cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Central Ethiopia Regional Health Bureau

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ 🔵 https://m.facebook.com/centralethiopiarhb 📞 📩

Show more
Advertising posts
3 496
Subscribers
+524 hours
+277 days
+7430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ2016 ዓ/ም የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኃላፊው በበዓል መልዕክታቸው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን  ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ይህን በዓል ስናከብር  እርስ በርሳችን በመከባበርና በመረዳዳት  መሆን እንዳለበት ገልፀው ከዚህ ባሻገር  በበዓል ወቅት የጤና ጉዳይ ጥንቃቄን የሚጠይቅ እንደሆነ ታሳቢ በማድረግ ቅባት የበዛባቸዉን ምግቦች ስንመገብ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ እና መጥኖ በመጠቀም በጤናችን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን  እክል መከላከል ይገባናል ሲሉም አሳስበዋል። በዚህ አጋጣሚ በበዓል ወቅት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በህክምና አገልግሎት ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋናን አቅርበዋል ። ኃላፊው አክለዉም የጤና ተግባር ሰፊና ከፍተኛ ትኩረት የሚጠይቅ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ቢሮአችን በ2016 በጀት ዓመት ህብረተሰብን ማዕከል በማድርግ በሽታን የመከላከል እና የፈዉስ ሕክምና አገልግሎቶችን በሁሉም አካባቢ ተደራሽ በማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ። በተለይም  የወባ ወረርሽን እና  ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን በዘላቂነት ለመቀነስ እየተደረገ ባለዉ ርብርብ እንዲሁም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ሂደት ጥረትና ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡ አቶ ሽመልስ አክለውም የጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/አብይ አህመድ "ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና" የሚለውን በጎ እና መላ ህብረተሰብን የሚያነሳሳ ሀሳብ በመተግበር እና በየአካባቢያችን በንፅህና ጉድለት የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን በመመከት  የክልላችን ህዝብ በጤና እንዲኖር ጠንክረን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል። በመጨረሻም በዓሉ የጤና፣የደስታ፣የፍቅር እና  የብልጽግና  ይሁንልን በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ። መልካም የትንሳኤ በዓል!!         አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ
Show all...
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሣኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ የሚል መልዕክት በማስቀደም በክርስትና ሀይማኖት ለባለፉት ወራት በጾም ያለፉት ግዜያትን በማሰብ፣ በአሉንም በመተዛዘን፣አቅመ ደካሞችን በመርዳትና በመደጋገፍ የምናሳልፈው መልካም በአል እንዲሆን ይመኛል፡፡ በዓሉን ስናከብርም ጥንቃቄ የተሞላበት የምግብ ዝግጅት፣ አያያዝ እና አመጋገብ ስርአት ህብረተሰቡ እንዲከተል እያስታወሰ የትንሣኤ በአልን ስናከብር በየደረጃው ህብረተሰባችንን ሊጎዱ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን አስቀድመን እየተከላከልና ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞች በህዝባችን ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትሉ ትርጉም ባለው መልኩ እየመከትን ሊሆን እንደሚገባም አሳስቧዋል። በተለይም በክልሉ በወረርሽኝ መልክ የሚነሱ በሽታዎች ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ስራዎችን ይበልጥ ለማሻሻል ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ኦፕሬሽን ማዕከል (EOC)ን በየደረጃው በማጠናከር በክልሉ የማህበረሰብ ጤና ስጋት ከሆኑ ግንባር ቀደም በሽታዎች መካከል የወባ በሽታ ስርጭት፣ የምግብ እጥረት ችግር፣ የኩፍኝና የኮሌራ ወረርሽኝ እንዲሁም ሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጠንካራ የአሰሳና የቅኝት ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ እና ከግብአት ብክነት፣ከመረጃ ጥራት ጉድለት ጋር የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም ሊረባረብና ሊደጋገፍ እንደሚገባ በዚሁ አጋጣሚ ለማስታወስ እንወዳለን ። መልካም የትንሣኤ በአል!!! የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Show all...
የስቅለትና ትንሳኤን በዓል በጤና! በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ የቢሮ ም/ሃላፊና የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ የስቅለትንና የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረክ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፉ። ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱና ለብርሃነ ትንሳዔው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!! ህዝበ ክርስቲያኑ ለሁለት ወር ያህል በጾም፣በጸሎትና ስግደት ሲያሳልፍ የነበረውን አብይ ፆም በማገባደድ እንሆ ለብርሃነ ስቅለቱና ትንሳዔው መድረሱን ያወሱት አቶ ፋሲካ አለሙ በዓሉ የሰላም፣የጤና ከፈጣሪ ዘንድ ምህረትን አግኝተን ድህነትን የምናገኝበት ትንሳኤ እንዲሆን ተመኝተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ይህ በዓል ከፍተኛ የሆነ የንግድ ስርዓት የሚከናወንበት በዓል በመሆኑ ከንግድ ስርዓቱ ጋር ተያይዞ ያሉ ምግብን ለጤና ጠንቅ ከሆኑ ባዕድ ነገሮች በመቀላቀል በመሸጥ ለመክበር የሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች የሚበዙበት ወቅት መሆኑን አውስተው ማህበረሰቡ የቅቤ፣በርበሬ፣ዘይትና መሰል ለምግብነት የሚውሉ ከበዓሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ምርቶች በሚሸምትበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እንዲሸምት እንዲሁም አጠራጣሪ ሁኔታዎች በሚኖሩበት ወቅት በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት አልያም ለጤና ባለሙያዎች ወይም ደግሞ በነፃ የስልክ ጥሪ መቀበያ 8482 በመደወል ጥቆማ እንድትሰጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ሲሉ ገልፀዋል። ሃላፊው አክለውም በፆም ወቅት ከቅባት ነክ ምግቦች ታቅበን የምንቆይበት ወቅት በመሆኑ ፍስኩን መሰረት በማድረግ ከምንመገባቸው ምግቦች ጋር ተያይዞ የሚከሰት ማንኛውም የጤና እክል በሚኖርበት ወቅት ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ህክምና በማድረግ የሚታዘዙልንን መድሃኒቶች በአግባቡ ወስደን መጨረስ ይጠበቅብናል ሲሉም የገለጹ ሲሆን ያለ ሃኪም ትዕዛዝ የሚወሰዱ ማናቸውም መድሃኒቶች የጤና ጉዳት የሚኖራቸው መሆኑን አውቆ ህብረተሰቡ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ ለህክምና የሚውሉ መድሃኒቶችን እንዳይጠቀም አሳስበዋል። በበዓል ወቅት ሌላው የሚስተዋለው አንዱ ችግር ያልተገባ የአልኮል አጠቃቀም ነው ያሉት ሃላፊው አልኮል እድሜው 21 ዓመት ላልሞላው ሰው መሸጥም ሆነ እንዲሸጥ ማድረግ በህግ የተከለከለ ነው ሲሉም ገልፀዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህን በዓል በሚያከብርበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሱንና ቤተሰቡን መከላከል ከሚችለው የጤና ጉዳት እንዲጠብቅም አሳስበዋል። የትንሳዔው ብርሃንና የጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ለሁላችን ይሁን በድጋሜ መልካም የስቅለትና የትንሳዔ በዓል እንዲሆን እንመኛለን። የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ
Show all...
የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓት የአተገባበር መመሪያ እና በቀጣይ ሁለት ወራት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው። የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ አሸናፍ ጴጥሮስ ባስተላለፉት መልዕክት የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተው የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና አተገባበር መመሪያ ቀጥታ በማህበረሰቡ የሚተገበር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በጤናው ሴክተር በርካታ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓትን መተግበር የጤናውን ሴክተር ተግባር በሚገባ ለማሳለጥ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው የጠቆሙት አቶ አሸናፊ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ያጠናከረ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል። የመረጃ አያያዝ ስርዓት አደረጃጀት እና አጠቃቀም ፣ ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ የሆኑ ቀበሌያትን የመፍጠር እንዲሁም ጽዱ ኢትዮጲያን የመፍጠር ተግባራትን በአግባቡ መፈጸም እንደሚገባ የጠቆሙት ምክትል ሀላፊው የክትባት ሳምንት፣ የቲቢ ካች አፕ ካምፔይን ተግባራት በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ በመግለጽ የምግብ እጥረት በሽታ ችግር ያለባቸውን ህጻናትና ነፍሰጡር እናቶች ልየታ በማጠናከር ወደታች የወረዱ ሀብቶችን ለታለመለት ዓላማ ተጠቅሞ በማወራረድ ወቅታዊ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል መላክ ይገባል ብለዋል። የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን በበኩላቸው ባለፉት ጊዜያት የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓትን በመተግበር የመጡ በርካታ ለውጦች መኖራቸው በመጠቆም የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አጋዥ የሆነውን ይህን ተግባር እንደገና በንቅናቄ መተግበር ለጤናው ሴክተር ተግባር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የማህበረሰብ አስተያየት ምዘና ስርዓት እና የቀጣይ ሁለት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ሰነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበትም ታውቋል። የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...