cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

በዚኽ ቻናል ጽሑፍ የሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው

Show more
Advertising posts
11 246
Subscribers
+3724 hours
+2417 days
+95730 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
የኦሲኤን ቴሌቪዥን እውነታዎች ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምሥረታ ጋር የቤተክርስቲያን መዋቅር ለማፍረስ በመናፍቃንና ፖለቲከኞች እርዳታ የተመሠረተ ነው። ከስምምነቱ በኋላ + ከኢኦቲሲ ቲቪ ጋር በአንድ ቦርድና በአንድ ሥራ አስኪያጅ እንዲመራ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የወሰነው በቋሚ ሲኖዶስ ተሽሮ በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን ሥር እንዲሆን ተደርጓል። + ለተቋሙ 8 ሚሊዩን ብር በጀት  የተለቀቀ ሲሆን ገንዘቡ በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን አንቀሳቃሽነት ያለ ምንም ሰነድ ሲባክን ቆይቷል። + ኦሲኤን 2 ካሜራ አንድ ኮምፒዩተር የተመዘገበ ሀብት ያለው እና 2 ካሜራ ማን 1 ኤዲተር 2 ጋዜጠኞች አንድ ዳይሬክተር በድምሩ 6 ሠራተኞች ቢኖሩትም ከ50 በላይ የቀድሞ የኦሮምያ ቤተክህነት ደጋፊዎች እና የቀሲስ በላይ ዘመዶች የቤት ሠራተኞችና ጥበቃ ማይቀር በሠራተኝነት ተመዝግበው ያለ ፔሮል ደመወዝ በጥሬ ገንዘብ ከባንክ ዝውውር ውጪ በስማቸው ወጪ ሲደረግ ቆይቷል። +ከኢኦቲሲ ጋር ሲዋሀድ በቋሚነት ትቀጠራላችሁ በሚል ብዙዎች ስማቸው ብቻ ተመዝግቦ ደመወዝ ሣይከፈላቸው እንደ ሠራተኛ እንዲመዘገቡ ተደርጓል። + ከጠቅላም ቤተክህነት የተሠጠው የሥራ ቦታ ለፓርኪንግና ስቶር በማከራየት ገቢው ለሊቀ አእላፍ በላይ ሲቀበል ቆይቷል። + ቴሌቪዥን ጣቢያው ከስብከት እና መግለጫ ውጪ አንድም መደበኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የለውም + ቴሌቪዥን ጣቢያው ባሉት ሁለት ካሜራዎች ቅዳሜና እሑድ የሠርግ ቀረጻ ሥራ በማከናወን ሠራተኞች የግል ቢዝነስ ይሠሩበታል። በአጠቃላይ ተቋሙ የግል እንጂ የቤተክርስቲያን ያልሆነ ሠራተኞቹ የተባሉትም ከሙያው ጋር የማይገናኙ የበላይ መኮንን ዘመዳ ዘመዶች ናቸዉ። + ቋሚ ሲኖዶስ አጣሪ በመድብም ቄስ በላይ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይጣራ ቀርቷል ይኸው አጀንዳ ሲኖዶሱ የሚወያይበት ይሆናል ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እውነታውን እንዲያውቁ ቢደረግ።
6272Loading...
02
Media files
5020Loading...
03
Media files
1 0590Loading...
04
ሲኖዶስ ሲኖዶስ ማለት ጉባኤ፣ አንድነት፣ ኅብረት፣ ማለት ነው፡፡ “አሐተኔ፣ ርክብ” የሲኖዶስ ተለዋጭ ቃላት ናቸው፡፡ ርክበ ካህናት የሚለውን ርክበ ጳጳሳት በማለት ሲኖዶስ ጋር በትርጉም ይመሳሰላል።  ይኹን እንጂ ርክበ ካህናት ሲባል ጳጳሳትን ብቻ የሚወክል ሳይሆን ካህናት የወል መጠሪያ ቢሆንም  ትርጉሙን ለጳጳሳት ብቻ ተሰጥቷል።  በሕገ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜው ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት፡- “ቅዱስ ፓትርያርክ፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚገኙበት ዐቢይ ጉባኤ ሆኖ ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ሕግ አውጪና ወሳኝ አካል ነው”። (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 2. 2)፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ደግሞ ሲኖዶስ (ጽርእ) ግሪክኛ መኾኑን ጠቅሰው “ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ ዩጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር እከባ ስብስብ) መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ (ገጽ 875)  ቅዱስ ሲኖዶስ “ብሂል (ትርጉም) ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የጽርዕ (የግሪክ) ሆኖ ትርጉሙ ዐቢይ ጉባዔ ጳጳሳት ወይም የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ጉባኤ ማለት ነው።  (Synod's Ecclesiastical Assembly) አቡነ መልከ ጴዴቅ (ሊቀ ሥልጣናት ሃብተ ማርያም ወርቅነህ) ያልታተመ ጽሑፍ። (ገጽ 1) ብሂል (ትርጉም) ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የጽርዕ (የግሪክ) ሆኖ ትርጉሙ ዐቢይ ጉባዔ ጳጳሳት ወይም የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ১৭৭ ১৯৮ ১৫: (Synod's Ecclesiastical Assembly) ሲኖዶስን ቅዱስ ያሰኘው የተሰበሰበት ዓላማና የቤተ ክርስቲያን በየበላይ መዋቅር መኾኑ ነው።  ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የአንድነት መገለጫ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ የሐዋርያት መንበር ወራሽ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን ኅብረታዊትና ጉባኤያዊት መሆን ማሳያ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት አስፋፊዎች እንጂ የመንደር ተወካዮች ስብስብ ማለት አይደለም።  አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ትውፊት እና አስተዳደር በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የሚመክሩበት ጉባኤ ነው።  የቅዱስ ሲኖዶስ አጀማመር በሐዋርያት ዘመን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተነሣው ጥያቄ ወይም ችግርን ለመፍታት በተደረገ ጉባዔ ነው።  ይኽውም ቤተክርስቲያን ከይሁዲነት ወደ ክርስትና ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና በመጡ አማኞች መካከል የባሕል ልዩነት ስለነበር ይኽንን መከፋፈል ለማስቀረት የተደረገ ጉባዔ ነው። በአራቱም መአዘን ለአገልግሎት ተበትነው የነበሩ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም መንበር በነበረው አረጋዊው ቅዱስ ያዕቆብ መሪነት በ50 ዓ.ም ሐዋርያት ከያሉበት መጥተው ጉባዔ አደረጉ።  “አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።” ሐዋ.15:1 በዚኽ ጥያቄ መሠረት “ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።” በማለት ስለመጀመሪያው ጉባኤ (ሲኖዶስ) ይነግረናል። ሐዋ.15:6 ከሐዋርያት ቀጥሎ የተነሡ ሐዋርያነ አበው በአብያተ ክርስቲያናት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ይሠበሰቡ ነበር። ሲኖዶስን የፈጠረው ችግር መኖር ነው። ችግሮችን ለመፍታት ነው።  የቅዱስ ሲኖዶስ ዋነኛ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የአንድነቷ መገለጫ ነው፡፡ በየጊዜው በሚወለዱ ክስተቶች ዶግማዊ ቀኖናዋ ሥርዓቷ ትውፊቷ እንዲሁም አስተዳዳሯ እንዳይፈታ መጠበቂያ ነው፡፡ በዚህም በመሠረት እምነቷ ላይ ጥያቄ ሲነሣ ማብራሪያ መስጠት አዳዲስ አስተምህሮዎች ሲመጡ በዶግማዊ መሠረት ማረቅ ማቅናት የጾም የጾሎት ሥርዓትን መሥራት ልጆቿን የሚመሩ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መሾም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋነኛ ተግባራት ናቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባርና ኃላፊነት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነቶች መካከል፡:-  ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት ይመራል፤ ይጠብቃል፡፡ ሕጎችንና ደንቦችን ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ይሽራል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አጠቃላይ የምጣኔ ሀብትና የሙዓለ ንዋይ አስተዳደር ደንቦችን ያወጣል፡፡ ዓመታዊውን የቤተ ክርስቲያን በጀት ያጸድቃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን  አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲሁም የተቋማትን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል፡፡ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በማስፋፋት ምእመናን እንዲበዙ ያደርጋል፤ የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያስተምራል ያስፋፋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትንና የሚኖራትን ግንኙነት ከሃይማኖትና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር እየገመገመ ያስፋፋል ያጠናክራል፡፡ (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17) መ/ር ንዋይ ካሳሁን
1 1076Loading...
05
Crews battling fire at historic St. Theodosius Orthodox Cathedral in Cleveland
1 1670Loading...
06
መቶ ዓመት ያስቆጠረው በኦሃዮ ግዛት ክሊቪላንድ Cleveland የራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት።
3240Loading...
07
https://www.wkyc.com/article/news/local/cleveland/fire-st-theodosius-orthodox-cathedral-cleveland-tremont/95-a01863fa-e5ae-4ff5-9a1d-43500b081e79
3240Loading...
08
የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሊመርጠ የ30 ቀን ጾም አውጀዋል። ሦስት እጩዎች ቀርበዋል። ምርጫው የዩክሬን ኦርቶዶክስ መገንጠልን ተከትሎ ፓለቱካዊ ጫና እንዳለ ገልጸው እመቤታችን ትረዳቸው ዘንድ ነው ሱባኤ የያዙት። ኦርቶዶክሳውያን በዓለም ደረጃ በሁሉም ሀገር ራሽያን ሳይጨምር ከፍተኛ ውጥረት ላይ ናቸው።
1 8236Loading...
09
"ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ" ሉቃ.22:31
1 6811Loading...
10
Christ is risen, Truly He is risen
1 5671Loading...
11
አብይ መግለጫችንን ይቁጠር!!
2 2931Loading...
12
2T3B6RFV6RW052871
11Loading...
13
Media files
2 57214Loading...
14
Media files
2 3515Loading...
15
"የዘራህው ካልሞተ አይነሳም"  1ቆሮ  15:36  ቅዱስ ጳውሎስ ትንሣኤን ያስረዳበት ትምህርት ነው። ከሞት በኋላ ትንሣኤ እንዴት እንደሚኖር።  አንዳንድ ሰው እግዚአብሔርን በአእምሯቸው ካልሳሉ ላያምኑ አይፈልጉም። እግዚአብሔር ደግሞ በሰው አእምሮ የሚረዳ አይደለም።  የስንዴ ዘር ከውጭ እስከ ሆነ ድረስ ደረቅ ወይም ሙት ነው። መሞቱን የምናውቀው እንቅስቃሴ ስለሌለው ነው። እንቅስቅሴ የህይወት ምልክት ነው። እንቅስቃሴ ከሌለ ሙት ነው። ካልተነፈስኩ ሞቻለሁ ማለት ነው። ከተንቀሳቀስኩ አለሁ ማለት ነው።  ይህ ዘር ካልቀበርከው ሕያው መኾን አይችልም። እንደ ቀበርከው ሕያው መኾን ይጀምራል ሕያው ነው። ካልቀበርከው ሕያው አይሆንም። ሙት ነው።  የምንወዳቸውን ስንቀብራቸው ሕያው መኾን ይጀምራሉ። በምድር ሳለን የሞቱ ዘሮች ነን። የሚንቀሳቀስ ዘር ነን። ስንቀበር እንኖራለን። እንደ ዘሩ። አፈር ሲጫነን ሕይወት እንጀምራለን።  አንድ ፍሬ ሲዘራ ብዙ ዘር ያፈራል። የምታገኘው የዘራህውን አይደለም እጥፍ ነው። ለቀበርነውን ሰው ሁሌ እናለቅስለታለን። ትክክል አይደለም። የምናምን ከሆነ የትንሣኤ ልጆች ነን። ለተነሣ ሰው አናዝንም። ስቀበር ሕያው ነኝ። ስኖር ሙት ነኝ።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
2 37012Loading...
16
https://youtu.be/Q-a0HEWn3FM?si=v_e1B9dRcd2Ggqim
1 7780Loading...
17
ሃምሳው ቀናት  ሃምሳው ቀናት እንደ አንድ ቀን ሆነው ይታያሉ። ረቡዕና ዓርብ ሳይቀር አይጾሙም። ጠዋት ይቀደሳል፣ በጠዋት ይበላል። በሃምሳው ቀን ጾም የለም። የጾም ቀኖና አይሰጥም።  እነዚህ ሃምሳ ቀናት ወጪ ገቢ በሆነው ወይም ሂያጅ linear ሓላፊ በሆነው አሁን ባለንበት ቀን አቆጣጠር Chronos በሆነው ጊዜ ሲታዩ ከሰኞ እስከ እሑድ እንዳሉት ቀናት ይኖራቸዋል  እንጂ በቤተ ክርስቲያን ወይም በትንሣኤ የቀን አረዳድ የማያልፈው ጊዜ (Kairos) ማሳያ ናቸው።  ይኽ ዘመን አልፎ ከትንሣኤ በኋላ መምሸት መንጋት የጊዜ መፈራረቅ የለም ሰኞ ማክሰኞ የሚባል ቀን የለም። አንድ ሕይወት ነው የሚኖረው። ከትንሣኤ በኋላ ያሉት ሃምሳ ቀናት የዚያ ዘለዓለማዊ ሕይወት ማሳያ ናቸው።  ሃምሳው ቀን ከትንሣኤ በኋላ ያለውን ሕይወት በጥቂቱ እየቀመስን ነው። “ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን” 2 ቆሮ.5:5  መያዥ ማለት ቀብድ ነው። ከዋጋው ያነሠ ሆኖ እቃውን ለመግዛት ማስያዣ ነው። ቀብድ የከፈለ ሰው ሙሉ ዋጋውን ከፍሎ እቃውን ይወስዳል። ቀብድ መክፈል እቃውን ለመግዛት ማረጋገጫ ነው። ዕቃውን ካልገዛ የከፈለው ቀብድ ይቀርበታል።  ክርስቶስ ከሞት በኋላ ለሚሰጠን ሕይወት ማረጋገጫ ሰጥቶናል። ለዚያ ሕይወት ማሳያ አንዱ ከትንሣው በኋላ ያለው የሃምሳው ቀን ነው። ትንሣኤ የሥጋ ትንሣኤ መያዣ ነው ትንሣኤ የሁሉም ነገር መሠረት ነው። ያለ ትንሣኤ ክርስትና አይኖርም ነበር። “ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት” 1.ቆሮ.15:17 ክርስትናችን የተመሠረተው በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ ነው። ወደ ክርስትና የምንገባበት በር ጥምቀት ነው። የምንጠመቀው በሞቱና በትንሣኤ ልንሳተፍ ነው። ወደ ውኃው ስንገባ ሞት ወይም መቀበር ነው። ስንወጣ ትንሣኤ ነው። “እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን” ሮሜ.6:4 ሞትና ትንሣኤውን እንመሰክራለን የመጠመቂያው ገንዳ (ቦታ) ጎልጎታ ነው። ጌታ ሞቶ ባይነሣ ኖሮ ጥምቀት የለም ነበር። የተጠመቅነው በሞቱና በመነሣቱ ነው።  የምንቀበለው ሥጋና ደም በሞቱና በትንሣኤው የተመሠረተ ነው። ባይሞትና ባይነሣ ኖሮ ሥጋና ደሙን አይሰጠንም ነበር። ሥጋው መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው ነው። ሥጋውን በመስቀል ላይ የሰጠን ስለ ሞተ ነው። ሞትን ድል አድርጎ የተነሣ ስለሆነ እንቀበለዋለን። ሞቶ ባይነሣ ግን አንቀበለውም ነበርም።  ሞት ይዞት ያላስቀረው ሕያው ስለሆነ ሞት ሊይዘው ያልቻለ ሕያወ ባሕርይ ስለሆነ ሕይወትን የሰጠን ስለሆነ የእርሱን ሥጋ እንደበላለን ደሙን እንጠጣለን። ሞትን ድልን አድርጎ ስለተነሣ ሕይወት ነው። ሞቶ ቢቀር ኖሮ  ሥጋውን ማን ይበላል ቢበላስ ምን ይጠቀማል?።  ሞትን ድል የሚያደርግ ሕይወት ስለሆነ የሞት መድኃኒት ስለሆነ The medicine of immortal “ኢመዋቲነትን የሚሰጥ ዘር” አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ።  ክህነት መሠረቱ ትንሣኤ ነው። በይሁዳ ምትክ ሰው ሲመርጡ መለኪያው የትንሣኤ ምስክር መሆንን ነው። “ስለዚህ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ፥ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ ከእኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፥ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል” ሐዋ.1:21  ክህነት ያስፈለገው ሞትና ትንሣኤውን መመስከር ነው። መምህራን ያስፈለጉትም ለዚሁ ነው።  ተክሊል መሠረቱ የክርስቶስ  ሞትና ትንሣኤ ላይ ነው። ጋብቻ ሊፈጽሙ የወሰኑ በአንድነት የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም በሚወስኑ አንድ ወንድና አንዲት ሴት ጥንዶች በጸሎት ከብረው ሥጋወደሙን ተቀብለው አክሊል ደፍተው ጋብቻ የሚፈጽሙት በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ላይ ነው። የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በተግባር ለመኖር ነው።  ክርስቶስ ሞትን ድል እንዳደረገ እናንተም በዚኽ ዓለም ያለ ውጣ ውረድን ክርስቶስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶ ድል እንዳደረገ እነርሱም ድል ያደርጉ ዘንድ አክሊል ይደፋሉ። ይኽ አክሊል ክርስቶስ የደፋው የአሸናፊነት  አክሊል ነው።  የክርስቶስ አክሊለ ሶክ ከብረት የጠነከረ ከጠንካራ የእንጨት እሾኽ የተሠራ ነው። የቤተ ክርስቲያን አክሊል የሚዋጋ ነው። ትዳር የደስታ ሕይወት አይደለም። ለብቻ ሆኖ የሚከብድን መስቀል ሁለት ሆኖ መስቀሉን ተሸክሞ መክበር ሕይወት ነው። የሚደፋው አክሊል የካሜራ ጌጥ አይደለም። አክሊለ ሶክ ነው።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
2 10214Loading...
18
Media files
1 9011Loading...
19
"የአማራ ክልል ጦርነት ከሰኔ መጨረሻ እስከ ሐምሌ መጀመሪያ ባለው ጊዜ ውስጥ ይቆማል" እኔ
1 8611Loading...
20
Media files
1 9270Loading...
21
https://rumble.com/v4xso4f-298629663.html
1 0671Loading...
22
https://youtu.be/5nbtGbWGpLU?si=522BJuD7RrQiDX9_
2 3223Loading...
23
ርክበ ካህናት የካህናት መገናኛ ማለት ነው። ትንሣኤ በዋለ በ 25 ኛው ቀን ጳጳሳት ጉባኤ ያደርጋሉ። ፍትሐ ነገሥት ቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ጊዜ በዓመት እንዲገናኙ ያዛል። በትንሣኤ በዋለ በ25ኛው ቀን የሚገናኙት ጌታ በተነሣ በ 25 ኛው ቀን በጥብርያዶስ ወንዝ ዳር ተገልጦ የታየበት የመጀመሪያው ቀን ነበር። "ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው" ዮሐ.21:1 መ/ር ንዋይ ካሳሁን
2 2587Loading...
24
ወሳኝ ጥያቄ ጌታ ከትንሣኤ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ድረስ በተለያየ ጊዜ ሲገለጥላቸው ከመቅደስላዊት ማርያም እንደ ሌሎች መጽሐፍት ደግሞ ከእመቤታችን ጀምሮ ሲገለጥላቸው አያውቁትም ነበር። በተደጋጋሚ እርሱ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እየሰጣቸው ይነግራቸው ነበር። ለምንድነው ያላወቁት?
2 3142Loading...
25
https://youtu.be/5nbtGbWGpLU?si=QXYs9YInkRqr6v7a
2 4601Loading...
26
Media files
2 9568Loading...
27
https://youtu.be/qIuQS8qY_t0?si=dWapc9k_h9TvlzwP
2 3811Loading...
28
https://youtu.be/qIuQS8qY_t0?si=hVOv2iZjdRa1t23p
10Loading...
29
https://youtu.be/qIuQS8qY_t0?si=hVOv2iZjdRa1t23p
10Loading...
30
ጌታችን በጥብርያዶስ ሰሐዋርያት  ተገለጠሳቸው “ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው፤  እንዲህም ተገለጠ፦ ስምዖን ጴጥሮስና ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ከገሊላ ቃና የሆነ ናትናኤልም የዘብዴዎስም ልጆች ከደቀ መዛሙርቱም ሌሎች ሁለት በአንድነት ነበሩ።  ስምዖን ጴጥሮስ፦ ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ አላቸው። እነርሱም፦ እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ በዚያችም ሌሊት ምንም እላጠመዱም” ዮሐ.21:1-3 “ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና ተገለጠላቸው” የትንሣኤ ዕለትና የዳግም ትንሣኤ ከተገለጠላቸው በኋላ በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ለሦስተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ማለት ነው። ጌታችን ሞትን አሸንፎ ከተነሣ በኋላ በደቀ መዛሙርቱ መካከል የተገኘው ሦስት ቀን ብቻ ነው። አርባው ዕለታት እስከሚፈጸሙና እስከሚያርግበት ቀን ድረስም ከዓይናቸው ተሰውሮ ነው የቆየው። በሥጋ ተገልጦ የሚሠራውን ሥራ ፈጸሟልና። መሰወር ከትንሣኤ በፊት በተወሰኑ ቀኖች እንደ ተደረገ። ዮሐ 8÷59  መገለጥም ከትንሣኤ በኋላ በተወሰኑ ቀኖች ተደረገ። ሉቃ 24÷36 ዮሐ 20÷19፡26 ም21÷1። የዘብዴዎስ ልጆች ያለው ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው። ማቴ 4፥21 ማር 1፥19:20። የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ጌታችንን ከመከተላቸው በፊት የስምዖን ጴጥሮስ ባልንጀሮች (ጓደኞች) ነበሩ ሉቃ 5፥10 አሣ በማጥመድ ይተባበሩ ነበርና። “ከደቀ መዛሙርቱም ሌሎች ሁለት” የሚለው የሁለቱ ደቀመዛሙርት ስም አልተገለጠም። በአንድምታው ትርጓሜ “ከሰብአ አርድእት ሁለቱ ሉቃስና ኒቆዲሞስ አንድም ይሁዳና ያዕቆብ በአንድነት ሳሉ ታያቸው” ተብሎ ተገልጾአል። “ስምዖን ጴጥሮስ አሣ ላጠምድ እሄዳለሁ አላቸው” ዮሐ.21:3 ደቀ መዛሙርት ሐዋርያት ከጌታችን ጋር ሳሉ ሕዝቡ ወደ ሙዳየ ምጽዋት በሚያስገቡት ገንዘብ እየገዙ ይበሉ ነበር። ጌታችንም እንጀራውን እያበረከተ ይመግባቸው ነበር። ከጌታችን ሞት በኋላ የሚመገቡት ስለአጡ ጴጥሮስ ወደ ቀደመ ሥራው “አሣ ወደ ማጥመድ” መመለስ ፈልጓል። ሌሎችም ተከትለውት ወደ ጥብርያዶስ ባሕር ሄዱ። “በዚያች ሌሊት ምንም አላጠመዱም” ቊ3 አሣዎች ወደወጥመዳቸው (መረባቸው) እንዲገቡ ኢየሱስ ክርስቶስ አልፈቀደም “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ም 15፥5 ብሏቸው ነበር። ስለወደፊት ኑሮአቸው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ሲገባቸው በራሳቸው ፈቃድ አሣ ለማጥመድ ስለሄዱ በራሳቸው ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ለማስረዳት አሣዎችን ወደ መረባቸው እንዳይገቡ ከለከለ።  “በነጋም ጊዜ ኢየሱስ በባሕር ዳር ቆመ ደቀመዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም። ኢየሱስም ልጆች ሆይ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው። የለንም ብለው መለሱለት እርሱም መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ አላቸው። ሌሊቱን ሁሉ ደክመን ምንም ያገኘነው የለም በትእዛዝህ ግን እንጥላለን? ስለዚህ ጣሉት በዚህ ጊዜ ከአሣው ብዛት የተነሣ ሊጎትቱት አቃታቸው። ኢየሱስ ይወደው የነበረውም ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ጌታ እኮ ነው አለው። ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ጌታ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዕራቁቱን ነበርና ልብሱን ታጥቆ ወደ ባሕር ራሱን ጣለ። ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከምድር ሁለት መቶ ክንድ ያህል እንጂ እጅግ አልራቁም ነበርና አሣ የሞላውን መረብ እየሳቡ በጀልባ መጡ” ዮሐ.21: 4-8 “ልጆች ሆይ አንዳች የሚበላ አላችሁን”?  የሚበላ ነገር እንደሌላቸው ያውቃል። መረባቸውም ከአሣው ጋር እንዳልተገናኘ ያውቃል። አንዳች የሚበላ ነገር ፈልገው የጥብርያዶስን ባሕር እየተማጸኑ ማደራቸውን ስለአወቀ ነው ወደ እነርሱ የሄደው። ራሱን ሊገልጥላቸው ስለፈለገ፣ አሣዎችንም ወደ መረባቸው ሊያስገባላቸውና የተዘጋጀውን ምግብ ሊመግባቸው ስለ ፈቀደ የሚሰጣቸውን ስጦታውን ስጡኝ በማለት ይጀምራል።  “መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት ታገኙማላችሁ”ቀኝ የመልካም ነገር ምልክት ነው። የሚከተሉትን ጥቅሶች እንይ “ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም” መዝ 141፥4 “የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ” ሕዝ 21፥22 “በቀኝህም የዘለዓለም ፍስሓ አለ” መዝ 15፥11 “ቀኝህጽድቅን የተሞላች ናት” መዝ 47፥10 “ወዳጆችህ እንዲድኑ በቀኝህ አድን” መዝ 59፥5 “ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን” መዝ 89፥12/፣ “በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ” ኢሳ 41፥10 እንዲል።  ደቀ መዛሙርቱም በጌታችን ትእዛዝ መሠረት መረቡን በታንኳይቱ በስተቀኝ ጣሉት።ጌታችን እንደ ተናገረ በታንኳይቱ በስተቀኝ የተጣለው መረብ አሣዎችን ሞልቶ ወጣ። “ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር” የዘብዴዎስ ልጅ ዮሐንስ መሆኑ ተረጋግጧል። ዮሐንስ እራሱን የሚገልጠው ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር፣ ሌላው ደቀ መዝሙር፣ ያም ደቀ መዝሙር ወዘተ በማለት ነው። ዮሐንስን ለመግለጥ ደቀ መዝሙር የሚለው ቃል በዚህ ወንጌል አሥራ አራት ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል።  @የዮሐንስ ወንጌል ትርጉም (መ/ር ስቡሕ አዳምጤ) መ/ር ንዋይ ካሳሁን
2 46714Loading...
31
Media files
2 0643Loading...
32
Media files
2 3366Loading...
33
Media files
2 3411Loading...
34
ዘንግቻት ነገ አንድ "ሹመት" ቢጤ አለች። ኮታ ለመሙላት።
2 5582Loading...
የኦሲኤን ቴሌቪዥን እውነታዎች ከኦሮሚያ ቤተክህነት ምሥረታ ጋር የቤተክርስቲያን መዋቅር ለማፍረስ በመናፍቃንና ፖለቲከኞች እርዳታ የተመሠረተ ነው። ከስምምነቱ በኋላ + ከኢኦቲሲ ቲቪ ጋር በአንድ ቦርድና በአንድ ሥራ አስኪያጅ እንዲመራ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የወሰነው በቋሚ ሲኖዶስ ተሽሮ በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን ሥር እንዲሆን ተደርጓል። + ለተቋሙ 8 ሚሊዩን ብር በጀት  የተለቀቀ ሲሆን ገንዘቡ በሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን አንቀሳቃሽነት ያለ ምንም ሰነድ ሲባክን ቆይቷል። + ኦሲኤን 2 ካሜራ አንድ ኮምፒዩተር የተመዘገበ ሀብት ያለው እና 2 ካሜራ ማን 1 ኤዲተር 2 ጋዜጠኞች አንድ ዳይሬክተር በድምሩ 6 ሠራተኞች ቢኖሩትም ከ50 በላይ የቀድሞ የኦሮምያ ቤተክህነት ደጋፊዎች እና የቀሲስ በላይ ዘመዶች የቤት ሠራተኞችና ጥበቃ ማይቀር በሠራተኝነት ተመዝግበው ያለ ፔሮል ደመወዝ በጥሬ ገንዘብ ከባንክ ዝውውር ውጪ በስማቸው ወጪ ሲደረግ ቆይቷል። +ከኢኦቲሲ ጋር ሲዋሀድ በቋሚነት ትቀጠራላችሁ በሚል ብዙዎች ስማቸው ብቻ ተመዝግቦ ደመወዝ ሣይከፈላቸው እንደ ሠራተኛ እንዲመዘገቡ ተደርጓል። + ከጠቅላም ቤተክህነት የተሠጠው የሥራ ቦታ ለፓርኪንግና ስቶር በማከራየት ገቢው ለሊቀ አእላፍ በላይ ሲቀበል ቆይቷል። + ቴሌቪዥን ጣቢያው ከስብከት እና መግለጫ ውጪ አንድም መደበኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የለውም + ቴሌቪዥን ጣቢያው ባሉት ሁለት ካሜራዎች ቅዳሜና እሑድ የሠርግ ቀረጻ ሥራ በማከናወን ሠራተኞች የግል ቢዝነስ ይሠሩበታል። በአጠቃላይ ተቋሙ የግል እንጂ የቤተክርስቲያን ያልሆነ ሠራተኞቹ የተባሉትም ከሙያው ጋር የማይገናኙ የበላይ መኮንን ዘመዳ ዘመዶች ናቸዉ። + ቋሚ ሲኖዶስ አጣሪ በመድብም ቄስ በላይ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሳይጣራ ቀርቷል ይኸው አጀንዳ ሲኖዶሱ የሚወያይበት ይሆናል ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እውነታውን እንዲያውቁ ቢደረግ።
Show all...
👍 12🤔 2👎 1
ሲኖዶስ ሲኖዶስ ማለት ጉባኤ፣ አንድነት፣ ኅብረት፣ ማለት ነው፡፡ “አሐተኔ፣ ርክብ” የሲኖዶስ ተለዋጭ ቃላት ናቸው፡፡ ርክበ ካህናት የሚለውን ርክበ ጳጳሳት በማለት ሲኖዶስ ጋር በትርጉም ይመሳሰላል።  ይኹን እንጂ ርክበ ካህናት ሲባል ጳጳሳትን ብቻ የሚወክል ሳይሆን ካህናት የወል መጠሪያ ቢሆንም  ትርጉሙን ለጳጳሳት ብቻ ተሰጥቷል።  በሕገ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜው ቅዱስ ሲኖዶስ ማለት፡- “ቅዱስ ፓትርያርክ፣ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የሚገኙበት ዐቢይ ጉባኤ ሆኖ ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ሕግ አውጪና ወሳኝ አካል ነው”። (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 2. 2)፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ደግሞ ሲኖዶስ (ጽርእ) ግሪክኛ መኾኑን ጠቅሰው “ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ ዩጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር እከባ ስብስብ) መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ (ገጽ 875)  ቅዱስ ሲኖዶስ “ብሂል (ትርጉም) ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የጽርዕ (የግሪክ) ሆኖ ትርጉሙ ዐቢይ ጉባዔ ጳጳሳት ወይም የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ጉባኤ ማለት ነው።  (Synod's Ecclesiastical Assembly) አቡነ መልከ ጴዴቅ (ሊቀ ሥልጣናት ሃብተ ማርያም ወርቅነህ) ያልታተመ ጽሑፍ። (ገጽ 1) ብሂል (ትርጉም) ሲኖዶስ ማለት ቃሉ የጽርዕ (የግሪክ) ሆኖ ትርጉሙ ዐቢይ ጉባዔ ጳጳሳት ወይም የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ১৭৭ ১৯৮ ১৫: (Synod's Ecclesiastical Assembly) ሲኖዶስን ቅዱስ ያሰኘው የተሰበሰበት ዓላማና የቤተ ክርስቲያን በየበላይ መዋቅር መኾኑ ነው።  ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የአንድነት መገለጫ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ የሐዋርያት መንበር ወራሽ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን ኅብረታዊትና ጉባኤያዊት መሆን ማሳያ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የእግዚአብሔር መንግሥት አስፋፊዎች እንጂ የመንደር ተወካዮች ስብስብ ማለት አይደለም።  አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስለ ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ትውፊት እና አስተዳደር በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የሚመክሩበት ጉባኤ ነው።  የቅዱስ ሲኖዶስ አጀማመር በሐዋርያት ዘመን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተነሣው ጥያቄ ወይም ችግርን ለመፍታት በተደረገ ጉባዔ ነው።  ይኽውም ቤተክርስቲያን ከይሁዲነት ወደ ክርስትና ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና በመጡ አማኞች መካከል የባሕል ልዩነት ስለነበር ይኽንን መከፋፈል ለማስቀረት የተደረገ ጉባዔ ነው። በአራቱም መአዘን ለአገልግሎት ተበትነው የነበሩ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም መንበር በነበረው አረጋዊው ቅዱስ ያዕቆብ መሪነት በ50 ዓ.ም ሐዋርያት ከያሉበት መጥተው ጉባዔ አደረጉ።  “አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎስና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ።” ሐዋ.15:1 በዚኽ ጥያቄ መሠረት “ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ።” በማለት ስለመጀመሪያው ጉባኤ (ሲኖዶስ) ይነግረናል። ሐዋ.15:6 ከሐዋርያት ቀጥሎ የተነሡ ሐዋርያነ አበው በአብያተ ክርስቲያናት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ይሠበሰቡ ነበር። ሲኖዶስን የፈጠረው ችግር መኖር ነው። ችግሮችን ለመፍታት ነው።  የቅዱስ ሲኖዶስ ዋነኛ ዓላማ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የአንድነቷ መገለጫ ነው፡፡ በየጊዜው በሚወለዱ ክስተቶች ዶግማዊ ቀኖናዋ ሥርዓቷ ትውፊቷ እንዲሁም አስተዳዳሯ እንዳይፈታ መጠበቂያ ነው፡፡ በዚህም በመሠረት እምነቷ ላይ ጥያቄ ሲነሣ ማብራሪያ መስጠት አዳዲስ አስተምህሮዎች ሲመጡ በዶግማዊ መሠረት ማረቅ ማቅናት የጾም የጾሎት ሥርዓትን መሥራት ልጆቿን የሚመሩ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መሾም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋነኛ ተግባራት ናቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባርና ኃላፊነት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነቶች መካከል፡:-  ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት ይመራል፤ ይጠብቃል፡፡ ሕጎችንና ደንቦችን ያወጣል፣ ያሻሽላል፣ ይሽራል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን አጠቃላይ የምጣኔ ሀብትና የሙዓለ ንዋይ አስተዳደር ደንቦችን ያወጣል፡፡ ዓመታዊውን የቤተ ክርስቲያን በጀት ያጸድቃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን  አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲሁም የተቋማትን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል፡፡ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በማስፋፋት ምእመናን እንዲበዙ ያደርጋል፤ የክርስቶስን ወንጌለ መንግሥትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ያስተምራል ያስፋፋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትንና የሚኖራትን ግንኙነት ከሃይማኖትና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር እየገመገመ ያስፋፋል ያጠናክራል፡፡ (ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 17) መ/ር ንዋይ ካሳሁን
Show all...
👍 6
30:35
Video unavailableShow in Telegram
Crews battling fire at historic St. Theodosius Orthodox Cathedral in Cleveland
Show all...
መቶ ዓመት ያስቆጠረው በኦሃዮ ግዛት ክሊቪላንድ Cleveland የራሽያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram

38👍 4
"ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ" ሉቃ.22:31
Show all...
👍 14 8