en
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Channel የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 14 395 subscribers, ranking 6 113 in the Religion & Spirituality category and 2 343 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 14 395 subscribers.

According to the latest data from 26 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 541 over the last 30 days and by 19 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 34.65%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects N/A% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 988 views. Within the first day, a publication typically gains 0 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 33.

📝 Description and content policy

Channel description not provided.

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 27 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

14 395
Subscribers
+1924 hours
+1197 days
+54130 days
Posts Archive
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት።" ኢያ 3፡3 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክ
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት።" ኢያ 3፡3 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

https://vm.tiktok.com/ZM6CACYuC/ ርዕዩከ የጥምቀት መዝሙር

AnimatedSticker.tgs0.22 KB

"አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።" መዝ 64፡4 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊ
"አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፤ ከቤትህ በረከት እንጠግባለን።" መዝ 64፡4 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

ርዕዩከ የጥምቀት ወረብ https://vm.tiktok.com/ZM6QpL5eD/
ርዕዩከ የጥምቀት ወረብ https://vm.tiktok.com/ZM6QpL5eD/

በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ትግበራ ላይ የሚገኙ በጅማ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች የመጀመርያ መንፈቀ ዓመት የአጋማሽ ፈተና ተሰጠ። ጥር 7/5/2016 ( የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በ2016 ዓ.ም በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ሲያስተምራቸው የነበሩ በ1ኛ ፣ 3ተኛ ፣ 4ተኛ ፣ 5ተኛ ፣ 6ተኛ እና 7ተኛ ክፍል ለሚማሩ ከ2,700 በላይ ተማሪዎች የ1ኛ መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ሰጠ። ፈተናው የተሰጠው ጥር 4 እና 5 ቀን 2016 ዓ.ም በጅማ ከተማ በሚገኙ 13 ሰንበት ት/ቤቶች ውስጥ ነው። ፈተናው በሀገረ ስብከት ደረጃ በማእከላዊ ቦታ እንደተዘጋ የተናገሩት የሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ዲያቆን ሀብታሙ አንድነቱ የሚፈትኑ መምህራንን ወደ ሁሉም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በመላክ አስፈላጊውን ክትትልና እገዛ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። አያይዘውም ይህ በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት የተሰጠው ፈተና በሀገረ ስብከቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ መሆኑንና ከፈተናው አሰጣጥ የተረዳነው ነገር ቢኖር ሰንበት ትምህርት ቤቶች ምን ያህል ለሥርዓተ ትምህርቱ ትኩረት በመስጠት እየሠሩ መሆቸውን ነው ብለዋል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

"ሁሉ በሥላሴ ፈቃድ ተፈጥረዋልና!" ሲራ 32፡21 እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያ
"ሁሉ በሥላሴ ፈቃድ ተፈጥረዋልና!" ሲራ 32፡21 እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

"የአምላክ ልጆች ሆይ ፤ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።" መዝ 28፡1 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https
"የአምላክ ልጆች ሆይ ፤ ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።" መዝ 28፡1 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

'' ራሱን ባዶ አደረገ፥” ፊል 2፥7 ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው ቅ/ጳውሎስ ነው!!!! ይህ ግሩም ቃል የክርስቶስን የስጋዌ ወራት(ሰው የሆነበትን) ጊዜ በሰፊው የሚያትት ነው። ወዳጄ ልብ ብለህ ይህንን የክርስቶስ ማዳን በዚህ ቃል ውስጥ ተመልከተው  ''የሰውን ልጅ የመውደድ ደግሞም የማፍቀር'' ሁኔታን ትመለከታለህ ። ለካስ ፍቅር እንዲህ ያደርጋል!!! ሁሉ የእርሱ ሆኖ እንዳልሆነ ፣ ሁሉን ማድረግ ሲችል እንደማይችል  ሆኖ በግእዘ ሕፃናት በበረት ተወልዶ ተገኘ!!! የክርስቶስ ግን ይለያል! ለሰሚውም ግርምትን ይፈጥራል እውነት ነው መጽሐፍ "የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።” ዮሐ 13፥1 እስከ በሌለው መጨረሻ  መውደድ ወደደን በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚታይ መውደድ፤ በሥራ የተፈተነ መውደድ ወደደን ይኸውም የኛን ደካማ ና የተናቀ ሥጋ እስከ ዘለዓለም በመዋሐድ ወደደን ወገኖቹም አደረን። ይህ እኛን የመውደዱ አምላካዊውሥራ ''ራሱን ባዶ ማድረግ ነው'' የአዳም እና የልጆቹን ትእቢት እና ትእዛዝ መተላለፍን ከእኛ ያርቅ ዘንድ እርሱ ''ራሱን ባዶ አደረገ'' ወዳጄ እውነት ነው እኛ ምን አለን? ምንስ መልካምነት ምንስ ጽድቅ አለን? ነገር ግን ያለመስፈርት ወደደን የከረፋ ማንነታችንን ያስተካክልልን ዘንድ ማንነታችንን ሳይጸየፍ ''በረት ሕይወታችንን ይቀይር ዘንድ በበረት ተወለደ'' እኛ ስንርቀው እርሱ እየቀረበን እኛ ስንጠላው እርሱ እየወደደን ስለ እኛ ፍቅር ራሱን ባዶ አደረገ።   ሁሉ አዋቂ ሲሆን የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ ''ራሱን ባዶ አደረገ'' ወዳጄ ይህንን ቃል በጥልቀት እስኪ እንመርምረው እርሱ ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉ በእርሱ የሆነ፣ ከሆነውም አንዳች ያለእርሱ ያልሆነ ጌታ አምላክ ሲሆን መላእክት ልሁን አላለም፤ ከነገሥታት ቤት ተወልጄ  ላድነው አላለም ነገር ግን ደካማውን ሰው ልሁን አለ አስቦም አልቀረም ሰው ሆነ! የማይራበው ተራበ የማይጠማው ተጠማ የማይራቆተው ተራቆተ በእጅ ያልተሰራ ቤት ውስጥ የሚኖር እርሱ በበረት አደረ። ይህ ሁሉ የፍቅር ሥራው ሲጠቃለል ''ለፍቅር ብሎ ራሱን ባዶ አደረገ'' ተባለለት። ወዳጄ :- ይህ አንድ ጊዜ የተከፈለ ቤዛነት ነው!!! ወልደ እግዚአብሔር ሕያው ብለን የምንዘምርበት ነው ''የትኛውንም ቃላት ብናሳምር ብንደረድር  የጌታችንን የማዳን ሥራውን ዘርዝረን አንጨርሰውም ምንም ንግግር ፣ ጽሑፍ ክብሩን አይመጥኑም ብቻ ቅ/ጳውሎስ የተጠቀመውን ቃል ''ራሱን ባዶ አደረገ'' የሚል ብቻ  ነው። ቅ/ቤተክርስቲያንም በቅዳሴ ላይ ይህንኑ ቃል ለታደሙ ልጆቿ ሁሉ ትናገረዋለች!!! አየህ ወዳጄ ዛሬ ተወልዶ እኛን የተዋሐደን እንዲሁም ከእኛ ጋር ያለው መድኅን ዓለም ክርስቶስ ነው። በፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2፡4 "እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።" በማለት በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን ተብሏል። ራስ ወዳድ እንዳንሆን ለባልንጀራችን የሚጠቅመውን እንድንመለከት በተግባር ያስተምረናል። ዛሬ መጨካከን መገዳደል ብሎም ኢ ሰብዓዊ ነገሮች በሚፈጸሙበት ወቅት ልንረዳው የሚገባን ባልንጀራ የተባለው የሰውን ልጅ በሚገባ መውደድ ብሎም በሰውነቱ ማክበር በተቸገረም ጊዜ ማገዝ የእኛ ሥራ ሊሆን ይገባል ''ምክንያቱም ክርስቶስ የወደደን እኛን እስከመሆን ነው። እኛም የተቸገሩንት እነርሱን እስከመሆን (እነርሱን መስሎ) ህመማቸውን መታመም ችግራቸውንም መቸገር ስቃያቸውን በማሰብ ልናጽናናቸው ብሎም ልንደርስላቸው አይዟችሁ ልንላቸው ይገባል! ላእከ ወንጌል ዳርዮስ ፍቃድ (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion ጥር 04/05/16 ዓ.ም

"አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።" መዝ 25፡8 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! መልካም ዕለተ ሰንበት! ✍️Youtu
"አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።" መዝ 25፡8 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! መልካም ዕለተ ሰንበት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ደብር ሰንበት ት/ቤት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የነድያን ጉባኤ አካሄደ። 04-05-2016 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ደብር ሰንበት ት/ቤት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የነድያን ጉባኤ ተደርጓል። በጉባኤውም ቃለ ወንጌል በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ደብር ሰንበት ት/ቤት ም/ሰብሳቢ ቀሲስ አርአያ ተሾመ "እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ" ሉቃ 2፥15 መነሻ በማድረግ "እረኞችን አክብሮ ጠራ እነሱም ሕፃኑን ከእናቱ ጋር አገኙት ፤ እግዚአብሔር እኛንም አክብሮ ወደ ቤቱ ጠርቶናልና ጌታን ከእናቱ ጋር እናገኘዋለን ወደ ቤቱ እንምጣ " በማለት ቃለ እግዚአብሔርን አካፋለዋል። በመቀጠልም ዝማሬ ፣ የኪነ ጥበብና የምስጋና መርሐ ግብር በደብሩ ሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ተካሂዷል። በመጨረሻም ለነድያኑ የሰበካ ወንጌል ደብተር ከክፍያ ነፃ በሆነ መልኩ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን ከ120 በላይ ለሚሆኑ ነድያን የምገባ መስተንግዶ እንዲሁም ለአረጋዊያን ወጣቶች እና ሕፃናት ከሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላትና ከአካባቢው ምዕመን የተሰበሰቡ የአልባሳት ልገሳ አምስት ለሚሆኑ እናቶች ደግሞ የመቁረቢያ ነጭ ልብስ ተሰጥቶ ጉባኤው ተጠናቋል። በጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ደብር ሰንበት ት/ቤት ወር በገባ በ21 እመቤታችንን በመዘከር ወርሐዊ የነድያን ምገባ እንደሚካሄድ ተገልጿል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion