cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

MORAL MEDIA ሞራል ሚዲያ ®️

👉 ታማኝ ዜናዎችና መረጃዎች በየዕለቱ የሚቀርብበት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🌍

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጥቅምት 10 ቀን 1961 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 54 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ በሜክሲኮ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ 2:20:26 ሰዓት በመግባት ለሀገሩ 🥇የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘበት ዕለት ነበር። አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ታሪክ በአንድ ኦሊምፒክ ሁለት ሜዳሊያ ያገኘ ቀዳሚው አትሌት ነው። ከማራቶን ድሉ አንድ ሳምንት በፊት በ 10 ሺሕ ሜትር በኬንያዊው ናፍታሊን ቴሙ በሽርፍራፊ ሴኮንዶች ተቀድሞ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ አግኝቶ ነበር። በአንድ እሎምፒክ ታሪክም ረጅም ኪሎ ሜትሮችን ሸፍኖ የሮጠ ኢትዮጵያዊ በመሆን በብቸኝነት ስሙ ይጠቀሳል። ክብርና ሞገስ ለጀግናው አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ 🙏 #ታሪክን_ወደኋላ Subscribe 👇 Our Youtube Channel ዩቲዩብ=youtube.com/channel/UC24UEZFXqoGKmb7v98wB55Q
Show all...
ከህወሓት ጋር የሚደረገው የሰላም ንግግሩ ከአራት ቀናት በኋላ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ! በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የሰላም ውይይት የፊታችን ጥቅምት 14/2015 ዓ. ም. በደቡብ አፍሪካ እንደሚደረግ ከአፍሪካ ኅብረት እንደተነገራቸው የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ የሆኑት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። አምባሳደር ሬድዋን በትዊተር ገጻቸው ዛሬ ጥቅምት 10/2015 ዓ. ም. እንደጻፉት፣ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የደረሳቸው መረጃ፣ የሚጠበቀው የሰላም ውይይት ከአራት ቀናት በኋላ በደቡብ አፍሪካ ይከናወናል። “በንግግሩ ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናችንን በድጋሚ አረጋግጠናል” ብለዋል አምባሳደር ሬድዋን። አክለውም “ሆኖም ግን ጥቂቶች የሰላም ንግግሩን ቀድመው ዋጋ በማሳጣታቸው እና ስለ መከላከል እርምጃቸው የተሳሳተ ክስ በማሰማታቸው አዝነናል” ብለዋል። እስካሁን ድረስ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሰላም ንግግርን በተመለከተ የተባለ ነገር ስለመኖሩ የትግራይ ኃይሎች ያሉት ነገር የለም። ከሁለት ሳምንታት በፊት የአፍሪካ ኅብረት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሊያካሂደው አስቦት በነበረው የሰላም ንግግር ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቦ፣ ሁለቱም ወገኖች ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸው እንደነበር ይታወሳል። ነገር ግን በሎጅስቲክስ አለመሟላት የንግግሩ ቀን እንዲሸጋገር ተወስኗል። በአፍሪካ ኅብረት አማካይነት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የሰላም ንግግር መሸጋገሩን ተከትሎ በነበሩት ቀናት ውጊያው ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፤ የፌደራሉ መንግሥት ሽረ እና  አላማጣን መያዙ አይዘነጋም።     ( ቢቢሲ )
Show all...
የራያ ቆቦዉን ምክትል ሳጂን አማረ በላይ(ጥቁር በላይን)ሳይታሰብ አጣነዉ። ወንድማችንን ጥቁር በላይን ዛሬ ሳንስበው አጣነው። እግዚአብሔር ነፍስህን በመንግስተ ሰማይ ይቀበላት።
Show all...
🔥#ልቀምልኝ💪 የሴት ቀሚስ የለበሱ የህወሓት አሸባሪዎች ከፍልፈል ገደላቸውና ከየስርቻው በጥምር ጦሩ እየተለቀሙ ነው💪
Show all...
"የኢትዮጵያ መከላከያ በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬን፣ አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር ችሏል።"፦ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የኢትዮጵያ መከላከያ በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬን፣ አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር መቻሉን የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትንና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ስለማስቀጠል አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትንና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ስለማስቀጠል የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተወሰኑ የትግራይ ክልል ከተሞችን መቆጣጠሩ ይታወቃል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከተሞች የጦርነት ቦታ እንዳይሆኑ የሚያደርግ የጥንቃቄ አካሄድ እንደሚከተል መግለጹ ይታወሳል። የመከላከያ ሠራዊት በከተሞች ጦርነት እንዳይደረግ የተከተለው ጥብቅ ዲሲፕሊን፣ በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል። የኢትዮጵያ መከላከያ በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬን፣ አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር ችሏል። ይህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከተለው ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩ አካላትን ሟርት ያመከነ ነው። ከልዩ ልዩ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ መከላከያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች እርዳታ በተሣለጠ መንገድ እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግሥት በቂ ዝግጅት አድርጓል። ይሄም የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን ተጠቅሞ እርዳታ ማድረስን ይጨምራል። መንግሥት ከሰብአዊ የእርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሰብአዊ እርዳታ የሚደርስባቸውን መንገዶች እያስፋፋ ነው። በተቀናጀ መንገድ በሰሜን ጎንደር በኩል ወደ ሽሬ የሚወስደውንና ከኮምቦልቻ -ደሴ-ወልድያ-ቆቦ-አላማጣ ያለውን መንገድ ለመክፈት እየሠራ ነው። ይሄንን ሥራ የሚያሣልጥ ኮሚቴ ከሚመለከታቸው አካላት ተወጣጥቶ ሥራ ጀምሯል። እነዚህ ሥራዎች ቴክኒካዊ የሆኑ ጥናቶችን እና ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ይጨምራል።
Show all...
መረጃ‼️ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬን፣አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር ችሏል! የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትንና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ስለማስቀጠል የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተወሰኑ የትግራይ ክልል ከተሞችን መቆጣጠሩ ይታወቃል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከተሞች የጦርነት ቦታ እንዳይሆኑ የሚያደርግ የጥንቃቄ አካሄድ እንደሚከተል መግለጹ ይታወሳል። የመከላከያ ሠራዊት በከተሞች ጦርነት እንዳይደረግ የተከተለው ጥብቅ ዲሲፕሊን፣ በሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል። የኢትዮጵያ መከላከያ በከተሞች ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት ሳያካሂድ ሽሬን፣ አላማጣና ኮረም ከተሞችን ለመቆጣጠር ችሏል።ይህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተከተለው ጥብቅ ወታደራዊ ዲሲፕሊን፣ የሕወሐትን ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋቡ የነበሩ አካላትን ሟርት ያመከነ ነው። ከልዩ ልዩ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት፣ መከላከያ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች እርዳታ በተሣለጠ መንገድ እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግሥት በቂ ዝግጅት አድርጓል።ይሄም የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን ተጠቅሞ እርዳታ ማድረስን ይጨምራል። መንግሥት ከሰብአዊ የእርዳታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሰብአዊ እርዳታ የሚደርስባቸውን መንገዶች እያስፋፋ ነው። በተቀናጀ መንገድ በሰሜን ጎንደር በኩል ወደ ሽሬ የሚወስደውንና ከኮምቦልቻ -ደሴ-ወልድያ-ቆቦ-አላማጣ ያለውን መንገድ ለመክፈት እየሠራ ነው። ይሄንን ሥራ የሚያሣልጥ ኮሚቴ ከሚመለከታቸው አካላት ተወጣጥቶ ሥራ ጀምሯል።እነዚህ ሥራዎች ቴክኒካዊ የሆኑ ጥናቶችን እና ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር የሚያስችሉ መሠረታዊ ሥራዎችን ይጨምራል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት  
Show all...
ለቸኮለ! ማክሰኞ ጥቅምት 8/2015 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች 1፤ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ክልል ሽሬ፣ አላማጣ እና ኮረም ከተሞችን መቆጣጠሩን መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሠራዊቱ እስካሁን በውጊያው ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ማድረግ መቻሉን የገለጸው መንግሥት፣ ሦስቱ ከተሞች የተያዙት የከተማ ላይ ውጊያ ሳይደረግ መሆኑን ገልጧል። በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ወደ ሽሬ እና ከወልዲያ፣ ደሴና ኮምቦልቻ ወደ አላማጣና ኮረም የሚወስዱ አውራ ጎዳናዎችን ለመክፈትና የሰብዓዊ ዕርዳታ መግቢያ መስመሮችን ለማስፋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል። በአካባቢው መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር መንግሥት ጥናት ያደርጋል ተብሏል። 2፤ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ "መቻሬ ሜዳ" በ50 ቢሊዮን ብር ወጪ የቅንጡ መኖሪያ አፓርታማዎችና የተለያየ ማዕከላት የግንባታ ሥራ እንደተጀመረ ዋዜማ ሰምታለች። ፕሮጄክቱ በ250 ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን፣ በውስጡ የገበያ ማዕከል፣ ግዙፍ ሆቴል፣ 1 ሺህ 300 ያህል አፓርታማዎች፣ ዘመናዊ ቪላዎችን፣ ሲኒማ ቤት እና ሰፋፊ መዝናኛዎችን ያካተተ ነው። "መሐመድ ሪል ስቴት ቪሌጅ" ተብሎ የተሰየመውን ፕሮጀክት የሚገነባው ሚድሮክ ግሩፕ ነው። Link- https://wazemaradio.com/%e1%89%a0%e1%8a%a0%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a3-%e1%89%a050-%e1%89%a2%e1%88%8a%e1%8b%a8%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8c%aa-%e1%8b%a8%e1%8a%a8%e1%89%b0%e1%88%9b-%e1%88%98/ 3፤ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ከሕወሃት ጋር ለሚደረገው የሰላም ንግግር "መንግሥት የአፍሪካ ኅብረት ቀኑን እስኪያሳውቅ እየጠበቀ ነው" በማለት በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። ሬድዋን አሁን ያለው ግጭት ከቁጥጥር ውጭ ወጥቶ የነበረው ወደ አጎራባች ክልሎች በተዛመተበት ወቅት እንደነበር ገልጸው፣ "ግጭቱ አሁን እየበረደ እንጂ ከቁጥጥር ውጭ እየወጣ አይደለም" ብለዋል። የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ "በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው" ሲሉ ትናንት አስጠንቅቀው ነበር። ሬድዋን ጨምረውም፣ ለትግራይ ክልል በቅርቡ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንደሚጀምር ጠቁመዋል። 4፤ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ቮከር ተርክ በትግራይ ክልል ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ግጭቱን ባስቸኳይ አቁመው ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልጉ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። ተርክ በትግራይ በቅርቡ የተካሄዱ የአየር ላይ ድብደባዎች ግጭቱ በሲቪሎች ላይ ያስከትለውን አደጋ አባብሰውታል ብለዋል። "በሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት ተቀባይነት የለውም" ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን ከጉዳት እንዲጠብቁና ሰብዓዊ ዕርዳታ ለተረጅዎች እንዲገባ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። 5፤ ንግድ ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን የነዳጅ አከፋፋዮችን የትርፍ ሕዳግ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ለመጨመር መስማማታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ባለሥልጣኑ በጥናት ላይ ተመስርቶ የትርፍ ሕዳግ ጭማሪ የውሳኔ ሃሳብ ለሚንስቴሩ ማቅረቡን ገልጧል። ከጥቂት ቀናት በፊት የነዳጅ አመላላሾች ማኅበር በመንግሥት ላይ ግፊት ለመፍጠር የሥራ ማቆም አድማ ለመጥራት ወስኖ የነበረ ሲሆን፣ ሆኖም ባለሥልጣኑ ችግሩን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ቃል በመግባቱ ማኅበሩ አድማውን ሰርዞ ነበር። አሁን ነዳጅ አከፋፋዮች የሚያገኙት ትርፍ በሊትር 0.23 ሳንቲም ሲሆን፣ ማኅበሩ ከሁለት ወራት በፊት የአምስት እጥፍ ጭማሪ መጠየቁ ይታወሳል። 6፤ ትምህርት ሚንስቴር ዛሬ ሁለተኛውን ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተናን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ማስጀመሩን አስታውቋል። ዛሬ የተጀመረው ሁለተኛ ዙር ፈተና ተፈታኞች የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ተፈታኞች ናቸው። ፈተናው ለተከታታይ አራት ቀናት ይቀጥላል ተብሏል። 7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 52 ብር ከ7547 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 53 ብር ከ8098 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 56 ብር ከ7539 ሳንቲም፣ መሸጫው 57 ብር ከ8890 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ51 ብር ከ4200 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ52 ብር ከ4484 ሳንቲም ሲሸጥ ውሏል። [ዋዜማ]
Show all...
በአዲስ አበባ በ50 ቢሊየን ብር ወጪ የከተማ መንደር ግንባታ ተጀመረ - Wazemaradio

ዋዜማ- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ መቻሬ ሜዳ በሚባለው ቦታ በ50 ቢሊየን ብር ወጪ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርታማን ጨምሮ የተለያዩ ማዕከላትን የያዘ አዲስ የፕሮጀክት ስራ መጀመሩን ዋዜማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። ይህ ፕሮጀክት በሁለት መቶ ሀምሳ ሺህ ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን የገበያ ማዕከል፣ ግዙፍ ሆቴልና አንድ ሺህ ሶስት መቶ የሚጠጉ አፓርትመንቶችና ዘመናዊ ቪላዎች የተካተቱበት ነው። የሼህ

የአማራ አንድነት ማህበር #በእስራኤል የጀግናው ምሬ ወዳጆን ጥሪ ተቀብለው የ1 ሚሊዮን ብር የሎጅስቲክ ድጋፍ ለጀግናዉ ምስራቅ አማራ ፋኖ አድርገዋል።
Show all...