www.zemaryhawaz.com #zemarihawaz #ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ #zemari hawaz tegegn
Open in Telegram
ይህ የዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ telegram channel ነው። በዚህ ቻናል ➟ በየቀኑ አዳዲስ ዝማሬዎችን ➟ ቆየት ያሉና ነባር ዝማሬዎችን ➟ የተለያዩ አስተማሪ ፅሁፎችን ያገኛሉ። #ሊያድነን_ከሰማያት_የመጣው #የእግዚአብሔር_ልጅ_መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ይወደናል። @HawazTegegn @HawazTegegn
Show more5 487
Subscribers
+424 hours
-67 days
+530 days
Posts Archive
በ Audio እነሆ
እንካን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም በጤና አደረሳችሁ::
መጽአ ቃል የጥምቀት ዝማሬ አዲስ ዝማሬ ዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ New song zemari Hawaz Tegegn . መጽአ ቃል እም ደመና ዘይብል::
https://youtu.be/57x7jDFFegQ
የመጨረሻው መጀመሪያ... ክፍል አንድ ... የተወለደላችሁ ሁሉ ሼር በማድረግ አብራችሁኝ አገልግሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ::
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሄም አዲስ መዝሙር በዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ New song zemari Hawaz Tegegn
https://youtu.be/15mnxUINFcY
ክፍል 2 የዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ቁጥር 4 የዝማሬ አልበም ምርቃት እና የመዝሙር ድግስ ሙሉ ፕሮግራም ቪዲዮ:: zemari hawaz tegegn
https://youtu.be/RWhc-OrnCrU
የዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ቁጥር 4 የዝማሬ አልበም ምርቃት እና የመዝሙር ድግስ ሙሉ ፕሮግራም ቪዲዮ:: zemari hawaz tegegn
https://youtu.be/Ni3XDH7v0_I
ባለምሕረት ባለይቅርታ
የፍቅር ንጉስ የፍቅር ጌታ
አለህ በውስጤ ዛሬም ከእኔጋ
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሆነኸኝ ጸጋ
ፍቅር ፍቅር ነህና
በህልውናህ ዛሬም ልፅናና
ፍቅር ፍቅር ነህና
ስለአብሮነትህ መንፈስ ቅዱስ ሆይ አለኝ ምስጋና
ወደተርሴስ ነጉዶ እምቢተኛው ልቤ
ስሸሽ ከፍቃድህ ሲናወጥ መርከቤ
በአሳንበሬው ጀልባ መከርኸኝ በጭንቁ
ያመነህ ተውጦ አይቀርም በጥልቁ
እኔን እኔን ማየትህ ሰው እንዳጣ በምድሩ
ዮናስ ነፍሴ ባይገባው የምሕረትህ ቀመሩ
ሳትተወኝ ለራሴ ሳይታክትህ ውድቀቴ
ስታቀናኝ ኖረሃል ሳይፀንህ እኔነቴ
በጥፋት ዘመን ላይ ሆንኸኝ ከለላ
ግራ ቀኝ ከብኸኝ ከፊትና ኋላ
ድብቅ ጦር ጥላዬ መሸሻ ድጋፌ
አሻግረኸኝ አለሁ ውጊያውን አልፌ
ሚገባኝ ሆኜ አይደለም ያዳንከኝ ከዚያ ሁሉ
እንደ እኔ ስህተት ብዛት ባሰጠመኝ ማዕበሉ
ተፍገምግሜ ሳልወድቅ ቀደምክልኝ ከፊቴ
አቅፈኸኝ አጽናናህኸኝ ጵራቅሊጦስ አባቴ
ሲያማትሩ አይኖቼ ስራመድ ለአመፃ
እጆቼ ሲያነሱ የኃጢአት ፍላፃ
ከፈቃድህ ስጎድል ሲጥለኝ ፈቃዴ
ኣልጨከንክብኝም ምረኸኛል ውዴ
የአባትነት ትዕግስትህ ከምድር ገዝፎ ከሰማይ
ኦ ስትችልበት ማፍቀር እንደእናት ከእናት በላይ
በበትርህ ተገስጬ ምርኩዝሕ አፀናንቶኝ
በአብሮነት ህልውናህ ኖራለሁ ሰላም መልቶኝ
እንዳጣህ አልፈልግም እወድሃለሁ አምላኬ
ራሴን ሰጥቼሃለሁ በፍቅርህ ተማርኬ
የታተምኩብህ ፀጋ ስለቤዛነት ቀኔ
ላሳዝንህ አልሻም ፍቅርህን አይቷል አይኔ
ፍቅር ፍቅር ነህና የተሰኘውን አዲሱን የዲያቆን ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝን ዝማሬ ለቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦቻችን እነሆ በ AUDIO ይህን የመጽናናት ዝማሬ ለብዙዎች ሼር እናድርገው::
ሙሉ ቪዲዮ ክሊፑን ለማግኘት 👇👇👉👉👉💽📲 https://youtu.be/4SUzXkyLTdc?si=W9ebdt0ns3D2Za87
ምሕረትህ እድሜው ስንት ነው ?
ይቅርታህስ መቼ ያበቃል ?
አትባልም !! የእህቴን የዘማሪት ዘመናይን አዲሱን ዝማሬ ተጋበዙልኝ and please share it for all
ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ከተዘመሩ ዝማሬዎች መሃል እጅግ ተለይቶ የማረከኝ ዝማሬ ነው ። በጣም ጥልቅ ትርጉም ያላቸው ስንኞች ይያዘ በንስሃ በምስጋና በፍቅር በእግዚአብሔር ፊት ልንሆንበት ምንችል ዝማሬ ነው ። እህቴ ዘማሪት ዘመናይ ጎሳዬ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልሽ ድካምሽን ሁሉ እርሱ ይቁጠርልሽ ። አብሬሽ በዚህ ዝማሬ ስላገለገልኩ ደስተኛ ነኝ ፣ በጣም ድንቅ ዝማሬ ይዘሽልን መጥተሻል። ይህንን ቻናል ከስር ባለው ሊንክ Subscribe በማድረግ አብረናት እንሁን በተከታታይ የሚለቀቁ 14 ዝማሬዎች ሌሎችም ዘማርያን ሚሳተፉበት አለ ገና አብረን እንሁን በእህታችን ቻናል ላይ :: https://youtube.com/@zemaritzemenaygosayeofficial?si=6bld-JHPBW5Xj-kU
