#አስተማሪ_መልዕክት_እነሆ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ይህ ሰው ውሀ ከወንዝ
እየቀዳ ቤተ-መንግስት ዘወትር ያመላልስ ነበር። ውሀ የሚያመላልስባቸው ሁለት እንስራዎችም ነበሩት በነዚህ እንስራዎች
ውሀ እየሞላ ወደ ቤተመንግስት ይውስድባቸው ነበር። ከሁለቱ እንስራዎች አንዱ ግን ቀዳዳ ነበረው፤ እና ምንም እንኳን ከወንዙ ሁለቱንም እኩል
ውሀ ሞልቷቸው ቢሄድም ቤተመንግስት ሲደርስ ግን አንደኛው እንስራ
#ሙሉ፤
ቀዳዳ ያለበት እንስራ ደግሞ
#ጎዶሎ ይሆን ነበር። በዚህ ሁኔታ ሰውዬው
በሁለቱ እንስራዎች አንድ ሙሉ እንስራ ውሀ፤ በሌላኛው ደግሞ ጎዶሎ ውሀ
እያመላለሰ ለረጅም ጊዚያት ቆየ።
ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ቀዳዳ ያለበት እና ዘወትር እያንጠባጠበ የሚሄደው
እንስራ እንዲህ ሲል ለሰውዬው አቤቱታ አቀረበ፡፡
እንስራው፦ "እኔን እና ጓደኛዬን እየተሸከምክ ውሀ ማመላለስ ከጀመርክ እንሆ ቆየህ።
#ሰባራ ሆኜም እንኳን ስታመላልስብኝ ሰነበትክ አሁን ግን ዘወትር ከጌታዬ ፊት
ጎዶሎ ውሀ እየያዝኩኝ መቅረብ
#አሳፈረኝ። ጓደኛዬ ዘወትር
#ሙሉ_ውሀ ሲወስድ እኔ ግን
#ሁሌ_ጎዶሎ ማቅረቡ አንገቴን አስደፈኝ። እናም በኔ ውሀ ማመላለሱ ቢበቃህ ይሻላል።" አለው። ይህን የእንስራውን አሳዛኝ ንግግር የሰማው ሰውዬ በማስተዋል ቀዳዳውን
እንስራ እየተመለከተ፡-
ሰውዬው፦ "ዛሬ ውሀ ቀድተን ስንመለስ አንድ ነገር አሳይሀልሁ" ሲል ነገረው።
ውሀ ቀድተው ሲመለሱ ሰውዬው የሚያንጠባጥበውን እንስራ
#ወደ_መሬት_እያስተዋለ እንዲሄድ ነገረው። እንስራውም እንደተባለው አደረገ።
#በእሱ_በኩል_እጽዋቶችን ተመለከተ
#ፍሬ_ያፈሩ አትክልቶችን አስተዋለ
የሚያማምሩ አበባዎችን አየ። በዛኛው እንስራ በኩል ግን ምንም አልነበረም።
ምንም እንኳን ዘወትር በተመሳሳይ መንገድ ቢሄዱም እንደዛሬው አስተውሎ
አያውቅም ነበር።
ሰውዬው፦ "አየህ ወደጄ አንተ
#እንደምታንጠባጥብ_ሳውቅ_ባንተ_በኩል_ዘሮችን_ዘራሁ፤ ዘወትር ካንተ በሚንጠባጠበው ውሀ ጥማታቸውን አራሱ፣ ፍሬ አፈሩ፣ አበቡም። ይህ የምትመለከተው አትክልት ሁላ ባንተ በኩል ብቻ ነው ያለው ሌላኛውን
እንስራ በምሸከምበት በኩል ምንም ነገር የለም እናም
#ጥቅም_የለኝም_አትበል።
ሌላው ቢቀር ደካማ ጎንህ እንኳን ለሌሎች ጥቅም አለው" ሲል አስረዳው።
📌 አንዳንዴ ልዩነታችንን አይተን፤
#በንጽጽር ብቻ ጥቅም የለኝም እርባና ቢስ ነኝ
ብለን እናስብ ይሆናል። ሌላው ሰው የቻለውን እኛ ባለመቻላችን ብቻ ጎዶሎ እንደሆንን እናስባለን።
📌 የሌሎች ብርሀን እንጂ የኛ ስለማይታየን ከጨለማ መውጣት ያቅተናል።
📌 ሰባራው እንስራ ሌላኛው እንስራ ሙሉ ውሀ መውሰዱን ተመለከተ እንጂ በሱ ውሀ ስንት የእጽዋት ነፍስ እንደበቀለ አላስተዋለም።
📌 እኛም እንዲህ ነን
#የየራሳችን_ብርሀን_አለን ነገር ግን
#የሌላው_ሰው_ጭላንጭል_ያስቀናናል።
📌 ሌሎች ሙሉ ውሀ መሸከም ቢችሉ እንዳንተ ነፍስ መዝራት አይችሉም። አንተ
እንደነሱ ሙሉ ውሀ መሸከም ቢያቅትህ ጉድለትህ ሌሎች እንዲያብቡ ያደርጋል።
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
⇨
@yefkrumrkognochShow more ...