኞች ተከታዮቻችን ዛሬ እንደተለመደው አንድ ነገር ይዘንላችሁ መተናል😊😊 👉እሱም ምንድነው ካላችሁ አንድ ሰው በጌታ ካመነ,ከተጠመቀ,እንዲሁም የቸርች አባልነት ካገኘ ሙሉ ክርስቲያን ሊባል ይችላል ወይ የሚለው ነው? መልሱም እንዲህ ይሆናል ማለት ነው።😊 #ሙሉ ክርስቲያን ልባል አይችልም። ይሄ ከፊል ክርስቲያን ነው ምለው እንደ እኔ🤷‍♂ 💮ምክንያቱም እምነቱን በስራ አላሳየም። #እምነት_ያለሥራ ከንቱ ነው ተብሎ ተጽፏልና ። " ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። " (የያዕቆብ መልእክት 2:26) #ታገለግላለህ( ምኩራብ ላይ) #ታዘምራለህ/ለሽ #ፓስተር ነህ #ወንጌላዊ ነህ #ዲያቆን ነህ #ናታንም ነህ/ነሽ #ነብይ ነህ #ዘማሪ ነህ 🔱በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ ልትሳተፉ ትችላላችሁ ፤ ነገር ግን #በጎ_ፈቃደኛ ካልሆናችሁ #ወንድማችሁ ተረቦ እናንተ ጠግባችሁ ምታድሩ ከሆነ #የወደቀውን ማታነሱት ከሆናችሁ። #እግዜር_ይስጥልኝ ብላችሁ ምታልፉ ከሆነ #እየኖራችሁ ያለው ሕይወት #ከፊል_ክርስትና ነው። #እምነታችሁም_በድን ነው። #እናም_ዛሬ የክርስትና ሕይወታችንን #upgrade እናድርገው። " ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:18) የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️
Show all...
#ይነበብ 🤦‍♂አንድ በጣም ተናዳጅ ወጣት ነበር አንድ ጊዜ ይህን ባህሪው ያስተዋለ አባት አንድ ትምህርት ሊሰጠው ፈለገ ከዚያም ጠራውና በርካታ ሚስማር አሸከመውና በቀኑ ውስጥ በተናደድክ ቁጥር ሂድና አጥራችን ላይ ያለው እንጨት ላይ ምታው አለው። ሚስማሩን ተቀበለና የመጀመሪያ ቀን 37 ሚስማር አጥራቸው ላይ መታ። አባት የሚሰጡትን ትምህርት ሳይታክቱ እየተከታተሉ አጥራቸው ላይ የሚመታው ሚስማር በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ። ከዚያም ልጁ ብዙም ሳይቆይ ንዴቱን መቆጣጠር ጀመረ እንደውም አንድም ሚስማር ሳይመታ መዋል ጀመረ። ይህን ባህሪ ለውጥ ለአባቱ እስኪነግር ድረስ በጣም ቸኩሏል አባትም በጣም ተደስቶ በል አሁን የመታከውን እያንዳንዱን ሚስማር ንቀለው አለው። ከዛም ከሳምንታት በኋላ ነቅሎ ጨረሰ እና ለአባቱ ነገረው። አባቱ የልጁን እጅ በፍቅር ይዞ ወደ አጥሩ አመሩ። "ጥሩ ስራ ሰርተሀል ልጄ ነገር ግን እነዚህን ቀዳዳዎች ተመለከትካቸው አንተም በንዴት ውስጥ ሆነክ አንድን ቃል ስትወረውር እንዲህ የማይመለስ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ምንም ይቅርታ ብትደጋግም ጠባሳውን አታጠፋውም"። ስለዚህ የምትናገረውን ቃላት ከመናገርህ በፊት አመዛዝነክ ተመልከት ሰውን የሚጎዳ ከሆነ አትጠቀመው የሚጠቅም ከሆነ ግን ተናገረው። ❤️"አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር ለወዳጅዎ ያካፍሉ"👍
Show all...
"ወንጌል፣የንግግር ችሎታ፣ ወይም ከአፍ የማያልፍ ሕይወት የለሽ ደረቅ ታሪካዊ ዶክትሪን ሳይሆን፤ ሥር-ነቀል የሆነ የሕይወት መልእክት ነው። በአእምሮ የጥረት፣ በረቀቀ አመንክዮና ሙት በሆነ ሃይማኖታዊ ግልብ የፊደል ሽምደዳ ሊረዱት አይችሉም። የወንጌልን ጉልበት መረዳት የሚቻለው፣ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ነፍስንና የውስጥ ልብንሰርስሮ ሲገባ ብቻ ነው።" ጆን ካልቪን
Show all...
ክፍል4:- አህን ሳንግ ሆንግ (1985) በደቡብ ኮሪያ የተወለደው ይህ ሰው በ1964 ዓ'ም የሀይማኖት ተቋም መስርቶ ነበር። በኋላ ላይ ደግሞ ሌላ ሀይማኖታዊ ድርጅት አቋቁሟል። ሳንግ ሆንግ እርሱ የዳግም ምፅአት ምልከት መሆኑን ይሰብክ ነበር፤ በራሱ ቤተክርስቲያን እንደመምህር ሲቆጠር በተከታዮቹ ደግሞ እንደ ታላቅ ሰው ይቆጠራል። የቤተክርስታያኒቱ ዋና አመራር የሆነችው ዛንግ ጊልጃህ የተባለችው ሴት በገላትያ 4:26 ላይ የተመለከተውን ትንቢት የምታሟላ እሷ ናት ስለሆነች ''የኢየሩሳሌም እናት'' ወይም "ታላቅ ሴት" ተብላ ትጠራለች። የቤተክርስቲያኑ መስራች ሳንግ ሆንግ ደግሞ "ታላቅ ሰው" ተብሎ ይጠራል። ❤️የፍቅሩ ምርኮኞች❤️
Show all...
ክፍል3:- ኤርነስት ኖርማን (1904-1971) አሜሪካዊ የኤሌክትሪካል ኢንጂነር ባለሙያ የነበረና (ዩራኒየስ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ) መስራች የሆነ ሰው በአንድ ወቅት ከሙያው ውጭ እብደት መሰል ስብከት ጀምሮ ነበር። ከዚህ በፊት በዚህ ምድር ላይ የተገለጸው ''ኢየሱስ'' እኔ የማሕበሩ አባል ለሚሆኑ ሰዎች ''ያላችሁን ሀብትና ንብረት ለማሕበሩ ገቢ አድርጉና ሰማያዊ መዝገብ አከማቹ'' በማለት ሀብታቸውን በመሰብሰብ ለበጎ አድራጎት ስራ ለማዋል የሞከረ ቢሆንም ሀብታቸውን ተሞልጨው ሚስቶቻቸውን በቬንታ የማማገጥ ተግባር የተፈጸመባቸው ሁለት ተከታዮቹ በቂም በቀል ተነሳስተው ቦንምብ በማፈንዳት አብረውት ሊሞቱ ችለዋል። የክሪንሽና ቬንታ የክህደት ተግባርም እስከወዲያኛው በዛው አክትሟል ❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️
Show all...
ክፍል2:- ሎ ደ ፓሊንግቦኧር (1898-1968) በዜግነቱ ኔዘርላንዳዊ የሆነው ፓሊንግቦኧር በሙያው የተዋጣለት አሳ አጥማጅ ነበር። በዓሳ አጥማጅነት ስራው ከሱ ዘንድ አሣ ለመግዛት ለሚመጡ ሸማቾች በትንሹ የጀመረውን ስብከት አሳድጎ በስህተት ሰው ወደ ማጥመድ ስራ አሳደገው። ተከታዮች ማፍራቱን እንዳረጋገጠ የዓሳ ጀልባውን በመሸጥ ስብከቱን የሙሉ ጊዜ ስራው በማድረግ የቀጠለ ሲሆን ዓለም ከክፉ ነገር ሁሉ የምትድነው እኔን በማመን ነው እያለ በየጎዳናው ይለፈልፍ ነበር። ትምህርቱን እንደ ትክክለኛ አድርገው የተቀበሉ ተከታዮቹ ትልቅ የመኖሪያ ቤት ገዝተው የሰጡት ሲሆን በስተመጨረሻም እኔ <<ኢየሱስ>> ነኝ በማለት ስብከቱን ገፍቶበታል። አንድአንዶች ይህ ሰው ከሀዲ ነው ብለው ቢያወግዙትም ፓሊንግቦኧር <<እግዚአብሔር>> ወደ መሆን ይለወጣል በማለት ይከራከሩለት የነበሩ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። ይሁን እንጂ ብዙ ጊዜ አግብቶ በመፍታት የሚታወቀው ይህ ከሀዲ እንኳን ሌሎችን ሊያድን ይቅርና ራሱን ከሞት ማዳን ሳይችል ቀርቶ እስከወዲያኛው አሸልቧል። ❤️የፍቅሩ ምርኮኞች ❤️
Show all...
ዘመኑ የፍጻሜ እንደመሆኑ መጠን ሀሰተኞች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ቢመጡም ሞት አሸንፎአቸው እንደ ታሪክ የሚፈጸሙ ትንቢቶች አድርገን እየተማርናቸው ነው፤ በመቀጠልም በተከታታይ እኔ ነኝ እያሉ ብቅ ብቅ ብለው የጠፉትን እነሆ፦ ክፍል1 ሚዝራ ጉላም አህመድ(1835-1908) ይህ በሀይማኖቱ እስላም የሆነ ሕንዳዊ ዜግነት የነበረው ሰው በአንድ ወቅት ራሱን እንዲህ ሲል ገልጾ ነበር። እስላሞች በመጨረሻው ቀን ከሰማይ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት "ማህዲ" የተባለውን ነብይና ክርስቲያኖች ለፍርድ ዳግም ይመጣል ብለው የሚጠባበቁት <<ኢየሱስ>>ን የምወክል ስሆን እነሆ ሁለቱም በእኔ ውስጥ በሥጋ ተገልጸዋልና ተከተሉኝ በማለት ሲለፍፍ ቆይቷል። ማሳሳት ጥንት ግብሩ የሆነው ሰይጣን በህንዳዊዉ አህመድ ውስጥ አድሮ እሱን ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች መሳሳት ምክንያት ሆኖ ከእስልምና ሴክት ክፍል አንዱ የሆነው <<አህመዲያ>> የተባለው ቅርንጫፍ ፈጥሮ በማለፍ ዛሬም ድረስ ብዙ ተከታዮች በዓለም ዙሪያ አፍርቷል።
Show all...
አስተውል_ይሄ_እውነታ_ነው ምርጥ ምክር ለሁሉም 👌ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ! 👌ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ! 👌ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ! 👌አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ! 👌ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ! 👌ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ! 👌ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ 👌ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ! 👌ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ! 👌ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ! 👌ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ! 👌እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ! 👌አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ! 👌ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ! 👌ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ! 👌አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ ❤️❤ የፍቅሩ ምርኮ❤️❤️
Show all...
"በአካል የተገለፅኩ ሌላ ክርስቶስ ነኝ " ያለውን መንፈሳዊ መሪ በማጭበርበር ወንጀል ዛሬ አሰሬዋለው ስትል ራሺያ አስታወቀች በራሺያ የሚገኘው የሳይበሪያ ፖሊስ" በአካል የተገለፅኩ ሌላ ክርስቶስ ነኝ " ያለውንና ከ4,000 በላይ ተከታይ ያለውን " የመጨረሻው አዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን " ሀይማኖት መሪን ሰርጂ ቴሮፖፕን በስነ ልቦና ጨዋታ ከተከታዮቹ ብር በመቀበል እና የስነልቦና ጉዳት በማድረስ በሚል ወንጀል ዛሬ ጠዋት መታሰሩን አርቲ ሚዲያ ዘግቧል። በቅፅል ስሙ ቪዣሮን ተብሎ የሚጠራው የሀይማኖት መሪ ጋርም ሁለት ተከታዮቹም ታስረዋል። የቪዣሮን ተከታዮች ከማጨስ ፣ከመጠጣት እና ስጋ ከመብላት የተቆጠቡ አዘውትረው አትክልት የሚመገቡ ናቸው ። ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን @NATIONALEXAMSRESULT
Show all...
ሰማዩን ክፈተዉ በዘማሪት አዲስአለም
Show all...
📚እራስህን ከሌሎች ጋር አታነፃፅር የሰው ልጅ ውድቀት የሚጀምረው እራሱን ከሌሎች ሰዎች ጋር ማወዳደር እና ማነፃፀር የጀመረ ቀን ነው።እንዴት አትለኝም? ይኸው ልነግርህ ነው እራስህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር አንተ በልጠህ ትገኝ እና ልብህ በትዕቢት ይወጠር ይሆናል አልያም ተበልጠህ ትገኝ እና ፍፁም በሆነ ምቀኝነት እና ቅንዓት ልብህ ይሞላል። ትዕቢት ቅንዓት እና ምቀኝነት ደግሞ ልብህን ከተቆጣጠሩ ላንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ፀጋ ይጋርዱብሀል። ትዕቢት ትርፉ የአምላክን ፊት መጋረድ ነው ቅንአትና ምቀኝነትም ሁከትን ይወልዳሉ ብሎም አጥንትን ፣ሰውነትን ያነቅዛሉ።ስለዚህ እራስህን ከሌሎች ጋር ከማነፃፀር ይልቅ በአንተ ውስጥ ያለውን እምቅ ሀይል ለማወቅ ጣር እርሱን ከተረዳህ በኋላ እራስህን ከማንም ጋር የመሮጫ ትራክ ውስጥ ሳታስገባ እምቅ ችሎታህን በደንብ ኑረው ያኔ ውጤታማ ነህ አምላክም በአንተነትህ ደስተኛ ነው። አምላክ እራስህን ከማንም ጋር እንድታነፃፅር አይሻም ይልቁንም በክርስቶስ በሰጠህ ልዩ ብቃት ውድ በሆነው ስጦታ ሰርተህ እራስህን ከማንም ጋር ሳታወዳድር ስኬታማ እንድትሆን ይሻል። እራሳችንን ከሌሎች ጋር አናወዳድር ይልቁኑ በተሰጠን የመሮጫ ትራክ ሩጫችንን በትዕግስት እንሩጥ።
Show all...
❇️ ያስተሳሰብዎን ጥራት ❇️ ያሻሽሉ ✅ አላስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች በተለይም ከሌሎች ሰዎች ጋር ስለተያየዙ ጉዳዮች ማሰብ ያቁሙ። የራስዎን ስራ ብቻ ይስሩ። በአላማ ላይ የሚያተኩር አእምሮ ይኑርዎ። ✅ ራስዎን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ያቁሙ። ይህን ማድርግ ራስን መስደብ ነዉ። እርስዎ እኮ ለአለም አዲስና ልዩ ሰዉ ነዎት ✅ ፍቅረ - ንዋይ አያብዙ። ከልክ ያለፈ የገንዘብ እና የንብረት ፍቅር የጭንቀት ምንጭ ነዉ። ✅ ይቅር የማለት እና ቅያሜን የመርሳት ልማድ ይኑርዎ። ቂምን ረዘም ላለ ጊዜ በአእምሮዎ የሚይዙ ከሆነ ራስዎን እየገደሉ ነዎት። ጭንቀት ስሮቹን በአእምሮዎ ዉስጥ እየሰደደ አካላዊና አእምሮአዊ ጤንነትዎን ቀስ በቀስ የሚያጠፋ መርዝ ነዉ ✅ ስለ ቀናነት የተነገሩ ጥራት ያላቸዉ ጥቅሶችና መጣጥፎች እያነበቡ መልእክቱን ይምጠጡ። ይህ የጠማማነትን ጀርም ይገድላል ✅ የማመስገን ልምድ ያዳብሩ። ማጉረምረም ያቁሙ። መንቀፍ እና መዉቀስን እንዲሁ አሉታዊ ሀሳብ ወደ አእምሮዎ ሲመጣ የነገሩን በጎ ገፅታ በማሰብ ወደ አዎንታዊ ሀሳብ ይቀይሩ
Show all...
Hin yaana New protestant song
Show all...
💠 መቆጣትን ወደ መልካምነት ይቀይሩ!! ✅ ቂም መቋጠር ልክ መርዝ እንደመጠጣት እና ሌላዉ እንዲሞት እንደመጠበቅ ነዉ ። ✅ ያን ሀሉ አሉታዊ ሀይል ቢሸከሙ ራስዎን ነዉ የሚጎዱት ። ለራስዎ ሲሉ ምሬትዎን ያስወግዱ። ✅ የነቀፌታን ናዳ ባወረደብዎ ሰዉ ላይ እርስዎ በንዴት ጦፈዉ በአዕምሮዎ የሞት ጨረር በመልቀቅ ዉድ ሕይወትዎን ሲያባክኑ እሱ ግን እርስዎን እስከ መፈጠርዎም ረስቶት ዓለሙን አየቀጨ ይሆናል ። ✅ ቁጠኝነትዎትን ይቆጣጠሩ በተቆጡ ቁጥር የሚጨምሩት ሰዉነትዎን ለበላ የሚችል የአሲድ መጠን ብቻ ነዉ ሌላ ምንም አይጨምሩም
Show all...
❤️አፍቃሪ ሰዉ ነዎት? ፈጣን መመዘኛ 1) የጓደኛዎን ስህተቶች በማስታወሻ ከትበዉ ይይዛሉ? 2)ጎረቤታችሁ ጥሩ ዕድል ሲገጥማቸዉ የቅናት ስሜት ይሰማዎታል? 3)ባለዎት ማኅበራዊ ደረጃ (ሀብት ፣ ስልጣን .....)ኩራት ቢጤ ይሰማዎታል? 4) ጠላትዎ መጥፎ ነገር ሲደርስበት ደስ ይለዎታል? 5) አዘዉትረዉ ያማርራሉ? መልስዎ "አዎ" ከሆነ ልበ - ደረቅ ነዎት ፤ አፍቃሪም ተፈቃሪም አይደሉም።
Show all...
ጥቂት የማንባል ሰዎች ችግራችን እግራችን ሲጓዝ🚶 ልባችን ❤️መቀመጡ ነው፤ ልባችን ሲቀመጥ ደግሞ እግራችን 🚶‍♀ይጓዛል። ራሳችንን በተቃራኒ አቅጣጫ እየጎተትን የነበርንበት ቦታ የሁሌው አድራሻችን ሆኗል። አካላችን፣ልባችን እና አእምሮአችን በተናጠል መሮጡ እስካላበቃ፣ባለንበት መርገጣችን ይቀጥላል። ዶ/ር ተካልኝ ነጋ(me and you)
Show all...
👉የፈጣሪን ስራ ያልተረዳዉ ባለ ስልጣን አንድ በጣም ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያለ ሰዉ በባህር ዳርቻ እየተዝናና ሳለ በድንገት ማህበል ይመጣበትና በማዕበሉ ይወሰዳል። ይህን ደንገተኛ ሁኔታ የተመለከተ አንድ ዋናተኛ ይጠጋና በል ወደ መሬት ላዉጣህ ብሎ ሲጠይቀው እኔ እየፀለይኩ ነዉ። ራሱ ፈጣሪ መጥቶ ያወጣኛል ይልና እንቢ ይላል። ከዚያም ወደ ዉቅያኖሱ እየራቀ ሲሄድ ሌላ ሰዉ በጀልባ ይመጣና ተመሳሳይ የእርዳታ ጥያቄ ሲያቀርብለት አሁንም አይ እኔን ፈጣሪ ረሱ ነዉ የሚያወጣኝ ይላል። እንዲሁ ወደ ዉቂያኖስ መሃል እየደረሰ ሳለ ዋናተኛዉ በመርከብ ወደ ግለሰቡ በመምጣት እንርዳህና ዉጣ ልናግዝህ መጥተናል ቢሉትም መልሱ ያዉ ሆነ። በመጨረሻም ለሀገር ጠቃሚ ሰዉ በመሆኑ እሱን ለማዳን የመጨረሻ አአማራጭ ተብሎ ሔሊኮፕተር ተላከ። ሆኖም ግለሰቡ መዋኘት አቃተዉና ሞተ። ከሞተ በኋላ ታዲያ ነፍሱ ፈጣሪ ዘንድ ትቀርባለች። ፈጣሪንም እንዲህ በማለት ስሞታ ያቀርብለታል ምነዉ እደዚያ ስፀልይ ያላዳንከኝ ምን አደረኩኝ። እድሜ ልኬን ለአንተ እና በአንተ ብቻ ኖሬ ምን አጠፋዉ?! በማለት አዝኖ ጠየቀ ። ፈጣሪም እንዲህ ሲል መለሰለት አይ ልጄ ማን መሰለህ በመጀመሪያ ዋናተኛ ፣ ጀልባ ፣መርከብ ከዚያ ደግሞ ሔሊኮፕተር የላከልህ አለዉ ❇️ ከታሪኩ ምን ተማርክ/ ሽ ?????
Show all...
ይቅር እላለሁ ጥላቻ መከፋፈልን ያነግሳል ይቅርታ ግን ከስህተቶች አርሞ በልእልና ያሸንፋል ይቅር አለማለት በአካልም በመንፈስም ያራርቃል ይቅር አለማለት ከአምላክ ጋር ያለያያል ስለዚህ ጎርቤት ከጎሬቤት ልጅ ከወላጁ ባል ከሚስቱ ታናሽ ከታላቁ ከተቀያየምንበት ከልባችን ይቅር ተባብለን ወደ ትልቅ ከፍታ እንደርሳለን በማወቅም ባለማቅም የበደልኳችሁ በሙሉ ይቅርታ🙏🙏
Show all...
ይቅርታ ዛሬን ለመኖራችን ትልቁ ምክንያት የእግዚአብሔር ምህርት የእግዚአብሔር እኛን ይቅር ማለቱ ነዉ ። ሀጢያተኞች ለነበርነዉ ለእኛ የሰማይ ደጆች የከፈተልንና ከጌታ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ህብረት እንድናደርግ መንገዱን የጠረገልን ይህ ይቅርታ የተሰኘዉ እዉነታ ነዉ። ይህ በይቅርታ የተጀመረዉ ሕብረታችን የሚቀጥለዉም በይቅርታ ነዉ። በመፅሐፍ ቅዱሳችን ዉስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የለንን ግንኙነት እዉነተኛነት የሚጠቁሙ ከወገኖቻችን ጋር ያለን ግንኙነት እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ ሀሳቦች አሉ። ለምሳሌ በአይናችን ያላየነዉን እግዚአብሔርን መዉደዳችን የሚታወቀዉ በአጠገባችን ያለዉን ወንድማችንን በመዉደዳችን እንደሆነ ይናግረናል። የይቅርታም ጉዳይ ቢሆንም በእግዚአብሔር ላይ ያለንን አመለካከት የሚጠቁም ሀሳብ ነዉ። ከጌታ ጋር የሰመረ ሕይወት ዉስጥ የመሆናችን ምልክቱ ከሰዉ ጋር ያለን ግንኙነት ነዉ። ስለዚህም የበደሉንን ይቅር የማለትን ልምምድ በሕይወታችን ትልቅ ስፍራ እንዳለዉ በማወቅ በሚገባ ልናጠናዉና ትኩረት ልንሰጠዉን የገባል ። የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የሚታወቀዉ የበደሉንን ይቅር ስንል ነዉ። እግዚያብሔር ይቅር ባይ እንደሆነ እኛም ይቅር ባዮች መሆን አለብን። ይቅር ማለት ያለብን የበደሉን ሰዎች እኛጋ መተዉ እግራችን ስር ሲወድቁ ይቅር በለኝ አጥፍቻለሁ እስኪሉ ድረስ ጠብቀን መሆን የለበትም በድለዉን እንኳን ቢሆን እኛ ወደ እነሱ ጋር ሄደን ይቅር ልንላቸዉ ይገባል ። እንዴት በድለዉኝ እኔ ወደ እነሱጋ መሄድ አለብኝ ካላችሁኝ እግዚያብሔርን እኛ በድለነዉ እሱ ይቅር ሊለን እኛጋ እንደመጣ እኛም የበደሉንን ይቅር ለማለት ወደ እነሱጋ መሄድ አለብን ። 👇እነዚህን ነገሮች ልብ ልትሉ👇 ይገባችዋል ✅ ለፀሎት በቆማችሁ ጊዜ በሰማያት ያለዉ አባታችሁ ደግሞ ኃጢያአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ በማንም ላይ አንደዳች ቢኖራችሁ ይቅር በሉት ማር 11:25 በዚህ ክፍል የእግዚአብሔር ቃል ሚናገረን ፀሎት ከመጀመራችን በፊት ይቅርታ ማድረግ እንደሚቀድም ነዉ ። ✅ እደሁም ይቅርታ ማድርግ ለራሳችን ነዉ ጥቅሙ ምክንያቱም ይቅር ካላልን ሀጢያታችንን ይቅር አንባልም። ✅የበደሉንን ይቅር የማለት ግዴታ አለብን የበደሉንን ይቅር ማለት የምርጫ ጉዳይ አይደለም የግዴታ ጉዳይ ነዉ። እኛ የማይገባንን ይቅርታ ከጌታ ስለ አገኘን እኛ ደግሞ ያንን ግዴታችንን ለመክፈል ከምንወስዳቸዉ እርምጃዎች አንዱ የማይገባቸዉን ሰዎች ይቅር የማለት እርምጃ ነዉ ። ማለት እንደበደሉን ከሆን አይገባቸዉም ይቅርታ በጣም ሰብረዉን ፣በጣም አሳዝነዉን፣ አስለቅሰዉ ማገገም ሁሉ አቅቶን ሊሆን ይችላል ከዚህም የተነሳ አይገባቸዉም ይቅርታዬ ልትሉ ትችላላችሁ ግን ሚገርመዉ ይቅር እንድትሉ ታዛችኋል። ስብራታችሁ የሚጠገነዉ ይቅር ስትሉ ነዉ ክርስቶስ ይቅር እንዳለን እኛ ደግሞ ይቅር ማለት አለብን(ቆላ3:13) ተመልከቱ ✅እግዚያብሔር ይቅር ብለን እስክንመጣ ይጠብቀናል መስዋት ከማቀረባችን በፊት በፊቱ ለምስጋናና ለፀሎት ከመቅረባችን በፊት እግዚያብሔር ይቅር ብለን እንድንመጣ ይፈልጋል። ከመንበረከከካችን በፊት ወደ ቤተ ክርስቲያናን ሄደን ፀሎት ከማድርጋችን በፊት ይቅርታ ማድረግ አለብን አለበለዚያ ፀሎታችንን ሁሉ ከንቱ ነዉ በማቴ.5 : 23 -24 ሚናገረን ይህንን ነዉ ከሁሉ በፊት ይቅርታ ማድረግ እንደ ሚቀድም ⚠️በቃ ዛሬ ይብቃ በዉስጣችሁ የያዛችሁትን ቂም እሷማ እሱማ እንዲ አደርጎኝ የምንለሁን ጉዳይ በይቅርታ እንግድለዉ እኛ ከወዳጆቻችን ጋር ብቻ የተጣላን ሊመስለን ይችል የሆናል ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነዉ።የተጣላነዉ ይቅር ባለማለታችንን ⚠️ አዲሱ አመት ከመግባቱ በፊት የበደሉንን የተቀያየምናቸዉን ሰዉዎች እንታረቃቸዉ በአካል ረቀዉን ቢሆን እንኳን በስልክ ደዉለን ይቅረታ እንጠይቃቸው
Show all...
🙏ይቅርታ🙏 👉ዛሬን ለመኖራችን ትልቁ ምክንያት የእግዚአብሔር ምህርት የእግዚአብሔር እኛን ይቅር ማለቱ ነዉ ። 👉 ሀጢያተኞች ለነበርነዉ ለእኛ የሰማይ ደጆች የከፈተልንና ከጌታ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ህብረት እንድናደርግ መንገዱን የጠረገልን ይህ ይቅርታ የተሰኘዉ እዉነታ ነዉ። 👉ይህ በይቅርታ የተጀመረዉ ሕብረታችን የሚቀጥለዉም በይቅርታ ነዉ። 👉 በመፅሐፍ ቅዱሳችን ዉስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የለንን ግንኙነት እዉነተኛነት የሚጠቁሙ ከወገኖቻችን ጋር ያለን ግንኙነት እንደሆነ የሚያሳዩ በርካታ ሀሳቦች አሉ። ለምሳሌ በአይናችን ያላየነዉን እግዚአብሔርን መዉደዳችን የሚታወቀዉ በአጠገባችን ያለዉን ወንድማችንን በመዉደዳችን እንደሆነ ይናግረናል። 👉የይቅርታም ጉዳይ ቢሆንም በእግዚአብሔር ላይ ያለንን አመለካከት የሚጠቁም ሀሳብ ነዉ። 👉ከጌታ ጋር የሰመረ ሕይወት ዉስጥ የመሆናችን ምልክቱ ከሰዉ ጋር ያለን ግንኙነት ነዉ። 👉ስለዚህም የበደሉንን ይቅር የማለትን ልምምድ በሕይወታችን ትልቅ ስፍራ እንዳለዉ በማወቅ በሚገባ ልናጠናዉና ትኩረት ልንሰጠዉን የገባል ። 👉የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የሚታወቀዉ የበደሉንን ይቅር ስንል ነዉ። እግዚያብሔር ይቅር ባይ እንደሆነ እኛም ይቅር ባዮች መሆን አለብን። 👉ይቅር ማለት ያለብን የበደሉን ሰዎች እኛጋ መተዉ እግራችን ስር ሲወድቁ ይቅር በለኝ አጥፍቻለሁ እስኪሉ ድረስ ጠብቀን መሆን የለበትም በድለዉን እንኳን ቢሆን እኛ ወደ እነሱ ጋር ሄደን ይቅር ልንላቸዉ ይገባል ። እንዴት በድለዉኝ እኔ ወደ እነሱጋ መሄድ አለብኝ ካላችሁኝ እግዚያብሔርን እኛ በድለነዉ እሱ ይቅር ሊለን እኛጋ እንደመጣ እኛም የበደሉንን ይቅር ለማለት ወደ እነሱጋ መሄድ አለብን ። 👇እነዚህን ነገሮች ልብ ልትሉ👇 ይገባችዋል ለፀሎት በቆማችሁ ጊዜ በሰማያት ✅ያለዉ አባታችሁ ደግሞ ኃጢያአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ በማንም ላይ አንደዳች ቢኖራችሁ ይቅር በሉት ማር 11:25 በዚህ ክፍል የእግዚአብሔር ቃል ሚናገረን ፀሎት ከመጀመራችን በፊት ይቅርታ ማድረግ እንደሚቀድም ነዉ ። እደሁም ይቅርታ ማድርግ ለራሳችን ነዉ ጥቅሙ ምክንያቱም ይቅር ካላልን ሀጢያታችንን ይቅር አንባልም። የበደሉንን ይቅር የማለት ግዴታ አለብን የበሉንን ይቅር ማለት የምርጫ ጉዳይ አይደለም የግዴታ ጉዳይ ነዉ። እኛ የማይገባንን ይቅርታ ከጌታ ስለ አገኘን እኛ ደግሞ ያንን ግዴታችንን ለመክፈል ከምንወስዳቸዉ እርምጃዎች አንዱ የማይገባቸዉን ሰዎች ይቅር የማለት እርምጃ ነዉ ። ማለት እንደበደሉን ከሆን አይገባቸዉም በጣም ሰብረዉን በጣም አሳዝነዉን አስለቅሰዉ ማገገም ሁሉ አቅቶን ሊሆን ይችላል ከዚህም የተነሳ አይገባቸዉም ይቅርታዬ ልትሉ ትችላላችሁ ግን ሚገርመዉ ይቅር እንድትሉ ታዛችኋል። ስብራታችሁ የሚጠገነዉ ይቅር ስትሉ ነዉ ክርስቶስ ይቅር እንዳለን እኛ ደግሞ ይቅር ማለት አለብን(ቆላ3:13) ተመልከቱ እግዚያብሔር ይቅር ብለን እስክንመጣ ይጠብቀናል መስዋት ከማቀረባችን በፊት በፊቱ ለምስጋናና ለፀሎት ከመቅረባችን በፊት እግዚያብሔር ይቅር ብለን እንድንመጣ ይፈልጋል። ከመንበረከከካችን በፊት ወደ ቤተ ክርስቲያናን ሄደን ፀሎት ከማድርጋችን በፊት ይቅርታ ማድረግ አለብን አለበለዚያ ፀሎታችንን ሁሉ ከንቱ ነዉ በማቴ.5 : 23 -24 ሚናገረን ይህንን ነዉ ከሁሉ በፊት ይቅርታ ማድረግ እንደ ሚቀድም በቃ ዛሬ ይብቃ በዉስጣችሁ የያዛችሁትን ቂም እሷማ እሱማ እንዲ አደርጎኝ የምንለሁን ጉዳይ በይቅርታ እንግድለዉ እኛ ከወዳቻችን ጋር ብቻ የተጣላን ልመስለን ይችል የሆናል ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነዉ የተጣላነዉ ይቅር ባለማለታችንን አዲሱ አመት ከመግባቱ በፊት የበደሉንን የተቀያየምናቸዉን ሰዉዎች እንታረቃቸዉ በአካል ረቀዉን ቢሆን እንኳን በስልክ ደዉለን ይቅረታ እንጠይቃቸው
Show all...