ru
Feedback
ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem

Открыть в Telegram

የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ። ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን። We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com

Больше
1 676
Подписчики
-124 часа
-17 дней
-1730 дней
Архив постов
Off By Elebethel Tessema Of first texts and rendezvous unplanned, Of shy glances and stare you down-s, Of hidden feelings and meaningless fooling around, Of no strings attached with cords so tight, Of burried feelings and longing eye contacts, Of joyful giggles, and confusion about what we are, Of quick falls and arms that catched, Of stolen kisses and territories marked so bright, Of rushing feelings and sensual touches, Of love spats and making up, Of your wild hair and my groomed one, Of your free spirit and my timid heart, Of your loud presence and my looming behind like a shadow; so I can go wherever you go, Of pushing limits and comfort zones, Of "he's mine" and "she's mine" so everyone knows, Of me showing you off and you hiding us, Of cigarettes and chewing gums, Of hard liquor and soft drinks in a club, Of insecurities and validations, Of pushing buttons and fishing out reactions, Of harsh words and hidden cries, Of your suspicions and my unwavering trust, Of your dressed up lies and my hands that refuse to strip your lies, Of empty threats and half promises, Of dodged touches and breath stealing kisses, Of warm hugs and cold shoulders, Of your indecisiveness and my assurance, Of your sudden lows and my failed attempts to pick you up, Of hotel rooms and car rides, Of my sobriety and of all your vices, Of all your flaws I embraced and my differences you couldn't accept, Of your stubbornness and my "let me fix this please", Of your tests and my flying color pass, Of your failure to be loved and me trying to prove myself time after time, Of your tainted soul and my unscathed one, Of growing close only to fall apart, Of lovers and of strangers just as fast, Of falling in love and falling out of love, Of I love yous turned into leave me alone's, Of forevers dissipating into see you Nevers, Of locked hands letting go one finger by one, Of you slipping away and my grasp on you to make you stay, Of you... Of me... Of our doomed love from the very start. 🥀

የተውሶ ገላ ©️ THomas Admasu የተዉሶ ገላ ያዉም ያልፈቀደ የእሳት ሬሳ ሳይነብል ያመደ በመታመን ሜዳ ዞትር የተካደ ላላገኘው መጥቶ ሳላገኘው ሄደ ሄደ ይሂድ ያምድ ምናባቱ... ነፍስ ስለተ ብርቱ... ቃል ከርታታ ገልቱ... ዓይን ቀና ገልበቱ... ጉልበት... ጉልበት የደከመ ህዋስ የታመመ ከንፈር የተመመ ሰርቆ ከንፈር ሳመ። ሳመ ይሳም የታባቱ መሳም የትናቱ ልብ የከዳ ለታ ዓይን የላመ ለታ የአካላትህ ጅማት የእዝኖችህ መስማት የእናት የአባት አስማት ሲከዱህ አንድ ላይ ቀና በል ወደላይ አቀርቅር ከመሬት ከመበደር በላይ ኬት ይመጣል ምሬት? ምሬት! ይምረር ምናባቱ ብድር የት እናቱ ልብ ከጎለመተ ነፍስ ከሻገተ ልሳን ከታገተ ተበድሮ ስሞ በብድር አሳሳም የተውሶ ፍቅር አይወፍር አይከሳም ....... ናፈቀ ቀና ምውት ነው ወደደ ጠላ አይሰራም ጨረቃ ቀን አታበራም። ....... ፍቅር አይዋስም ቃል አይላወስም የተበደሩት ልብ የልብ አያደርስም። ...... አያድርሳ ደሞ እሱም የተውሶ አያጠግብ አጉርሶ ነፍስ አያክም ደርሶ ..... (እንኳን ፍቅር ቀርቶ) የተዉሶ ግጥም ቤት በቅጡ አይገጥም ሳቁ ለጆሮ አይጥም ቢገጥ ባያገጥም . . የትውሶ ገላ የተውሶ ፍቅር /ይቅር/

photo content

የደበቅነው ዕውነት © ታመነ መንግስቴ በኔም ቤት በአንችም ልብ የታመቀው ነገር አንድ ቀን ቢወጣ ያቃጥላል አገር፡፡ የኔንስ ልንገርሽ በልቤ ያልኩትን ለሃሜት ስጎመጅ በክፋት ስኳትን: እንኳም ሰው አልሰማው ስቦጭቀው ነበር እግዚሃርን ሳማው፡፡ እሱ እንደሁ ታጋሹ እያወቀ ረሳኝ: ዋሽቸ ሰርቄ ብበላም አከሳኝ፡፡ እናልሽ ዐለሜ! የደበቅነው ዕውነት ጭሶ ተጫጭሶ ሳያቀጣጥለን፡ ውድ ሃሳብ እንሸምት የረከሠ ጥለን! የመነሻ ሃሳቤ በአዲስ አበባ መካነ አዕምሮ በቆየሁባቸው ወራት እውነተኛ መምህር ሆነው ያገኘሗቸው የኔታ #ማቴወስ ታደሠ ክፍል ውስጥ ያወጉን ነገር ነው፡፡

ሲያምር - ሲያስጠላ (ሲያስጣምር) --------------------------------- ውበትሽ ሲያስጠላ - ውበትሽ ክፋቱ ፈገግታሽ አይገባ - ልብሽ ላልገቡቱ፡፡ ዐይንሽ ሲመነጥር - ነፍስያን እ’ያየ ጣትሽ ያሳምማል - ልብ እያበራየ! ውበትሽ ሲያስጠላ - ማማርሽ ሲያስጠላ እውነቱን ሸሽጎ - በውሸት የሚያጣላ፡፡ . . . ደሞስ ይሄ መርገም መጥላት ይሉት መክሰም ስንቱን አስጠልቶ ስንቱን አስጠልሽቶ! ‘ሚሰራው ሲያሳጣው - የሚያረገው ሲያጣ እንዴት ባንዷ ባንቺ - በውበትሽ ይምጣ?! . . . ‘ውበትሽ ሲያስጠላ!’ - ያስባለን ያ… መጥላት በራሱ እንዳያስረን - ነገር ተሳክቶለት አዙረን አየነው - አየነው በዙረት እንኳንስ ፈገግታሽ እንኳን አይንሽ እና እንኳን'ና ጣትሽ . . . ማስጠላትሽ ሲያምር - ሲያምር ማስጠላትሸ! ሰይፈ ተማም 2012 #ግጥም_ሲጥም #ሰይፈተማም #poetic_Saturdays #ሰይፉ_ወርቁ_አ.

እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆቻችን! በአሉን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሽልማት አለን:- አሁን የያዝነው ዓመት ዘመነ ምን ይባላል? በ 12ሰዓታት ውስጥ ትክክለኛውን መልስ ለሰጡን የመጀመሪያ 3 ሰዎች የዐየር ሰዓት ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።

ተጀነት አለት ስር የፈለቀች ግጥም •••፨••• ........ሰ.ወ.አ.... •፨•••፨•••፨•••፨•••••፨•••፨•••፨•••፨• ተጀነት አለት ስር - የፈለቁ ግጥሞች ጥም እየፈወሱ -የሚያስጠሙ ጥሞች ... ተጀነት አለት ስር - የፈለቀች ግጥም ጥም እየፈወሰች - የምታስጠማ ጥም .. ታንቺ ወዲያ ዜማ - ታንቺ ወዲያ ቅኔ ስትስሚኝ ለፈለፍኩ - ቃላት ሆንኩኝ እኔ ... ማሪቱ ለገሠ በቁም ቀረች ቀልጣ አስቴር 'እግዞ!' አለች ድምጥሽን አድምጣ ውብ ቅኔሽ ቀንቅኖት የአያ ሙሌ ቅኔ - በፀፀት ተቀጣ እንኳንም ሼክስፒር አማርኛ አልቻለ ቀሽም ግጥሞቹን ይረግም ነበረ! ... ታድያ እኔ መናኛሽ - በከንፈርሽ ጉልበት ወዝ ወንዝ አፈለቅሁኝ - ተገረጣሁበት ... ስታዜሚ አዚም - ክንፉ ተሰበረ በቅኔሽ ተመቶ - ጁሃን ደነበረ ድምጥሽ ነው ያነሳኝ፤ ሰባራ አጥንቴ ውስጥ፣መቅኒ እየፈጠረ ... እናንት ጅል ገጣሞች፣ አታስቆንጁ ሥንኝ - ግጥም አትኳሉ ተሷ ቃል አያምርም - የተጣፈው ሁሉ ... አንቺ የልቤ ወይን - የመንፈሴ ስካር ካልተደበቅሽለት፣ ይኮስሳል ውበት፤ መልኩን ያጣል ማማር! .... ይቅር አትድገሚኝ - የከንፈርሽን ጠበል አፌን እየከለስኩ - እሰይ እሰይ ልበል! እንኳን ተደግሜ - የእንጆሪሽን ጉርሻ አንዱንም ጠንቶብኛል - እየሆነ ግርሻ መኖርም አልሻ መሞትም አልሻ አፍሽ ዳር ያድርገው - የአፌን መጨረሻ! ... ተጀነት አለት ስር - የፈለቅሽው ግጥም ጥሜን እየቆረጥሽ - አነደድሺኝ በጥም .......... •••]ሰይፉ ወርቁ.አ[•••

ታመነ መንግስቴ ውቤ, [03.09.19 11:36] [Forwarded from አዲስ ጉራማይሌ (ታመነ መንግስቴ ውቤ)] አብዮት ©በታመነ መንግስቴ ቅጠል እያኘከ ኒያላ አቦነነ! በወሲብ ነደደ በኳስ ሱስ አበደ ፣ እያልኩኝ አልፅፍም ትውልዴ ተነነ፡፡ ሌላ ሌላ አሠኘኝ በአብዮት ዋዜማ፡ ልብ አረስርስ ግጥም ተስፋ ያለው ዜማ፡፡ ዘንድሮ የጫት ማሳው ደርቆ ሲተከል በርበሬ አድዋ ሲያዘምር የባሌ ገበሬ፡ ዋሽንግተን ሲናኝ የኢትዮጵያ ዝና ዕንደ ህልም ዕነደ ህልም ይታየኛልና!!! መልካም የጳጉሜን መሻገሪያ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያት፡፡ ነሃሴ 28/ 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ

እግዜሩ ፈርሟል! ©በታመነ መንግስቴ እሱ ጥበበኛው፡ አንችን ለማሳመር እንዳይሆኑ ሆኖ፡ የማይደክመው ደክሟል! እና ከዚያ ወዲህ፡ ከአንች የበለጠች የውበት ማሳያ ላይፈጥር ፈርሟል፡፡

photo content

ጽደቅ እንደ ችግኝ አፍላ እንደ ሾላ ከአለም ደጉን ወስደህ መልካም ፍሬ ዝራ ዘለአለም ለመኖር አሁንን አትፍራ ሰይፈ ተማም 2011

📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 7 💰 ፓኬጅ ከገዙ በ0.90 ብር ብቻ 💰

The Arts Mailing List newsletter 5th Aug 2019 is out!!!!! https://bit.ly/2YDyWNA bringing you an extensive list of open calls
The Arts Mailing List newsletter 5th Aug 2019 is out!!!!! https://bit.ly/2YDyWNA bringing you an extensive list of open calls, competitions, residencies etc for the Ethiopian creative practitioner. So do apply!!!!!! This week featuring visual artist @Mesfinarts Book-worm, @Freelance_ethio, @LinkUpAddis, @BiGDreamET and so much more

📠 መልካም74 ቅፅ ፩ ቁጥር 6 💰 ፓኬጅ ከገዙ በብር 1.20 ብቻ 💰

The next Arts Mailing List newsletter is out, with over 70 opportunities for the Ethiopian Creative check it out https://bit.
The next Arts Mailing List newsletter is out, with over 70 opportunities for the Ethiopian Creative check it out https://bit.ly/2Mji35E This week we feature Awell Kedir Afro Fair Fest, Gebeya Talent, @BigDreamET, Addis Foto Fest (AFF), Addis Insight, BAM Ethiopia, Awtar Multimedia, LinkUp Addis, Betty G., Startup Ethiopia, @talktolife and so much more

Come for the shopping and stay for the Entertainment. Join us for An experience like never before
Come for the shopping and stay for the Entertainment. Join us for An experience like never before

ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል!!! ከ 40 በላይ እድሎች አሉ https://bit.ly/2WKZuZ2 Featuring @Mykeyliyew, @Big
ውድ አርቲስቶቻችን፣ የዚህ ሳምንት Art Mailing List newsletter ወጥቷል!!! ከ 40 በላይ እድሎች አሉ https://bit.ly/2WKZuZ2 Featuring @Mykeyliyew, @BigDreamEt, @melkam74, @habeshawian, @Sabegnn and so much more

photo content

ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem - Статистика и аналитика Telegram-канала @gitemsitem