cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሰሌዳ | Seleda

የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ! @seleda_support ለማንኛውም አይነት ጥያቄ

Show more
Advertising posts
50 535Subscribers
+524 hours
-207 days
+25930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለ28 አመት ታጥፎ የኖረውን ግለሰብ ያዳነው የህክምና ጥበብ👏 ሊ ኋ ይባላል፡፡ ቻይናዊ ነው፡፡ ታዲያ ሊ አንኪሎሲንግ ስፖንዲላይትስ (Ankylosing spondylitis) በተሰኘ የአጥንት በሽታ ለ28 አመታት ፊቱን ከጉልበቱ ላይ ማንሳት ሳይችል እንደታጠፈ ኖሯል፡፡ የሊኋ የጀርባ አጥንቶች በጣም ስለታጠፉ መቀመጥም ሆነ መነሳት ወይንም ጋደም ማለት ባለመቻሉ 28 የስቃይ አመታትን አሳልፏል፡፡ ይህ እጥፋቱም የቻይናዊውን ቁመት ወደ 90 ሳንቲ ሜትር አውርዶት ነበር፡፡ ታዲያ እ.ኤ.አ በ2018 ህክምና ሊደረግለት ቢሞከርም ቀዶ ጥገናው እጅግ አደገኛ ስለነበር ሐኪሞቹ ሊሰሩለት አልመረጡም ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት ግን ሊኋን ለማዳን ቆርጠው ተነሱ፡፡ በዛ ላይ ኋ ቀና ካልተደረገና በልቡና ሳንባው ላይ ያለውን ጫና መቀነስ ካልተቻለ ሕይወቱ አስጊ ወደ ሆነ ደረጃ በመሸጋገሩ ህክምናው የግድ ሆነ፡፡ በመሆኑም በቻይና ሸንዘን ዩኒቨርስቲ አጠቃላይ ሆስፒታል የአጥንትና መገጣጠሚያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ዌይረንን ጨምሮ ሌሎች የሕክምና ቡድን አባላት ሊን ቀጥ አድርጎ የሚያራምደውን ህክምና ጀመሩ፡፡ ህክምናው የግለሰቡን ታጥፈው የነበሩትን የጀርባ አጥንቶ አንድ በአንድ እየሰበሩና ድጋሚ ቀጥ አድርጎ የመገጣጠም ስራ ነበር፡፡ በዚህም ከአራት ዙር አስቸጋሪ ቀዶ ጥገናዎች በኋላ የተሳካ ስራ መስራት ችለዋል፡፡ የእግሩ አጥንቶችም እንደዚሁ ተሰብረው መልሰው መጠገን ቻሉ፡፡ ሆስፒታሉ የቀዶ ጥገናውን ክብደት ሲገልጽ የኤቨረስት ተራራን እንደመውጣት ነበር ነው ያለው፡፡ በዚህም ሊ በድንቅ የህክምና ጥበብ ከ28 አመት በኋላ ቀጥ ብሎ መቆምና መራመድ ችሏል፡፡ Via አዲስ ዋልታ
Show all...
👏 96👍 29 2😱 2
አምና የወረደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተመልሷል 🔥 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ አንድን እየመራ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኦሮሚያ ፖሊስ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከወዲሁ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ማደግ ችሏል። ባለፈው አመት ወደ ታችኛው ሊግ የወረደው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሪቱ ትልቅ ሊግ መመለሱን ማረጋገጥ ችሏል። ምንጭ :- የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን
Show all...
👍 23
"የስፖርት ውርርድ / የቤቲንግ ቤቶች ሊታገዱ ይገባል" ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አሳሰበ። ሚኒስቴሩ ዛሬ የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለተ/ም/ቤት አቅርቦ ነበር። በዚህ ወቅት ፤ " የወጣቶች ሱሰኝነት በሀገር ደረጃ እየተባባሰ መጥቷል ፤ በተለይ አሉታዊ መጤ ልማዶች እና አደንዛዥ ዕጽ እንደ ሀገር እየተስፋፋ መጥቷል " ሲል ገልጿል። ይህም ብዙ ወጣቶችን እያሳጣን ነው ሲል አስረድቷል። ወጣቶች ሰብዕና ግንባታ ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ ከሚገኘው አንዱ የስፖርት ውርርድ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ " የስፖርት ውርርድ ለሀገሪቱ ከሚያስገባው ገቢ አኳያ ብቻ መታየት የለበትም " ብሏል። " ' ስፖርት ቤቲንግ ' ላይ ያሉት፣ ካሁን በፊት የወጡት መመሪያዎች፣ ደንቦች፤ ጥናትን መሰረት አድርገው ሊታገዱ ይገባል " ሲል ገልጿል። ፓርላማውም በዚህ ረገድ እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል። " ገቢ አንድ ነገር ነው። ሀገር ገቢ ማግኘት አለባት " ያለው መ/ቤቱ ነገር ግን ፦ ➡️ በወጣቶቹ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያስከተለ ስለሆነ፣ ➡️ ብዙ ወጣቶች እያሳጣ ስለሆነ፣ ➡️ ብዙ ቤተሰብም #እየፈረሰ ስለሆነ ሊታገድ እንደሚገባ ገልጿል። በህ/ተ/ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ " ብሔራዊ ሎተሪ ከገቢ ጋር አይቶታል። በዚህም በኩል ደግሞ ሌላ ችግር እየፈጠረ ነው " ያለ ሲሆን " ተማሪዎች ዩኒፎርማቸውን እያወለቁ የስፖርት ውርርድ ቤት ይገባሉ። ስለዚህ መቼ ያጥኑ። አእምሮአቸው ሊጎዳ ስለሚችል ጥንቃቄ ተደርጎ መሰራት አለበት " ብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስፖርት ውርርድ ላይ በተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በቅርቡ የወሰደውን እርምጃ " ጥሩ ስራ " ሲል አወድሷል። በሌሎች አካባቢዎች በተሞክሮ ሊወሰድ ይገባል ሲል ጠቁሟል። የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ፤ ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ያለውን የወጣቶች ሁኔታ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ እንዲያየው እና ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ መክሯል። ከዚህ ቀደምም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ' #ቁማር ' ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ እንዲታገድ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን ፤ " ቤቲንግ " ' #ጨዋታ ' እንጂ ' ቁማር ' ነው ብሎ እንደማያምን ገልጾ ነበር። ቤቲንግ አትራፊና ብዙ ወጣቶች ስራ እንዲያገኙ ያደረገና በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ መሆኑንም አስረድቶ ነበር። በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎች ወጥተውለት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ሲል ነበር የመለሰው። via - tikvahethiopia
Show all...
👍 38👎 15
የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በፍተሻ ኬላዎች አላግባብ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ ነው ተባለ ለአገር አጠቃላይ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ዋነኛ መሆኑ የሚነገርለት የትራንስፖርቱ ዘርፍ በርካታ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ያስታወቀው የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማህበር ነው፡፡ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዴ ከዚህ ቀደም የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች እገታ፤ ዝርፊያ፤ ግድያ እና ሌሎች ጥቃቶችም ሲደርስባቸው እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ግን በአንጻራዊነት መሻሻሎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ላይ አሽከርካሪዎች በሚያቀኑባቸው አከባቢዎች ባሉ የፍተሻ ኬላዎች አላግባብ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን እና ይህም በዘርፉ ላይ ችግር እየፈጠረ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት ከሆነ ተሸከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ኬላዎች ከ5ሺህ እስከ 30 ሺህ የሚደርስ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው፡፡ ዘርፉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ማህበሩ ያስታወቀ ሲሆን፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በበኩሉ በአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራው ነው ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡(መናኸሪያ ሬዲዮ)
Show all...
👍 22 2
የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጠው ድጋፍ ለኢትዮጵያ እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ያለው ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተለያዩ ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ያለው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ዛሬ የቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ሱዝማን እና ቡድናቸውን በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል" ሲሉ ገልጸዋል። የቢል እና ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ ጤና፣ በስርዓተ ምግብ፣ በአካታች የፋይናንስ ስርዓት እና በሌሎች ዘርፎች የሚሰጠው ጠቃሚ ድጋፍ ለኢትዮጵያ እድገት ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ይህን ትብብር በማላቅ እና በአዳዲስ ዘርፎች በመተባበር እንሰራለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
Show all...
👎 32👍 17 3🤔 1
ራይድ በኤሌክትሪክ መኪና የታገዘ የትራንስፖርት አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ ራይድ የአረንጓዴ ትራንስፖርት አገልግሎት አካል የሆነውን የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎትን ማስጀመሩን በዛሬው እለት በአድዋ ሙዚየም የተለያዩ ተቋማት ሚንስትሮች፣ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የዓለም አቀፍ እና የአህጉራዊ ድርጅት ተወካዮች፣ አምባሳደሮች እና ዘርፉን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የሚገኙ ግለሰቦች በተገኙበት ገልጿል፡፡ የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳምራዊት ፍቅሩ የራይድ የትራንስፖርት ዘርፉ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች የሚያደርገዉን ሽግግር በይፋ በሚጀመርበት በዚህ ቀን እንደገለጹት በሀገራችን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ዘርፉን ለማስፋት እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ራይድ በርካታ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ አገልግሎት በማስገባት ከቴከኖሎጂው ፈር ቀዳጆች ተርታ ተቀምጧል ብለዋል ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በሞባይል መተግበሪያ እና በጥሪ ማዕከል አማካኝነት ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት በማቅረብ ላይ የሚገኘዉ ራይድ የኤሌክትሪከ መኪኖች ወደመገልገል መሸጋገሩ የተገለፀ ሲሆን ይህ አግልግሎቱ "የራይድ ራዕይ 2030” አንዱ (RIDE'S 3G, Vision 2030) ማስጀመሪያ ጭምር መሆኑም ተነግሯል። እነዚህ የተስላ ብራንድ የሆኑት ከ150 በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ወደ አገልግሎት የሚገቡበት የመጀመሪያ ዙር የራይድ የአረንጓዴ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ተቋማት እና የመኪና አስመጪዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል ። ራይድ በአሁን ሰአት ከ400 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። (በድሬቲዩብ ሪፖርተር)
Show all...
👍 25👎 4 1
የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት እየተጠናቀቀ ባለው በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፡፡ ይህ መጠን ከ2015 በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ የሚኖረው ነው፡፡ በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ አቶ መስፍን አስታውሰዋል፡፡ አየር መንገዱ እየሰፋ ያለውን የደንበኞች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ አሁን በአመት ማስተናገድ ከሚችለው 25 ሚሊየን መንገደኞች ከ4 እጥፍ በላይ ማስተናገድ የሚችል አየር ማረፊያ እና ማስተናገጃ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፡፡ ሆኖም ይህ ማእከል የአለም አቀፍ እና በተወሰነ መልኩ የጭነት ማስተናገጃ ሆኖ የሚሰናዳ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልጸዋል፡፡ የቦሌ አየር ማረፊያ እያደገ የመጣውን የአገር ውስጥ በረራ በማሰተናገድ ይቀጥላል ያሉት አቶ መስፍን ; የጥገና እና የጭነት ማእከሉም በቦሌ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ አየር መንገዱ ለአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ የአየር መንገዶች የጥገና አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ስራ ለማስፋት ተጨማሪ የመለዋወጫ ማስቀመጫ እና የጥገና ማእከል እየሰራ ሲሆን እስከመጪው ታህሳስ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል:: በተመሳሳይ እጅግ ዘመናዊ የጭነት ማእከል የገነባው አየር መንገዱ ዋነኛ የችነት ማእከሉን በቦሌ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቀው፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ ቢሾፍቱ 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው አዲስ የአየርመንገድ ከተማ ከቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ጋር በፈጣን ባቡር እንደሚገናኝ ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡(Capital)
Show all...
👍 27😁 11👎 4
አዲስ አበባ‼ ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት እና መታወቂያ በመያዝ አገልግሎት ለማግኘት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር  ዋለ   በየካ ክፍለ ከተማ  በሀሰተኛ  ማስረጃ  አገልግሎት  ለማግኘት የሞከሩ አራት ደንበኞች እና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን  የአዲስ አበባምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሁለት ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው አገልግሎት ለማግኘት የቀረቡ ተገልጋዮችን ጨምሮ  ሌሎች ሁለት በወንጀል ተግባሩ የተጠረጡ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አግልግሎት ኤጀንሲ  ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ተናግረዋል  ። አንደኛው ግለሰብ ሃሰተኛ የመታወቂያ እና ያላገባ ህገ ወጥ ማስረጃ በመያዝ ለጽ/ቤቱ ሰራተኛ ጉቦ በመስጠት አገልግሎት ለማግኘት የሞከረ ሲሆን   ከዓመታት በፊት ማስረጃውን በሌላ አገናኝ ደላላ ያገኘው መሆኑን ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም  ደላላው እና  ሁለተኛው ተጠርጣሪ የቂርቆስ ክ/ከተማ ነዋሪነት መልቀቅያን አስመስሎ በማሰራት አገልግሎት ለማግኘት ሙከራ ሲያደርግ ሃሰተኛ ሰነዱን ካዘጋጀው አስመዝጋቢ የቤት ባለቤት ነዋሪ ግለሰብ ጋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ብስራት ሬዲዮ
Show all...
👍 17🤔 3 1
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የትንሣኤ በዓል ገበያን ለማረጋጋት ግብረሃይል አቋቁሜ እየሰራሁ ነው አለ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድና ግብይት ዘርፍ ኃላፊ ፍሰሐ ጥበቡ በትንሣኤ በዓል በምርት አቅርቦትና ዋጋ ላይ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሚያስችል ግብረሃይል መቋቋሙን አስታውቀዋል። በከተማዋ የሚገኙት 188 የእሁድ ገበያዎች ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት ይሰጣሉ። በተጨማሪም ከመደበኛው ግብይት ጎን ለጎን በለሚኩራ፣ በኮልፌና አቃቂ የሚገኙት የግብርና ምርቶች ማዕከላት ቅጥር ግቢ ባዛሮች መዘጋጀታቸው ተገልጿል። ከአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሰብል፣ የእንስሳት ተዋፅዖ ምርቶች በተጨማሪ በቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት በቂ ፍየል፣ በግና የዳልጋ ከብት የሚቀርብበትን ትስስር ፈጥሬያለሁ ብሏል። በንግድ ዘርፉ ህግና ስርዓት እንዲከበር ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ሊስተዋሉ የሚችሉ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር መዘጋጀቱን ሰምተናል። Arada_Fm
Show all...
👍 30👎 6😁 3🤔 1