cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates. This page is not a gov't page.

Show more
Advertising posts
69 291
Subscribers
+524 hours
+1187 days
+36330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአዲስ አበባ የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታችሁን በዚህ ሊንክ ግቡና እዩ ተብላችኋል። https://aa.ministry.et/account#/student-result ላይ በመግባት መለያ ቁጥር እና ስም በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ።
Show all...
👍 2 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጠቃሚ መረጃ! ❖ የታክሲ ሹፈሮች ለልማት የተሰረው ኮሊደር ላይ እና ሳር የተተከለበት ቦታ ላይ ሰዎችን ማውረድ ፣ መጫን እና መኪና ማቆም የተከለከለ ነው። ሲጭንም ሆነ ሲያወርድ መሻገሪያ ቦታ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ ህግ ያስገድዳል፡፡ * ይህን ተግባራዊ ካላደረጉ ላጠፉት ጥፋት በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ የተቀመጠውን ብር 2000 እሰከ 100000 እንደ ጥፋቱ ክብደት እንዲከፍል ይገደዳሉ ::
Show all...
👎 41👍 39😁 18 5
00:41
Video unavailableShow in Telegram
1.24 MB
👍 14👎 10 1
የቤት ዋጋ እንዴት ሊቀንስ ይችላል? "ቤት አትግዙ " የሚል የሶሻል ሚዲያ ቻሌንጅ የማከብረው ወዳጄ ልኮልኝ ተመለከትኩ። አላማው በደምሳሳው ቤት ውድ ስለሆነ እስኪቀንስ ድረስ አትግዙ የሚል ነው...ይሄ ብዙም ውጤታማ ሊሆን የማይችል ቻሌንጅ እንደሆነ ቢታወቅም ሀሳቡ ግን የሚበረታታ አይደለም ምክንያቱም ስሁት ነው። የሪል እስቴት ዘርፍን በቅጡ ካለመገንዘብ የመጣ ቤት ተወዷል ብሎ ለውድነቱም አልሚዎችን ብቻ ተወቃሽና ተከሳሽ ለማድረግ የታሰበ የችግሩን መሰረት ያልተረዳ ነው። እስኪ የዘርፉን አሰራርና ችግሩን እንድንረዳ ስለ ሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዋና ተዋናዮችና አስተዋጽኦዋቸው ጥቂት እንበል። ሀ) ባለድርሻ አካላትና ድርሻዎቻቸው የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት አምስት ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት አሉት። የሀገራችንን ሁኔታ ታሳቢ አድርገን ስናቀርበው ከዚህ በታች የተገለጸውን ሊመስል ይችላል:- ፩) አልሚ (Developer) :- ስራ ፈጣሪ ነው፣ መሬትን ወደ ውጤታማ የሆነ ተፈላጊ የመኖሪያ ስፍራ በመቀየር ትርፍን የሚያገኝ መላ ፈጣሪ ነው፣ የገንዘብ አምጪ፣ የኪሳራሃላፊነት ወሳጅ፣ ቀጣሪ ሲሆን ዓላማው የገንዘብ ትርፍ ማግኘት፣ የቤት ችግር መቅረፍ ቢዝነሱ ያደረገ፣ ዘላቂ ንብረት ማፍራት፣ ጥሩ ስም መገንባት ... ፪) መንግስት(public organization):- መንግስት ዜጎች ቤት እንዲያገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና መመሪያዎችን ያወጣል፣ ለቤት ልማት የሚሆን መሬት ያቀርባል፣ የግንባታ ሂደቱን ይከታተላል፣ የግብይት ሂደቱን ይቆጣጠራል.... በሪል እስቴት ልማት ውስጥ የመንግስት ዋና ፍላጎት የልማቱ ሂደት በስኬት ተከናውኖ ዜጎች ቤት እንዲያገኙ ማድረግ፣ የህዝብ ሃብት የሆነው መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ .... ፫) ካፒታል ማርኬት:- ይህ ለግንባታም ሆነ ለቤት ገዢዎች ብድር የሚሆን የገንዘብ አቅርቦትን የሚያቀርቡ ባንኮችንና ሌሎች ወደፊት የሚመጡ የገንዘብ አቅርቦት የሚሰሩ ተቋማት ሲሆኑ ተሳትፏቸውም ለልማቱና ለቤት ገዢዎች ገንዘብ ማቅረብና ከልማት ሂደቱ ማትረፍ ነው። ፍላጎታቸው ኢንቨስትመንቱ አዋጭ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ፬) የቤት ገዢዎች (ተከራዮች) (ደንበኞች):- ዋና ፍላጎታቸው ለመኖር በቂ የሆነ ፣ በጊዜው ተጠናቅቆ መረከብ፣ በቂ ስፋት ያላቸው መገልገያ ክፍሎች ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ማግኘት ሲሆን። የቤት አልሚው ይህንን የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት በገበያ ጥናት አጥንቶ መገንባት ይጠበቅበታል። ፭) የተለያዩ ባለሙያዎች (Development Team ) :- የሪል እስቴት ዘርፍ ብዙ ሙያዎችን የሚጠቀም ዘርፍ ነው። ለምሳሌ አርክቴክቶች፣ መሃንዲሶች፣ ገንቢዎች፣ የግብይት ሂደት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች፣ የፋይናንስ፣ የባንኪንግ ፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለሙያዎች፣ IT ባለሙያዎች፣ የህግ ባለሙያዎች ወዘተ.... ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ። ባለሙያዎቹ በግልም በህብረትም በየሙያቸው ያለውን ከፍተኛና ፈጠራ የተካተተበት የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ውጤት እንዲመጣ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው። ለ) ቤት ዋጋ እንዲቀንስ የሚጠበቅባቸው አስተዋጽኦ የሪል እስቴት ልማትና ግብይት የተሳካ እንዲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ባለድርሻ አካላት የሚጠብቃቸውን ያለማጓደል ሊያበረክቱ ይገባል። ለምሳሌ :- ፩) መንግስት ለአልሚዎች መሬት በቅናሽና በብዛት ካቀረበ፣ የዲዛይን ማጽደቅና ክትትል ስራውን ካሳለጠ፣ ግብይቱ የሚመራበት መመሪያና ግብይቱን የሚመራ አካል ሰይሞ በስርዓት እንዲመራ ካደረገ፣ በርካታ ቤቶችን ለሚገነቡ አልሚዎች የግንባታ ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ካደረገ። ፪) የገንዘብ አቅራቢ ተቋማት ለአልሚዎችና ለቤት ገዢዎች በቂ የሆነ የገንዘብ አቅርቦት ካደረጉ ፫) ቤት ገዢዎች ጠንክረው ሰርተው ቁጠባን ባህላቸው ቢያደርጉና እቅም ከፈጠሩ ፬) ባለሙያዎች ገበያውንና የቤት ገዢዎችን አቅምና ፍላጎት ያገናዘቡ ቤቶች የሚገነቡበትን ዲዛይን፣ ወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂ ፣ የአከፋፈል ስርዓት በጥናት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ካዘጋጁ ፭) አልሚዎች ዘርፉን በእውቀት በባለሙያዎች እንዲመራ ካደረጉ ሐ) መውጫ በምሳሌ ነገር ግን ከአምስቱ አንዱ ሲያጎድል ዘርፉ ውጤታማ እንዳይሆን ሊያደርግ ይችላል በሌሎቹ አካላት ላይም ተጽዕኖን ያሳድራል ። ለምሳሌ :- ባለሙያዎች ገበያውን ያላገናዘበ ውድ ቤቶች ንድፍ ቢሰሩና የሰሩትም ቢገነባ ቤት ገዢዎች ሊገዙት አይችሉም፣ ካልተሸጠ ባንኮች ያበደሩት ብር በወቅቱ አይመለሰም፣ የቤት ችግርን ስለማይቀረፍ መንግስት ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ከልማቱ ማግኘት የነበረበትን ገቢ ያሳጣል፣ አልሚውም ይከስራል... ስናጠቃልለው የቤት ዋጋ ሊቀንስ የሚችለው በአልሚዎች ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት አካላት የተናበበ የጋራ ተሳትፎ ሲኖር ብቻ ነው። በ ደሳለኝ ከበደ (አቶ ደሳለኝ ከበደ ሲቪል መሀንዲስ፣ ስራ ተቋራጭ፣ አሰልጣኝ እና ጸሀፊ ሲሆኑ በግንባታው ዘርፍ ላይ ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያ ናቸው) በቴሌግራም ይከታተሉን። https://t.me/ethiopianarchitectureandurbanism
Show all...
Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

It is a platform for information on historical and contemporary architecture, urbanism, landscape, and the construction industry inside Ethiopia. It will also include similar issues from across the world.

👍 91👎 16 10
👍 2 1
ሀይባይ ያጣው መንገድ በድንኳን ዘግቶ መደገስ ይህ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከፊጋ መብራት እስከ የረር ጎሮ ፖሊስ ጣብያ በሚገኝ ዋና መንገድን ሙሉ በሙሉ ዝግ በማድረግ መኪኖች መተላለፍ አልቻሉም።
Show all...
👍 24👎 9🤔 4👏 2 1
ገበጣ የሚያጫውተው የሰሚት 72 መንገድ!!
Show all...
😁 49👍 21😢 4 3🥰 1🤬 1
00:14
Video unavailableShow in Telegram
3.99 KB
👍 59😁 40 7🤬 4👎 2
01:52
Video unavailableShow in Telegram
የንግድ ቦታ ኪራይ #ቅድሚያ_ፍላጎትን ለማወቅ የወጣ ማስታወቂያ!
Show all...
22.10 MB
👍 22
Photo unavailableShow in Telegram
ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ የቤት ለቤት የፓስፖርት አገልግሎት መሰጠት እንደሚጀምር ተገለጸ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የቤት ለቤት የፓስፖርት አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል። የቤት ለቤት አገልግሎት የሚሰጠው ለየት ባለ እና ተጨማሪ ክፍያን በሚጠይቅ መልኩ ሲሆን አገልግሎቱ በልዩ ሁኔታና ደረጃ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡ አገልግሎቱ የ 2016 አመት የስራ አፈጻጸሙን በማስመልከት በሰጠው መግለጫ በበጀት ዓመቱ በርካታ ማሻሻያ መደረጋቸው ያነሳ ሲሆን 14.7 ቢሊዮን ብር ገቢ እንዳገኘም አስታውቋል፡፡ ይህ አገልግሎት በባለሃብቶች እና ታዋቂ ሰዎች ጥያቄ መሰረት ለመጀመር መታቀዱን የገለጸው ተቋሙ አዲሱ የፓስፖርት እደላ አገልግሎት የተለየ ክፍያ የሚተመንለት ስለመሆኑ ነው የጠቆመው፡፡ የፓስፖርት አገልግሎቱን ለማሳመን አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ እንደሚያደርግ በመግለጽም አሁን ላይ ፓስፖርት የማሰራጨት አቅሙን በቀን ከ2ሺህ ወደ 14 ሺህ ማሳደጉን አንስቷል፡፡ ይሁን እንጂ ተቋሙ ይህን ቢልም ፓስፖርት ለማግኘት ወራትን መጠበቅ ግድ የሆነባቸው ተገልጋዮች በተቋሙ አሰራር በተደጋጋሚ ሲማረሩ ይደመጣሉ፡፡ Addis Maleda
Show all...
😁 103👍 66 7🤔 5👎 4😱 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.