PsychBooks
Open in Telegram
9 082
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
Day 2 of 365 (2016)
To fly, you must let go of the things holding you down.
ዛሬ ያለፈ ሸክማችንን እና ገድቦ የያዘንን ነገር ከላያችን ላይ ቀስ በቀስ ለማውረድ የጀመርንበት 2ኛ ቀን ይሁን!
👉https://youtu.be/CJuOwz-4ir8
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
የመርሳት ችግር ያለበት ባል ሚስቱን ሰርፕራይዝ ለማድረግ አይንሽን ጨፍኝ ብሏት ከጨፈነች በኋላ ሰርፕራይዙን ረስቶት እኔን ላለማየት ነው አይንሽን የጨፈንሽው ብሎ ከቤት አባረራት። አሁንም ማባረሩን ረስቶት የት ሄዳ ነው ብሎ እየፈለጋት ነው።
(ከሜም የተገኘ)
https://youtu.be/xjxt8qg-sJs
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
አንድን ሕልሙን የሚያሳድድ ሰው ተስፋ አስቆራጭ ቃላት አትናገር። ሕጻንነት ወይም እርጅና ከሞት ጋር አይያዙም። ሕልም ካለህ በእድሜ አትገደብም። ምንም ቢሆን መቼም ማድረግ ትችላለህ። ማንንም በእድሜው ምክንያት እንደማይሰራ አድርገህ አትመልከት።
Subscribe!
YouTube: 👉https://youtu.be/fKqH0fq-D80
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
ትውልድ ያስፈልገናል፣ መልካም ትውልድ እንሻለን። አብዛኛውን ትውልድ ማህበራዊ ሚዲያ እየነጠቀን ነው። በየቤቱ በማንነት ብዥታ (identity confusion) ውስጥ ያሉ ሕጻናት እና ወጣቶችን እያየን ነው። አወቅን የሚሉ እና በማህበራዊ ሚዲያ ማንነት የተገነቡ፣ የሚናገሩትን የማያውቁ፣ የሚከተሉትን እና የሚከተላቸውን የማይረዱ፣ ቶሎ የሚሰበሩ ግልብ (shallow) ትውልዶች እየተፈጠሩ ነው።
በአሁኑ ሰዓት ከሜይንስትሪም ሚዲያው (ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ) በበለጠ የማህበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ እጅግ ከባድ ነው። ማህበራዊ ሚዲያውን ለጥሩም ለመጥፎም የሚጠቀሙ ቢኖሩም መጥፎው እየጎላ የሚሄድበት የራሱ ምክንያት አለው። ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ነገር የሚጠቀሙ ሰዎች እየተተቹ እና ተከታዮቻቸው በቁጥር እያነሱ፣ በወከባና በአልባሌ ነገሮች እየተተኩ ነው። ይህ በጣም አሳሳቢ ነው።
ወጣቶች በራሳቸው ገመድ እየተጠለፉ ነው። ትናንት ባለማወቅ፣ በመታበይ ወይም በምንያመጣሉ ለተናገሩት መጥፎ ንግግር በሚቀርብባቸው ትችትና ወቀሳ ጸጸት ውስጥ እየገቡ፣ ቤተሰባቸውንም እያሳዘኑና እያሸማቀቁ ይገኛሉ። ይህ የማህበራዊ ሚዲያው ከፍተኛ ተግዳሮት ነው። ቀድሞ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ...አይነት የሥነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ መግባት እና ከዚያ ለመውጣት ደግሞ ደብቁኝ ማለት ከፍተኛ ሕመም አለው።
በመሆኑም ብዙ የሥነ-ልቦና ባለሙያዎች፣ ብዙ የአዕምሮ ሀኪሞች፣ ብዙ መልካም የሀይማኖት አባቶች፣ የጥናት ባለሙያዎች፣ የሥነ-ማህበረሰብ ባለሙያዎች ያስፈልጉናል። እንደ ማህበረሰብ የአብሮአዊነት (collectivism) የአኗኗር ዘይቤን ስለምንከተል ትቸቱም ሆነ ሙገሳው ሁሉንም ሊጠቅም ወይም ሊጎዳ ይችላል።
በአዲሱ አመት አዲስ ነገር ይዘን እንመጣ ዘንድ ይህንን ሀሳብ የምትደግፉ አግዙን።
"...አሁንም አልረፈደም፣ ግን ይረፍዳል..." (ማንያዘዋል ፊልም)
ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ ጠብቁን!
https://youtu.be/VuyUr7KoiMo
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
10 Life Rules for Men
1. If you’re winning, keep your mouth shut.
Sometimes people are loosing in life because they talk excessively.
2. Be brutally honest with your brothers.
If they fuck up, you need to tell them.
Keep your brothers on the right track.
Hold each other accountable.
3. Competence is everything.
If you’re clumsy, forgetful, or disoriented…
You won’t be respected, especially by girls.
Admit your flaws and work hard to fix them.
The greatest teachers in the history world are mistakes.
4. Do not tell lies about yourself to impress other people.
Become genuinely impressive instead.
5. Never stop working to be better.
The idea of “good enough” is weakness.
Push yourself to the limit every single day.
Never be satisfied, never grow comfortable.
6. Keep your ability to always walk away.
A man without options is a slave to his environment. The person who cares less is the person in control of the interaction.
Expand your options in every aspect of life.
7. Destroy any sense of complacency.
Weak men think they’re doing enough.
Men destined for success are always angry at themselves for not doing more.
Be afraid of feeling too comfortable.
8. Be wary of who you spend your time with.
Your circle greatly influences who you are.
Make an effort to keep it free of losers.
Push your brothers to greater heights.
The more you push others to succeed the more you’re succeeding too..
9. Guard your reputation at all costs.
What people see of you determines how they will treat you.
Always be groomed and well put together.
10. Make your word mean something.
Any man can talk a big game, but few can back it up with real-world actions.
Nobody can respect a man who only talks.
Believe and mean every word you say.
https://youtu.be/htXnLCzVFUY
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
"...በማህበራዊ ሚዲያ እየተነሱ የሰው ችግር መፍትሔ አለን የሚሉ ሰዎች ተበራክተዋል። ፍላጎት ገበያን ይፈጥራል። ዘመኑን መዋጀት ተገቢ ነው። መፍትሔዎችን መማተር፣ ማንበብና መጠየቅ፣ ለማወቅም መሞከር የሚበረታታና ይበል የሚያሰኝ ነው። ችግሩ አብዛኛው ሰው እውቀት ጠልና ጊዜያዊ ማስታገሻ (temporary fix) ፈላጊ መሆኑ ነው። ምርምርና እውቀት ተኮር ዲስኮርስ አንወድም ኢትዮጵያውያን። ቧልትና ወሬ ነው የሚቀናን። ፈውሶቻችን እንዲሰሩልን መመርመርና መፈተሽ ያስፈልገናል ..."
(Dr. Yonas A.)
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
የብርጭቆው ውሃ፤
===========
አንድ ሳይኮሎጂስት ለተማሪዎቿ ስለ Stress Management (የውጥረት መቆጣጠሪያ መንገዶች) እያስተማረች በክፍሉ ውስጥ ትንጎራደዳለች፡፡ በመሀሉም አንድ ብርጭቆ ውሃ በእጇ አነሳች፡፡ በክፍሉ ውስጥ የነበሩት ተማሪዎችም አንድ ሁልጊዜ የሚጠብቁትን ጥያቄ ልትጠይቀን ነው ብለው አሰቡ፡፡ የ‹‹ግማሽ ሙሉ፣ግማሽ ጎደሎ/ 'Half Empty, Half Full Principle'›› ጥያቄ፡፡ በአንጻሩ እሷ ፈገግ በማለት ‹‹ይህ ውሃ ምን ያህል ይከብዳል›› ብላ ጠየቀች፡፡ ብዙ ምላሾችና ግምቶች ተሰነዘሩ፡፡
እርሷ ግን መለሰች ‹‹የዚህ ትክክለኛ ክብደት አያሳስበኝም፣ ክብደቱ የሚወሰነው ምን ያህል ጊዜ እጄ ላይ ባቆየሁት ልክ ነው›› አለች፡፡ ማብራራቷን ቀጠለች ‹‹ለምሳሌ ለአንድ ደቂቃ ያህል ባቆየው ያን ያህል ችግር የለውም፣ ለአንድ ሰዓት ያህል እጄ ላይ ባቆየው ግን ትንሽ እጄ ሊዝል ይችላል፣ ለአንድ ቀን እንደያዝኩት ቢቆይ ደግሞ እጄ ይደነዝዛል፣ እንዲያውም ፓራላይዝ ሊሆን ይችላል፡፡›› ሳይኮሎጂስቷ ቀጠለች ‹‹ከላይ ባየናቸው ሶስቱም ሁኔታዎች የውሃው ክብደት አልተቀየረም፣ ነገር ግን ለብዙ ጊዜ በያዝኩት መጠን የመክበድ ሁኔታውም እየጨመረ መጣ፡፡››
ባለሙያዋ አሁንም ማብራራቷን ቀጠለች፡፡ እንዲህ በማለት ‹‹በሕይወታችን የሚያጋጥሙን ውጥረቶችና ጭንቀቶች በዚህ ብርጭቆ ውሃ ይመሰላሉ›› ስለዚህም ‹‹ውጥረቶቻችሁን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ብታስቧቸው ምንም አይፈጠርም፣ ትንሽ ረዘም ላለ ጊዜ ብታስቧቸው ግን እናንተን መጉዳት ይጀምራሉ፣ ሁልጊዜ ስለ እነሱ ካሰባችሁ ደግሞ ጭራሽ ፓራላይዝድ ሆናችሁ ምንም ነገር መስራት ያቅታችኋል፡፡››
ስለዚህም ውጥረቶቻችሁን ለማስወገድ ጣሩ፡፡ ገና ጧት ከመኝታችሁ ስትነሱ አሽቀንጥራችሁ ጣሏቸው፡፡ እስከ ማታ ድረስ ይዛችሁ አትዋሉ፡፡
በአጭሩ አስታውሱ! ሁልጊዜም ቢሆን ብርጭቆውን ከእጃችሁ ላይ ቀስ በቀስ አውርዱት!!
©ሥነ-ልቦና ለሕይወት
https://youtu.be/KeUjk1uWRu8
9 082
Repost from Psych Addis - ሳይክ አዲስ
አሁን የመጀመርን ልማድ ከአሁን ይጀምሩ! አሁን ካልሆነ መቼ? አንተ/ቺ ካልሆነክ/ሽ ማን?
አማራጭ ቻናሎቻችንን ሰብስክራይብ በማድረግ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!
ዩቲዩብ፦ https://youtu.be/F08vJtJilOA
ቴሌግራም፦ https://t.me/psychaddis
