cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Show more
Advertising posts
1 351 100
Subscribers
+52724 hours
+3 8987 days
+17 06330 days
Posts Archive
ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከአሁን ቀደም ሲጠቀምባቸው የነበሩ ትኬቶችን (ህትመት) ሙሉ በሙሉ በአዲስ እንደሚለወጥ አሳውቋል። ይህ አዲሱ ትኬት (ህትመትታ #ከነገ ሀሙስ 19/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ ይውላል። ከአሁን ቀደም ከነበሩት በዋጋ ወጥነታቸው፣ በቀለማቸው እና በሚስጥራዊነታቸው የተለዩ ናቸው ተብሏል። ለአገልግሎት የሚውሉ ህትመቶች (ትኬቶች) ባለ 5 ፣ ባለ 10 ፣ ባለ 15 ፣ ባለ 20ና ባለ 25 የዋጋ ተመን (ብር) ያላቸው ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ፦ - የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት እና - የሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ተዋህደው በአዋጅ ቁጥር 74/2014 የተቋቋመ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#CBE የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ገንዘቡን እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል። ባንኩ ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር። በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መልሰዋል ብሏል። 5166 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ ከወሰቡትን ገንዘብ በከፊል ተመላሽ ያደረጉ ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ ቀሪውን ገንዘብ አልመለሱም ሲል ገልጿል። ባንኩ ወደ ቀጣዩ #ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ቀሪውን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ገንዘቡን የማይመልሱ ከሆነ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል። እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን #የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ፦ - ሙሉ ስማቸው - ፎቷቸው - በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት ይገለጻል ለሕዝብም ይፋ ይደረጋል ብሏል። ከሕግ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ #የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔር እና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎችም እንደሚወሰዱ በጥብቅ አስጠንቅቋል። ስም ዝርዝሩን በዚህ መልከቱ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/86375 @tikvahethiopia
Show all...
🤔 348😡 186 123👏 99😱 36😭 29🕊 22😢 17🥰 15🙏 10
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸውን ያለሆነ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወስደው በከፊል የመለሱ ወይም ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ያላደረጉትን 5,166 ግለሰቦች ስም ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል። ግለሰቦቹ ቀሪ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ይህንን የማያደርጉ ከሆነ ወደ ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚገባ ገልጿል። ስማቸውን ከፎቷቸው ጋር በማድረግ ህገወጥ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን ለህግ አካላትና ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል። @tikvahethiopia
Show all...
😡 121👏 66 25🤔 24😱 13🕊 5🙏 3
ራያ ላይ ምን እየሆነ ነው ? “ ህወሓት የፕሪቶርያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” - የአላማጣና አካባቢው አመራር የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚያነሱበት አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ አካባቢ ትላንትና " ህወሓት " ተኩስ መክፈቱን፣ በዚህም በሰው ሕይወት ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ሙድረሱን አካባቢውን ከሚያስተዳድሩ አመራሮች (ባለስልጣን) አንደኛው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አንድ የአካባቢው አመራር (ባለስልጣን) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ ራያ ላይ  አዲስ ነገር አለ። ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልፅ በመጣስ ራያ ላይ ጦርነት ከፍቷል ” ብለዋል። “ ቀን ላይ አንድ ሰው ሕይወቱ አልፏል። ሁለት ቆስለው ወደ ደሴ ሪፈር ተብለዋል። ደንበሩን በማለፍ የራያ አላማጣ ወረዳ አዳዲስ ቀበሌዎች ተቆጣጥሯል ” ሲሉ አክለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጦርነቱ የተከፈተው በምን ሰዓት ነው ? በዬት በኩል ነው የተከፈተው ? አሁን ተኩስ አለ ? በቁጥጥር ስር የሆኑት ቀበሌዎች እነማን ናቸው ? ከሰሞኑን ለጦርነት አመላካች ጉዳዮች ነበሩ ? ሲል ለአመራሩ ጥየቄ አቅርቧል። አመራሩም ፣ “ ጦርነቱን የጀመሩት ሰኞ ሌሊት 6:00 አከባቢ ሲሆን፣ እስከ ቀን 6:30 ድረስ ነበር። መከላከያ ለራያ ምሊሻ ‘ወደ ኋላ ተመለሱ እነርሱም ይመለሳሉ’ በማለቱ ምክንያት ጦርነቱ ቁሞ የራያ ምሊሻ ወደ ኋላ ቢልም TDF መልሶ ቦታውን ተቆጣጥሮታል ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ተኩሱ የተጀመረበትን ልዩ ቦታ በተመለተ በሰጡት ምላሽም ፣ “ የተጀመረበት ቦታው ‘ጮጓራ’ ይባላል። የራያ አላማጣ ቦታ ነው። አሁንም እሱን በማለፍ ወደ ‘ኮስም’ የሚባል አከባቢ እየተጠጉ ነው። ተጨማሪ ኃይልም እያስጠጉ ይገኛሉ ” ብለዋል። የአካባቢው አመራር የተኩሱን መነሻ በገለጹበት አውድ ፣ “ የዚህ ዋናው መንስኤ አማራ ክልል #ወልቃይት እና #ራያ በስርዓተ ትምህርቱ ካርታ ላይ ተካተዋል በሚል በወጣው መግለጫ ነው ” ሲሉ አስረድተዋል። “ የራያ ህዝብ የዘመናት ትግሉ በህጋዊ መንገድ ፍትህ ማግኘት እንጂ ጦርነት አይፈልግም። እነሱ እየተከተሉ ደጋግመው እያቆሰሉት ነው ” ሲሉም አክለዋል። በህወሓት ተከፈተ ስለተባለው ተኩስ በትግራይ ክልል በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ አስታዳዳሪዎችን አግኝቶ የነበረ ሲሆን ስብሰባ ላይ እንደሆኑና ወደ በኃላ ማብራሪያ እንደሚሰጡን ገልጸዋል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፣ “ የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል " ማለቱ አይዘነጋም። አስተዳደሩ ፤ በአማራ ክልል መንግሥት በኩል በትግራይ ህዝብ ላይ ግፍ እና በደል ሲፈፀም እንደቆየ አሁንም እንደቀጠለ ገልጾ ክልሉ የሰላም ስምምነቱን የሚያናጋ ጠብ አጫሪ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሆነ ከሶ ነበር። የፌደራል መንግስት በካርታው ላይ ምንም አይነት እርማት እንዳልሰጠ ፣ የአማራ ሕዝብም ሆነ ሌለው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎን እንዲቆሙ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ ግን የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል " ሲል አስጠንቅቆ ነበር። መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
😭 631👏 294😡 205 162🕊 99😱 33🥰 18🤔 18🙏 18😢 17
የ3 አመቷን ህጻን አስገድዶ በመድፈር #ገድሎ ተሰውሮ የነበረ ተጠርጣሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ። ቢሊሱማ መሃመድ የተባለችን የ3 አመት ህጻን የእንጀራ ልጁን አስገድዶ በመድፈር ገድሎ ተሰውሮ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ መልካ ጀብዱ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የሟቿ ህጻን እናት ከባለቤቷ ጋር በትዳር መቀጠል ባለመቻላቸው ምክንያት ከተለያዩ በኃላ ወደ ሀሮማያ ከተማ በመሄድ ሌላ ባል አግብታ ህጻኗም ከእናቷ እና እንጀራ አባቷ ጋር ትኖር ነበር፡፡ ተከሳሹ የእንጀራ አባቷ ግለሰብ ለ15 ቀን በትዳር ከቆየ በኃላ ገና ምንም ነፍስ እንኳን ያላወቀችውን ህጻን አስገድዶ ደፍሮ መግደሉ ተገልጿል። ለ11 ወራት ያህል ተሸሽጎ የቆየው ተጠርጣሪው መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ጠዋት ከተሸሸገበት ወጥቶ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ  በቁጥጥር ስር ውሎ ለሀሮማያ ከተማ ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተጠቁሟል። ግለሰቡ ለምን ይችን ገና ነፍስ እንኳን ያላወቀች፣ ክፉ ደጉን የማትለይ ህፃን አስገድዶ እንደደፈረና እንደገደለ ሲጠየቅ " ሰይጣን አሳስቶኝ ነው " ማለቱን ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። Via @TikvahethMagazine
Show all...
😭 2459😡 747😢 79 74😱 46🙏 22🕊 19🤔 16🥰 14👏 3
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ እረፍት ለመውሰድ ወደ ቤተሰቦቹ አርባ ምንጭ ከተማ በሄደበት በድንገት ህይወቱ እንዳለፈ ተነግሯል። ህይወቱ ያለፈው ለሊት ላይ መሆኑ ተሰምቷል። ወደ አርባምንጭ የሄደው ያጋጠመውን መጠነኛ ጉዳት ተከትሎ እረፍት ለመውሰድ ነበር። የህልፈቱ ምክንያት " ድንገተኛ " ተብሎ ከተገለፀው ውጭ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም። ተጫዋቹ ባለትዳር ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር በስርዓተ ቁርባን ጋብቻውን የፈፀመው። የአለልኝ አዘነ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መጋቢት 18 በትውልድ ከተማው አርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ታውቋል። Via @tikvahethsport @tikvahethiopia
Show all...
😭 2498😢 158 94🕊 52🙏 32😱 20🥰 10😡 9🤔 8👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ልዮ የኪነ-ጥበብ ምሽት " አብሮነት ኢትዮጵያዊነት " የተሰኘ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት አ/አ ካዛንቺስ በሚገኘው በኢንተርኮኒቲኔታል ሌግዤሪ አዲስ ሆቴል ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከ9 ሰዓት ጀምሮ በአብርሃም  ግዛው  ኢንተርቴመንት አዘጋጅነት ይቀርባል። በእለቱ ፦ - መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ፣ - አባሣደር ዲና ሙፍቲ፣ - ዲያቆን መምህር ዳንኤል ሠይፈሚካኤል - ደራሲ ገጣሚ ፀሀፊ ተውኔትና ባለ ቅኔ አያልነህ ሙላቱ፣  - ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ ፣ - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ - ዶ/ር ዮናስ ዘዉዴ  - አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ - ጋዜጠኛና ደራሲ ጥበቡ በለጠ - አርቲስት ተስፋዬ ሲማ በእለቱ ግጥም ወግ መነባንብ ዳስኩር በሻሎም የባህል ባንድ ታጅበዉ ያቀርባሉ። መግቢያ 500 ብር የመግቢያ ትኬቱን ~ ለገሃር በጃፋር ቤተ መፅሀፍት ~ ብሔራዊ አይናለም ቤተ መፅሀፍት ~ በካዛንቺዝ ኢንተር ኮንትኔንታል ሌግዠሪ አዲስ ሆቴል ያገኙታል። 0930470847 ወይም 0912374014
Show all...
😡 68 65🙏 11😭 11🤔 6😱 4😢 4🕊 3🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
#ራታዝ_ብራንድ ራታዝBrand ጥራት ያላቸው ጫማዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በፈለጉት መጠን እኛ ጋር ያገኛሉ፤ እንዲሁም በየግዜው እቃ ስናስገባ እንዲደርሶ በቴሌግራም ገጻችን ቤተሰብ ሆነው ይከታተለሉ🔽 https://t.me/+OpJ4wNqSEqZhNTA8 አድራሻ ፦ አ.አ ቦሌ መ/ም አደባባይ ራክሲም ፕላዛ 3ኛ ፎቅ ሱ.ቁ 03። Free delivery 📱0911799616 ✉️@properties6 RATAZ:-thrive with us you will get greater value!
Show all...
8🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች  ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
Show all...
18🕊 1
“ የመሪጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው  ” - የዓይን እማኝ በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። አንድ ሟቾቹ መቀበራቸውን የተመለከቱ የዓይን እማኝ በሰጡት ቃል፣ “ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት። የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ ተፈጽሟል ” ብለዋል። “ ትላንት 3 ሰዓት ላይ ነው የተገደሉት። አንድ መሪጌታ ከእነባለቤቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋ፣ አንድ ዲያቆን ከእነባለቤቱና እህቱ ጋር 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት። የመርጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው ” ሲሉ አክለዋል። ገዳዮቹ ማን ናቸው ? የት ነው የገደሏቸው ? ሟቾቹ ከዚህ በፊት ዛቻና መስፈራሪያ ደርሷቸው ነበር ? ከግድያው ባሻገር የቆሰሉ አሉ? የሟቾቹ መኖሪያ ልዩ ቦታ ምን ይባላል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል። ነዋሪው በሰጡት ምላሽ፣ “ ገዳዮቹ ማን እንደሆኑ አልታወቀም። እቤታቸው ነው የገደሏቸው። በሟቾቹ ላይ ከዚህ በፊት የደረሰ ማስፈራሪያ አልሰማንም። ከህብረተሰቡ ጋር ጤነኛ በሆነ ግንኙነት በሰላማዊ መንገድ ኑሯቸውን ከመምራት ውጪ ምንም ግጭት አልነበራቸውም። ቦታው ዶዶላ 02 ቀበሌ ነው ” ብለዋል። ከሟቾች ውጪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እንደሌሉ፣ የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ በቅዱስ ገብረ ክስስቶስ ገዳም 8፡30 እንደተፈጸመ፣ ገዳዮቹ እንዳልተያዙ አስረድተው፣ መንግሥትና በተዋረዱ ያሉ አካላት ለእንዲህ አይነት ድርጊት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።  በቤተክርስቲያኗ ሆነ በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ የሚሰጥ ምላሽ ካለ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
😭 3163😡 382😢 131 124🕊 118🙏 44😱 30👏 28🥰 14🤔 14
“ የመሪጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው  ” - የዓይን እማኝ በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ሁለት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። አንድ ሟቾቹ መቀበራቸውን የተመለከቱ የዓይን እማኝ በሰጡት ቃል፣ “ በአጠቃላይ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት። የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ ተፈጽሟል ” ብለዋል። “ ትላንት 3 ሰዓት ላይ ነው የተገደሉት። አንድ መሪጌታ ከእነባለቤቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋ፣ አንድ ዲያቆን ከእነባለቤቱና እህቱ ጋር 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት። የመርጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ ነው የቀረው ” ሲሉ አክለዋል። ገዳዮቹ ማን ናቸው ? የት ነው የገደሏቸው ? ሟቾቹ ከዚህ በፊት ዛቻና መስፈራሪያ ደርሷቸው ነበር ? ከግድያው ባሻገር የቆሰሉ አሉ? የሟቾቹ መኖሪያ ልዩ ቦታ ምን ይባላል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል። ነዋሪው በሰጡት ምላሽ፣ “ ገዳዮቹ ማን እንደሆኑ አልታወቀም። እቤታቸው ነው የገደሏቸው። በሟቾቹ ላይ ከዚህ በፊት የደረሰ ማስፈራሪያ አልሰማንም። ከህብረተሰቡ ጋር ጤነኛ በሆነ ግንኙነት በሰላማዊ መንገድ ኑሯቸውን ከመምራት ውጪ ምንም ግጭት አልነበራቸውም። ቦታው ዶዶላ 02 ቀበሌ ነው ” ብለዋል። ከሟቾች ውጪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እንደሌሉ፣ የቀብር ስርዓታቸው ዛሬ በቅዱስ ገብረ ክስስቶስ ገዳም 8፡30 እንደተፈጸመ ፣ ገዳዮቹ እንዳልተያዙ አስረድተው፣ መንግሥትና በተዋረዱ ያሉ አካላት ለእንዲህ አይነት ድርጊት ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።  ቤተ ክርስቲያኗ ሆነች የመንግሥት ባለስልጣናት በኩል ስለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ የሚሰጥ ምላሽ ካለ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
#ሶማሌለንድ የራስ ገዟ ሶሌላንድ ሲቪል አቬዬሽንና ኤርፖርቶች ባለስልጣን እንዲሁም የሶማሌላንድ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ አንድ መረጃ አሰራጭተዋል። ይኸውም " የኢትዮጵያ አውሮፕላን በሱማሌላንድ አየር እየበረረ በሌላ አቅጣጫ ሲመጣ ከነበረ የኤሚሬትስ አውሮፕላን ጋር ከመጋጨት ለጥቂት ተርፏል " የሚል ነው። ባለስልጣን መ/ቤቱ ባሰራጨው በዚህ መረጃ " በ37,000 ጫማ ከፍታ ላይ ሲበር የነበረዉ የኤምሬትስ አየር መንገድ በተመሳሳይ ርቀት ላይ ከነበረው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ከመጋጨት ለጥቂት ተርፏል " ብሏል። " ከሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ #ተቆጣጣሪዎች በተሰጠ ትዕዛዝ በተመሳሳይ የጫማ ከፍታ ላይ ሲበሩ የነበሩት ንብረትነታቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የኢትዮጵያ የሆኑት አዉሮፕላኖች በድጋሚ ከመጋጨት አደጋ ተርፈዋል " ሲል ገልጿል። የካቲት ወር ላይ በተመሳሳይ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገዶች ንብረት የሆኑ አውሮፕላኖች ከመጋጨት ለጥቂት መትረፋቸውን የሶማሌላንድ የሲቪል አቬሽንና ኤርፖርቶች ድርጅት ገልጾ ነበር። የአሁኑ ክስተት የተፈጠረው እሁድ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው ተብሏል። በዕለቱ በ37,000 ጫማ ከፍታ ሲበር የነበረ የኤምሬትስ አየር መንገድ አዉሮፕላን በረራ ቁጥር UAE722 እና በተመሳሳይ በ37,000 ከፍታ ላይ ከነበረዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ETH690 ለመጋጨት ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ሲቀራቸዉ የሶማሊላንድ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪ ባደረጉት ጥረት አብራሪው በፍጥነት ከፍታውን በመቀየር ወደ 39,000 ጫማ ከፍ እንዲል በማድረግ የተፈራው አደጋ ለጥቂት ሳይደርስ እንዲቀር ተደርጓል ተብሏል። ለተፈጠረዉ ለዚህ ክስተት የሶማሌላንድ የሲቪል አቪዬሽን እና ኤርፖርቶች ባለስልጣን  የሞቃዲሾ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን ወቅሷል። " መሰል ቸልተኝነት እና የእውቀት ማነስ ሞቃዲሾ በሚገኙ የሱማልያ የአቪዬሽን ባለሞያዎች በተደጋጋሚ እየተፈጠረ መሆኑን ዓለም ይወቅ "ም ብሏል። ሁኔታው የአየር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶበታል። በዚህ ጉዳይ እስካሁን በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ አየር መንገድ የተባለ ነገር የለም። መረጃውን የሶማሌላንድ የሲሺል አቬዬሽን እና ኤርፖርቶች ድርጅትን ዋቢ በማድረግ ያጋራን ካፒታል ጋዜጣ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
😱 623 111😡 90🙏 74😭 67👏 27🤔 21😢 20🕊 19
ታዳጊዋ የት ናት ? በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታገተችውና ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊዋ ማህሌት ተኽላይ እስካሁን እንዳልተገኘች እና ድምጿም እንዳልተሰማ ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው ከተፈፀመ 7 ቀናት ሆኖታል። የ16 አመቷ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 11 ባጃጅ ይዘው በመጡ ' ማንነታቸው አልታወቀም ' በተባሉ ሰዎች ታፍና ከተወሰደች በኃላ በራሷ ስልክ ለአባቷ ተደውሎ " መልሳችሁ በህይወት ልታገኙዋት ከፈለጋችሁ 3 ሚሊዮን ብር ክፈሉ ፤ አለበለዚያ እንገድላታለን " የሚል የማስፈራሪያ ተላልፎ ነበር። ይህንንም የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አባቷን ዋቢ በማድረግ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል። ዛሬም የማህሌት አባትን አነጋግሯቸው ነበር። " ምንም አዲስ ነገር የለም። ስልኩም አይሰራም ከዛ ቀን በኃላ ተደውሎም አያውቅም ቤተሰብ ሁሉ ጭንቀትና ለቅሶ ላይ  ነው " ብለዋል። የዓድዋ ፖሊስ ታዳጊዋን ለማግኘት ርብርብ እያደረገ ነው ተብሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ባለው የቤተሰቡ አባል አማካኝነት ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ ያሳውቃል።                                                 @tikvahethiopia            
Show all...
😢 915😭 287 97😡 78🙏 55🕊 24😱 16👏 15🤔 15🥰 6
#ATTENTION ሁሉም ምዕመናን ወደ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር በኢትዮጵያ-4 ሲመጡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች የሚከተሉት ናቸው። 1ኛ. ለጸጥታ አካላትና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ለፍተሻ ትብብር ማድረግ ይገባል። 2ኛ. የሰላት መስገጃ እና ጥላ ይዘው መምጣት እንዳይዘነጉ። 3ኛ. ለማፍጠሪያ የሚሆንና ሙስሊም እህትና ወንድሞችን በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። ምግቦቹ እንደ ፦ - ቴምር፣ - ውሃ - የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 4ኛ. ማንኛውም ለደህንነት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ማሳወቅ ይገባል። 5ኛ. ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋናው ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅርና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሞች ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይገድባቸው ህብር ብሄራዊ  አንድነታቸውን በማሳየት ለሃገር ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀኑበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል። 6ኛ. በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ወገኖችን ድጋፍ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸምቱ ጥሪ ተላልፏል። 7ኛ. የዝግጅቱ አላማ መዓድ መጋራት እንደመሆኑ ከአላሰፈላጊ የምግብ ብክነት በመቆጠብ ምዕመኑ ሃይማኖታዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል። 8ኛ. ንፅህና የሙስሊም መገለጫ እንደመሆኑ ሁሉም ምዕመን የተጠቀመባቸው እቃዎች በአግባቡ እንዲያስወግዱ። (ከአዘጋጆቹ ሀላል ፕሮሞሽን እና ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት) ከ5:00 ሰዓት ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች 👇 https://t.me/tikvahethiopia/86345 @tikvahethiopia
Show all...
648😡 312🕊 30🙏 22😭 15🥰 11👏 7😢 7😱 2
#ATTENTION ሁሉም ምዕመናን ወደ ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር በኢትዮጵያ-4 ሲመጡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ደንቦች የሚከተሉት ናቸው። 1ኛ. ለጸጥታ አካላትና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ለፍተሻ ትብብር ማድረግ ይገባል። 2ኛ. የሰላት መስገጃ እና ጥላ ይዘው መምጣት እንዳይዘነጉ። 3ኛ. ለማፍጠሪያ የሚሆንና ሙስሊም እህትና ወንድሞችን በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል። ምግቦቹ እንደ ፦ - ቴምር፣ - ውሃ - የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 4ኛ. ማንኛውም ለደህንነት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ማሳወቅ ይገባል። 5ኛ. ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋናው ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅርና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሞች ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይገድባቸው ህብር ብሄራዊ  አንድነታቸውን በማሳየት ለሃገር ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀኑበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል። 6ኛ. በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለተፈናቀሉ ወገኖችን ድጋፍ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸምቱ ጥሪ ተላልፏል። 7ኛ. የዝግጅቱ አላማ መዓድ መጋራት እንደመሆኑ ከአላሰፈላጊ የምግብ ብክነት በመቆጠብ ምዕመኑ ሃይማኖታዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል። 8ኛ. ንፅህና የሙስሊም መገለጫ እንደመሆኑ ሁሉም ምዕመን የተጠቀመባቸው እቃዎች በአግባቡ እንዲያስወግዱ። (ከአዘጋጆቹ ሀላል ፕሮሞሽን እና ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት) ነገ የሚዘጉ መንገዶች 👇 https://t.me/tikvahethiopia/86345 @tikvahethiopia
Show all...
#ኢፍጧር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል። በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚካሄደው የአደባባይ ላይ የኢፍጥር ፕሮግራም በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጀት ማጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ  ግብረ-ሐይሉ አስታወቀ ፡፡ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት፡- - ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክርስቲያን - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ - ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡ - ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ - ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ - ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ - ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ። በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል። ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል። @tikvahethiopia
Show all...
1025😡 744🕊 62😭 47👏 32🙏 27🥰 25🤔 25😢 18😱 9
#ኢፍጧር በኢትዮጵያ የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ለአራተኛ ጊዜ ነገ መጋቢት 18/2016 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የከናወናል። የነገው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መሪ ቃል " ኢፍጧራችን ለአንድነታችን " የሚል ነው። ዓላማው በታላቁ የረመዳን ወር ሰዎችን በአንድነት በማሰባሰብ በጋራ ጾማቸውን እንዲያፈጥሩ በማስቻል የአብሮነትና የመተባበር መንፈስ ለማዳበር ነው ተብሏል። በዚህ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የህዝበ ሙስሊሙ፦ - አንድነት የሚንፀባረቅበት ፣ - ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ + ወረሐ ረመዷን ከመሆኑ አንፃር የቁርአን ክብር በአደባባይ የሚልቅበት እንደሚሆን ተነግሯል። ዝግጅቱ ሀላል ፕሮሞሽንና ከነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው። @tikvahethiopia
Show all...
636😡 396👏 19🤔 17🕊 14🙏 6😱 5😢 5😭 2