cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዋን ዑማ ተውሂድ

ወደ ተወሂድ @eislamm እንጣራ እኛ አንድ ነን የነቢዩ መሀመድ (ሰ .ዐ .ወ) ኡማወች የቻናሉ አላማ አገራችን ወስጥ ሺርክ በጣም እየተስፋፋ ነው ሰውችን ከሺርክ እንዲሩቅ ማድረግ ነው አላህ ዘንድ ከሺርክ የበለጠ ወንጀል የለም #ማንኛውም አስታየት ካላቹ በዚህ አድሩሱለኝ @abdiiis

Show more
Advertising posts
462
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ!! አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ!! አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን ትተህ ከእስልምና ምን ቀረህ? ሶላት የኢስላም ምሰሶ ፤ የኢማን መገለጫ -ካባ- መሆኑን አታውቅምን!? አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! አንተ ስትቀር ሁሉም ፍጥረታት ለጌታቸው ሰጋጆች ናቸው። አላህ እንዲህ ብሏል፡- “በሰማያት ያለው ሁሉ፤ በምድርም ያለው ሁሉ፤ ፀሀይና፣ ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራሮችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሶችም፣ ከሰዎች ብዙዎችም ለአላህ የሚሰግዱ መሆናቸውን አታውቅምን!? ብዙዎችም ቅጣት ተገባቸው። አላህ የሚያዋርደው ሰው ለርሱ ምንም አክባሪ የለውም፤ አላህ የሻውን ይሰራልና።” አንተም የማትሰግድ ከሆነ ከነዚያ ቅጣት ከተወሰነባቸው አንዱ ትሆነናለህ።አ ንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው ክህደትና (በአላህ ላይ) ማጋራት መሆኑን አታውቅምን!? ነቢዩ < አንዲህ ብለዋል፡- « ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﻭﺑﻴﻦ ﺍﻟﺸﺮﻙ ﻭﺍﻟﻜﻔﺮ ﺗﺮﻙ ﺍﻟﺼﻼﺓ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ] «በሰውየውና በሽርክ ወይም በክህደት መሀል (ያለው) ሶላትን መተው ነው።” « ﺍﻟﻌﻬﺪ ﺍﻟﺬﻱ ﺑﻴﻨﻨﺎ ﻭﺑﻴﻨﻬﻢ ﺍﻟﺼﻼﺓ : ﻓﻤﻦ ﺗﺮﻛﻬﺎ ﻓﻘﺪ ﻛﻔﺮ ‏» ‏[ﺃﺧﺮﺟﻪ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ]. “በኛና በነሱ (በካህዲያን) መሀል ያለው ቃል-ኪዳን (ድንበር) ሶላትን መተው ነው። (ሶላትን) የተወ በእርግጥ ካደ።” አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው እንዲሁም (ከሶላት) መዘናጋት ሙናፊቅነት መሆኑን አታውቅም!? አላህ እንዲህ ብሏል፡- ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ : ١٤٢ “ሙናፊቆች አላህን ሊያታልሉ ይፈልጋሉ፤ እሱ አታላያቸው ሲሆን። ወደ ሶላት ሲቆሙ እየሰለቹ፣ ለሰዎች የሚያሳዩ ሆነው ይቆማሉ። አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም።” ነቢዩም < ይህን ማስተላለፋቸው ተዘግቧል። « ﺃﺛﻘﻞ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻤﻨﺎﻓﻘﻴﻦ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺸﺎﺀ ﻭﺻﻼﺓ ﺍﻟﻔﺠﺮ، ﻭﻟﻮ ﻳﻌﻠﻤﻮﻥ ﻣﺎ ﻓﻴﻬﻤﺎ ﻷﺗﻮﻫﻤﺎ ﻭﻟﻮ ﺣﺒﻮًﺍ‏» ‏[ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ ]. “በሙናፊቆች ላይ እጅግ የሚከብደው ሶላት ኢሻዕ እና ሱብሂ ነው። (ሁለቱን በመስገድ) የሚገኘውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን (ወደ መስጊድ) ይመጡ ነበር።” አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! እስቲ አስተንትን ሙናፊቆች ለይዩልኝ (ሪያዕ) ቢሆንም እንኳ ይሰግዳሉ፤ አንተ ግን በፍጹም አትሰግድም!! አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ፡- ሶላትን መተው ዝንጉነት እና የልብ መድረቅ መሆኑን አታውቅምን!? ነቢዩ < እንዲህ ብለዋል፡- « ﻟﻴﻨﺘﻬﻴﻦ ﺃﻗﻮﺍﻡ ﻋﻦ ﻭﺩﻋﻬﻢ ﺍﻟﺠﻤﻌﺎﺕ، ﺃﻭ ﻟﻴﺨﺘﻤﻦ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻗﻠﻮﺑﻬﻢ، ﺛﻢ ﻟﻴﻜﻮﻧﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﻐﺎﻓﻠﻴﻦ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ]. “ህዝቦች የጁምዓ ሶላትን ከመተው ይከልከሉ! ወይም አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽግባቸዋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።” አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ፡- ሶላትን መተው ስራን ሁሉ እንደሚያበላሽ አልሰማሐሃምን!? የሚከተለውን የነቢዩን < ንግግር ተመልከት። « ﻣﻦ ﺗﺮﻙ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ ﺣﺒﻂ ﻋﻤﻠﻪ ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ]. “የአስርን ሶላት የተወ ስራው በርግጥ ተበላሸበት።” አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው ከከሀዲያንና ወንጀለኞች ጋር ለእሳት ቅጣት እንደሚዳርግ አታውቅምን!? የጀነት ሰዎች የጀሀነም ሰዎችን (ጀሀነም የገቡበትን ምክንያት) ሲጠይቋቸው የሚሰጧቸውን ምላሽ ሲናገር አላህ እንዲህ ይላል፡- “ሰቀር (የገሀነም ጉድጓድ) ውስጥ ምን አስገባችሁ? (እነሱም) ይላሉ፡- ከሰጋጆች አልነበርንም…።” እንዲሁም በሌላ ምዕራፍ፡- “ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጔደሉ፣ ስሜታቸውንም የተከተሉ ምትኮች ተተኩ። ለወደፊት ገይን (የገሀነም ሸለቆ) ይገባሉ።” አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን በመተውህ ከባድ መዓት (ጥፋት) ያረፈብህ መሆኑን አታውቅምን!? ነቢዩ < እንዲህ ብለዋል፡- « ﺍﻟﺬﻱ ﺗﻔﻮﺗﻪ ﺻﻼﺓ ﺍﻟﻌﺼﺮ، ﻓﻜﺄﻧﻤﺎ ﻭﺗﺮ ﺃﻫﻠﻪ ﻭﻣﺎﻟﻪ‏» ‏[ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ] “የአስር ሶላት ያመለጠው ቤተሰቦቹንና ንብረቱን እንደ አጣ (እንደ ተነጠቀ) ነው።” የአምስቱንም ወቅት ሶላት መተውህስ ምን ያስከትል ይሆን!? አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ሶላትን መተው መረበሽን፣ አለመረጋጋትን፣ ጭንቀትን፤ የኑሮ ጥበትን (እንደሚያመጣ) አታውቅምን!? አላህ እንዲህ ይላል፡- «ከግሳጼዬ የዞረ፤ የጥበት ህይወት አለለት፤ የትንሳኤም ቀን እውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን። ጌታይ ሆይ ለምን እውር አድርገህ ቀሰቀስከኝ? በርግጥ አይናማ የነበርኩ ስሆን ይላል። (ነገሩ) እንደዚሁ ነው። ተዓምራችን መጥቶልህ ሳለ እንደዘነጋኀው አንተም ዛሬ ትዘነጋለህ ይለዋል።» ዋ ንዴትህ! ዋ ፀፀትህ! አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ። እንዴት ጊዜ ያልፋል፤ እድሜህ (ያለ አግባብ) ይገባደዳል; ልብህ ከጌታህ ተጋርዶ ሳለ!? እንዴትስ በቅርቢቱ አለም (ዱንያ) ከሚገኙት ነገሮች ሁሉ ይበልጥ ጣፋጭ እና ማራኪ የሆነውን ነገር ሳትቀምስ ዱንያን ትሰናበታታለህ!? ይህም አላህን በማምለክ፣ በማውሳት፣ በማመስገን እና ለርሱም በመስገድ የሚገኝ ሲሆን። አንተ ሶላትን የተውክ ሆይ! ለሶላትህ ቀላል ስፍራ የሰጠኀው አንተ ዘንድ ታላቅ ስፍራ የሚሰጠው ምን ይሆን? ሶላቱን ያጓደ ሌሎች ስራዎቹን ይበልጥ እንደሚያጓድል አታውቅምን!? ሀሰን እንዲህ ብሏል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! ሶላትህ አንተ ዘንድ ጥሩ ስፍራ ከሌለው ምንድን ነው አንተ ዘንድ ጥሩ ስፍራ ሊኖረው የሚችለው!?” አንተ ዝንጉ የሆንክ ሆይ! ወደ ጌታህ ተመለስ! ሶላትህን ትተህ ሞት ከመምጣቱ በፊት። አንተ ሶላትን ችላ የምትል ሆይ! • የታላቁን ሶላት ደረጃ ካወቅክ • የሰጋጆችን ቁጥር ስፍር የሌለውን ሽልማት መመልከትከቻልክ (እና) • ሶላትን የሚያጓድሉ ሰዎችን ብርቱ ቅጣት ከተገነዘብክ በኋላ አሁንስ ምላሽህ ምን ይሆን? ሶላትን በማጓደልና ችላ በማለት ትቀጥላለህን!? ሶላትን ትቶ መተኛትንና ከወቅቱ ማዘግየትን ትገፋበታለህን!? ወንድሜ ሆይ! የት አለ ከፍ ያለው ሞራልህ? የት አለ ጠንካራው ቁርጠኝነትህ? የቱ ላይ ነው ለጀነት ታጥቆ መነሳት? የት አለ የሶላትን ወቅት መጠባበቅ? (ኧረ) የት አለ ወደ ጁምዓ እና ወደ ጀምዓ ሶላት በጊዜ መሄድ? @eslamm @eislamm
Show all...
#አክስት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል! {الخالة بمنزلة الام } "አክስት ልክ እንደ እናት ነች የእናት አይነት ደረጃ ነው ያላት።"
Show all...
በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ! ﷺ 🌹 .............................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ! ﷺ 🌹 .............................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ! ﷺ 🌹 .............................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ! ﷺ 🌹 .............................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ! ﷺ 🌹 .............................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ 🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ! .ﷺ 🌹.............................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ🥀 ..................🥀 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ......🥀 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🥀.... ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ .ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ 🌹
Show all...
ፈውዛን 0ቂደቱ አ ሱ ክ 3.mp312.48 MB
Show all...
ጫት በኮንትራት.mp31.59 MB
00:09
Video unavailableShow in Telegram
0931213121 Sheh Muhammed Amin 0912784898 Abdurahman Muhammed
Show all...
8.57 MB
እጅ ከፍንጅ ክፍል 22
Show all...
እጅ ከፍንጅ ክፍል 22.mp31.16 MB
01:22
Video unavailableShow in Telegram
2.08 MB
00:26
Video unavailableShow in Telegram
3.78 MB
አሰለሟአለይኩ ወራህመቱ ላይሂ ወበረካአቱ እስታዝ ዱአ እድታረጉልኝ እጠይቃለሁ
Show all...