cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

MINSTER OF EDUCATION

Show more
Advertising posts
25 304
Subscribers
+224 hours
+627 days
-8630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በኦንላይን ለመስጠት እየተከናወኑ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል። በውውይይቱ የክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል። የመልቀቂያ ፈተናውን በአዲስ አበባ በበይነ መረብ ለመስጠት ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልፀዋል። ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስፈልጉ፦ ➭ ኮምፒውተሮች፣ ➭ ላፕቶፖች፣ ➭ ታብሌቶችና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን የማሟላት ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከወዲሁ ማዘጋጀት በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሐግብር እንዲሰጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል። #አዲስአበባትምህርትቢሮ @minster_of_education
Show all...
#DambiDolloUniversity ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የመውጫ ፈተና ለሚወስዱ ዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች #ሞዴል የመውጫ ፈተና መስጠት ጀምሯል፡፡ የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14-21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይወቃል፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዕጩ የቅድመ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎቻቸው #ሞዴል የመውጫ ፈተና እንዲሰጡ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ያስገድዳል፡፡ @minster_of_education
Show all...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስታርት አፕ ማዕከል በቅርቡ ሥራ እንደሚያስጀምር ገልጿል፡፡ መንግሥት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለማስፋፋት የስታርት አፕ ልማትን የሚያጎለብቱ የተለያዩ ፖሊሲዎች እያተዘጋጁ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ በቅርቡም የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች ሐሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር የሚችሉበትን አዲስ አሠራር መዘርጋቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውም የውጭ አገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ ማዋል የሚችልበት አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ተገልጾ ነበር። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚከፍተው የስታርት አፕ ማዕከል በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን የበለጠ ለማጠናከር አጋዥ እንደሚሆን ይታመናል፡፡ @minster_of_education
Show all...
#ምስላዊ_መረጃ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-11/2016 ዓ.ም ይሰጣል። በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁ ይታወሳል፡፡ @minster_of_education
Show all...
👍 2🥰 1
#የቻናል_ጥቆማ 🔔 ለኢንጂነሪንግ ተማሪዎች እና Construction ዘርፍ ላይ ለተሰማራችሁ በሙሉ‼️ የኮንስትራክሽን፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ የአርክቴክቸር ተማሪ ነዎት? በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት? 📚 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መጻሕፍት፣ ቪዲዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን ዕውቀት ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን! 👉 ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣ 👉 አዲስ የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣ 👉 እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣ 👉 በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሌክቸር የምታገኙበት፡፡ Join Us :- ✅on Telegram 👇 https://t.me/ethioengineers1 https://t.me/ethioengineers1 ✅on TikTok tiktok.com/@ethiocons tiktok.com/@ethiocons
Show all...
👍 1🔥 1
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው። @minster_of_education
Show all...
"ትምህርት ለትውልድ" በተባለውና የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መሰብሰቡን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተጀመረው ሕዝባዊ ንቅናቄ፤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አሰተዳደሮች ከ25.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መሰብሰቡን በሚኒስቴሩ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገልፀዋል። በ2016 ዓ.ም ብቻ በትምህርት ለትውልድ መርሐግብር ከ4 ሺህ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ የትምህርት ቤቶች ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ሥራ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገልጿል። @minster_of_education
Show all...
🥰 1
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ጀመረ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃደኛ መምህራን በመታገዝ በተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡ በጉዲኦ ዞን ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስት ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሦስት ዓመታት አንድም ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ አለማሳለፋቸውን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ያደረገው ጥናት ያሳያል፡፡ በመሆኑም የማጠናከሪያ ትምህርቱ በጌዴኦ ዞን የሚታየውን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር ማነስን ለማሻሻል ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን፤ በተመረጡት ትምህርት ቤቶች አርብ፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። @minster_of_education
Show all...
#ጥቆማ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በክረምት የስልጠና መርሐግብር የሚሳተፉ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል። እነማን ይመዘገባሉ? የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦ ከሚያዝያ 17 እስከ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም ስልጠናው መቼ ይጀምራል? ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 1/2016 ዓ.ም (ለሁለት ወራት) (በሳምንት ለአራት ቀናት) ስልጠናው ትኩረት የሚያደርግባቸው፦ ➭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ➭ ሮቦቲክስ፣ ➭ ፕሮግራሚንግ፣ ➭ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም። ምዝገባ የማድረጊያ አማራጮች፦ 👉 forms.gle/9B79pzGLdo84W2LY8 👉 https://www.aii.et/summer-camp-registration-form-for-student/ @minster_of_education
Show all...
👍 9 5
#ጥቆማ በ Ethiopian Capital Market (ካፒታል ገበያ) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ይሳተፉ! መቼ? ነገ ሰኞ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም ጠዋት 2:30 የት? በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ስልጠናውን ማን ይሰጠዋል? የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለሙያዎች @minster_of_education
Show all...
👍 2 1