cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

6 ማዕዘን

ወቅታዊ፣ ሀገራዊ፣ ታሪካዊ፣ አስተማሪ፣ አዝናኝ እና ቁምነገራዊ ጉዳዮች ብቻ የሚስተጋባበት ቻናል ነዉ። ✍ It is a channel where only current, national, historical, educational, entertaining and serious issues are echoed.

Show more
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ወደር-የለሽ አበርክቶት #Ethiopia  | ከዓመታት በፊት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንድ የሆነ ዶኩመንት ለማዘጋጀት ከተለያዩ ካምፓሶች የተውጣጣን የሥራ ኃላፊዎች በአቃቂ ካምፓስ (አሁን ለቀድሞ ባለቤቱ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመለሰ) ተገናኝተን ነበር። በወቅቱ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የነበሩት ታዋቂ የአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ተማሪ የነበሩ (ስላላስፈቀድኩ ስማቸውን አልጠቅስም) በአጋጣሚ ስለ መምህራቸው ብዙ ነገር አጫወቱኝ። አንድ የማልረሳው ፕሮፌሰር አሥራት በአንዱ ቀን ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልገውን የቀዶ ሕክምና ትምህርት (ትምህርቱ ቀዶ ሕክምና በሕመምተኛ ላይ እየተከናወነ ነው የሚሰጠው) ክላስ ተደራርቦባቸው በከፍተኛ መጠን እግራቸው ተንቀጥቅጦ ሊወድቁ ሲሉ እያጫወተኝ ያለው ፕሮፌሰር እና ሌሎች ተማሪዎች አፈፍ አድርገው ያዟቸው። ''ያን ቀን ምን ያህል ቢያስተምሩ ነው?'' አልኩት። ''ለተከታታይ 18 ሰዓት'' አላለኝም??? ለፕሮፌሰር አሥራት እና ለአጋር የሕክምና መምሕራን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን። ምሥጋና በጣም ያንሳል! ልክ የዛሬ 25 ዓመት በዛሬው ዕለት ሕይወታቸው ያለፈው ፕሮፌሰር አሥራት እጅግ የተከበሩ እና የተወደሱ (Most Distinguished) የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት፣ የሕክምና ፕሮፌሰር፣ የአፄ ኃ/ሥላሴ የግል ሐኪም፣ ፖለቲከኛ እና በሁለት መንግሥታት የግፍ እስር የደረሰባቸው ኋላም ለሞት ተላልፈው የተሰጡ ምርጥ ዜጋችን ነበሩ። ፕ/ር አሥራት ወ/የስ በሕክምናው በኩል ላደረጉት ወደር-የለሽ አበርክቶ፤ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ እንዲቆይ ላደረጉት ተጋድሎ እንዲሁም የመጣ የሔደው አጀንዳውን ለማስፈጸም እንደ ጆከር ለሚመዘው አሳዛኙ የአማራ ሕዝብ ለከፈሉት የበዛ መስዋዕትነት በእኔ በ Ordinary ዜጋዋ ልብ ውስጥ ዘላለም ተከብረው ይኖራሉ። 🙏🙏🙏 Via Hawulet Ahmed
Show all...
👍 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ወደር-የለሽ አበርክቶት #Ethiopia | ከዓመታት በፊት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንድ የሆነ ዶኩመንት ለማዘጋጀት ከተለያዩ ካምፓሶች የተውጣጣን የሥራ ኃላፊዎች በአቃቂ ካምፓስ (አሁን ለቀድሞ ባለቤቱ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመለሰ) ተገናኝተን ነበር። በወቅቱ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የነበሩት ታዋቂ የአእምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ተማሪ የነበሩ (ስላላስፈቀድኩ ስማቸውን አልጠቅስም) በአጋጣሚ ስለ መምህራቸው ብዙ ነገር አጫወቱኝ። አንድ የማልረሳው ፕሮፌሰር አሥራት በአንዱ ቀን ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልገውን የቀዶ ሕክምና ትምህርት (ትምህርቱ ቀዶ ሕክምና በሕመምተኛ ላይ እየተከናወነ ነው የሚሰጠው) ክላስ ተደራርቦባቸው በከፍተኛ መጠን እግራቸው ተንቀጥቅጦ ሊወድቁ ሲሉ እያጫወተኝ ያለው ፕሮፌሰር እና ሌሎች ተማሪዎች አፈፍ አድርገው ያዟቸው። ''ያን ቀን ምን ያህል ቢያስተምሩ ነው?'' አልኩት። ''ለተከታታይ 18 ሰዓት'' አላለኝም??? ለፕሮፌሰር አሥራት እና ለአጋር የሕክምና መምሕራን ተከፍሎ የማያልቅ ውለታ አለብን። ምሥጋና በጣም ያንሳል! ልክ የዛሬ 25 ዓመት በዛሬው ዕለት ሕይወታቸው ያለፈው ፕሮፌሰር አሥራት እጅግ የተከበሩ እና የተወደሱ (Most Distinguished) የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት፣ የሕክምና ፕሮፌሰር፣ የአፄ ኃ/ሥላሴ የግል ሐኪም፣ ፖለቲከኛ እና በሁለት መንግሥታት የግፍ እስር የደረሰባቸው ኋላም ለሞት ተላልፈው የተሰጡ ምርጥ ዜጋችን ነበሩ። ፕ/ር አሥራት ወ/የስ በሕክምናው በኩል ላደረጉት ወደር-የለሽ አበርክቶ፤ የኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ እንዲቆይ ላደረጉት ተጋድሎ እንዲሁም የመጣ የሔደው አጀንዳውን ለማስፈጸም እንደ ጆከር ለሚመዘው አሳዛኙ የአማራ ሕዝብ ለከፈሉት የበዛ መስዋዕትነት በእኔ በ Ordinary ዜጋዋ ልብ ውስጥ ዘላለም ተከብረው ይኖራሉ። 🙏🙏🙏 Via Hawulet Ahmed
Show all...
ነብስ ይማር ድምፃዊ ዳምጠው አየለ !! የሸዋ ሰማይ ከመሬት ጋር ፀብ ያለው ይመስል እንደ መድፍ ሲያስገመግም ጀማና ወንጪት ጃራና ወለቃ ከሰምና አዳባይ የፍቼ ወንዝና ዜጋመል የጃማና ደጎሎ ጉም ሲጎምም በክረምቱ ወራት ሃምሌ በዕለተ ጊዮርጊስ በቀን 23 1944 ዓ/ም ከመሬ ሚዳ ከሸዋዋ ደርባባ ከእናቱ ወይዘሮ ሸዋየ ተካና ከአራሽ ገበሬው ከመንዜ መራኛው አባቱ ከአቶ አየለ ካሰኝ በመራቤቴ መራኛ ሸዋ ተወለደ። እንደማንኛውም ልጅነቱን በእረኝነት፥ በግብርና እንዲሁም በቆሎ ተማሪነት እንደማንኛውም ልጅ የልጅነት ጊዜውን አሳልፏል። እድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ባአቅራቢያው በሚገኘው መራኛ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብቶ ተምሯል። ዳምጠው አየለ ህይወቱ እስካለፈችበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ጊዜ አብሯት የኖረው ባለቤቱ አልማዝ ይመር ትባላለች። ከአልማዝ ይመር አብዩ ዳምጠውና ቤቴልሄም ዳምጠው የሚባሉ ሁለት ልጆችንም አፍርቷል። ዳምጠው አየለ መራቤቴ እያለ በየባዕላቱ መዝፈን፣ ማቅራራት እንዲሁም መሸለል ይወድ እንደነበር ተናግሯል። በተለይም ጥምቀትን በማድመቅ ይታወቅ ነበር። የ 6ኛ ክፍል ተማሪ እያለ ክፍሌ ሞገስ የሚባል መምህሩ ወደ አዲስ አበባ ይዞት እንደመጣ ይናገራል። በአጣሚም የምድር ጦር ማስታወቂያ አውጥቶ ስለነበር ይፈተንና ያልፋል። የምድር ጦር ካምፕ ውስጥም እንዲኖር ይደረጋል። የዘፋኝነት ሙያው በዚህ አጋጣሚ ነበር የጀመረው። ዳምጠው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማዉና መነሻ የሆነው አበበ ተሰማ እንደሆነ ይናገራል። ዳምጠው አየለ በምድር ጦር ከ 30 አመት በላይ አገልግሏል። የኢትዮዽያ ምድር ጦር በ1927 አ/ም ተመስርቶ በ1983 አ/ም የፈረሰ የሙዚቃ ቡድን ነበር። ዳምጠው በመንግስት ለውጥ ምክንያት እስከፈረሰበት ጊዜ ድረስ አብሮ እንደነበር ይናገራል። ምድር ጦርም እያለ ከነታምራት ሞላ፣ ሲራክ ታደሰ፣ ተክሌ ደስታ ፣ ጥላየ ጨዋቃ፣ ክፍሌ አቦቸር እንዲሁም ሌሎች የጦሩ አባላት ጋር ሰርቷል። ከሌሎች የሙዚቃ ቡድንም ጋር አብሮ ሰርቷል። ለምሳሌ ያክል ከነ ክቡር ጥላሁን ገሰሰ፣ ሙሃሙድ አህመድ፣ ብዙነሽ በቀለ ፣ ሙሉቀን መለስ፣ ፀሃየ ዮሃንስ፣ ቴድሮስ ታደሰ፣ቴድሮስ ካሳሁን እንዲሁም ሌሎችም ጋር ሰርቷል። የዳምጠው አየለ የመጀመሪያ የህትመት ስራው በ1963 አ/ም ሲሆን ወፌ ላላ የሚለው የሸክላ ስራ ነበር። ዳምጠው አየለ ባጠቃላይ 13 ሲዲዎችን ሰርቷል። ድምፃዊ ዳምጠው አየለ ከብዙዎች ለየት የሚያደርገው የባህል ሙዚቃ ዘፋኝነቱ ብቻ ሳይሆን የአዘፋፈን ስልቱ በተለይ በዚያን ዘመን የህዝቡን ድምፅ እንደ ከያኒነቱ በቅኔም ሆነ በመጋፈጥ የተንጋደደ ስረዓትን ሲተች ማህበረሰብን ሲያነቃ እንደነበር ከዘፈኖቹ መረዳት እንችላለን። ለየት ባለ ቱባ የሆነውን ባህል ሳይበረዝ ሳይሸራረፍ ከዳር እስከ ዳር የኢትዮጲያን አካባቢ ከምድር ጦር ጋር በመሆን የማይረሳ ጥበባዊ አሻራ አስቀምጦ ማለፉ ነው። ለአብነትም ወደ ጎጃም አባይን ተሻግሮ ግርማው ገቢ ነበር ዋ ጎጃም አዘነ ዋ ጎጃም አዘነ አገሬ ምን ነካው አዘነ ጎጃም ቆላ ደጋ ዳሞት ፍኖት ሰላም ሸማኔው አንበሳ አሰሪው ነብር አሁን በምንጊዜው ቆረጡት ያን ድር ወይ ሀገር ወይ ሀገር ወይ ሀገር ቢቸና መላ አትለኝም ወይ ህመሜ ሲጠና መፍተሉን ነው እንጂ አሳዩኝ ያልኩኝ ነድፎ መጣሉማ እኔ መች ጠፋኝ ሸማኔማ ብሆን እንዴት በአማረብኝ በማጠንጠን ብቻ-------- ቀረብኝ ሀገራችን ዳሞት ብር ነው ወንዛችን ፍቅራችን ነው እንጂ አይመች ፀባችን # ወደ ወሎ በጃማ ደጎሎ ተሻግሮ ነይ ደሞ ነይ ደሞ ጨለማ ነው ያልሽው የታል ጨለማው ደሴ ሙጋድ ሜዳ ይታየኛል ሰው ከወልዲያ በላይ ስሙ ነው አብዬ ቆቦ መግባቴ ነው አንቺን ተከትዬ ዳምጠው አየለ ሸዋ አካባቢ በመወለዱ ያደገበትን ባህል ወግ ስረዓት በደንብ አስተዋውቋል። ያመራኛ ነው ወይ ጉብል ጠንበለሌን አንረሳውም ! በደንጎሬ ማርያም በጉስቋማ እናቴ አውጭኝ ከዳገቱ አልቻለም ጉልበቴ ፈጣሪ በኮላሽ በአስወደደሽ ላይ ደብር ግል ብትገቢ ግፍ አይሆንም ወይ ! ከሸዋ ምንጃር ተነስቶ ቡልጋን አንኮበር ተጉለትን መንዝን ከማማ እስከ ግሼ ራቤል ቃኝቶታል።ጅሩ አንጎለላ ጠራን ደራ እንሳሮ ማጀቴ ይፋትን ዳሶታል። የምንጃር ልጅ ናት የቡልጋ መቼም ሳላያት አይነጋ የቀያ ልጅ ናት የግሸ ማነው ከእርሷ ጋር ያመሸ አገሯ ይፋት ማንስ ሊደፍራት ምኑን ይዤ እገባለሁ መንዝ በእሷ ጉዳይ ጦር ሳልማዘዝ ደሞ ለመንዝ ሰው ደሞ ለቡልጋ ሰው እኮ ለተጉለት ምን ብለው ሊያሙት ነው ስም ሊያወጡለት ! ጎንደር ደንቢያ አርባያ በላሳ አላፋ ጣቁሳም ተሻግሮ እንዲህ ተቃኝቷል። # እደገቷ ነበር ጎንደር እስራኤል ገብታ ባትቀር ወገራ በላሳ መተማ ደባርቅ ትዝታዋ ጠራኝ ከአይኔ ስትርቅ ኧረ ገዳምዬ ኧረ ገዳሜዋ አምላክ በጥበቡ የሰራት ቀድሞ ምን ይወጣላታል ለጎንደር ልጅ ደግሞ ማሞ ደብረታቦር ወገራ ጋይንት ቀረች እንደወዛ የኔ መድሃኒት ድምፃዊ ዳምጠው አየለ ስለ ምድር ጦር ትዝታው ወንድሞቹን እህቶቹን የጦረኞች ትዝታውን እንዲህ አስቀምጦት አልፏል። ከማስልጠኛ እስከ መልከዓምድሩ በራሱ ግጥምና ዜማ _ ሂድ በለው ሂድ በለው ኮረኩረው ፈረሱን * አካሂዱን አይተው የፊት ኋላውን አሁን ማን አወቀው የመጨረሻውን መስኖ ማሰልጠኛ እንዴት ነው አጋርፋ ቀና ማለቱ አይቀር አንገቱን የደፋ እንደ ምነው ጎጃም ብር ሸለቆ ዳሞት የጨነቀ ጊዜ ያወጣል ከዳገት ሀገሬ ላይ ሆኜ ናፈቀኝ ሀገሬ እንዲህ ይረሳል ወይ የትናንቱ ዛሬ ሀዋሳ ሲዳሞ ብላቴ ጦረን ከንጉስ ጦና ሀገር እንዴት መላጣን ነቀምት ተምሮ ሊያውም በደዴዴሳ ያለቀለት ነገር አይቀር ሳይነሳ አዋሽ አርባ ሆኖ ሲፎክር ሲያቅራራ ትዝ አለኝ ያጎበዝ አፋር አሊቢራ ያም እየተነሳ ሱሪ ሲታጠቅ ምንይልክ በሸዋ ትዝ አለኝ ታጠቅ ! እያለ ብሶቱን ትውስታውን በግሪም ዜማና ግጥም ሙዚቃዊ ውህደት ፈጥሮ አስቀምጦልናል። እያለ ቃኝቶታል።ከእነ ገመልከ-ዓምድሩ ከእነ ባህል ወግ ስረዓቱ የማይረሳ የጥበብ አሻራውን አስቀምጦልናል። በመከፋት በመገፋት በብስጭት በስደት ሀገሩን ቤተሰቡን ትቶ ወደ ኖርወይ ሄዶ ህይወቱ እስከ አለፈችበት ሰኔ 27/2006 ዓ/ም ድረስ እንዲሁ በናፍቆት እንደባባ በዚች አለም ለመኖር የተፈቀደለትን ጊዜ ጨርሶ ላይመለስ ሄዷል። ድምፃዊ ዳምጠው አየለ የሰራውን ያበረከተውን ያክል ያልተወሳ ያልተነገረለት እንቁ የባህል ድምፃዊ ነበር። በተለይ የአካባቢው ተወላጆች የሙያ አጋሮቹ ስራዎቹን ማስታወስ ልጆቹን መጠየቅ መደገፍ እንዳለባችሁ ይሰማኛል። ዳምጠው ቆፍጣናና ለክብሩ ለሙያው ለሀገሩ የሚጨነቅ ጀግና እንደነበር ይታወቃል። ወዳጆቼ ስለ ድምፃዊ ዳምጠው አየለ እናንተም የምታውቁትን አካፍሉን። # ዳምጠው አየለ /ድምፃዊ ነፍስህ በሰላም ትረፍ # አቤል ወርቁ ዘ-ኮተቤ
Show all...
😢 1
#የአፍንጫ አለርጂ የሰውነት በሽታ ተከላካይ ህዋሶች፤ ሰውነት ውስጥ ለሚገባ ባዕድ ነገርየሚሰጡት የመቆጣት ምላሽ አለርጂ ይባላል፡፡ አለርጂ በአፍንጫ እና በሌሎች የመተንፈሻ አካላት ላይ ይከሰታል፡፡ አንዳንድ የአለርጂ ህመሞች ከባድ ህመም የሚያስከትሉ እና አጣዳፊ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ናቸው ተብሏል። ዶክተር ብስራት ጌታቸው ከአንገት በላይ ስፔሻሊስት ሃኪም ናቸው፤ የአፍንጫ አለርጂ አንድ ነገር ወደ አፍንጫ ሲገባ እና ሰውነት የተጋነነ ምላሽ ሲሰጥ አለርጂ ይባላል ብለዋል፡፡ አለርጂው ያስነሳው የአፍንጫ መቆጣት የአፍንጫ አለርጂ እንደሚባል ተናግረዋል፡፡ #የአፍንጫ አለርጂ መነሻ ምንክያቶች፤ • አቧራ • ቅዝቃዜ • ሙቀት • ጭስ • ኬሚካሎች • በአንዳንድ ሰዎች ላይ መጥፎም ሆነ ጥሩ ሽታ ለምሳሌ እንደ ሽቶ ፣ እጣን ለአለርጂ ምክንያት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአፍንጫ አለርጂ ወቅት እየጠበቀ የሚነሳባቸው ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩት ባለሞያው ሁሌም ቢሆን በአንዳንዶች ላይ ለአለርጂ ተጋላጭ ከሆኑ ህመሙ እንደሚነሳባቸው ተናግረዋል፡፡ #ምልክቶች፤ • የአፍንጫ ፈሳሽ መዝረክረክ • አይን አከባቢ መብላት ወይም ማሳከክ • የአፍንጫ ማፈን እና ማስነጠስን • ንጹ ፈሳሽ ከአፍንጫ መውጣት • የአፍንጫ መድማት • ጉንፋን መሰል ምልክቶች በታማሚው ላይ የሚስተዋሉ ይሆናል፡፡ #ህክምናው፤ በቅድሚያ ለአለርጂው ከሚያጋልጡ ነገሮች መጠንቀቅ እና አፍንጫን በውሃ እና በጨው ማጠብ እንደሚመከር ተጠቁሟል፡፡ በህክምናው ሰውነትን ሊያረጋጋ የሚችሉ መድሃኒቶች በሚዋጥ ኪኒን እንዲሁም አፍኝጫ ውስጥ በሚነፉ መድሃኒቶች ህመሙ የሚታከም መሆኑን ነግረውናል፡፡ #መከላከያ መንገዶች፤ ከጉፋን የሚለይበት መንገድ በህክምና ወቅት መሆኑን የሚናገሩት ባለሞያው፤ በተደጋጋሚ የሆነ ማስነጠስ፣ አይን አከባቢ ማሰከኩን እና አፍንጫ በመታፈኑ አማካኝነት በመጠኑ ሊለይ ይችላል ተብሏል፡፡ አሁን ያለንበት ወቅት የአፍንጫ አለርጂ የሚቀሰቀስበት እንዲሁም ህመሙ ያለባቸው ሰዎች የሚቸገሩበት ጊዜ መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ብስራት አለርጂውን ከሚቀሰቅሱ፤ አቧራ፣ ብናኝ ፣ ኬሚካሎች እና ሽቶዎች መጠንቀቅ እንደሚያስፈል እና ቀደም ሲል የተነገሩ ምልክቶችን የሚስተዋሉ ከሆነ ግን ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ይገባል ብለዋል፡፡ Ethio Fm
Show all...
አንድ ሰዉ"አብዷል"የሚባለዉ ሦስት ነገሮች ሲጎድሉት ነዉ ፤ ፩, እግዚአብሔርን መፍራት ሲያቆም ፪,ማኅበረሰቡን ማፈር ሲተዉ ፫,ህሊናዉ ማዳመጥ ሲሳነዉ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ❤
Show all...
ወጣቱ ኢዩኤል ታዬወርቅ፦ ሞቱ ልብ ይሰብራል። እንዝላሎች የፈጠሩት ሞት መሆኑ ደግሞ አንጀት ያሳርራል። አያቱ ቤት አድሮ ከታናሽ ወንድሙ ጋ ይጓዛል። ማን ያውቃል 'ከሁለት ወር በኋላ ትምህርቱን አጠናቆ እንደሚመጣ፣ስለምርቃቱ እያወጉ ይሆናል፣ ማን ያውቃል ስለሁለተኛ ዲግሪው፣ሊሰራ ስላሰበው እቅዱም እያወሩ ይሆናል። ማን ያውቃል ታናሹን ብርቱ ተማሪ እንዲወጣው እየመከረውም ሊሆን ይችላል።' ሞት ከአየር ላይ ተምዘግዝጎ ይመጣል ብለው እንዴት ይጠርጥሩ!? የሆነው ግን እንደእዛ ነው። የእንዝላሎች ብረት ከህንጻው ላይ ወድቆ የወንድማማቾቹን ጅምር ወሬ በአጭሩ ቀጨው። የእንዝላሎቹ የፌሮ መቆልመሚያ ብረት የ24 ዓመቱ ኢዩኤል ላይ አረፈ። ይህ አጠገቡ ለነበረው ታናሽ ወንድሙ የዕድሜ ልክ ጸጸት ነው። በወንድሙ ደም ርሶ "እባካችሁ ወንድሜን አትርፉልኝ!" ብሎ በተማጽኖ ቢጮህም አልተሳካለትም። በቃ። የኢዩኤል ምዕራፉ እዚህ ላይ ተዘጋ። አምስት አመት ለፍቶ ሊመረቅ ሁለት ወር ነበር የቀረው፤ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ። በአርክቴክት፣ስነ ህንጻ። ከህንጻ ግንባታ ጋር በተያያዘ እንዝላልነት ይታያል። ህንጻ አሰሪዎቹም ህንጻውን ከማቆም ውጪ ዙሪያ ገብ ጥንቃቄ አያደርጉም። እኔ እንኳን በዓይኔ በብረቱ የህንጻ መወጣጫ አጠና ተደርምሶ ለሞት የበቁ የቀን ሰራተኞችን አይቻለሁ። ህንጻ ላይ ሆነው ሲታገሉም ወድቀው አደጋ የደረሰባቸውን ሰራተኞች አስታውሳለሁ። ብሎኬት ወድቆ የተፈነከቱ፣አካላቸው የጎደለ ንፁሀን ቀላል አይደሉም። ይህ ልጎም ካልተበጀለት ነገም ይቀጥላል። በእዚህ አጋጣሚ የኢዩኤልን ነፍስ ለማትረፍ ርብርብ ያደረጋችሁት በተለይ ቤዛ ተፈራ የምትባል የአካባቢው ኗሪና መኪናውን አስነስቶ ወደጤና ጣቢያ ያደረሰው ሾፌር ልትመሰገኑ ይገባል። ወዳጆቼ ከእንዲህ ያለ መከራ፣ሀዘን ይጠብቃችሁ። የኢዩኤልን ነፍስ እግዚአብሔር በቀኝ ያኑርልን። ለቤተሰቡ፣ለጓደኞቹ፣በኢዩኤል ሞት ልባችሁ ላዘነ ሁሉ ፈጣሪ ጽናቱን ይስጣችሁ። ***
Show all...
😢 2👍 1👎 1
መልካም የአርበኞች ቀን ደጃዝማች አያሌው ብሩ ፣ በሰሜን ጎንደር በኩል የሚዋጉ ወታደሮቻቸውን አሰልፈው የጦር መሳሪያ ለሌለው እያደሉ እያለ እንዲህ ሆነ፣ “ የአስራ ስምንት ዓመት ልጅ በኩራት መንፈስ ዱላውን በቀኝ ትክሻው ላይ አድርጎ ይንጎራደድ ነበር። ዱላው የእንጨት ሲሆን ቀይ ቀለም ያለው ሆኖ እላዩ ላይ ጌጥ ተቀርፆበታል። የዚህ ወጣት ልጅ የተለየ ኩራት እና አካሄድ የሰዎችን አይን የመሳብ ችሎታ ፈጥሯል። ፣ ደጃዝማችም አስጠሩትና ... "በዚህ የሚያምር ዱላህ ምን ልታደርግበት ነው? " "በዚህ ዱላ ነጭ ልገልበት ነው።" "እንደሱ እንኳን ማድረግ አትችልም፣ በምትኩ ጠመንጃ ልስጥህ" "የለም አመሰግናለሁ ፤ ለአባቴ የማልኩት ቃለ መሀላ ጣልያን ገድዬ ፣ ጠመንጃውን ወስጄ አሳያለሁ ፤ አለዚያ በዚህ በጦር ሜዳ እቀራለሁ” እናመሰግናለን ኮርታችሁ መላውን የጥቁር ህዝብ ያኮራችሁ ጀግኖች አባት አርበኞቻችን ❤ ምንጭ፣ ሀሮልድ ናይስትሮም ፅፎት ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ ተብሎ ከተተረጎመው መፅሀፍ ገፅ 64 የተወሰደ።
Show all...
✝✝ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ፣ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ። ✝✝ "ምድር ጸዳች ሐሴት አደረገች  በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች።"
Show all...
“ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡” ሮሜ 6፡5 ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርኃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ! ሰናይ በዓል ይሁንላችሁ
Show all...
2