cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

mieraf secondary school(for satffe)

School

Show more
Advertising posts
632
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+630 days
Posts Archive
የምዕራፍ አጠቃ.2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት 1.ሰላማዊ የመማር ማስተማር ዙርያ. 2.የሁለተኛ ስምስተር ሚድ ፈተና እና የ12ኛ ክፍል ሞደል ፈተና እንድሁም ፖርሽን ከቨሬጅ ላይ ውይይት ተደርጓል።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም የተከበራችሁ የመምህራን ማኅበር አባላት 🙏 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ስራ ኮሚሽን  አባላት ለምዝገባ ሲመጡ ከላይ የተዘረዘሩትን 12 ጉዳዮች ማሟላት እንዳለባቸው አሳውቆናል። ስለሆነም ከዚህ በፊት ከተጠየቁት 4 መስፈርቶች በተጨማሪ በተራ ቁጥር 11 ላይ የተጠቀሰውን ማስረጃ ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን ማስታወሻ:- የተጠየቁትን ማስረጃዎች ከወሳኝ ኩነት ወይም ከቀበሌ ወይም ከወረዳ ለማቅረብ እየተቸገራችሁ መሆኑን ስለተረዳን የምዝገባ ጊዜ የሚራዘም ስለሚሆን እስከዛው ድረስ ለማሟላት ጥረት አድርጉ።
Show all...
ለሙስሊሙ ማህበር በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳች በዓሉ የሰላም:የአንድነት:የፍቅር ይሁንልን!!! መልካም በዓል!!
Show all...
የዒድ አልፈጥር በዓል ረቡዕ ነው። ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ አልታየችም ፤ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ 1445ኛው የዒድ አል ፊጥር በዓል ደግሞ እሮብ ሚያዝያ 2 እንደሚከበር ይፋ ተደርጓል።
Show all...
🔝 Main Menu
Show all...
መመልመያ መስፈርት.docx0.26 KB
2016 Summer need format for principals.xlsx0.29 KB
2016 to 2017 All director and teacher transfer format.xlsx0.33 KB
2016 to 2017 Summer teachers need format.xlsx0.34 KB
የክረምት ተከታታይ ትምህርት እና የዝውውር መሙያ ቅፅ በሶፍት ኮፒ የላክን ሲሆን በተላከላችሁ ቅፅ መሰረት እስከ ሚያዝያ 05 ድረስ የክፍለ ከተማ ክፍለ ከተማና የክልል ዝውውር እንዲሁም ክረምት ተማሪዎች መረጃ በየዘርፉ ለይታችሁ በማስሞላት እንድትልኩልን ስንል እንጠይቃለን፡፡
Show all...
Started like this
Show all...
ቀን:- 20/07/16 በምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፅዳት ዘመቻ በፎቶ Guyyaa፦ 20/07/16 Mana barumsaa Mi'iraaf waliigalaa sad. 2ffaatti duula qulqullina mooraa mana barumsaa suuraan
Show all...
(ቀን መጋቢት 20/2016 ዓ.ም) መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Show all...
የፈተና መረጃ ለ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ✅ የ6ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ) በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:- 👉አማርኛ 👉እንግሊዘኛ 👉ሒሳብ 👉አካ/ሳይንስ  እና 👉ሞራል ሲሆኑ ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል ✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፍል ብቻ(5ኛ ክፍልን አይጨምርም) ✅ 8ኛ ክፍል በተመለከተ(ለአዲስ አበባ) በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:- 👉አማርኛ 👉እንግሊዘኛ 👉ሒሳብ 👉ሶሻል ሳይንስ 👉አጠ/ሳይንስ 👉የዜግነት ት/ት እና ለአፋን ኦሮሞ ተማሪዎች አፋን ኦሮሞ እና ገዳ ይጨምራል ✍️ሁሉም ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል ብቻ(7ኛ ክፍልን አይጨምርም) ✅12ኛ ክፍል በተመለከተ 👉በ2016 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን  በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው::   እነሱም :- ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ ✍️እንግሊዝኛ ✍️ሒሳብ ✍️ባዮሎጅ ✍️ፊዚክስ ✍️ኬሚስትሪ ✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት ለ/የማህበራዊ ሣይንስ ✍️እንግሊዝኛ ✍️ሒሳብ ✍️ታሪክ ✍️ኢኮኖሚክስ ✍️ጅኦግራፊ ✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት የፈተና ዝግጅትም:- 1. የኢኮኖሚክስ ፈተና ከ12ኛ ክፍል ብቻ 2. ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ -11ኛ በአሮጌው ስርአተ ትምህርት እና 12ኛ ክፍል በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ያጠቃልላል:: 3. ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት በነበረው አሠራር መሠረት ይቀጥላል:: 👉የሚከተሉትን  ምክሮች በመተግበር  የማስታወስ ችሎታችንና የትኩረት አቅማችንን ማዳበር እንችላለን :- ✅ 1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች. 👉ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል። 👉ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል። 👉ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው። ✅ 2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት 👉ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል። 👉ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።ጠዋት ጥናት የምንጀምርበትና የምናበቃበት ሰዓት ከፈተናው በፊት ባሉት ሁለት ወይም ሦስት ሳምንታት ውስጥ ተመሳሳይ ለማድረግ መሞከርም ውጤታማ ያደርጋል። 3. ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባችሁ ወስኑ በመጀመሪያ ፈተናው የጽሁፍ ነው ወይስ የተግባር? ወይስ ቃለመጠይቅ ነው የሚለውን መለየት ወሳኝ ነው። 👉ሁሉም ዓይነት ፈተናዎች የራሳቸው የሆነ የተለያየ አይነት አቀራረብ አላቸው። በምሳሌ አስደግፎ ማብራሪያ መስጠት የሚጠይቅ ዓይነት ፈተና ከሆነ ከዚህ በፊት የተሠሩ ፈተናዎችን እያመሳከሩ ጥቂት ቦታዎች ላይ በትኩረት መዘጋጀት። ምናልባት ፈተናው ምርጫ አልያም አጭር መልስ የሚፈልግ ዓይነት ከሆነ ቀለል ያለና አጠቃላይ መረጃዎችን ለመያዝ መሞከር። ✅ 4. እቅድ ማዘጋጀት 👉ምናልባት ነገሮችን ቦታ ቦታ ለማስያዝና እቅድ ለማውጣት የምናጠፋው ጊዜ የባከነ መስሎ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን እውነታው በተቃራኒው ነው። ምክንያቱም ምን ማጥናት እንዳለባችሁና መቼ ማጥናት እንዳለባችሁ እቅዳችሁ ይነግራችኋል። ከዚህ በተጨማሪም ምን ያክል እንደተጓዛችሁ ለመመዝገብና ለመከታተል ይረዳል። 👉የትኞቹን ማስታወሻ ደብተሮች መቼ መመልከት እንዳለባችሁ፣ የትኞቹን መጻህፍት ለተጨማሪ ማብራሪያ እንደምትጠቀሙ እንዲሁም የፈተና ጥያቄዎችን መቼ መለማመድ እንዳለባችሁ በእቅድ ውስጥ ማስገባት ውጤታማ ያደርጋል።እዚህ ጋር መርሳት የሌለብን ለእረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴም ቦታ መስጠት እንዳለብን ነው። ✅5. ከፋፍሎ ማጥናት 👉የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል። 👉ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ። ✅ 6. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ 👉የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል። 👉ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው  ።የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል። ✅ 7. መምህር መሆን 👉ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ። ✅8. ከተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ራቅ በሉ 👉ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ። 👉ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።ብትችሉ ስልካችሁን አጠገባችሁ እንኳን አታድርጉት። ✅9. ሙዚቃ መቀነስና በጸጥታ ማንበብ 👉በጸጥታ ውስጥ ሆነው ጥናታቸውን የሚያከናወኑ ተማሪዎች ሙዚቃ እየሰሙ ከሚያጠኑት ጋር ሲወዳደሩ በእጅጉ የተሻለ የማስታወስና የትኩረት አቅም እንዳለቸው ማረጋገጥ ተችሏል። ✅10. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ 👉ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል። 👉ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል። 👉አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ። ✅11. እንቅልፍ 👉ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
Show all...
Document from [email protected]
Show all...
CTE Career Pathway Selection Manual 1 9 Feb 24.pdf2.86 KB
Gumii wal gargaarsaa(የበጎ አድራጎት ክበባት ስራ).....
Show all...
20230329_122111.mp463.42 MB