en
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

Open in Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

Show more
1 720
Subscribers
-124 hours
-47 days
-1430 days
Posts Archive
ሲያምር - ሲያስጠላ (ሲያስጣምር) --------------------------------- ውበትሽ ሲያስጠላ - ውበትሽ ክፋቱ ፈገግታሽ አይገባ - ልብሽ ላልገቡቱ፡፡ ዐይንሽ ሲመነጥር - ነፍስያን እ’ያየ ጣትሽ ያሳምማል - ልብ እያበራየ! ውበትሽ ሲያስጠላ - ማማርሽ ሲያስጠላ እውነቱን ሸሽጎ - በውሸት የሚያጣላ፡፡ . . . ደሞስ ይሄ መርገም መጥላት ይሉት መክሰም ስንቱን አስጠልቶ ስንቱን አስጠልሽቶ! ‘ሚሰራው ሲያሳጣው - የሚያረገው ሲያጣ እንዴት ባንዷ ባንቺ - በውበትሽ ይምጣ?! . . . ‘ውበትሽ ሲያስጠላ!’ - ያስባለን ያ… መጥላት በራሱ እንዳያስረን - ነገር ተሳክቶለት አዙረን አየነው - አየነው በዙረት እንኳንስ ፈገግታሽ እንኳን አይንሽ እና እንኳን'ና ጣትሽ . . . ማስጠላትሽ ሲያምር - ሲያምር ማስጠላትሸ! ሰይፈ ተማም 2012 #ግጥም_ሲጥም #ሰይፈተማም #poetic_Saturdays #ሰይፉ_ወርቁ_አ.

እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆቻችን! በአሉን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሽልማት አለን:- አሁን የያዝነው ዓመት ዘመነ ምን ይባላል? በ 12ሰዓታት ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ለሰጡን የመጀመሪያ 3 ሰዎች የዐየር ሰዓት ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።

ተጀነት አለት ስር የፈለቀች ግጥም •••፨••• ........ሰ.ወ.አ.... •፨•••፨•••፨•••፨•••••፨•••፨•••፨•••፨• ተጀነት አለት ስር - የፈለቁ ግጥሞች ጥም እየፈወሱ -የሚያስጠሙ ጥሞች ... ተጀነት አለት ስር - የፈለቀች ግጥም ጥም እየፈወሰች - የምታስጠማ ጥም .. ታንቺ ወዲያ ዜማ - ታንቺ ወዲያ ቅኔ ስትስሚኝ ለፈለፍኩ - ቃላት ሆንኩኝ እኔ ... ማሪቱ ለገሠ በቁም ቀረች ቀልጣ አስቴር 'እግዞ!' አለች ድምጥሽን አድምጣ ውብ ቅኔሽ ቀንቅኖት የአያ ሙሌ ቅኔ - በፀፀት ተቀጣ እንኳንም ሼክስፒር አማርኛ አልቻለ ቀሽም ግጥሞቹን ይረግም ነበረ! ... ታድያ እኔ መናኛሽ - በከንፈርሽ ጉልበት ወዝ ወንዝ አፈለቅሁኝ - ተገረጣሁበት ... ስታዜሚ አዚም - ክንፉ ተሰበረ በቅኔሽ ተመቶ - ጁሃን ደነበረ ድምጥሽ ነው ያነሳኝ፤ ሰባራ አጥንቴ ውስጥ፣መቅኒ እየፈጠረ ... እናንት ጅል ገጣሞች፣ አታስቆንጁ ሥንኝ - ግጥም አትኳሉ ተሷ ቃል አያምርም - የተጣፈው ሁሉ ... አንቺ የልቤ ወይን - የመንፈሴ ስካር ካልተደበቅሽለት፣ ይኮስሳል ውበት፤ መልኩን ያጣል ማማር! .... ይቅር አትድገሚኝ - የከንፈርሽን ጠበል አፌን እየከለስኩ - እሰይ እሰይ ልበል! እንኳን ተደግሜ - የእንጆሪሽን ጉርሻ አንዱንም ጠንቶብኛል - እየሆነ ግርሻ መኖርም አልሻ መሞትም አልሻ አፍሽ ዳር ያድርገው - የአፌን መጨረሻ! ... ተጀነት አለት ስር - የፈለቅሽው ግጥም ጥሜን እየቆረጥሽ - አነደድሺኝ በጥም .......... •••]ሰይፉ ወርቁ.አ[•••

ታመነ መንግስቴ ውቤ, [03.09.19 11:36] [Forwarded from አዲስ ጉራማይሌ (ታመነ መንግስቴ ውቤ)] አብዮት ©በታመነ መንግስቴ ቅጠል እያኘከ ኒያላ አቦነነ! በወሲብ ነደደ በኳስ ሱስ አበደ ፣ እያልኩኝ አልፅፍም ትውልዴ ተነነ፡፡ ሌላ ሌላ አሠኘኝ በአብዮት ዋዜማ፡ ልብ አረስርስ ግጥም ተስፋ ያለው ዜማ፡፡ ዘንድሮ የጫት ማሳው ደርቆ ሲተከል በርበሬ አድዋ ሲያዘምር የባሌ ገበሬ፡ ዋሽንግተን ሲናኝ የኢትዮጵያ ዝና ዕንደ ህልም ዕነደ ህልም ይታየኛልና!!! መልካም የጳጉሜን መሻገሪያ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያት፡፡ ነሃሴ 28/ 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ

እግዜሩ ፈርሟል! ©በታመነ መንግስቴ እሱ ጥበበኛው፡ አንችን ለማሳመር እንዳይሆኑ ሆኖ፡ የማይደክመው ደክሟል! እና ከዚያ ወዲህ፡ ከአንች የበለጠች የውበት ማሳያ ላይፈጥር ፈርሟል፡፡

ጽደቅ እንደ ችግኝ አፍላ እንደ ሾላ ከአለም ደጉን ወስደህ መልካም ፍሬ ዝራ ዘለአለም ለመኖር አሁንን አትፍራ ሰይፈ ተማም 2011

📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7 💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰

The Arts Mailing List newsletter 5th Aug 2019 is out!!!!! https://bit.ly/2YDyWNA bringing you an extensive list of open calls
The Arts Mailing List newsletter 5th Aug 2019 is out!!!!! https://bit.ly/2YDyWNA bringing you an extensive list of open calls, competitions, residencies etc for the Ethiopian creative practitioner. So do apply!!!!!! This week featuring visual artist @Mesfinarts Book-worm, @Freelance_ethio, @LinkUpAddis, @BiGDreamET and so much more

📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6 💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.20 ብቻ 💰

The next Arts Mailing List newsletter is out, with over 70 opportunities for the Ethiopian Creative check it out https://bit.
The next Arts Mailing List newsletter is out, with over 70 opportunities for the Ethiopian Creative check it out https://bit.ly/2Mji35E This week we feature Awell Kedir Afro Fair Fest, Gebeya Talent, @BigDreamET, Addis Foto Fest (AFF), Addis Insight, BAM Ethiopia, Awtar Multimedia, LinkUp Addis, Betty G., Startup Ethiopia, @talktolife and so much more

Come for the shopping and stay for the Entertainment. Join us for An experience like never before
Come for the shopping and stay for the Entertainment. Join us for An experience like never before

ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል!!! ከ 40 በላይ እድሎች አሉ https://bit.ly/2WKZuZ2 Featuring @Mykeyliyew, @Big
ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል!!! ከ 40 በላይ እድሎች አሉ https://bit.ly/2WKZuZ2 Featuring @Mykeyliyew, @BigDreamEt, @melkam74, @habeshawian, @Sabegnn and so much more

ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል with over 20 opportunities for you to explore!!! https://bit.ly/2Ve5RH
ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል with over 20 opportunities for you to explore!!! https://bit.ly/2Ve5RHs This week featuring @michaelfelleke, Beza Hailu Lemma, Ethiopian Records. የኢትዮጵያ ልጅ, Yefikir Design, @kunjina_ltd, Gobeze, Seife Temam, Ayni's, @melkam74, @LinkUpAddis, Contemporary Nights

📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 5 💰 ፓኬጅ ከገዙ በ 0.70 ብር ብቻ 💰

የኋላ የኋላ የታሰረን መምታት የወደቀን መግፋት ጀግንነት ነው ወይ ከሌለው መቀማት ጦስ ይሆን የለም ወይ የመቱት ሲፈታ ሲበቅል የገፉት ሰብል እኮ ይሆናል ዘርን ሲበትኑት ሰይፈ ተማም 2010

The Arts Mailing List newsletter - 11th March 2019 is out now, featuring @Royalphotography22, Fekat Circus, @behagerlij, Habe
The Arts Mailing List newsletter - 11th March 2019 is out now, featuring @Royalphotography22, Fekat Circus, @behagerlij, Habesha Animation, Fano Creatives, Association of Ethiopian Architects, Designlab ETH, Everted, Artistic Ethiopia, Art in Addis, Zoma Museum - https://bit.ly/2Ho5ZvO We hope you enjoy!!