cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ግጥም ብቻ 📘

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13@wegoch @Words19@seiloch @shiyach_bicha@zefenbicha @leul_mekonnen1

Show more
Advertising posts
72 562
Subscribers
-1424 hours
-667 days
-21930 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ ፍፁም አንዳልጓጓ ህመም በርትቶብኝ ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሞቴን ሲጠባበቅ ህመሜን ሳዳምጥ ስሜቶቼን ሳረቅ . . .          መኖር ማለት ስቃይ          መኖር ምለት ህመም          መኖር ማለት ጭንቀት          መኖር ማለት ድካም.... ወደ ተስፋ መንደር እልፍ ጊዜ ባመራ የ እድሌን ልሻማ ከ እኩዮቼ ጋራ ብፈልግ... ብጠብቅ ድርሻ የለኝ ሁኖ ጠብታ እንኳን ሳይቀር ከ እኔነቴ ተኖ ፀሐይ የለኝ ሁና ሕይዎቴ ዳምኖ . . .        ትላንት በመኖሬ ተስፋ እንኳን ሳይኖረኝ        ምንም ያህል ባዝን የሚያልፍ ባይመስለኝ        ቀን እየቆጠረ ቀን እየጨመረ        የደመናው ጥቁረት መጠኑ ቀንሶ        የስቃይ ዉርጅብኝ ከነበረው አንሶ        ከ ሕይወቴ ጠፋ ቀስ በቀስ ጨርሶ... . . . የ ፀሐይ ዉበቷ የፀሐይ ድምቀቷ የዉበት ፍካቷ ዛሬ ላይ ብሸፈን ደመናው ሲገፈፍ ወደጎን ሲበተን.... . . .        ህመም ብርድ ሁኖ ያገረጣው ትናንት        ተንፏቆ እየዳሀ ዛሬን በመጠጋት        አንድ ቀን ልጨምር ብዬ በመኖሬ        ተስፋ ፀሐይ ሁኖ ከች አለልኝ ዛሬ!!                        📆ሚያዚያ 25 - 2016                 ✍ዘይድ ሁሴን @getem @getem @paappii
9699Loading...
02
ያደረግሽኝ በዝቶ.... ልቤን ያሳረረው ጩኸቴን እንዳፍን ምኑን ቀባብቼ ምኑን ልሞሽረው??! ፡ ወልውዬ ሰጥቼሽ አፈር ካለበሽው ጤነኛውን ልቤን መርዝ ካቀመሽው በምን አማርኛ ትህትናን ጠልፌ እንደው እንዲቀልሽ እንዴት ልበል ፅፌ??!! ፡ አንቺ ኮ አታፍሪም ከበደልሽ በላይ በጥሩ አማርኛ ስምሽ ገኖ ቢታይ እንዳ-ላ-ጠፋ እንዳ-ል-በደለ በከንቱ ንፁህ ........ እንዳልገደለ ስጠብቂ ሳይ                    ...... ያመኛል ብትይ!!!! ፡ ነበረኝ ጥሩ ቃል ላንቺ ያላነሰ ከልብ የተቀዳ ስንቱን የቦነሰ የገፋሽው ድሮ .... ቀለለብኝ ያልሽኝ ነበር አማርኛ ንቀሽ ያልሰማሽኝ ከቃሉ ያደረ ... ፍፁም የከበረ ብሰጥሽ ንፁህ ልብ ....... ያኔ ተሰበረ !! እንደሞኝ ቆጥረሽው የተግባሬን ነገር ባልኩት መገኘቴ ላንቺ ቀልድ ነበር ፡ ታዲያ............. ተመልሰሽ ዛሬ ለምን ትይኛለሽ ተነካብኝ ክብሬ ያኔ አቅቶኝ ስቀጣ እያየሽኝ መራቅ እንዴት ይገርምሻል ደስታዬ ሲያድንሽ ፡ ሲሆንብሽ ጭራቅ! ig & tiktok @be_Olyon        ✍️ Olyon                                                   አስተያየት (@be_Olyon)      @getem                    @getem                                   @getem                
2 83011Loading...
03
እሱና እሷ እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣ ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣ ተፈቃቅረው ከርመው ዓመታትን ቆጥረው፣ ጎጆ ለመቀለስ በአንድ ለመጠቅለል ሽማግሌ ልከው፣ ህይወት በአዲስ መልኩ ተጀመረ ይኸው። የአንድ ቀን እይታ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ፣ ሙሽሪት ፀንሳ ቤተሰብ መስርቶ፣ ሁለትነት ቀርቶ በዝተው ተበራክተው፣ ዘር የሚያስቀጥል አዲስ ትውልድ ፈጥረው፣ ባል አክብሮ ሚስቱን ሚስት ለባል ተገዝታ፣ ፍቅርና መቻቻል በእነሱ ላይ ታይታ፣ ለማየት በቅተናል ፍቅራቸው አፍርታ። በሳምሪ የዝኑ ልጅ @getem @getem @getem
4 46437Loading...
04
#ፀሃይና_ጨረቃዬ . . . በራሷ ልክ ለምታውቀኝ የኔን ናፍቆት ያቺን ድሃ፣ ላንዱ ልቤ የልቡ ራ'ብ ሆና ብትፈልቅ የፍቅር ውሃ። ነይ ብሏታል ሰርክ ናፍቆ እዝነ ነፍሴ ተመልክቷት፣ ከሺ ልባም ከሴት መሃል ከቀይ እንቁ እሷን ሽቷት። ትመጣለች እኔን ብላ፤ ትመጣለች ሀሳብ ጥላ፤ የምታውቀው ሩህሩህ መላዕክ በፍቅር ዘንግ እየመራት፣ መቼም እሱ ያውቅበታል፤ ከመጨከን ሳይቀላቅል ልቤ መሃል እሷን 'ሰራት ። ከቆምኩበት ከዚያው ስፍራ፤ ባክሽ ፍጠኝ ድረሽ እያልኩ ከራሴ ጋር ሳጉረመርም፣ ከሀሳብ ባህር የወደቀን ብኩን እኔን ቆሜ ሳርም። መጣችልኝ ያይኔ አበባ መጣችልኝ የልቤ ሰው፣ እንባና ሳግ ወንድ አንጀቴን ቁጡ ፊቴን ሳቅ ወረሰው። ( እኔ የምልሽ ? መቼ ነው ግን፤ ) ( ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ከጥጋብ ደጅ የምደርሰው ? ) እንጃ'ባቴ !!!!! ልብላ አላለች ወይ ልጠጣ፤ ልውረድ የለም ወይም ልወጣ፤ ናፍቆት ሆኖ የሷም ረሃብ ካለም ሁሉ የተለየ፤ ከወንዶቹ አስበልጦ ከህዝበ አዳም እኔን ያለ። ፍቅር  አይኗን ከደነችው፤ ጠፍር አልጋ መሃሉ ላይ ግራ እጄን ተንተርሳው፣ ሙቅ ትንፋሿ እፍፍ ሲለኝ ወንድ አካሌ ነፍሴን ረሳው። አጀብ መቼም ያየሁትን፤ ስትነካካኝ በጣቶቿ ስትዳብሰኝ በመዳፏ፣ ንጉስ መሆን የዛን'ለት "የኔ አባት" ሲለኝ አፏ። በነፍሷ ጫፍ ምኑ ዳሬን የቱ ጋር ነው የነካችኝ፣ የተጣላሁ ከራሴ ጋር በምን ብልሃት አስማማችኝ ? በአርምሞ በፀጥታ፤ አይኗን አየሁ ሽፋሽፍቷን፤ ተመለከትኩ የነፍሷን ሀቅ ተኝታለች አለም ረስታ፣ አንገቴ ስር ካገኘችው ስስ ህይወቷን ተጠግታ። የዛን'ለታ........ እያለ እያለ እያለ "ልሂድ" አለኝ፤ እኛን ሲያዩ የፈገጉ ሰማይ ምድር ተላቀቁ፤ በመሄድ ውስጥ ተከርችመው ነገን ሊሉ ሲታረቁ። እቅፍ ብርሃን ፈነጠቀ ከአፅናፍ አፅናፍ ተዘረጋ፣ ፀሃይና ጨረቃዬን፤ በአክናዴ እንዳቀፍኳት ሆነ አዲስ ቀን ሌቱ ነጋ። . . . "አይኗን ገልጣ አይኔን አየች ከኔ ማዶ የራሷን ሀቅ፣ ፈገግ ብላ አዋሰችኝ የሰጧትን የ'ግዜሯን ሳቅ።"                                   ስትችልበት !!!!!! ✍ ዓቢይ ( @abiye12 ) @getem @getem @getem
5 46956Loading...
05
ረዘምዘሜ -------------- ይወድሻል ቢሉሽ ጸሀይ ትገባለች ቢሉሽ በስተምስራቅ፣ ውሸት ነው በያቸው፣ ከነሱ በመራቅ፡፡ ምድር ጠፍጣፋ ነች፣ ቢሉሽም መልሰው፣ ሀሰት ነው በያቸው፣ ሳትቆጥሪያቸው ከሰው፡፡ አውራ ዶሮ እንቁላል ይጥላል በማለት አጉል ቢሞግቱሽ፣ ቅጥፈት ነው በያቸው፣ የማይሆን ቢግቱሽ፡፡ ጽጌረዳ አበባን፣ ቢሉሽ ይች አደይ ናት፤ ሀቅ አይደል በያቸው፣ ትጊና በጽናት፡፡ ይሆናልም ቢሉሽ ሰው እያደር እሸት፣ ብለሽ አጋልጫቸው--- ‹‹አቤት! አቤት ውሸት! ›› ከኤሊና ጥንቸል፣ ቢሉሽ ኤሊ ፈጣን፣ ቀላማጅ! በያቸው፣ ተሞልተሸ በሥልጣን፡፡ ይህ ሰው አስር ሺ ዐመት፣ የሚኖር ነው ቢሉሽ ያለቅንጣት እፍረት፣ ይህ እውነት አይደለም፣ በያቸው በድፍረት፡፡ በዙ ውሸት ዋሽተው፣ ግን ቢሉሽ አንችዬ፣ ‹‹ፍቅሬ ይወድሻል ከነፍሱ አስበልጦ!›› አንዳች ሳታመነች ‹‹እውነት ነው!›› በያቸው፣ ድምጽሽን ከፍ አርገሽ ፣ ሰምተሸ በተመስጦ፡፡ 4/30/2017 By fikre tolosa @getem @getem @paappii
4 79735Loading...
06
ሙሾ አውራጅ እንባ አርጋፊ ምሬት ዘሪ ሞት አቃፊ ደስታ ማላቅ ሐዘንተኛ ሁሌ አልቃሽ ብሶተኛ ግና ዛሬ ድቅድቅ ጥሼ እንባ ላፈስ በመንገድ ላይ ስንከላወስ ድንገት ቆመ የቅጽሩን ጥግ እግሬ ታኮ ይጸልያል ምዕመኑ ተንበርክኮ አሰገግኩ ወደ ውስጥ አማተርኩ አጮልቄ ምን ልተንፍስ? ... ምን አውቄ? ምስጋና እንደው አልለመደኩ በዝምታ አለቀስኩ {ለቅሶ አይደል የለት ጉርሴ? ምሬት አይደል እስትንፋሴ?} እመቤቴ በእንባ መሐል አየሁ ምስልሽን ስታጫውች ውብ ልጅሽን በዛች ቅጽበት ተሰለበ ሹል ብሶቴ ተገፈፈ ጽልመት ፊቴ ልቤ ጠጣ ከእቅፍሽ ሀሴት ቀድቶ እንኳን እኔ ሐዘን ሳቅ አንቺን አይቶ #ኤልዳን @eldan29 @getem @getem @getem
6 36846Loading...
07
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ። ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ! @seiloch @seiloch
7 0823Loading...
08
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ። ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ! @seiloch @seiloch
7 4311Loading...
09
ድብልቅልቅ ነው ውስጡ ውልቅልቅ ነው ጌጡ .... ሰባራ ነው ውበት  ጥቁር አለው የኛ ሽበት! ወጣት ነው የጠገበ ነበልባል ነው የረገበ መዳፍ ነው የማይሞላ ፍቅር አለን የሚያባላ ! ሰላም ነው የሚረብሽ ንፁህ ነው የሚቆሽሽ መሬት ነው ሁሉንም ቻይ እያኖረ ገዳይ! ሰፊ ነው ገፀ ብዙ ጠባብ ነው ፅንስ ሙሉ በቂ ነው ቻይ ተራፊ ለ'ኔ ና አንቺ ሰፊ! ባህር ነው ሞገደኛ ሃይቅ ነው ሰላምተኛ አለም ነው ዥንጉርጉሩ አንጀት ነው ለኛ ሩሩህ! ፍቅር ነው ፍፁም ልዩ!!     Follow my IG & Tiktok @be_Olyon        ✍️ Olyon                                                   አስተያየት (@be_Olyon)      @getem                    @getem                                   @getem
7 73934Loading...
10
ሲያምርብሽ ቀሚስ ጥልፉ ሲያምርብሽ ነጭ በነጩ ህፃናቶች ከእግርሽ ስር ተኮላትፈው የሚንጫጩ እረበሹሽ ከጸሎትሽ የዳዊቱን ቦታ አጣሽ? እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ ቤተመቅደስ ምን አመጣሽ? ከመልክሽ ላይ ይታየኛል የአብ እጁ ልዕልና በሁዳዴ ቤቱ መጣሽ ጌታን ልትይ ሆሳዕና? ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ንጉስ አየን ከድንግል ሴት ፀሀይ ወጣ ከአርያም ከቅዳሴው ዜማ ሰማን መንበር መሃል እጣን ጨሰ ህዝበ እስራኤል ጨርቁን ሁሉ እመሬት ላይ አለበሰ የምስጋናው ዜማ ጦፈ መንፈስ ቅዱስ ህዝቡን መላ በወንጌሉ ክብር አገኘች የያዘችው ውርንጭላ ህዝቡ ሞልቷል ከመቅደሱ ወንዱም ሴቱም ለየብቻ በነጠላ ተሸፍነሽ ምትታዪኝ አንቺ ብቻ ከአጠገብሽ ጎልማሳ ሴት ሲደገፉሽ ማትከፊ የደከማት አራስ እናት ልጇን ይዘሽ የምታቅፊ በነጠላ የሚያምር ገጽ ለመንካትም የሚያሳሳ ጸጉርሽን ሸፍነሻል ዋናው ነገር ፊትሽሳ? ላለማየት እጥራለው ነጣላሽን ስታጣፊ ወዴት ላርገው ይዤ ቆምኩኝ የዘንባባ ዝንጣፊ ምን ላድርገው ዘንባባውን ? መስቀል ልስራ ለግንባርሽ ከብልጭልጭ ከወርቅ አልማዝ መስቀሉ ነው ሚያሳምርሽ በቢጫዋ ዘምባባስ ግን አይኔ አይቶ ከመረጣት ቀለበትን ልስራ ይሆን ለእጆችሽ ሰልካካ ጣት? በአራቱም መአዘናት ተነበበ ወንጌል ለአለም ምህላችን ይቀጥላል እስኪመጣ ለዘላለም አንድ ሳምንት የፆም ስግደት ህማማቱ ሊጠብቀን ከበሮውን ሰማይ ሰቅለን አመስግነን ለአንድ ቀን ከመድረኩ ነጭ ለብሰው ከበሮውን እየመቱ ክብ ሰርተው ሲዘምሩ እንደያኔው ህፃናቱ ምን ተሰማሽ በድምቀቱ አይኔ ካንቺ ተመልክቷል ጠብታ ውሃ የምታክል ዘለላ እንባ ከአይንሽ ወቷል ለምን አዘንሽ በደስታ ቀን ይታወቃል የልቦናሽ   ንጽህና የእግሮችሽን ጣቶች ላንፃ ፀሎተ ሀሙስ ይድረስና? አትፈልጊም አውቃለሁኝ እንኳን ማጠብ እንዲያዩሽም የኤደን ውስጥ በለስ እንጂ የዱር ኮሽም አይደለሽም ታዲያ ያለሙን ጣጣ ረስቶ ልቤ ሰከን ከሚልበት እንዲታወክ ቤተ መቅደስ ባትመጪ ምን አለበት? ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ንጉስ አየን ከድንግል ሴት ፀሀይ ወጣ ከአርያም የገላውን ስጋ ቆርሰው በቀናት ውስጥ የሚገሉት ጨርቃቸውን አገላድመው በእልልታ ተቀበሉት የኛ ህዝብም ደምቋል ዛሬ መስቀል ሰርቷል ከመረጠው ጎልጎታ ላይ እስኪሰቀል ወዳጅ ስሞ እስኪሸጠው የኔ ግና ተበጥሷል የአይኔ ላይ መቀነቻ ከዚህ ሁሉ ተነጥለሽ ምትታዪኝ አንቺ ብቻ ምናለበት ባገለግል ቤተመቅደስ ሌላ አላጣሽ እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ እኔ ደብር ምን አመጣሽ? By @mikiyas_feyisa @getem @getem @paappii
7 945108Loading...
11
▪️▪️አባቴ▪️▪️▪️ ምተማመንብህ ምኮራብህ አባዬ ስወድቅ ምታነሳኝ የኔ መከታዬ ለቤትህ ምሰሶ ትከሻህ ጠንካራ ለልጆችህ ስትል ሳትደክም ምትሰራ። : : ፍቅርህን ሳትሰስት ሰጥተህ ያሳደከኝ መልካም ሰው መሆንን ለኔ ያስተማርከኝ አባቴ ውለታህ እጅጉን ብዙ ነው ከማመስገን በቀር ሌላ ምን እላለው። : : ምፈልገው ቢኖር ታላቁ ምኞቴ ደስታህን ማየት ነው ሳለው በህይወቴ አባቴ አድምጠኝ ስማኝ ይሄን ስልህ በጣም ወድሀለው እኔ ያንተ ልጅህ። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 33080Loading...
12
..... እሱ እኮ.. እያሉ ባሞገሱህ ቁጥር፤ አንተን እያነሱ ባወደሱህ ቁጥር፤ ልብህን አይሙቀዉ ፍፁም ደስ አይበልህ፤ ቀን የከፋ ለታ......... ቁልቁል ይጥሉሃል....... እላይ የሰቀሉህ። ...................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
6 78838Loading...
13
ጊዜ ደጉ 🕔 ሰው ከኔ ሲለየኝ ያመንኩት ሲርቀኝ መሄጃው ሲጨንቀኝ ፍረሀት እምነቴን እየሸረሸረ እንዴት እሆን ብዬ እሰጋ ነበረ : : : ለካ ጊዜ ደጉ ለሁሉም ይደርሳል እምባዎች ያብሳል ቁስል ይፈውሳል ፈጠነም ዘገየም መከራን ያስረሳል። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 31075Loading...
14
ልማድ ቢሆንብን ቃሉ ከአፋችን "እንዴት ነህ?" ስንባል ደህና ነው መልሳችን ለሰው የማይነግሩት ቢሆን ታሪካችን ይሸሸግ ጀምሯል በሶስት ፊደላት ጥልቁ ህመማችን :- "እንዴት ነህ?" :- ደህና ነኝ!! በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr @getem @getem @getem
7 69176Loading...
15
ጥላሞት (shadow) አንድ ጥያቄ አለ ነብሴን ሁልግዜ የሚያብሰለስላት ገሀድ የማይገልጠው ማነው የኔ ጠላት? ማነው እንቅፋቴ ጉድባ ለመንገዴ ሌላ አካል አለ ወይስ ክፉ ገዴ? ማነው ከነብሴ ጋር ያረገኝ ባላንጣ ህዋው ነው ጠላቴ ወይስ ክፉ እጣ? ጀርባዬን ለህልሜ ማነው ያሰጠኝ ሰብ ወይስ አቅቶኝ ነው ተስኖኝ ነው ማሰብ? ማነው ማነው ማነው? በዳይ ስጋ ችሮኝ 'ሚያስረግም ዕለቴን ሬት ሆኖ ኑሮ 'ሚያስናፍቀኝ ሞቴን ማነው ማነው ማነው? ስደምር ስቀንስ ስመትር ስለካ እኔ ፊት የቆምኩት ራሴው ነኝ ለካ። ይሄን ያወቅሁኝ ቀን ይሄ የገባኝ 'ለት ፊት የቆመው እኔን ገለል አረግሁለት። አሁን ጸሐይ ወጣ። ✍️©እስራኤል @AdamuReta @getem @getem @getem Inspiration(ንሸጣ) : psychological podcast about self sense and shadow
8 92634Loading...
16
እዉነት እንዳይመስልሽ . . ዛሬ ......ምን ብትደምቂ፤ ከቆነጃጅቱ እጅጉን ብትልቂ፤ ኑሮ ተመችቶሽ ያ.... ፊትሽ ቢወዛ፤ ወደድኩሽ የሚለዉ አፍቃሪሽ ቢበዛ ፤ ሴትነትሽ ማለት... መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ፤ አንቺን ሳያማክር........ የጠቆረዉ ፀጉርሽ.. በሽበት ይተካል፤ ጸአዳዉም መልክሽ በፍጥነት ይረግፋል፤ ሴትነትሽ ማለት መልክ ከመሰለሽ፤ ፍፁም አትመኪ እዉነት እንዳይመስልሽ። .......................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
7 41775Loading...
17
ትናንትና ጠዋት ፀሐይ የመሰለች ቆንጆ ልጅ አይቼ በሊቀ መልዓኩ እንዴት ምታምሪው አልኩኝ ድምፅ አውጥቼ ትንሽ ኮራ እያለች ጥቂት ፈገግ ብላ አለችኝ "ከላይ ነው" ባለቤቱ የፈራው "ዉስጥሽ"ስ እንዴት ነው ?                   ዘረ-ሠናይ @SenayArt @getem @getem @paappii
7 25344Loading...
18
ሀገር ስጠኝ... ሀገር ስጠኝ እስቲ ወዳጄ ማለት ሚያስችለኝ ''እዛ ሄጄ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ" ሀገር ስጠኝ የምኮራበት መልስ የሌላቸው እንቆቅልሾች የማይበዙበት ግራ ሲገባኝ ምን አውቄልህ ማልባልበት እስቲ ሀገር ስጠኝ አንድ ትልቅ ከሰፈር ጎሳ ከብሄር ሚልቅ ሀገርን ስጠኝ ሰላም ያለበት ሰው ለፍቶ ሰርቶ የሚያተርፍበት ካለሰቀቀን የሚኖርበት:: 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 70637Loading...
19
እኔ እንደናፈቅኩሽ ታውቂያለሽ አውቃለሁ አንቺ ሌላ ወደሻል ሌላ ተላምደሻል አዎን ሰምቻለሁ የሰማሁት ነገር ሀሰት ይሁን ብዬ አምላክ ለምኛለሁ ሻማውን ለኩሼ ጧፍ እያበራሁኝ ተማፅኘዋለሁ አንቺን ያጣሁ ዕለት ጠፍቷል የኔ ብርሃን እንደ አምላክ ስቅለት ያውም በእኩለ ቀን ይሄን ሁሉ መዓት እያየሽው ባይንሽ  ነገ የተሻለ ነው ለምን ትይኛለሽ ? የኔ ፀሐይ ትናንት ማለፉን እያየሽ የኔ ጀንበር አንቺ መሆንሽን እያወቅሽ ? በርግጥ ነገ እንዳለ በልቤ አምናለሁ ቀኑ መሽቶ ይነጋል ይህንን አውቃለሁ ግን ታውቂያለሽ አንዳንዴም የ ጀንበር መውጣቷ ሌሊት አያነጋም ጎህ መቅደዱ ብቻ ጨለማ አያጠፋም በትር የያዘ ሁሉ ባህሩን አይከፍልም ባለ ወንጭፍ ሞልቶ ጎልያድን አይጥልም ገባኦን ካልሆነ አትቆምም ፀሐይም አንቺ የሌለሽበት ሁሌ ጨለማ ነው ጀንበር ባትጠልቅም                         ዘረ-ሠናይ                @SenayArt @getem @getem @getem
8 51780Loading...
20
የትኛው ነሽ አንቺ ፀደይ ነሽ መስከረም ? ግማሽ መልክሽ አደይ ግማሽ መልክሽ አረም። ግማሽ የሚቀጠፍ ግማሽ የሚነቀል ፣ የትኛውን ልመን ምንሽን ልቀበል፤ የተኛው ነሽ አንቺ ምህረት ወይስ በቀል? ስምዖንን መስለሺኝ መስቀሌን ስትይዢ ለአንድ ሠሞን ፍዳ፣ በየት ዞረሽ ሸጥሽኝ ለብቻ መከራ ደግሞ እንደ ይሁዳ። ✍️©እስራኤል    (@AdamuReta) @getem @getem @getem
8 67477Loading...
21
🗣የሰው ወሬ🗣 መቼም ቢሆን ላይቆም ነገር ምን ብትሰራ ላይቀየር ላያስገኝህ ትንሽ ፍሬ ጆሮ አትስጠው ለሰው ወሬ። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 56154Loading...
22
ትናንትና ማታ እጅጉን ናፍቀሽኝ ያ ክፉ ትዝታሽ አላስተኛህ ብሎኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስምሽን ጠራሁኝ እንደ ደብተራ አስማት እንደ ጴጥሮስ ክህደት በአንዴ ባይሆንልኝ ሶስቴ ደጋገምኩት ሰልስቱም አልሆነ ሃያ አንዴ ጮኬ በማርያም ለመንኩኝ አርባ አንድ አድርጌ ኪሪያላየሶን አልኩኝ ጠራሁሽ በናፍቆት ጠራሁሽ በፍቅር ወይ አንቺ ነይልኝ ወይ ትዝታሽ ይቅር                    ዘረ-ሠናይ                 @SenayArt @getem @getem @getem
8 363110Loading...
23
አምላኬ ባትረዳኝ ብትከዳኝ እንደሰው  ሀጥያቴን ብትቆጥር በደሌን ብትጠቅሰው እንኳንስ በአንተ ዘንድ አልመችም ለሰው ክፋት ያገረሸ ተንኮል ያጠለሸ ሰውነት አዝዬ ከፊትህ ቆሜያለሁ ዛሬም ማረኝ ብዬ ምን ይሆን ምላሽህ አልልም በአንተ ፊት አውቀዋለሁኛ!! ባትምረኝ ከጥፋት ባታወጣኝ ከመዓት አልኖርም አንድ ቀን እንኳንስ ለአመታት። BY፦LIONEL YOHANNES @getem @getem @paappii
7 63070Loading...
24
( አትፍረድ ... ) ============== እኔ ድንግሉ ሰው ትዕዛዙን ልሽር ስወድቅ ከአልጋ ገዳም ገባች አሉኝ ዘማይት ያልኳት ሴት .. አምላኳን ፍለጋ እንዲያ የረገምኳት እንዲያ ያሻሟጠጥኳት ድንጋይ ተንተርሳ ስትጸልይ ለኔ ሞኙ ከዓለም ገባሁ ለበደል መስዋእት ለኃጢአት ምናኔ ግዴለም ምን ቢከብድ ፍጻሜህን ሳታይ አትፍረድ ወገኔ !!!! By @Kiyorna @getem @getem @paappii
8 01547Loading...
25
ወሰን አልባው ደግነሽ ለካ ልክ ኖሯል ሞኝነሽ የዛሬ መሳዩ አዋቂ መነሻ ነጥቡን ናቂ ገፁ ሲታይ ጥበበኛ ለራሱ ከራሱ ጠበኛ By yidne @getem @getem @getem
7 20317Loading...
26
.     👄አፍና ልብ❤️ 🙅‍♂ አፌን አትመኝው አንዳንዴ ይዋሻል 🤥 በመግደርደር ብዛት እውነትን ያሸሻል ❤️ ልቤ ግን ሞኝ ነው ትንሽ ብትቀርቢው             ሁሉም ይታይሻል 💓ከሌላ አብልጦ አንቺን እንደሚወድ          በደንብ ይነግርሻል።❤️‍🔥 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 811104Loading...
27
ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤ ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤ የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤ መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤ ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤ ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤ ይድረስልኝ ላንቺ......... ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤ ምን ፅልመት ቢከብሽ፤ ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤ አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል። ............................................. በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
8 42865Loading...
28
የማይጨንቀው ሲጨንቅ... (በሳሙኤል አለሙ . በኩለ ቀንን አይባል በኩለ ሌሊቱ አይባል ሀብታም የውስኪ ፅዋውን ሲያጋጭ ድሃ የቋጠረውን ዕንባውን ሲራጭ "ተፈፀመ" ተብሎ ታይቶ ለሚጠፋው ያፈጣል ከኩርሲው ያፈጣል ከሶፋው . አንተስ ላይባሉት... በኖረበት ሲያዝን በኖረበት ሲደሰት መልሶ መላልሶ ድራማው ህይወቱን አይቶ ጨርሶ በድራማው ዓይኑ ቀልቶ ዓይኑን ያሻል ይቀጥላልን ሲጠባበቅ ውሎ ያመሻል ።።።።። ሳሙኤል አለሙ @Samuelalemuu @getem @getem
8 54610Loading...
29
ስሚኝ እህቴ ሲያንቋሽሹሽ---- አርገው አሳሳች ሲያስቀምጡሽ-----ከሰው በታች ፊት ሲነሱሽ----- ስታዪአቸው ሲያጣጥሉሽ----- በቃላቸው በዝምታ ንቀሽ አልፈሽ በፈገግታሽ ግረፊያቸው:: 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 35465Loading...
30
ስማኝ ወዳጄ ሲያንቋሽሹህ--- አርገው አሳሳች ሲያስቀምጡህ---- ከሰው በታች ፊት ሲነሱህ---- ስታያቸው ሲያጣጥሉህ---- በቃላቸው በዝምታ ንቀህ አልፈህ በፈገግታህ ግረፋቸው:: 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 05938Loading...
31
ይድረስልኝ ላንቺ ቀንሽ ለጨለመ፤ ልብሽ ለሚያነባ ዉስጥሽ ለታመመ፤ የመኖርሽ ዉሉ የህይወትሽ 'ጣሙ፤ መሪር ለሆነብሽ ሳይገባሽ ትርጉሙ፤ ይድረስልኝ ላንቺ ተስፋን ለቆረጥሽዉ፤ ከራስሽ ተጣልተሸ ሞት ለተመኘሽዉ፤ ይድረስልኝ ላንቺ......... ምን ድቅድቅ ቢዉጥሽ ፤ ምን ፅልመት ቢከብሽ፤ ሌቱም ይገፍና ደግሞ ይነጋጋል፤ አሮጌዉ ያልፍና 'ባዲስ ቀን ይተካል። ............................................. በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem
7 84559Loading...
32
🤫🤫ዝምታ🤐🤐 🚫🧠ካላዋቂ ወሬ 🚫💶ከሌለበት ፍሬ፣ 🚫🕐ጊዜን ከሚገድለው፣ 🚫📚እውቀት ከማይሰጠው፣ 🤥🗣ከውሸት ጋጋታ፣ 👍🤐 ይበልጣል ዝምታ። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
8 96378Loading...
33
▪️▪️የውሸት ብርሀን🔸🔸 ዙሪያክ ገደል ቢሆን መሄጃው መንገዱ ያመንካቸው ሰዎች አንተኑ ቢከዱ ተንዶ ቢከስም የነበረክ ተስፋ ያካበትከው ሀብትህ በሙሉ ቢጠፋ አዝነህ እየተከፋ ድቅድቁ ጨለማ ዙሪያህን ሲከበው መውጫ ቀዳዳህን ጨንቆህ ስትፈልገው ድንገት ምታያቸው ብርሀኖች ሁሉ እንዳያታልሉክ ተስፋ እየመሰሉ: : ምክኒያቱም ካላየኸው በቀር በጥሩ እይታ የጅቦችም አይን ያበራል በማታ::   📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
9 77395Loading...
34
💗❤️ወድሻለው💗❤️ ወ - ወደኔ ተራምደሽ ቆመሽ ካጠገቤ ድ - ድንገት አይኔ አይቶሽ ሲደነግጥ ልቤ ሻ - ሻል እንዳለኝ ወዲያው ከጎንሽ እንዳለው ለ - ለመናገር ሀቁን አይንሽን እያየው ው - ውስጤን አሳወኩሽ ብዬ ወድሻለው።          :          : 🎈 ወንዶች ለምትወዷት ሴት ላኩላት   📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
11 541172Loading...
35
💗❤️ወድሀለው💗❤️ ወ - ወደኔ ተራምደህ ቆመህ ካጠገቤ ድ - ድንገት አይኔ አይቶህ ሲደነግጥ ልቤ ሀ - ሀሳቤን ሰብስቤ ከጎንህ እንዳለው ለ - ለመናገር ሀቁን አይንህን እያየው ው - ውስጤን አሳወኩህ ብዬ ወድሀለው።          :          : 🎈 ሴቶች ለምትወዱት ወንድ ላኩለት    📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
10 727149Loading...
36
..........ፍቅር እንደ Icarus....... ካልጠፋ ከዋክብት ካልጠፋ ጨረቃ ፀሐይን መዉደዴ ፍቅርሽ አሸንፎኝ ተፈጥሮን ስታገል ላውልሽ ከክንዴ ስቀርብሽ ብቃጠል ስጠጋሽ ብነድድ ፍቅር ሆነበትና ቢችልልኝ ሆዴ ተቃጥዬም ቢሆን ከእቅፍሽ ልደር አትከልክይኝ ዉዴ ህልሜ አንቺን ማቀፍ ነው ሞቼም ቢሆን ነይ ልሳምሽ አንዴ                    ዘረ-ሠናይ            @Prince_Zeresenay @getem @getem @getem
9 26842Loading...
37
🤰ውዷ እናቴ🤰 ሲከፋኝ ሚከፋሽ ስስቅ የምትስቂ ስሳሳት ምትመክሪኝ አንቺ የኔ አዋቂ የአምላክ ስጦታ ለአንዷ ህይወቴ ምን ይውጠኝ ነበር ያላንቺ እናቴ : : ጓደኛ ወዳጄ ከኔ ማትርቂ ጉዳዬን ማዋይሽ ሚስጥሬን ጠባቂ በማንም በምንም መተኪያ የሌለሽ በደስታ ኑሪልኝ ሳለሽ በህይወትሽ ሁሌም ወድሻለው እኔ ያንቺ ልጅሽ:: 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝        ✍️ @BEGITIMENAWGA @getem @getem @getem
10 245139Loading...
38
ሞት . ያ....ክፉ ነጣቂ፤ ከሥጋ ለይቶ እስትንፋስ ፈልቃቂ፤ ወሳጅ መልአከ ሞት በሰዎች ጀርባ ላይ፤ ተንጠልጥሎ ሚኖር በእድሜ ገደብ ጣይ፤ ቀናትና ወራት በቀመር ሲለኩ፤ ወራትና አመታት ፈጥነዉ ሲተካኩ፤ የሰዉ ልጅ ማለፊያዉ፤ የእስትንፋሱ ማብቂያው ፤ ከአይን ጥቅሻ እጅጉን ይቀርባል፤ ከአፈር እንደመጣ ከአፈር ይከተታል። ..................................................... በዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
10 39639Loading...
ማያልፍ የመሰለኝ ዳምኖ ህይዎቴ ባዘነብኩት እንባ ታጥቦ ማንነቴ ግርዶሹ በርትቶ ነገየን ጋርዶብኝ ፍፁም አንዳልጓጓ ህመም በርትቶብኝ ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሞቴን ሲጠባበቅ ህመሜን ሳዳምጥ ስሜቶቼን ሳረቅ . . .          መኖር ማለት ስቃይ          መኖር ምለት ህመም          መኖር ማለት ጭንቀት          መኖር ማለት ድካም.... ወደ ተስፋ መንደር እልፍ ጊዜ ባመራ የ እድሌን ልሻማ ከ እኩዮቼ ጋራ ብፈልግ... ብጠብቅ ድርሻ የለኝ ሁኖ ጠብታ እንኳን ሳይቀር ከ እኔነቴ ተኖ ፀሐይ የለኝ ሁና ሕይዎቴ ዳምኖ . . .        ትላንት በመኖሬ ተስፋ እንኳን ሳይኖረኝ        ምንም ያህል ባዝን የሚያልፍ ባይመስለኝ        ቀን እየቆጠረ ቀን እየጨመረ        የደመናው ጥቁረት መጠኑ ቀንሶ        የስቃይ ዉርጅብኝ ከነበረው አንሶ        ከ ሕይወቴ ጠፋ ቀስ በቀስ ጨርሶ... . . . የ ፀሐይ ዉበቷ የፀሐይ ድምቀቷ የዉበት ፍካቷ ዛሬ ላይ ብሸፈን ደመናው ሲገፈፍ ወደጎን ሲበተን.... . . .        ህመም ብርድ ሁኖ ያገረጣው ትናንት        ተንፏቆ እየዳሀ ዛሬን በመጠጋት        አንድ ቀን ልጨምር ብዬ በመኖሬ        ተስፋ ፀሐይ ሁኖ ከች አለልኝ ዛሬ!!                        📆ሚያዚያ 25 - 2016                 ✍ዘይድ ሁሴን @getem @getem @paappii
Show all...
17👍 2
ያደረግሽኝ በዝቶ.... ልቤን ያሳረረው ጩኸቴን እንዳፍን ምኑን ቀባብቼ ምኑን ልሞሽረው??! ፡ ወልውዬ ሰጥቼሽ አፈር ካለበሽው ጤነኛውን ልቤን መርዝ ካቀመሽው በምን አማርኛ ትህትናን ጠልፌ እንደው እንዲቀልሽ እንዴት ልበል ፅፌ??!! ፡ አንቺ ኮ አታፍሪም ከበደልሽ በላይ በጥሩ አማርኛ ስምሽ ገኖ ቢታይ እንዳ-ላ-ጠፋ እንዳ-ል-በደለ በከንቱ ንፁህ ........ እንዳልገደለ ስጠብቂ ሳይ                    ...... ያመኛል ብትይ!!!! ፡ ነበረኝ ጥሩ ቃል ላንቺ ያላነሰ ከልብ የተቀዳ ስንቱን የቦነሰ የገፋሽው ድሮ .... ቀለለብኝ ያልሽኝ ነበር አማርኛ ንቀሽ ያልሰማሽኝ ከቃሉ ያደረ ... ፍፁም የከበረ ብሰጥሽ ንፁህ ልብ ....... ያኔ ተሰበረ !! እንደሞኝ ቆጥረሽው የተግባሬን ነገር ባልኩት መገኘቴ ላንቺ ቀልድ ነበር ፡ ታዲያ............. ተመልሰሽ ዛሬ ለምን ትይኛለሽ ተነካብኝ ክብሬ ያኔ አቅቶኝ ስቀጣ እያየሽኝ መራቅ እንዴት ይገርምሻል ደስታዬ ሲያድንሽ ፡ ሲሆንብሽ ጭራቅ! ig & tiktok @be_Olyon        ✍️ Olyon                                                   አስተያየት (@be_Olyon)      @getem                    @getem                                   @getem                
Show all...
👍 23 8
እሱና እሷ እሱና እሷ ከአንድ ቀን እይታ፣ ወዳጅነት ፈጥረው ፍቅር ተገንብታ፣ ተፈቃቅረው ከርመው ዓመታትን ቆጥረው፣ ጎጆ ለመቀለስ በአንድ ለመጠቅለል ሽማግሌ ልከው፣ ህይወት በአዲስ መልኩ ተጀመረ ይኸው። የአንድ ቀን እይታ ዛሬ ፍሬ አፍርቶ፣ ሙሽሪት ፀንሳ ቤተሰብ መስርቶ፣ ሁለትነት ቀርቶ በዝተው ተበራክተው፣ ዘር የሚያስቀጥል አዲስ ትውልድ ፈጥረው፣ ባል አክብሮ ሚስቱን ሚስት ለባል ተገዝታ፣ ፍቅርና መቻቻል በእነሱ ላይ ታይታ፣ ለማየት በቅተናል ፍቅራቸው አፍርታ። በሳምሪ የዝኑ ልጅ @getem @getem @getem
Show all...
43👍 18👎 2🔥 1🎉 1
#ፀሃይና_ጨረቃዬ . . . በራሷ ልክ ለምታውቀኝ የኔን ናፍቆት ያቺን ድሃ፣ ላንዱ ልቤ የልቡ ራ'ብ ሆና ብትፈልቅ የፍቅር ውሃ። ነይ ብሏታል ሰርክ ናፍቆ እዝነ ነፍሴ ተመልክቷት፣ ከሺ ልባም ከሴት መሃል ከቀይ እንቁ እሷን ሽቷት። ትመጣለች እኔን ብላ፤ ትመጣለች ሀሳብ ጥላ፤ የምታውቀው ሩህሩህ መላዕክ በፍቅር ዘንግ እየመራት፣ መቼም እሱ ያውቅበታል፤ ከመጨከን ሳይቀላቅል ልቤ መሃል እሷን 'ሰራት ። ከቆምኩበት ከዚያው ስፍራ፤ ባክሽ ፍጠኝ ድረሽ እያልኩ ከራሴ ጋር ሳጉረመርም፣ ከሀሳብ ባህር የወደቀን ብኩን እኔን ቆሜ ሳርም። መጣችልኝ ያይኔ አበባ መጣችልኝ የልቤ ሰው፣ እንባና ሳግ ወንድ አንጀቴን ቁጡ ፊቴን ሳቅ ወረሰው። ( እኔ የምልሽ ? መቼ ነው ግን፤ ) ( ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ስሜሽ ከጥጋብ ደጅ የምደርሰው ? ) እንጃ'ባቴ !!!!! ልብላ አላለች ወይ ልጠጣ፤ ልውረድ የለም ወይም ልወጣ፤ ናፍቆት ሆኖ የሷም ረሃብ ካለም ሁሉ የተለየ፤ ከወንዶቹ አስበልጦ ከህዝበ አዳም እኔን ያለ። ፍቅር  አይኗን ከደነችው፤ ጠፍር አልጋ መሃሉ ላይ ግራ እጄን ተንተርሳው፣ ሙቅ ትንፋሿ እፍፍ ሲለኝ ወንድ አካሌ ነፍሴን ረሳው። አጀብ መቼም ያየሁትን፤ ስትነካካኝ በጣቶቿ ስትዳብሰኝ በመዳፏ፣ ንጉስ መሆን የዛን'ለት "የኔ አባት" ሲለኝ አፏ። በነፍሷ ጫፍ ምኑ ዳሬን የቱ ጋር ነው የነካችኝ፣ የተጣላሁ ከራሴ ጋር በምን ብልሃት አስማማችኝ ? በአርምሞ በፀጥታ፤ አይኗን አየሁ ሽፋሽፍቷን፤ ተመለከትኩ የነፍሷን ሀቅ ተኝታለች አለም ረስታ፣ አንገቴ ስር ካገኘችው ስስ ህይወቷን ተጠግታ። የዛን'ለታ........ እያለ እያለ እያለ "ልሂድ" አለኝ፤ እኛን ሲያዩ የፈገጉ ሰማይ ምድር ተላቀቁ፤ በመሄድ ውስጥ ተከርችመው ነገን ሊሉ ሲታረቁ። እቅፍ ብርሃን ፈነጠቀ ከአፅናፍ አፅናፍ ተዘረጋ፣ ፀሃይና ጨረቃዬን፤ በአክናዴ እንዳቀፍኳት ሆነ አዲስ ቀን ሌቱ ነጋ። . . . "አይኗን ገልጣ አይኔን አየች ከኔ ማዶ የራሷን ሀቅ፣ ፈገግ ብላ አዋሰችኝ የሰጧትን የ'ግዜሯን ሳቅ።"                                   ስትችልበት !!!!!! ✍ ዓቢይ ( @abiye12 ) @getem @getem @getem
Show all...
👍 25 20🔥 3
ረዘምዘሜ -------------- ይወድሻል ቢሉሽ ጸሀይ ትገባለች ቢሉሽ በስተምስራቅ፣ ውሸት ነው በያቸው፣ ከነሱ በመራቅ፡፡ ምድር ጠፍጣፋ ነች፣ ቢሉሽም መልሰው፣ ሀሰት ነው በያቸው፣ ሳትቆጥሪያቸው ከሰው፡፡ አውራ ዶሮ እንቁላል ይጥላል በማለት አጉል ቢሞግቱሽ፣ ቅጥፈት ነው በያቸው፣ የማይሆን ቢግቱሽ፡፡ ጽጌረዳ አበባን፣ ቢሉሽ ይች አደይ ናት፤ ሀቅ አይደል በያቸው፣ ትጊና በጽናት፡፡ ይሆናልም ቢሉሽ ሰው እያደር እሸት፣ ብለሽ አጋልጫቸው--- ‹‹አቤት! አቤት ውሸት! ›› ከኤሊና ጥንቸል፣ ቢሉሽ ኤሊ ፈጣን፣ ቀላማጅ! በያቸው፣ ተሞልተሸ በሥልጣን፡፡ ይህ ሰው አስር ሺ ዐመት፣ የሚኖር ነው ቢሉሽ ያለቅንጣት እፍረት፣ ይህ እውነት አይደለም፣ በያቸው በድፍረት፡፡ በዙ ውሸት ዋሽተው፣ ግን ቢሉሽ አንችዬ፣ ‹‹ፍቅሬ ይወድሻል ከነፍሱ አስበልጦ!›› አንዳች ሳታመነች ‹‹እውነት ነው!›› በያቸው፣ ድምጽሽን ከፍ አርገሽ ፣ ሰምተሸ በተመስጦ፡፡ 4/30/2017 By fikre tolosa @getem @getem @paappii
Show all...
18👍 17🔥 2😁 1🤩 1
ሙሾ አውራጅ እንባ አርጋፊ ምሬት ዘሪ ሞት አቃፊ ደስታ ማላቅ ሐዘንተኛ ሁሌ አልቃሽ ብሶተኛ ግና ዛሬ ድቅድቅ ጥሼ እንባ ላፈስ በመንገድ ላይ ስንከላወስ ድንገት ቆመ የቅጽሩን ጥግ እግሬ ታኮ ይጸልያል ምዕመኑ ተንበርክኮ አሰገግኩ ወደ ውስጥ አማተርኩ አጮልቄ ምን ልተንፍስ? ... ምን አውቄ? ምስጋና እንደው አልለመደኩ በዝምታ አለቀስኩ {ለቅሶ አይደል የለት ጉርሴ? ምሬት አይደል እስትንፋሴ?} እመቤቴ በእንባ መሐል አየሁ ምስልሽን ስታጫውች ውብ ልጅሽን በዛች ቅጽበት ተሰለበ ሹል ብሶቴ ተገፈፈ ጽልመት ፊቴ ልቤ ጠጣ ከእቅፍሽ ሀሴት ቀድቶ እንኳን እኔ ሐዘን ሳቅ አንቺን አይቶ #ኤልዳን @eldan29 @getem @getem @getem
Show all...
55👍 14🤩 2😁 1😢 1
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ። ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ! @seiloch @seiloch
Show all...
3👍 2
ሥዕል ለወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ማበርከት የምትፈልጉ በ+251984740577 ይደውሉ። ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ! @seiloch @seiloch
Show all...
👍 5 4
ድብልቅልቅ ነው ውስጡ ውልቅልቅ ነው ጌጡ .... ሰባራ ነው ውበት  ጥቁር አለው የኛ ሽበት! ወጣት ነው የጠገበ ነበልባል ነው የረገበ መዳፍ ነው የማይሞላ ፍቅር አለን የሚያባላ ! ሰላም ነው የሚረብሽ ንፁህ ነው የሚቆሽሽ መሬት ነው ሁሉንም ቻይ እያኖረ ገዳይ! ሰፊ ነው ገፀ ብዙ ጠባብ ነው ፅንስ ሙሉ በቂ ነው ቻይ ተራፊ ለ'ኔ ና አንቺ ሰፊ! ባህር ነው ሞገደኛ ሃይቅ ነው ሰላምተኛ አለም ነው ዥንጉርጉሩ አንጀት ነው ለኛ ሩሩህ! ፍቅር ነው ፍፁም ልዩ!!     Follow my IG & Tiktok @be_Olyon        ✍️ Olyon                                                   አስተያየት (@be_Olyon)      @getem                    @getem                                   @getem
Show all...
👍 49 21👎 3😱 3🔥 2
ሲያምርብሽ ቀሚስ ጥልፉ ሲያምርብሽ ነጭ በነጩ ህፃናቶች ከእግርሽ ስር ተኮላትፈው የሚንጫጩ እረበሹሽ ከጸሎትሽ የዳዊቱን ቦታ አጣሽ? እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ ቤተመቅደስ ምን አመጣሽ? ከመልክሽ ላይ ይታየኛል የአብ እጁ ልዕልና በሁዳዴ ቤቱ መጣሽ ጌታን ልትይ ሆሳዕና? ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ንጉስ አየን ከድንግል ሴት ፀሀይ ወጣ ከአርያም ከቅዳሴው ዜማ ሰማን መንበር መሃል እጣን ጨሰ ህዝበ እስራኤል ጨርቁን ሁሉ እመሬት ላይ አለበሰ የምስጋናው ዜማ ጦፈ መንፈስ ቅዱስ ህዝቡን መላ በወንጌሉ ክብር አገኘች የያዘችው ውርንጭላ ህዝቡ ሞልቷል ከመቅደሱ ወንዱም ሴቱም ለየብቻ በነጠላ ተሸፍነሽ ምትታዪኝ አንቺ ብቻ ከአጠገብሽ ጎልማሳ ሴት ሲደገፉሽ ማትከፊ የደከማት አራስ እናት ልጇን ይዘሽ የምታቅፊ በነጠላ የሚያምር ገጽ ለመንካትም የሚያሳሳ ጸጉርሽን ሸፍነሻል ዋናው ነገር ፊትሽሳ? ላለማየት እጥራለው ነጣላሽን ስታጣፊ ወዴት ላርገው ይዤ ቆምኩኝ የዘንባባ ዝንጣፊ ምን ላድርገው ዘንባባውን ? መስቀል ልስራ ለግንባርሽ ከብልጭልጭ ከወርቅ አልማዝ መስቀሉ ነው ሚያሳምርሽ በቢጫዋ ዘምባባስ ግን አይኔ አይቶ ከመረጣት ቀለበትን ልስራ ይሆን ለእጆችሽ ሰልካካ ጣት? በአራቱም መአዘናት ተነበበ ወንጌል ለአለም ምህላችን ይቀጥላል እስኪመጣ ለዘላለም አንድ ሳምንት የፆም ስግደት ህማማቱ ሊጠብቀን ከበሮውን ሰማይ ሰቅለን አመስግነን ለአንድ ቀን ከመድረኩ ነጭ ለብሰው ከበሮውን እየመቱ ክብ ሰርተው ሲዘምሩ እንደያኔው ህፃናቱ ምን ተሰማሽ በድምቀቱ አይኔ ካንቺ ተመልክቷል ጠብታ ውሃ የምታክል ዘለላ እንባ ከአይንሽ ወቷል ለምን አዘንሽ በደስታ ቀን ይታወቃል የልቦናሽ   ንጽህና የእግሮችሽን ጣቶች ላንፃ ፀሎተ ሀሙስ ይድረስና? አትፈልጊም አውቃለሁኝ እንኳን ማጠብ እንዲያዩሽም የኤደን ውስጥ በለስ እንጂ የዱር ኮሽም አይደለሽም ታዲያ ያለሙን ጣጣ ረስቶ ልቤ ሰከን ከሚልበት እንዲታወክ ቤተ መቅደስ ባትመጪ ምን አለበት? ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም ንጉስ አየን ከድንግል ሴት ፀሀይ ወጣ ከአርያም የገላውን ስጋ ቆርሰው በቀናት ውስጥ የሚገሉት ጨርቃቸውን አገላድመው በእልልታ ተቀበሉት የኛ ህዝብም ደምቋል ዛሬ መስቀል ሰርቷል ከመረጠው ጎልጎታ ላይ እስኪሰቀል ወዳጅ ስሞ እስኪሸጠው የኔ ግና ተበጥሷል የአይኔ ላይ መቀነቻ ከዚህ ሁሉ ተነጥለሽ ምትታዪኝ አንቺ ብቻ ምናለበት ባገለግል ቤተመቅደስ ሌላ አላጣሽ እንደ መልአክ ነጭ አልብሶ እኔ ደብር ምን አመጣሽ? By @mikiyas_feyisa @getem @getem @paappii
Show all...
71👍 18🎉 5😢 4🔥 1😱 1